አበይት ጉዳዮች
ዲሰምበር 11, 2025
|
|
የትምህርት ቦርድ የትምህርት አመት 2026–2027 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር አጽድቋል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በዛሬው (ዲሰምበር 11) ስብሰባ ላይ የትምህርት ዓመት 2026-2027 መደበኛ እና ኢኖቬቲቭ የቀን መቁጠሪያዎች/ካለንደሮችን አጽድቋል።
የመደበኛ የቀን መቁጠሪያ/ካላንደር አጠቃላይ እይታ፦
-
ካላንደሩ አራት የአስቸኳይ ሁኔታ ቀናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 181 የትምህርት ቀናትን ያካትታል።
-
የተማሪዎች የሽግግር ቀን፣ ትምህርት የማይሰጥበት ቀን፡ ሰኞ፣ ኦገስት 24, 2026።
-
የመጀመሪያ የትምህርት ቀን፡ ማክሰኞ፣ ኦገስት 25, 2026።
-
ትምህርት ቤት የመጨረሻ ቀን፡ እሮብ፣ ጁን 16, 2027።
-
የዊንተር/የክረምት ዕረፍት ዲሰምበር 23, 2026 እስከ ጃኑዋሪ 3, 2027 ይሆናል። የስፕሪንግ/ፀደይ እረፍት ከማርች 26, 2027 እስከ ኤፕሪል 4, 2027 ይሆናል።
-
ዋናዎቹ በዓላት እና የእረፍት ጊዜያት፦ የሠራተኞች ቀን/ሌበር ዴይ፣ የምስጋና ቀን/ታንክስጊቪንግ ቀን፣ የዊንተር/ክረምት እና የስፕሪንግ/የጸደይ እረፍቶች እና ሌሎች ታስበው የሚውሉ ክብረበዓላትን ጨምሮ ከስቴት መስፈርቶች ጋር የተሣለጡ ናቸው።
የአርኮላ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ኢኖቬቲቭ የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር፦
-
ከጁላይ 6, 2026 ጀምሮ በነሐሴ ወር ከሚኖረው የተራዘመ እረፍት ጋር 206 የትምህርት ቀናትን ይኖሩታል።
-
ተጨማሪ የማስተማሪያ ቀናትን እና ልዩ የመርሃግብር ባህሪያትን በማካተት ለበዓላት ከሚዘጉ ቀናት ጭምር ከመደበኛው የቀን መቁጠሪያ ጋር ይጣጣማል።
|
|
|
የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ውጤት፡ ለቤተሰቦች የሚተላለፍበት ጊዜ
የመጀመሪያ የማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ ሪፖርት ካርዶች ሁሉ አሁን ParentVue ላይ ይገኛሉ። የሁለተኛ ማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ የልጅዎን የትምህርት እድገት እና ውጤቶችን ለማግኘት እባክዎን "ParentVue" ላይ ይመልከቱ። ሁለተኛው የማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ የሚያበቃው አርብ፣ ጃኑዋሪ 23, 2026 ነው። የሁለተኛው የማርክ መስጫ ወቅት ጊዜያዊ ውጤቶች አርብ፣ ዲሰምበር 19 "ParentVue" ላይ ማግኘት ይቻላል። ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|
ስለ ሪጅናል ፕሮግራሞች የተሳሳቱ መሠረተቢስ አመለካከቶችን ማረም
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በእያንዳንዱ ማህበረሰብ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ተማሪ የቦታ ርቀት ወይም ዕድል ያለማግኘት እንቅፋቶች ሳይኖሩበት ከፍላጎቱ፣ ከዝናባሌው እና ከዓላማው ጋር የሚጣጣሙ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራሞች ማግኘት እንዲችል ለማድረግ በቁርጠኛነት ይቀጥላል። ዲስትሪክቱ እያከናወነ ያለው ሥራ ወደ ፍትሃዊ ስርዓት የሚያመራ አስፈላጊ እርምጃ ነው።
ቤተሰቦች ስለዚህ ሥራ አሁንም ጥያቄዎች ሊኖሯቸው እንደሚችል እናውቃለን። እነዚህ የሰማናቸው ሦስት የተሳሳቱ አመለካከቶች እና እውነቱ ይህን ይመስላል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
የቅርብ ጊዜ EdTalk ትኩረት የተማሪ መሪዎችን በመገንባት ላይ ይሆናል።
በትምህርት ቦርድ አባል ጁሊ ያንግ/Julie Yang የተዘጋጀው አዲሱ የኤድቶክ ፖድካስት "EdTalk podcast" ለተማሪዎች የአመራር ልምዶችን መስጠት ያለውን ጠቀሜታ እና ጥቅሞቹን እና እነዚህ ልምዶች እንዴት እንደሚሰጡ ያብራራል። እንግዶች በሥራ ጉዞአቸው ላይ የተማሩትን የአመራር ልምዶቻቸውን እና ክህሎቶቻቸውን ያካፍላሉ። የቀረበውን ይመልከቱ።
|
|
|
ቀኑን ያስታውሱ፦ በጀት ዓመት FY 27 የሥራ ማስኬጃ በጀት ዲሰምበር 17 ይቀርባል።
ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር የበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት እቅዳቸውን ረቡዕ፣ ዲሰምበር 17 ከቀኑ 6፡30 p.m. ላይ ያቀርባሉ። በይነመረብ MCPS TV ኬብል ቻናል፣ (Comcast 34፣ Verizon 36 እና RCN 88) ላይ ይከታተሉ።
ሱፐርኢንቴንደንቱ ከማህበረሰብ አስተያየት በሚሰጥበት ክፍለ ጊዜ ከሠራተኞች፣ ከወላጆች፣ እና ከማህበረሰብ አባላት የቀረቡ ሀሳቦችን አድምጠዋል። ተሳታፊዎች አስፈላጊ ጥያቄዎችን ከማንሳታቸውም በላይ ሐቀኛ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
ተጨማሪ የድንበር ጥናት አማራጮችን ይመልከቱ እና አስተያየትዎን ያጋሩ
ቤተሰቦች ስለ ውድዋርድ/ኖርዝውድ እና ክራውን/ዳማስከስ የድንበር ጥናቶች ላይ ተጨማሪ አማራጮችን መመልከት እንዳለባቸው የቀረበ ማሳሰቢያ፦ እነዚህ አማራጮች (ዲሰምበር 1, 2025 የተጨመሩ) ሲሆን በድንበር ጥናት ድረ-ገጾች ላይ ከሚገኙት A–D አማራጮች በተጨማሪ የቀረቡ ናቸው፣ ስለዚህ እባክዎን እስከ አርብ፣ ጃንዋሪ 9 ድረስ በሚደረግ የዳሰሳ ጥናት ላይ አስተያየትዎን ያጋሩ።
የድንበር ጥናት ድረ-ገጽ
|
|
|
|
|
አመታዊ HBCU ትርኢት ፌብሩዋሪ 13 ይካሄዳል
18ኛው አመታዊ HBCU ትርኢት ምዝገባ ዓርብ፣ ዲሰምበር 12 ይከፈታል። ይህ ነፃ በአካል የሚካሄድ ዝግጅት አርብ፣ ፌብሩዋሪ 13 ከቀኑ 6-8:30 p.m. ሮክቪል በሚገኘው ሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ አድራሻ ላይ ይካሄዳል።
አድራሻ፦ The Universities at Shady Grove, 9630 Gudelsky Drive in Rockville. ይህ ትርኢት በሚካሄድበት ወቅት 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች 30 በላይ በታሪክ ጥቁር ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተወካዮችን የማግኘት እድል ይኖራቸዋል። የዘንድሮው ዝግጅት ቦታው ላይ የመግቢያ ክንውን፣ ስለ ፋይናንሻል ኤይድ/ገንዘብ ድጋፍ ላይ የሚደረጉ አውደ ጥናቶች FAFSA፤ እንዲሁም ለመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጀ የተለየ አውደ ጥናት እና እንቅስቃሴዎችን ያካትታል።
|
|
|
የወላጅ አካዳሚ ወርክሾፖች ጃኑዋሪ 6 እስከ 14 ይካሄዳሉ
ወላጆች በጃኑዋሪ ወር የሚካሄዱ ሁለት ቨርቹዋል "Parent Academy To Go workshops" እንዲከታተሉ እናበረታታለን። "Parent Academy TO GO" ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ትምህርት በሚመለከት አቀንቃኞች እና አጋሮች መሆናቸውን እውቀት ይሰጣቸዋክ እና ያበረታታል። መጪዎቹ ክፍለ-ጊዜዎች የሚከተሉት ናቸው፦
-
ማክሰኞ፣ ጃኑዋሪ 6፣ ከቀኑ 6-7 p.m., ስለ ቅዳሜ ትምህርት ቤት ትኩረት፡ ክህሎቶችን ማሳደግ፣ በራስ መተማመንን መገንባት
-
ረቡዕ፣ ጃንዋሪ 14፣ ከቀኑ 6-7 p.m., ተፈጥሮን እንደ ትምህርት ክፍል፡ የስሚዝ የአካባቢዊ ተሞክሮ
የወላጅ አካዳሚ አውደ ጥናት ላይ መሳተፍ ካልቻሉ፣ በቪድኦ የተቀረጹ ክፍለ ጊዜዎችን ለመከታተል MCPS YouTube ቻናል ይጎብኙ።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
|
ተማሪዎች SSL ሰዓቶችን እስከ ጃንዋሪ 9 ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
ከጁን 1, 2025 ጀምሮ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያጠናቀቁ ተማሪዎች፣ አስፈላጊውን SSL መተግበራቸውን የማረጋገጫ ቅጽ ለትምህርት ቤቶቻቸው SSL አስተባባሪ እስከ አርብ፣ ጃንዋሪ 9, 2026 ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
ሁሉም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት SSL ሰዓቶችን አገልግሎት መስጠት አለባቸው፤ በየዓመቱ ከትምህርት ክፍል ውጭ ቢያንስ አምስት SSL ሰዓታት እያገኙ ከቀጠሉ ተማሪዎች ይህንን መስፈርት ለማሟላት በትክክለኛው መንገድ ላይ እንዲቆዩ ይረዳቸዋል። የዊንተር/የክረምት ዕረፍት ከትምህርት ቤት ውጭ SSL እድሎች ላይ ለመሳተፍ አመቺ ጊዜ ነው! ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ። በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎመ መረጃ እዚህይገኛል። በአካል እና ቨርቹዋል የመሳተፍ እድሎች፣ ማሳሰቢያዎች እና ወቅታዊ መረጃዎች SSL Hub ላይ ይገኛሉ።
|
|
|
አስተያየትዎን ያቅርቡ!
የትምህርት ቦርዱ በአራት ፖሊሲዎች ላይ በተደረጉ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይፈልጋል፤ የፖሊሲ DIG፣ የኦፕሬቲንግ ፈንድ ኢንቨስትመንቶች፣ ፖሊሲ DAA፣ የፊስካል ኃላፊነት እና ቁጥጥር፣ ፖሊሲ GIG፣ ጡረታን ለመደገፍ/የጡረታ ስርዓት የገንዘብ ድጋፍ እና ፖሊሲ IGS፣ አዳዲስ የትምህርት ቴክኖሎጂዎች። አስተያየቶቹ የሚቀርቡበት ቀነገደብ ረቡዕ፣ ዲሰምበር 17 እና ሰኞ፣ ጃንዋሪ 26 ድረስ መቅረብ አለባቸው።
ረቂቅ ፖሊሲዎቹን ይመልከቱ እና አስተያየት ይስጡ።
|
|
|
የራሳችንን ለመምረጥ ድምጽ ይስጡ!
ባለፈው ወር የትምህርት ቦርድ ቤተሰቦች በትምህርት ዘርፍ አጋር ሆነው የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና በማክበር እና ትምህርት ቤቶች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች የተማሪዎችን ትምህርት እና ደህንነት በመደገፍ ረገድ ያላቸውን የጋራ ኃላፊነት በማንፀባረቅ ብሔራዊ የቤተሰብ ተሳትፎ ወርን አክብሯል። በእርግጥ፣ የቤተሰብ ተሳትፎ መምሪያ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ኤቨረት ዴቪስ፣ ለኮንስታንቲኖ የቤተሰብ ተሳትፎ ባለሙያ ሽልማት ከዘጠኙ የመጨረሻ እጩዎች አንዱ ናቸው። ተጨማሪ ያንብቡ እና ድምጽ ይስጡ።
|
|
|
ስለ አዲሶቹ የደህንነት ፕሮቶኮሎች ማሳሰቢያ
MCPS ደህንነትን በሚመለከት መጨረሻ መስመር ላይ እየተቃረብን ነው፣ ስለሆነም ሁላችንም ከባድ ክስተት በሚፈጠርበት ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለብን በማወቅ እና ወደሚመለከታቸው በማስተላለፍ ኃላፊነት እንጋራለን። ከዚህ የትምህርት ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ፣ MCPS ለአደጋ ጊዜ ክስተቶች አዲስ መደበኛ የምላሽ አሰጣጥ ፕሮቶኮል (SRP) ሲጠቀም ቆይቷል። አዲሶቹን ፖስተሮች በመማሪያ ክፍሎች፣ በቢሮዎች፣ እና በሁሉም MCPS ሕንፃዎች ውስጥ ተመልክተው ይሆናል። አዲሶቹ ፖስተሮች አምስቱን SRP እርምጃዎች በግልጽ ያሳያሉ፡ መረጋጋት፣ መስኮቶች እና በሮችን መዝጋት/መሸሸግ፣ መቆለፍ፣ ከቦታው መልቀቅ እና መጠለያ ማግኘት። ስለእነዚህ እርምጃዎች የበለጠ ያንብቡ።
|
|
|
ለትምህርት ቤቶቻችን ደህንነት ቅድሚያ መስጠት
ባለፈው ሳምንት፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቡድኖች ስፕሪንግብሩክ እና ደማስከስ ትምህርት ቤቶች የሚገኙበትን ክለስተሮች ጎብኝተዋል። ዲስትሪክቱ በዚህ ወር የሠራተኞችን የበፊት ታሪክ ፍተሻ፣ የጣት አሻራ፣ እና የባጅ መስጠት ሂደትን ለማጠናቀቅ በትክክለኛው መንገድ ላይ ይገኛል። ከዚህ በታች እስካሁን ድረስ ስለተከናወነው ሂደት ወቅታዊ መረጃ ይገኛል፣ ይህም እንደገና ማጣሪያ ያጠናቀቁ ሠራተኞችን ቁጥር የሚያንፀባርቅ ነው።
ሜትሪክ/Metric |
ቫልዩ/Value |
እስከ ዛሬ እንደገና ማጣራት የተደረገላቸው ጠቅላላ ሠራተኞ ብዛት |
8,583 |
% የተጠናቀቀ የትምህርት ቤት ሠራተኞች |
70% |
# የተጠናቀቀ የትምህርት ቤቶች ብዛት |
202/211 |
|
|
|
ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
-
SMOB ምን ያደርጋል?፡ ማክሰኞ፣ ዲሰምበር 16 ከሰዓት በኋላ 6-7:30 p.m. የሚካሄድ ቨርቹዋል ስብሰባ። ስለ ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል (SMOB) የምርጫ ሂደት እና SMOB ምን እንደሚያደርግ ግንዛቤ ያግኙ።
-
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሳይንስ ትርኢት፦ ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳይንቲስቶች እና መሐንዲሶች ስራቸውን ለማሳየት እና የገንዘብ ሽልማቶችን ለማግኘት የመወዳደር እድል ይሰጣል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
-
በግልጽ ይናገሩ፤ ሕይወት ያድኑ፦ በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች የኦፒዮይድ/ፌንታኒል አላግባብ መጠቀምን እና ከመጠን በላይ የመውሰድን አደጋዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ኦሪጅናል ቪዲዮ በመፍጠር ሕይወት አድን ትምህርት ሰጪ የሆነ ማስገንዘቢያ ያቅርቡ። የመጨረሻው ቀነገደብ፦ እሁድ፣ ጃኑዋሪ 4, 2026ነው።
-
ሲ-ስፓን ተማሪካም ውድድር "C-SPAN StudentCam Competition"፡ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ከውድድሩ ጭብጥ ጋር በተያያዘ "ከነፃነት መግለጫ ጋር በማነጻፀር የአሜሪካን ታሪክ ማሰስ"/“Exploring the American Story through the Declaration of Independence.” በሚል ርዕስ ላይ የቪዲዮ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። ከፍተኛው ሽልማት $5,000 ነው። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 20, 2026 ነው።
-
ስለ ጥቁሮች ታሪክ ንግግር የሚደረግበት ውድድር "Black History Oratory Contest"ይህ የድርሰት ጽሑፍ ውድድር 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ክፍት ነው። ሃያ የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች የሽልማት ገንዘብ ለማሸነፍ ድርሰቶቻቸውን በቀጥታ ታዳሚዎች ፊት እንዲያነቡ ይጋበዛሉ። የመጨረሻ ቀነገደብ እሑድ፣ ጃኑዋሪ 25፣ 2026ነው።
-
"Choose Respect Video Contest"/አክብሮትን መምረጥ የቪዲዮ ውድድር ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው፣ ይህ ውድድር ታዳጊዎች በወጣቶች መካከል ስለ ፍቅር ጓደኝነት ጥቃት ግንዛቤ ለማዳበር የሚረዳ ኦሪጅናል ቪዲዮ እንዲፈጥሩ ያበረታታል። ቪዲዎችን የሚያዘጋጁት በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ያስገኛል። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ እሑድ፣ ፌብሩዋሪ 15, 2026 ነው።
-
የአሜሪካ የመስክ ጉዞ/"America’s Field Trip"፦ ይህ ውድድር 3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች አሜሪካ ለእነርሱ ምን ማለት እንደሆነ ያላቸውን አመለካከት ለማካፈል ጽሑፍ ወይም የስነጥበብ ስራ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል — እና ታሪካዊ እና ባህላዊ ምልክቶች ያሏቸእው የመስክ ጉዞ ልምዶችን ተጉዘው የማየት እድል ያገኛሉ። የመጨረሻ ቀነገደብ፡ ማርች 30, 2026ይሆናል።
|
|
|
ከዜና አምዳችን
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
|
|