አበይት ጉዳዮች
ኦገስት 21, 2025
|
|

|
የመጀመሪያው የትምህርት ቀን ሊጀመር አምስት ቀናት ቀርተዋል—መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
ወደ አዲሱ የትምህርት አመት እንኳን ደህና መጣችሁ! ከሽግግር ቀንን ጨምሮ ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት አሰጣጥ እና ስለ ተማሪዎች ደህንነት የተደረጉ የመመሪያ ለውጦችን በሚመለከት፥ ሳምንታዊው "የሀሙስ መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች" ቤተሰቦች አዲሱን የትምህርት አመት ለመቀጠል እንዲችሉ ማወቅ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል። ሳምንታዊ መረጃዎቻችን እንዳያመልጥዎት!
|
|
|
ወደ ት/ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ | የትምህርት ቤት ግንኙነት መድረክ | የሽግግር ቀን | የተማሪ ስነምግባር ደንብ/ኮድ | ስለ ውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት ማድረግ | በት/ቤት ስለ ሞባይል ስልክ አጠቃቀም | ስለ ዳራ ማንነት ማጣራት ወቅታዊ መመሪያ | Vape መመርመሪያ መሣሪያ | ስለ ት/ቤቶች የአውቶቡስ መስመሮች | "ሪፍሪጅሬተር ከሪኩለም" | የትምህርት ቤት መጀመሪያ ቀን ፎቶዎች | ስለ FARMS ማመልከቻ | ወደ ት/ቤት መመለሻ ወቅት ላይ አስፈላጊ ክትባቶች | ከዘገባዎች አምድ
|
|
ቅዳሜ፣ ኦገስት 23 ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢት ላይ ይቀላቀሉን
MCPS ቅዳሜ ኦገስት 23 ከጠዋቱ 10 a.m.–1 p.m. አመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ ያስተናግዳል።
አድራሻ፦ Westfield Wheaton mall, 11160 Veirs Mill Road in Wheaton. ይህ የነጻ ዝግጅት ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን፣ መዝናኛዎችን፣ እና የክትባት ክሊኒክ፣ እንዲሁም በደርዘን የሚቆጠሩ የትምህርት ቤት ቢሮዎች እና ዲፓርትመንቶች፣ እና በካውንቲ ስለሚከናወኑ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች መረጃዎችን እና ግብአቶችን ማግኘት ይችላሉ።
MCPS ከፌርግራውንድ ከዊተን፣ ከጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ ከሞንትጎመሪ ብሌር፣ ከፔይንት ብራንች እና ከሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ነጻ የማመላለሻ አውቶቡሶችን ያቀርባል።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
|
Remind፣ ParentSquare፣ ParentVUE — ልዩነቱ ምንድን ነው?
ቤተሰቦች ከት/ቤቶች ጋር ግንኙነት ለማድረግ ብዙ ጊዜ የተለያዩ መድረኮች መኖራቸውን ይሰማሉ፣እና በዚህ ግራ መጋባት እንዳለ እንገነዘባለን። ፈጣን መመሪያ እነሆ።
|
|
|
ስለ ሽግግር ቀን ጥያቄዎች አሉ? መልስ ለመስጠት ተዘጋጅተናል!
ሰኞ፣ ኦገስት 25 ቀን MCPS በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተማሪ የሽግግር ቀን ያካሂዳል፣ ቀኑን ሙሉ፣በክፍል ትምህርት የማይሰጥበት የትምህርት ቤት ልምድ የሚያገኙበት፣ ወደ አዲስ የት/ቤት ደረጃ የተሸጋገሩ ወይም ወደ አዳዲስ ህንፃዎች የሚገቡትን ተማሪዎች ሽግግር ለማቃለል የታለመ ነው። ለሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሳቸው በፊት የትምህርት ቤት ውሎን ለመሞከር እና ለመዘጋጀት ጥሩ ቀን ይሆናቸዋል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ
|
|
|
ምን አዲስ ነገር አለ? እና ለምን አስፈላጊ ሆነ?
ተማሪዎች በት/ቤት ደህንነት እንዲሰማቸው፣ የት/ቤት አካል እንደሆኑ እና የትምህርት ቤት ድጋፍ እንዳላቸው ለማረጋገጥ፣
2025–2026 የትምህርት አመት MCPS የተማሪ የስነምግባር ደንብ ተሻሽሏል። ለውጦቹ፦ ለተማሪዎች የስነምግባር ደንቡን ለመረዳት ቀላል ማድረግ እና በዲስትሪክቱ ውስጥ የሚፈጠሩ ደንብ የመጣስ ክስተቶችን መደበኛ የምርመራ እና እርምጃ የመውሰድ አፈጻጸም ሂደት ማቋቋምን ያካትታሉ። ይህ ሰነድ ከተማሪ ባህሪ የሚጠበቁ ነገሮችን እና የተለያዩ ፖሊሲዎችን፣ ደንቦችን እና ደንቦችን መጣስ የሚያስከትለውን መዘዝ ይዘረዝራል። ትኩረቱ ተማሪዎች ከስህተቶቻቸው እንዲማሩ፣ የደረሰ ጉዳት እንዲጠገን፣ እና በራስ መተማመን እንዲኖር ለመርዳት ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
2025–2026 የስነምግባር ደንብ ስለማክበር
|
|
|
በትምህርት የውጤት አሰጣጥ ስሌት አሠራር ላይ ለውጦች ይደረጋሉ።
በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችየትምህርት ውጤት አሰጣጥ ስሌት እና ሪፖርት አሰጣጥ ላይ አስፈላጊ ክለሳዎች የተደረጉ ስለሆነ በዚህ የትምህርት አመት ተፈጻሚ ይደረጋሉ። ከ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የማጠናቀቂያ ውጤቶች ስሌት የሚሠራው በአራቱ የማርክ መስጫ ወቅት አማካይ ውጤት ላይ ተሞርኩዞ ይሆናል። ይህ ለውጥ፣ ከሌሎች ሁኔታዎች ጋር፣ ወጥነት ያለው አሠራር ለማዳበር፣ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ የሚጠበቅባቸውን ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው ለማጠናከር እና በትምህርት ቤት ውስጥ ትክክለኛ የተማሪዎችን የትምህርት ችሎታ ለመለካት የተነደፈ ነው።
በተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
|
|
|
አነስተኛ የስልክ ጊዜ = ተጨማሪ የመማሪያ ጊዜ
2025–2026 የትምህርት አመት፣ MCPS በትምህርት ቀን እንዴት የግል ሞባይል ስልኮችን/መሳሪያዎችን መጠቀም እንደሚቻል ገደብ አስቀምጧል። በትምህርት ክፍለ ጊዜ ወቅት የስልክ መጠቀምን መገደብ ተማሪዎች እንዲያተኩሩ፣ እንዲሳተፉ እና መረጃን የበለጠ መያዝ እንዲችል ይረዳል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
"Away All Day" በራሪ ወረቀት
|
|
|
የተማሪዎች ደኅንነት ቅድሚያ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው፡ እያደረግን ያለነውን ይመልከቱ።
ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የዋና ኢንስፔክተር ፅህፈት ቤት የቅርብ ጊዜ ግኝቶች፦ የት/ቤት ሰራተኞች፣ የስራ ተቋራጮች እና በጎ ፈቃደኞች የበፊት ዳራ እንዴት እንደሚጣራ እና ክትትል እንደሚደረግ መሻሻል ያለባቸውን ሁኔታዎች በነቂስ አሳይተዋል። ልጆችዎ በትምህርት ቤት ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው፣ እና በዚያው ሁኔታ መቆየቱን ለማረጋገጥ አፋጣኝ እና ቀጣይነት ያለው እርምጃ እየወሰድን ነው።
እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
|
|
|
በትምህርት ቤቶች ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ አካባቢ እንዲኖር ማድረግ
የትምባሆ ማጬሻ እቃዎች፣ የትምባሆ ምርቶች፣ እና ህገወጥ መድሃኒቶች/አደንዛዥ እጾች በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የተከለከሉ ናቸው። እነዚህን እቃዎች ይዘው ወይም ሲጠቀሙ የተገኙ ተማሪዎች MCPS የተማሪዎች የስነምግባር ደንብ መሰረት የቅጣት እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል። MCPS በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች መፀዳጃ ክፍሎች ውስጥ የትምባሆ እና ሌሎች የተከለከሉ መድኃኒቶችን ማጬሻ እቃ ይጠቀሙ እንደሆን የሚለይበት የመቆጣጠሪያ መሣሪያዎችን አስቀምጧል። እነዚህ የፍተሻ መሣሪያዎች ያስፈለጉበት ምክንያት በትምህርት ቤቶች ውስጥ የቫፕ መሳሪያ እንዳይጠቀሙ ያለውን ችግር ለመፍታት እና ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለጎብኝዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የመማሪያ አካባቢን ለመጠበቅ ለት/ቤት አስተዳዳሪዎች ጠቃሚ የመቆጣጠር አገልግሎት እንዲሰጡ ነው። እነዚህ የፍተሻ መሣሪያዎች የኒኮቲን እና THC (በማሪዋና ውስጥ ያለ ንጥረ ነገር) ጨምሮ የሚጬስ ጠረን ለመለየት ጠቃሚ ናቸው።
ስለ VAPE ዘወትር የሚቀርቡ ጥያቄዎች
|
|
|
የአውቶቡስ መስመርዎን ያግኙ — 1, 2, 3 ቀላል ነው!
የ 2025-2026 የትምህርት አመት የአውቶቡስ መስመሮች አሁን ተዘጋጅተዋል 1, 2, 3 የአውቶቡስ መስመርዎን ማግኘት ቀላል ነው! እንዴት እንደሆነ ከዚህ ይወቁ።
|
|
|
ልጅዎ በክፍል ውስጥ የሚማረው/የምትማረው ምንድነው? ማወቅ ያለብዎት ነገር እነሆ
ሥርዓተ ትምህርቱን የበለጠ ግልጽ እና ለቤተሰብ አመቺ ለማድረግ MCPS አዲስ ተነሳሽነት አዘጋጅቷል። ከዚህ የትምህርት አመት ጀምሮ፣ ቤተሰቦች በዋና ዋና የትምህርት ጭብጦች እና ተማሪዎች በእያንዳንዱን የማርክ መስጫ ጊዜ የሚያጠኑት ቀላል ባለ አንድ ገፅ አጠቃላይ ገፅታ ያለው መረጃ ያገኛሉ — በቅፅል ስሙ "ሪፍሪጅሬተር ከሪኩለም" ይባላል፥ ምክንያቱም በፍሪጅ ላይ በቀላሉ ለጥፎ ለማየት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ተጨማሪ ማስገንዘቢያ.
|
|
|
የመጀመሪያ ቀን ምርጥ ፎቶ ላኩልን!
ልዩ ሁኔታዎችን በማጋራት የመጀመሪያውን የትምህርት ቀን ደስታ እንድናበስር ያግዙን! ወላጆች እና ተማሪዎች ማክሰኞ፣ ኦገስት 26 የሚወዱትን የት/ቤት የመጀመሪያ ቀን አጓጊ ገፅታዎችን ፎተግራፎች እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። ፎቶዎቹ ከማክሰኞ ጠዋት ጀምሮ በዲስትሪክቱ ድረ-ገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይጋራሉ። በኢሜል በመላክ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መለያ በመስጠት ፎቶ ማጋራት ትችላላችሁ።
|
|
|
ስለ ምሳ ማወቅ ያለብዎትን ነገር ሁሉ ያገኛሉ
2025–2026 የትምህርት አመትየነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦች (FARMS) ማመልከቻ እዚህ ይገኛል። በእያንዳንዱ የትምህርት ዓመት አዲስ FARMS ማመልከቻ መቅረብ አለበት። ለፕሮግራሙ ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች ምግብ ነፃ ነው። በአንድ ቤተሰብ ለሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች የሚያስፈልገው አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
የቁርስ እና የምሳ ዝርዝርMySchoolBucks ላይ ስለሚገኝ በልጅዎ አካውንት ላይ ገንዘብ እንዴት እንደሚጨምሩ መረጃ ለማግኘት "Department of Food and Nutrition and Services" ድረገጽ ላይ ይመልከቱ።
|
|
|
ስለ ክትባቶች እንዳይረሱ!
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጆች በካውንቲ የተለያዩ ቦታዎች እስከ ሴፕቴምበር ድረስ ወደ ትምህርት ቤት የሚመለሱ ልጆችን ክትባቶች በነፃ ይሰጣል።
ተጨማሪ መረጃ
|
|
|
የዘገባዎች አምድ
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|