የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ፌብሩዋሪ 19, 2026

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

ከበረዶ ቀናት በኋላ 2025–2026 የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያ ተስተካክሏል።

ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 19፣ በሥራ ስብሰባው ወቅት፣  የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ጃኑዋሪ መጨረሻ እና በፌብሩዋሪ መጀመሪያ ላይ ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ በርካታ የት/ቤቶች መዘጋትን ተከትሎ በ 2025-2026 የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ ላይ የቴክኒክ ለውጦች መደረጋቸውን ተቀብሏል። እነዚህ ለውጦች ቤተሰቦች ማወቅ የሚያስፈልጋቸውን ወቅታዊ መረጃዎች ያካትታሉ።

የሜሪላንድ ስቴት ሁሉም የሕዝብ ትምህርት ቤቶች በየዓመቱ 180 የትምህርት ቀናትን እንዲያስተምሩ ይደነግጋል። በአየር ሁኔታው ​​ምክንያት በመዘጋቱ ፣ MCPS ይህንን የስቴት መስፈርት ለማሟላት አራት የትምህርት ቀናትን ማካካስ አለበት። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

ጠመንጃን ወይም ሽጉጥን በጥንቃቄ ማስቀመጥ ሕይወት ያድናል።

የጠመንጃ/የሽጉጥ ጥቃት ሲፈፀም እና ማህበረሰባችንን ሲያውክ በተለይም በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ተጽእኖው ሁሉንም ሰው ይሰማዋል፣ ትምህርት ቤቶቻችን ሁልጊዜ ለመማር እና ለማደግ ምቹ የሆኑ አስተማማኝ ቦታዎች መሆን አለባቸው። ኃላፊነት የተሞላበት የጠመንጃና የሽጉጥ በጥንቃቄ መያዝ በእያንዳንዱ ማህበረሰብ ውስጥ የተማሪዎችን እና የቤተሰቦችን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። የልጆቻችንን ሠላም እና ደህንነት የሚነካ አንድ ወሳኝ ጉዳይ ላይ ትኩረትዎን ለመሳብ እንፈልጋለን። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በህጻናት እና በወጣቶች ላይ ለሚደርሰው ሞት የህፃናት እና የታዳጊዎች (ከ 1-19 ዓመት ዕድሜ ያላቸው) ከጦር መሣሪያ ጋር የተያያዙ ጉዳቶች ዋነኛ መንስኤ ናቸው። ይበልጥ ያንብቡ።

የትምህርት ቦርድ የተሻሻለውን የበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት አጽድቋል።

ዛሬ፣ ፌብሩዋሪ 19፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለበጀት ዓመት 2027 $3.78 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት አጽድቋል። በሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ W. ቴይለር የቀረበው የተሻሻለው የበጀት ረቂቅ ሀሳብ አሁን ካለው ወጪ ጋር ሲነጻጸር 5.2% ጭማሪ መኖሩን ያመለክታል።

የመጀመሪያው የበጀት ረቂቅ ዲሰምበር ወር ላይ ከቀረበ በኋላ MCPS ከአካባቢው የካውንቲ ታክስ ገንዘብ ጥያቄ $331,161 ዶላር ቀንሷል። ይህ ቅነሳ የተደረገው የትምህርት ቤት መሪዎች በማህበረሰብ ስብሰባዎች ወቅት በተሰጡ የግብረ መልስ አስተያየቶች ምክንያት ማስተካከያዎችን ካደረጉ በኋላ ቢሆንም ስቴቱ መጀመሪያ ከተጠበቀው በላይ ድጋፍ እየሰጠ ነው። ይበልጥ ያንብቡ።

ሶስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች AI - የተደገፈ የደህንነት መሳሪያን ሙከራ ሊያካሄዱ ነው።

MCPS የትምህርት ቤቶችን ደህንነት ለማጠናከር በሚያደርገው የጥረት አካል፣ ዲስትሪክቱ ከሶስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር የአንድ ወር የሙከራ ፕሮግራም ይጀምራል —እነዚህም ቤተዝዳ -ቼቪቼዝ፣ ኮ/ል ዛዶክ ማግሩደር፣ እና ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ናቸው። የሙከራ ፕሮግራሙ ሰኞ፣ ማርች 2 እንደሚጀመር ታቅዷል።

ይህ የደህንነት ቴክኖሎጂን ለመሞከር የሚከናወን፣VOLT-AI፣ ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ግብረ መልስ ለማግኘት እና ሰራተኞች እና ትምህርት ቤቱ የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ስራ የሚደግፍ መሆኑን ለማረጋገጥ እና ለመወሰን የታቀደ ለአጭር ጊዜ የሚካሄድ ሙከራ ነው። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ማርች ወር ላይ ይጀመራል።

የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ሰኞ፣ ማርች 9 ይጀመራል። ስለ ምዝገባ መረጃ ለማግኘት፣ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን ካውንስለር ማነጋገር አለባቸው። ስለ መርሃ ግብሮቹ እና ክፍያዎችን በተመለከተ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ያንብቡ። 

አስተያየትዎን ይስጡ፦ ስለ ት/ቤቶች ወሰን ምክረ ሀሳቦችን ለማግኘት የታቀዱ የህዝብ አስተያት መስጫ መድረኮች ላይ በመሳተፍ አስተያየትዎን ይስጡ።

ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር የቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ስለ መክፈት የተሻሻለ አማራጭ B እና የቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ስለ ማዛወር የተሻሻለ አማራጭ H ጭምር የተለያዩ የድንበር ጥናት ሀሳቦችን አቅርበዋል። በተጨማሪም ለተማሪዎች የፕሮግራሞችን ተደራሽነት የበለጠ የሚያሰፋ የሪጅናል ሁለተኛ ደረጃ ሞዴል አቅርበዋል። ይበልጥ ያንብቡ።

የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ወቅታዊ መረጃ፦ ጊዜያዊ ውጤቶች ማርች 6 ላይ ይወጣሉ።

ተማሪዎች ወደ ሦስተኛው የማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ አጋማሽ እየተቃረቡ ናቸው። የማርክ መስጫ ክፍለጊዜው የተጀመረው ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 3 ነው። የቅርብ ጊዜው የበረዶ ክስተት በማርክ መስጫ ክፍለጊዜ የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ባሉት ቀናት ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል። በዚህም ምክንያት፣ መምህራን ለማስተማር ወደ ክፍል የሚገቡበት የጊዜ ገደብ እስከ ማክሰኞ፣ማርች 3 እንዲሆን ተስተካክሏል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲሱ MSDE የሂሳብ ትምህርት ፖሊሲ ​​ማለት ምን ማለት ነው?

ፌብሩዋሪ 5 በካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ፣ MCPS የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ (MSDE) የሂሳብ ትምህርት ፖሊሲን ማጠቃለያ ለቦርዱ አቅርቧል። አዲሱ ፖሊሲ ከቅድመ-መዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል የሂሳብ ትምህርትን ለማጠናከር እና ለማዘመን የታለመ ነው። ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዋና ዋና ነገሮች የተሻሻሉ የትምህርት ደረጃዎችን፣ የነባራዊውን ዓለም ችግሮችን ለመፍታት የሂሳብ ትምህርትን መጠቀም ላይ የበለጠ ትኩረት መስጠት፣ የተቀናጀ የአልጀብራ ትምህርት፣ በየቀኑ 60 ደቂቃ የሚፈጅ ከመዋእለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል (K-8) የሂሳብ ብሎኮችን እና ተማሪዎችን የላቀ የኮርስ ስራ እና ለወደፊት ስራዎች ለማዘጋጀት ባለብዙ እርከን የማስተማር ድጋፍ ስርዓትን ያካትታሉ። ይህ ሁሉ ለተማሪዎችና ለቤተሰቦች ምን ማለት ነው? እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.

የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ አሁን ክፍት ነው

2026-2027 የትምህርት አመት፣ የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ አሁን ክፍት ሲሆን ParentVUE portal ፖርታል ላይ በኦንላይን ማስመዝገብ ይቻላል። ሴፕቴምበር 1, 2026 ድረስ 5 ዓመት የሚሞላቸው ልጆች ብቁ ናቸው። ቤተሰብዎ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ ከሆኑ፣ እዚህ PreentVue አካውንት መክፈት ያስፈልግዎታል። አካውንት ከከፈቱ በኋላ፣ መጀመሪያ ሲከፍቱት ማስመዝገብ ይችላሉ።

ሰኞ፣ ማርች 16 ጀምሮ የምዝገባ ክፍለ ጊዜዎች በአካል ይካሄዳሉ። ትምህርት ቤቶች ስለ መዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ ተጨማሪ መረጃዎችን ለቤተሰቦች ያጋራሉ። ወደ መዋእለ ህጻናት እና አንደኛ ክፍል ቀደም ብሎ የሚገቡ ተማሪዎችን ለማስመዝገብ ሰኞ፣ ማርች 9 ይከፈታል።

ለቤተሰቦች የሚደረግ ድጋፍ፦ የሚቀጥለው ሳምንት የልዩ ትምህርት ዝግጅቶች

የግል የትምህርት ፕሮግራም (IEP) ላለው/ላላት ልጅዎ ግብዓቶችን ይፈልጋሉ? ከማህበረሰብ ድርጅቶች ወይም ከሌሎች MCPS IEP የሚማሩ ተማሪዎች ወላጆች ጋር መገናኘት ይፈልጋሉ? የሚፈልጉ ከሆነ፣ ይህ ለእርስዎ የሚጠቅም ዝግጅት ነው! ረቡዕ፣ፌብሩዋሪ 25 ቀን ከቀኑ 5-7 p.m. ሮክቪል በሚገኘው ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል አዳራሽ "Carver Educational Services Center auditorium, 850 Hungerford Drive in Rockville" 850 በሚካሄደው የልዩ ትምህርት የዊንተር ሪሶርስ አውደ ርዕይ ላይ ለመገኘት እቅድ ያዘጋጁ።

በሌላ የልዩ ትምህርት ዘገባ ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 26 ከቀኑ 7-8:30 p.m. በሚካሄደው "February Special Education Citizens Advisory Committee (SECAC)" Zoom meeting ዙም ስብሰባ ላይ ይሳተፉ። የስብሰባው አጀንዳ እና የዙም/Zoom መረጃ እስከ ፌብሩዋሪ 23 ድረስ የቤተሰብ ድጋፍ ማዕከል ድረ-ገጽ ላይ ይለጠፋል

ማርች 11 ቀን SAT ፈተና ለመውሰድ ተዘጋጁ፦ Ready, Set, SAT: March 11 Is Test Day

SAT የትምህርት ቀን በፍጥነት እየተቃረበ ነው! MCPS ዓመታዊውን የትምህርት ቤት SAT ፈተና ረቡዕ፣ ማርች 11 ያካሂዳል። ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር ተማሪዎች (2023-2024 የትምህርት አመት ለመጀመሪያ ጊዜ 9ኛ ክፍል የገቡ ተማሪዎች) በዚህ ቀን SAT ፈተና መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። MCPS ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተማሪዎችን ወጪ ይሸፍናል። ይበልጥ ያንብቡ።

የማሰላሰልና እውቅና የሚሰጥበት ወር

የትምህርት ቦርድ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጥቁሮች ታሪክን ቁርጠኝነት፣ ጽናትና፣ ዘላቂነት ቅርስ በመዘከር ኩራት ይሰማዋል። ትምህርት መማር፣ አመራር እና ማህበረሰቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰባሰቡት "Scotland A.M.E. Zion Church in Potomac. "ፖቶማክ በሚገኘው የስኮትላንድ A.M.E. ጽዮን ቤተክርስቲያን ነበር። የቀደምት አባቶች ያስተጋቡትን ድምፅ ይመልከቱ

የታሪክ ውርስና ቅርስ የካርቨር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ቅርስና ውርስ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ይህም ለትውልዱና ለተማሪዎች የኩራት፣ የስኬት፣ እና የማህበረሰብ መሰረት በመሆን ይዘከራል።

የትምህርት ቦርድ ምክትል ፕሬዝዳንት ብሬንዳ ዎልፍ ስለ ጥቁሮች ታሪክ ወር እና የጥቁሮችን ልህቀት በመዘከር አንፀባርቀዋል። እዚህ ይመልከቱ: እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish

እንዲሁም፣ አመራር፣ ውክልና እና ቤተሰብ በየቀኑ ተማሪ አትሌቶችን እንዴት ሊያነሳሳ እንደሚችል በጉልህ ያሳዩትን የእናት እና የሴት ልጃቸውን "duo Dessalyn and Dasia Dillard" ታሪክ ያንብቡ 

በተጨማሪ የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ የነበረውን የአንድሬ ዊዝ/Andre Wise ታሪክ ያንብቡ፣ እሱም ተጠራጣሪነት እና እርግጠኛ አለመሆንን ወደ ቁርጠኝነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት መቀየር የቻለ ቆራጥ ግለሰብ ነው።

ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

በኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሶፎሞር ተማሪ ልኡል ዳዊት/Leul Dawit, እና ዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር ተማሪ ሬሜይ ገርሜይ/Reemey Ghermay 49ኛው የትምህርት ቦርድ (SMOB) የተማሪ አባል ለመሆን የመጨረሻ እጩዎች ናቸው። ምርጫ የሚካሄደው ረቡዕ፣ ኤፕሪል 22 ነው። ተጨማሪ ያንብቡ

አሁን ማወቅ ያለብዎት ጉዳይ፦ ሁሉንም ተማሪዎች በደስታ እንቀበላለን

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተወሰደ ያለው የፌዴራል የኢሚግሬሽን እርምጃ ለብዙ ቤተሰቦች በተለይም በልጆችና በትምህርት ቤት ጉዳይ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል። የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ለእያንዳንዱ ልጅ ደህንነታቸው የተጠበቁ ቦታዎች ናቸው። MCPS ተማሪዎች በሚመዘገቡበት ወቅት ወይም በማንኛውም ጊዜ ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታ አይጠይቅም፣ እና የተማሪዎች ግላዊ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

ከጨዋታ በላይ ነው፡- የባለቤትነትን ስሜት መገንባት

በዚህ የጸደይ/ስፕሪንግ ወቅት፣ ሁሉንም 25 የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአካታችነት፣ በቡድን ስራ፣ እና በእድገት ላይ ያተኮረ የዩኒቨርሲቲ ስፖርት ምልመላ ይካሄዳል። ተማሪ አትሌቶች በራስ መተማመንን፣ ጓደኝነትን እና የትምህርት ቤት ወዳጅነትን ይገነባሉ፤ በተመሳሳይ ጊዜ ቫርስቲ ደብዳቤዎችን ያገኛሉ እንዲሁም ለሻምፒዮና ይወዳደራሉ። ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ParentVUE ላይ መመዝገብ ይችላሉ፤ ወይም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የትምህርት ቤታቸውን የአትሌቲክስ ዳይሬክተር ማነጋገር ይችላሉ።

በሌላ የአትሌቲክስ ዘገባ፣ ሐሙስ፣ ማርች 19 ለሚካሄደው የተማሪ-አትሌቶች የአመራር ኮንፈረንስ ምዝገባ ተጀምሯል/ተከፍቷል። ይህ ኮንፈረንስ የአመራር ደረጃቸውን ከፍ ለማድረግ፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለማሰማት እና ከሌሎች የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አትሌቶች እና ከሜሪላንድ አትሌቶች ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ለሆኑ 9ኛ፣ 10ኛ እና 11ኛ ክፍል ተማሪ-አትሌቶች ሁሉ ክፍት ነው። ለመመዝገብ የአትሌቲክስ ዳይሬክተርህ(ሽ)ን ማነጋገር ያስፈልጋል።

እና፣ ከዛሬ (ፌብሩዋሪ 19) እስከ ፌብሩዋሪ 21 ድረስ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚካሄደው ቫርሲቲ የካውንቲ ሬስሊንግ ሻምፒዮና ቲኬቶችን ያግኙ። 

ማሳሰቢያ

ቪዡዋል እና የኪነጥበብ ዝግጅቶች እየመጡ ነው!

እነዚህ ዝግጅቶች እንዳያመልጥዎት። ለሁሉም የሚሆን ጠቃሚ ዝግጅት ይኖራል!

  • አርብ፣ ፌብሩዋሪ 20 ከቀኑ 7 p.m., በሞንትጎመሪ ኮሌጅ የባህል ስነጥበባት ማዕከል፣ ሲልቨር ስፕሪንግ ካምፓስ፣12ኛው አመታዊ የዳንስ ትርኢትይካሄዳል። አድራሻ፦ Montgomery College’s Cultural Arts Center, Silver Spring campus, 7995 Georgia Avenue.ለሕዝብ የሚቀርቡ ትኬቶች ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 14 ላይ ይገኛሉ።

  • ረቡዕ፣ ፌብሩዋሪ 25 ከቀኑ 7:30 p.m., የጌይትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ኦነርስ መዘምራን ኮንሰርትይካሄዳል። 

  • አርብ፣ ፌብሩዋሪ 27 ከቀኑ 6 p.m. የአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ድራምላይን ትርኢት ያቀርባሉ። 10 በላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድረምላይንስ ያካትታል። ቲኬቶች የሚሸጡት $5 ዶላር ሲሆን በር ላይ ይገኛሉ።

አስደናቂ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አርቲስቶች ማርች እና ኤፕሪል ላይ የማህበረሰብ ትርኢቶችን ያቀርባሉ። በካውንቲው ውስጥ የሚገኙ የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ቅርንጫፎች ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) ተማሪዎች የተውጣጡ የጥበብ ስራዎች የሚቀርቡባቸውን እነዚህን ትርኢቶች ያስተናግዳሉ። እያንዳንዱ ትርኢት ለብዙ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የመዝጊያ ግብዣም ይኖራል። ሶስት ትርኢቶች ይካሄዳሉ፡-

  • አፕካውንቲ፡ማርች 11–15፣ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ የጀርመንታውን ካምፓስ፣ አድራሻ፦ Montgomery College Germantown Campus, 20200 Observation Drive, Germantown

  • ሚድካውንቲ፡ ኤፕሪል 8–10፣ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ሮክቪል ካምፓስ፣ አድራሻ፦ ontgomery College, Rockville Campus, 51 Mannakee St., Rockville

  • ዳውንካውንቲ፡ ማርች 18–25፣ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ ሲልቨር ስፕሪንግ ካምፓስ፣ አድራሻ፦ Montgomery College Silver Spring Campus, 930 King St., Silver Spring

ተጨማሪ መረጃ

የቀጥታ ቲያትር ማሳየት ተመልሷል! From Alice in Wonderland to Annie, Jr. እና ሌሎችም ብዙ የሚታዩ ነገሮች ይኖራሉ፣ በአቅራቢያዎ የሚገኝ ትርኢት ለማወቅ Fine Arts calendar ወይም የትምህርት ቤትዎን ድረ ገጽ ይመልከቱ። 

ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች

  • ዲሲ ዩናይትድ አንድ ይግዙ፣ አንድ በነፃ ያግኙ/D.C. United Buy One, Get One Free፦ ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 21 ከፊላደልፊያ ዩኒየን ጋር ለሚደረገው የዲሲ ዩናይትድ የመክፈቻ ጨዋታ ትኬት የሚገዙ ተማሪዎች ነፃ ትኬት ያገኛሉ። የቲኬቶች ዋጋ $32 ጀምሮ ይሸጣል። እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish

  • ስልክ ያቁሙ፣ ትኩረት ይስጡ፦ በሚል ርዕስ የእግረኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ትምህርት ሰጪ የሆነ 30 ሰከንድ ቪዲዮ ያዘጋጁ። በእግር ስትጓዙ፣ መኪና፣ ወይም ብስክሌት ስትነዱ በስልክዎ ላይ ሳይሆን በአካባቢዎ ዙሪያ ላይ ማተኮር አስፈላጊመሆኑን ይገንዝቡ። በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። Macbook Air ወይም በመቶዎች የሚቆጠሩ የስጦታ ቪዛ ካርድ ማሸነፍ ይችላሉ። መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 28ነው።

  • የላቲኖ ሌጋሲ ኮንፈረንስ፡ ቅዳሜ፣ ማርች 7 በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። ኔትወርኪንግ፣ ወርክሾፖች፣ ዋና ንግግር የሚያቀብ እንግዳ፣ የፓናል ውይይት እና ትርኢቶችን ያካትታል። ይመዝገቡ/Register. 

  • «ከንቲባ ብሆን ኖሮ»/If I Were Mayor” የድርሰት ውድድር፡ የአራተኛ ክፍል ተማሪዎች በሜሪላንድ ሙኒሲፓል ሊግ በሚካሄደው “ከንቲባ ብሆን ኖሮ…” የተሰኘ የድርሰት ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። የመጨረሻው ቀን፦ ሐሙስ፣ ማርች 5 ነው።

  • የማት ፓፒርሜስተር ሽልማት/The Matt Papirmeister Award፡ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኪነጥበብ/አርት ተማሪዎች ክፍት ነው። የገንዘብ ሽልማት፡ $3,500 ዶላር፣ $3,000 ዶላር እና $2,500 ዶላር ተዘጋጅቷል። መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን እሑድ፣ ማርች 15 ነው።

  • BWI አየር ማረፊያ የወጣቶች የስነጥበብ ጋለሪ፡- ከሜሪላንድ የስነጥበብ ትምህርት ማህበር ጋር በመተባበር፣ አየር ማረፊያው በዚህ የጸደይ/ስፕሪንግ ወቅት ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) የስነጥበብ ትርኢት ያስተናግዳል። መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን እሑድ፣ ማርች 1 ነው።

  • የሜሪላንድ የትምህርት ቤት ደህንነት ማዕከል 2026 የስነ ጥበብ ትርኢት ያዘጋጃሉ፦ የዘንድሮው ጭብጥ፣ የወደፊት ዝግጁ ትምህርት ቤቶች፣ 3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ደህንነት ለእነርሱ ምን ማለት እንደሆነ ያላቸውን አመለካከት እንዲያካፍሉ ጥሪ ያቀርባል። የመጨረሻ ቀን፡ እሑድ፣ ሜይ 31 ነው።  

የአንስታይን ጨረታ ፌብሩዋሪ 20 ይካሄዳል፤ Bid የሚለውን ጠቅ ያድርጉ፣ ይወዳደሩ፣ ያሸንፉ።

ማህበረሰቡ ፌብሩዋሪ 20-28 ድረስ በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመታዊ በኦንላይን የሚካሄድ ጨረታ ላይ እንዲሳተፍ ተጋብዟል። እቃዎቹ የምግብ ቤት የስጦታ ካርዶችን፣ የስፖርት ዝግጅቶችን፣ የቲያትር ትርኢቶችን እና ሙዚየሞችን የሚጎበኙበት ትኬቶች፤ የልጆች መጫወቻዎች፤ ለልጆች፣ ለታዳጊዎች እና ለአዋቂዎች የቤት ውስጥ እና የውጪ መዝናኛዎች፤ ትምህርቶች፤ የሠመር ካምፕ እና የመዋኛ ቦታ ቅናሾችን እና የተለያዩ ሙያዊ አገልግሎቶችን ያካትታሉ። ይህን sneak peek; መመዝገብዎን ያረጋግጡ።

በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

  • Poms Dazzle with Precision and Power፡- ከ 25 የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ቡድኖች በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው 29ኛው አመታዊ Pompons ውድድር ላይ በደስታ ፈንድቀዋል፣ ደንሰዋል፣ ጨፍረዋል። 

  • በእንቅስቃሴ ላይ ያለ ወግ፡ በስፓርክ M. ማትሱናጋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጨረቃ አዲስ ዓመት አከባበር ይመልከቱ።

  • ናሙና፣ ውጤት መስጠት እና ቅርፅ ማስያዝ፦ 150 በላይ ተማሪዎች አዳዲስ MCPS የምግብ ዝርዝር ፅንሰ ሀሳቦችን ገምግመዋል፤ የወደፊት የምግብ ዝርዝር ለማዘጋጀት የሚረዱ አዳዲስ ጣዕሞችን ናሙና ቀምሰዋል።

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2026 Montgomery County Public Schools