MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS አርማ

አበይት ጉዳዮች

ሜይ 28, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  የክራወኒግ ስኬት

2026 ዓ.ም ተመራቂዎች — እንኳን ተሳካላችሁ! በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሚገኙ ቤተሰቦች፣ መምህራን እና ሰራተኞች በሺዎች የሚቆጠሩ ተመራቂ ሲኒየር ተማሪዎቻችን ባሳዩት ስኬት እጅግ በጣም ይኮሩባችኋል። የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 2026 ዓ.ም የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ዛሬ በደማስከስ፣ ሴኔካ ቫሊ እና በሼርውድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተመራቂዎች የሚጀምር ሲሆን፤ ነገ የኩዊንስ ኦርቻርድ፣ የቶማስ S. ውተን እና ብሌር G. ኢዊንግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተመራቂዎች ይከተላሉ። የምረቃ ሥነ ሥርዓት እስከ አርብ፣ ጁን 12 ድረስ ይቀጥላል።

 ከቤተሰቦቻችን እና ከመላው የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ ጋር በመሆን፣ 2026 ዓ.ም የተመራቂዎችን ጠንካራ ስራ፣ጽናት እና ስኬቶች በኩራት እናከብራለን። የምረቃ ጊዜያችሁን — በአድናቆት እናከብራለን! ፎተግራፎቹን ይመልከቱ። 

የምረቃ ሥነ-ሥርዓት መረጃዎች

 

የተመራቂዎችዎን MCPS Google Data ውሂብ ከመሰረዙ በፊት ያስቀምጡት

12ኛ ክፍል ተማሪዎ ለመመረቅ እየተዘጋጀ(ች)፣ MCPS Google Workspace account/ጉግል ዎርክስፔስ አካውንት 2026–2027 የትምህርት አመት የመጀመሪያ ቀን በፊት ክፍት እንደማይሆን ማወቅ አለብዎት። ከዚያ ቀን በኋላ፣ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን Gmail እና Google Drive ላይ የተከማቹ ፋይሎችን በሙሉ ማግኘት አይችሉም። የትምህርት ስራቸውን፣ ፕሮጀክቶቻቸውን፣ እና የመረጃ ቋት ውስጥ ያሉትን ስራዎቻቸውን ለመጠበቅ፣ ተማሪዎ የትምህርት አመቱ ከማለቁ በፊት Google Takeout በመጠቀም ውሂቦቹን በሙሉ በሌላ የራሱ(ሷ) የመረጃ ቋት ላይ ገልብጦ ማስቀመጥ ያስፈልጋል። 

ተማሪዎች ውሂባቸውን እንዴት ገልብጠው ማስቀመጥ እንደሚችሉ፦ 

  • ወደ MCPS አካውንት በመግባት Google Takeout ገፅ ይክፈቱ።
  • መገልበጥ የሚፈልጓቸውን መረጃዎች (Drive፣ Gmail እና Calendar) ይምረጡ።
  • "Next step." የሚለውን መርጠው ጠቅ ያድርጉ።
  • "Send download link via email" የሚለውን እንደ መገልበጫ ዘዴ ይምረጡ።
  •  ከማህደር ላይ የመገልበጥ ሂደቱን ለመጀመር "Create export" የሚለውን ጠቅ ያድርጉ። 

ማሳሰቢያ፦  የመገልበጥ ሂደቱ እንደ ፋይሎቹ መጠን ከጥቂት ደቂቃዎች እስከ ብዙ ቀናት ሊወስድ ይችላል። ማህደሩን ለመገልበጥ ዝግጁ ሲሆን Google አገናኝ ሊንኩን በኢሜይል ይልካል።

 
  አሁን ያውቁታል — የተሻሻሉ ParentVUE እና StudentVUE መተግበሪያዎች

በአሁኑ ጊዜ "ParentVUE" ወይም "StudentVUE" መተግበሪያዎችን እየተጠቀሙ ነው? ከሆነ፣ እነዚህ ጠንካራ መተግበሪያዎች መሆናቸውን አስቀድመው ያውቃሉ ማለት ነው—በቅርብ ጊዜ ደግሞ ይበልጥ ተሻሽለዋል። የተሻሻሉት መተግበሪያዎች የትምህርት ውጤቶችን፣ የቤት ስራዎችን፣ ተማሪ በትምህርት ላይ የመገኘት ሁኔታን፣ የመማሪያ ክፍል መርሃ ግብሮችን እና የትምህርት ቤት መልዕክቶችን በፍጥነት ለማግኘትና ለመከታተል ቀላል ያደርጉታል። ለራስዎ በሚመች ሁኔታ ለማስተካከል የሚችሉ የማስታወቂያዎች፣ በግል ሁኔታ የተስተካከሉ ቅንብሮች፣ እና የተሻሻሉ የቋንቋ አማራጮችን የመሳሰሉ ጠቃሚ አዳዲስ ገፅታዎች አሉት። ዛሬውኑ የእርስዎን ParentVUE ወይም StudentVUE መተግበሪያ ለማውረድ ወይም ለማዘመን App Store ወይም Google Play ይጠቀሙ!

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

 

JEF (ክፍት የምሳ ፖሊሲ) በሚመለከት ቦርዱ በፖሊሲው ላይ ምንም እርምጃ አልወሰደም

የትምህርት ቦርድ ሜይ 21 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ስለ ፖሊሲ JEF (ክፍት የምሳ ጊዜ ፖሊሲ) ላይ የቀረቡ ለውጦችን በሚመለከት ተወያይቷል። ቦርዱ ፖሊሲውን ለመሻር እና ክፍት የምሳ ጊዜ ሆኖ ክትትል የማድረግ ኃላፊነቱን ለሱፐርኢንቴንደንቱ ውሳኔ እንዲተው የፖሊሲ ማኔጅመንት ኮሚቴ ያቀረበውን ሀሳብ ግምት ውስጥ አስገብቷል። ይሁን እንጂ፣ በቀረበው ሀሳብ ላይ የሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይቅረብ የሚለው አስተያየት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። የፖሊሲውን ቋንቋ ለማሻሻል ኮሚቴው ያቀረበው ሀሳብም አልተወሰነም። በዚህ ምክንያት ቦርዱ ምንም አይነት እርምጃ ስላልወሰደ ፖሊሲው እንዳለ ሳይለወጥ ቆይቷል።

 ይህ ለቤተሰቦች ምን ማለት ነው፡

  • ስለ ምሳ ሠዓት ከዚህ በፊት በነበረው አሠራር ላይ ምንም አይነት ለውጥ አልተደረገም፦ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የምሳ ሰዓት አሠራር እስካሁን ባለው አይነት ይቀጥላል።
  • የሕዝብ አስተያየት መስጫ ጊዜ አልተመደበም፦ ፖሊሲው የሕዝብ አስተያየት እንዲቀርብበት ይፋ አልተደረገም/አልቀረበም።
  • እንዳለ ይቀጥላል፡ፖሊሲ JEF ከዚህ በፊት በሚሠራበት አይነት ይቆያል።
 
  የትምህርት ቦርድ በሥነ ምግባር ፓነል ክፍት የሥራ ቦታዎችን ለመሙላት አመልካቾችን ይፈልጋል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አምስት አባላት በሚኖሩት የሥነ ምግባር ፓነል ክፍት የሥራ ቦታዎችን ለመሙላት አመልካቾችን እየፈለገ ነው። ምደባው ከጁላይ 1, 2026 ጀምሮ ለሶስት ዓመት የሥራ ዘመን የሚቆይ ነው። አመልካቾች የፍላጎት ደብዳቤ፣ የስራ ልምድ ማስረጃ፣ ወይም ሌላ ደጋፊ ሰነዶችን እስከ አርብ፣ ጁን 12 ከቀኑ 5 p.m. ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ምደባው የሚካሄደው ጁን 25, 2026 በሚደረገው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

 
  ቤተሰቦች ስለመጪው የሂሳብ ትምሕርት ለውጦች ግንዛቤ እንዲያገኙ ተጋብዘዋል

MCPS ጠንካራ የሂሳብ ትምሕርት መሰረት ለመገንባት እና በራስ የመተማመን የሂሳብ ክህሎት አሳቢዎችን ለማዳበር ወደሚያተኩር አዲስ የማስተማሪያ ሞዴል እየተሸጋገረ ነው። 

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ፣ MCPS ለሂሳብ ትምህርት የክላስተር ሞዴል ተግባራዊ ያደርጋል። የክላስተር ቡድን ዝግጅት ተማሪዎች ዝግጁ ሲሆኑ ወደ ላቀ የመማሪያ እድል እንዲሸጋገሩ ለማስቻል የተነደፈ ነው። በመማሪያ ክፍል ውስጥ ያለውን የተለያየ ​​የትምህርት ደረጃዎች ለመቀነስ ተማሪዎች እንደየችሎታቸው በተለያየ ቡድን ይደራጃሉ፣ ይህም መምህራን ትምህርትን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲያቅዱ፣ የተማሪዎችን የመማር አቅም እንዲለዩ እና ለተማሪዎች ችሎታ የሚመጥናቸውን ወቅታዊ ድጋፍ እና ማበልጸጊያ እንዲሰጡ የበለጠ ምቹ ያደርገዋል። 

ይህ ሞዴል 2026-2027 የትምሕርት አመት 4ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ በሚቀጥሉት ዓመት በቀጣዮቹ የክፍል ደረጃዎች ይተገበራል። ልጅዎ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ከሆነ(ች)፣ ከትምህርት ቤት ዝርዝሮችን ለማጋራት በቅርቡ መልክት ይደርስዎታል። MCPS ለቤተሰቦች የበለጠ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የማህበረሰብ ስብሰባዎችን ያዘጋጃል። ሁሉም ስብሰባዎች የሚደረጉት ከቀኑ 7-8:15 p.m. ነው 

  • ማክሰኞ፣ ጁን 2፣ ቨርቹዋል በዙም/Zoom ይካሄዳል
  • ማክሰኞ፣ ጁን 9 ሲልቨር ክሪክ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል፤ አድራሻ፦ Silver Creek Middle School, 3701 Saul Road, Kensington
  • ማክሰኞ፣ ጁን 16 ቨርቹዋል በዙም/Zoom ይካሄዳል

የሂሳብ ትምህርት

በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች/FAQs

 
  እርስዎ ጥያቄዎች አሉዎት፣ እኛ መልሶች አሉን!

Just Ask MCPS! ይጠይቁ MCPS ጥያቄዎችዎን እና ተሳትፎዎን በደስታ ይቀበላል! ለጥያቄዎችዎ በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት ሰባት ቀናት በማንኛውም ቋንቋ መልስ ማግኘት ይችላሉ። በማንኛውም ቋንቋ የእኛን chatbot ጥያቄ ይጠይቁ። እንዲሁም በማንኛውም ቋንቋ ወደ ትምህርት ቤቶች እና ወደ ቢሮዎቻችን መደወል ወይም ኢሜይል መላክ ይችላሉ። አጥጋቢ መልስ ካላገኙ፣ ወደ AskMCPS በስልክ ቁጥር 240-740-3000 ወይም ስፓንሽኛ በስልክ ቁጥር 240-740-2845 ይደውሉ። ወይም በዚህ ኢሜል ይላኩ፦ AskMCPS@mcpsmd.org ሰራተኞች ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 4 p.m., ባለው ጊዜ ውስጥ ምላሽ ይሰጣሉ።

 ይህ ድረ ገጽ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን እና በአብዛኛው የሚጠየቁ ቁጥሮችን ዝርዝር ያካትታል።

 እዚህ ያለነው እርስዎን ለመርዳት እና ለጥያቄዎችዎ መልስ ለመስጠት ነው። ስለዚህ ከ MCPS ይጠይቁ!

 
  ማሳሰቢያ
  • ሕያው ቅርስ፡ ገዢ ባህል፡ የኤዥያን አሜሪካን፣ የሃዋይ ተወላጆች እና የፓሲፊክ ደሴት ተወላጆች (AANHPI) ታሪካዊና ባህላዊ ቅርስ የሚዘከርበት ወር እንደመሆኑ፣ የትምህርት ቦርድ በሙዚቃ፣ በጭፈራ እና በተለያየ ወግ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ትውልዶች እንዴት እንደሚገናኙ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ተመልካቾች የህንድ ኩቺፑዲ ዳንስ፣ የሃዋይ ሁላ እና የቻይና ላዮን ዳንስ፣ ታሪክን የሚያንፀባርቁ፣ ማህበረሰቡን የሚያጠናክሩ እና ባህላዊ ማንነትን የሚገልጹ የጥበብ ስራዎችን ውበት እና ትርጉም ይገነዘባሉ።ታሪኩን ይከታተሉ።
  • ለሠመር ወቅት የተያዘ፦ ይህ የሠመር ወራትን ለመቃኘት የተዘጋጀ MCPS ዲጂታል መመሪያ ልጆችን በመኸር ወቅት ዝግጁ እና ጤናማ ለማድረግ ስለ አካዳሚክ ፕሮግራሞች፣ የማህበረሰብ መዝናኛዎች፣ የሠመር ምግቦች እና የአእምሮ ጤና ሪሶርሶች የሚገኙበት መረጃ ይሰጣል። 
  • የወደፊት ዝግጅቶች፦ 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች ስለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማራጮች የበለጠ ለማወቅ የመረጃ ክፍለ ጊዜዎችን እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል። 2027 የመኸር ወራት ጀምሮ፣MCPS በካውንቲው ውስጥ ልዩ ፕሮግራሞችን የማግኘት እድሎችን በማስፋፋት አዲስ የሪጅናል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሞዴል ይጀምራል። ተማሪዎች በፍላጎታቸው መሰረት ለሪጅናል ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሪጅናል ፕሮግራሞችን ድረ ገጽ ይጎብኙ። በአቅራቢያዎ የሚገኝ ዝግጅት ይቃኙ። 
  • የስራ ቃለ መጠይቅ የሚካሄድበት ቀን፡- ሐሙስ፣ ጁን 25 Bethesda Marriott, 5151 Pooks Hill Road in Bethesda ይካሄዳል፣ ሠዓቱ ወደፊት ይገለጻል። መረጃው በኮሌጅ እና በሙያ ናቪጌተሮች እና በትምህርት ቤት ካውንስለሮች በኩል በቅርቡ ይፋ ይደረጋል። ቀደም ብለው የተመዘገቡ ተመራቂዎች በዝግጅቱ ላይ እንዲገኙ በግል የኢሜይል አድራሻዎቻቸው ይጋበዛሉ።
  • Raptor Ready Scholarships፡ የሞንትጎመሪ ኮሌጅ 2026 ዓ.ም የጸደይ/ስፕሪንግ ወቅት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመረቁ እና በዚህ መኸር ቢያንስ ስድስት MC ክሬዲት ሰዓት ለሚወስዱ ነዋሪዎች $1,000 ዶላር ስኮላርሽፕ ዕድል ይሰጣል። ስኮላርሽፑ 2026 ዓ.ም የመኸር ወቅት/ፎል የትምህርት ክፍያ መሆን አለበት። ማመልከቻዎቹ የሚቀርቡት እስከ ሰኞ፣ ኦገስት 3 ነው።
  • የሞንትጎመሪ የታሪክ ስነጥበብ ኤግዚቢሽን፦የካውንቲው 250ኛ ዓመት ክብረ በዓል አካል እንደመሆኑ መጠን (8ኛ ክፍል እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) ተማሪ አርቲስቶች ስራቸውን “MoCo at 250: Then and Now.” በሚል ርእስ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። የመጨረሻ ቀን፦ እሁድ፣ ኦገስት 2, 2026ነው። 
  • ስለ ልዩ ትምህርት የወላጆች የዳሰሳ ጥናት፦ የሜሪላንድ ስቴት ትምህርት መምሪያ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የልዩ ትምህርት አገልግሎት የሚያገኙ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች የሜሪላንድ ልዩ ትምህርት የወላጆች ተሳትፎን የሚመለከት የዳሰሳ ጥናት ሞልተው እንዲያቀርቡ እየጠየቀ ስለሆነ የልዩ ትምህርት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት ለመምራት የሚረዳ በመሆኑ ሞልተው እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን። የዳሰሳ ጥናቱን እስከ አርብ፣ ጁን 5 ድረስ ሞልተው ይመልሱልን።
 

KID Museum's 'Invent the Future Expo' ሜይ 31 ቤተዝዳ ኤክስፖ ይከፈታል።

በቤተዝዳ የሚገኘው KID ሙዚየም እሑድ፣ ሜይ 31 ከጠዋቱ 10 a.m.-3 p.m. ድረስ "Invent the Future Expo" ኤክስፖ የፈጠራ፣ የሳይንስ እና የተግባራዊ ትምህርት ኤክስፖ ያካሄዳል። ይህ በነፃ የሚገቡበት ዝግጅት ሮቦቲክስ፣ የእጅ ሥራ፣ ቨርቹዋል እውነታዎች፣ የዘላቂነት ኤግዚቢሽን፣ እና በሁሉም የዕድሜ ክልል ላሉ ቤተሰቦች እና ተማሪዎች የሚስማማ የቴክኖሎጂ ሞዴሎችን ያካትታል። አድራሻ፦ KID Museum is located at 3 Bethesda Metro Center, adjacent to the Bethesda Metro station.

 
  በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
  • ኮርነርስቶን በተማሪዎች የተሠራ ቤት መጠናቀቅን የሚያሳይ ሥነ ሥርዓት፡የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ከህንፃ ሥራ ባለድርሻ አካላት እና በሪል ስቴት መስኮች ካሉ አጋር መሪዎች ጋር በመሆን፣ 44ኛውን ቤት ገንብተዋል። በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል።
  • 2026 ዓ.ም የአመቱ ምርጥ ካውንስለሮች ጋር ይገናኙ፦ የዘንድሮው አሸናፊዎች የቤተዝዳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሎረን ሞርላንድ፤ የሌክላንድስ ፓርክ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላቲሻ ኔልሰን እና የዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስቴፋኒ ፓውል ናቸው።
  • ከዋክብትን መቃኘት፦ የውድ ኤከርስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በወላጅ በጎ ፈቃደኞች በሚመራ ልዩ የስነ ፈለክ ፕሮግራም፣ በተግባር እየሠሩ መማር ላይ የተመሰረተ ትምህርት እና ለአስርተ ዓመታት የዘለቀ የዳሰሳ ቅኝት አማካኝነት ከዋክብትን ማየት ጀምረዋል።
  • ለውጥን ለመምራት የፈጠራ ችሎታን መጠቀም፡ የዊተን ውድስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቅርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው የኪነጥበብ፣ የባህል፣ እና የፈጠራ ፕሮግራም ሥነ ስርአት ላይ “Our Art, Our Voices.” በሚል ርዕስ እውነተኛ ወደሆነ አገላለጽ ተቀይሯል።
  • የልዩ ትምህርት ቤት ጉብኝት፦ ጄን ፓይለ ሃሪስ 97 ዓመታቸው ላይ የቶማስ W. ፓይለ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለመጀመሪያ ጊዜ ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት፣ የአባታቸውን የቶማስ W. ፓይለ ትዝታዎች ተናግረዋል፣ እንደውም ተማሪ ሆነው መመዝገብ እንደሚፈልጉ እንደቀልድ ገልጸዋል።
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
©1995–2026 Montgomery County Public Schools