MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS አርማ

አበይት ጉዳዮች

ሴፕተምበር 03, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 

በክፍል ውስጥ ምን ይማራሉ? ልጅዎ ምን እየተማረ እንዳለ እና ከክፍል ደረጃው ጋር የተያያዙ ሌሎች ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያካትቱ ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር (district) የሚላኩ ኢሜይሎችን ይከታተሉ። በሚቀጥለው ሳምንት ስለሚኖረው ትምህርት የሚያሳውቁ አስፈላጊ ወይም ጠቃሚ መረጃዎች ሲኖሩ፣ ለMCPS ቤተሰቦች አዳዲስ መረጃዎች አርብ ጠዋት ይላካሉ።

 
  በአዲስ ሥርዓተ ትምህርት በራሳቸው የሚተማመኑ የሂሳብ ተማሪዎችን መገንባት

በዚህ የትምህርት አመት፣ ከቅድመ-መዋእለ ህጻናት እስከ አልጀብራ 1 ያሉ ተማሪዎች የሂሳብ ትምሕርት ፕሮብሌሞችን እንዴት መፍታት እንደሚችሉ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ስልቶች ለምን እንደሚሰሩ እና የሂሳብ ትምሕርትን በነባራዊ ዓለም አውድ ላይ እንዴት መጠቀም እና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ እንዲያውቁ ለመርዳት የተነደፈAmplify Desmos Mathየተባለ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ይማራሉ። ተማሪዎች በአሳታፊ የሒሳብ ትምህርት ፕሮብሌሞችን በውይይት እና በትብብር በመሥራት እንዲሁም አስተሳሰባቸውን የማስረዳት እድሎችን በመጠቀም ይማራሉ። ተማሪዎች እንደየፍላጎታቸው ተጨማሪና ጠንካራ የሒሳብ ሥራ ተግዳሮት ሲያሻቸው አስተማሪዎች ድጋፍ ይሰጧቸዋል። ግቡ እያንዳንዱ ተማሪ ጠንካራ የሂሳብ ትምሕርት ዕውቀት/ክህሎት በማዳበር፣ ግንዛቤን ማጠናከር እና በራስ መተማመን እና ብቃት ያለው/ያላት የሂሳብ ተማሪ በምሆን እንዲያድግ/እንድታድግ መርዳት ነው። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  ወደ ትምህርት ቤት ደህንነቱ የተጠበቀ የእግር ጉዞ ማድረግ የሚጀምረው ጥቂት ቀላል ተሞክሮዎችን በመተግበር ነው።

ወደ ትምህርት ቤት በእግር መሄድ ተማሪዎች ቀኑን ለመጀመር ጥሩ መንገድ ነው፣ ነገር ግን በንቃት መራመድ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ምርጫ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ቤተሰቦች ከተማሪዎች ጋር ቀላልና ጥቂት የእግረኛ ደህንነት አጠባበቅ ልምዶችን በመነጋገር መርዳት ይችላሉ፦

  • በተቻለ መጠን የእግረኛ መንገዶችን እና ለእግረኞች የተመደቡ መተላለፊያዎችን/የመንገድ ማቋረጫዎችን/መሻገሪያዎችን ይጠቀሙ
  • መንገድ ከመሻገራችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ወደ ግራና ቀኝ ተመልከቱ መንገዱን ለማቋረጥ አመቺ ሲሆን — እና ግራና ቀኛችሁን እያያችሁ ተሻገሩ።
  • ከአሽከርካሪዎች ጋር አይን ለዓይን መተያየት ያስፈልጋል፤ እና ተሽከርካሪ አይቶ/አውቆ ይቆማል ብላችሁ በጭራሽ አታስቡ።
  • መንገዶችን ስታቋርጡ ወይም የመኪና ትራፊክ ባለበት አጠገብ ስትራመዱ ስልኮችን እና የጆሮ ማዳመጫዎችን አስቀምጡ/አትጠቀሙ
  • ሁልጊዜ የማቋረጫ መንገድ ትዕዛዞችን እና የትራፊክ ምልክቶችን መመሪያዎች ተከተሉ
  • በተለይ በአውቶቡሶች እና በትምህርት ቤት የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች አካባቢ ጥንቃቄ አድርጉ፣ ተሽከርካሪዎች በድንገት ሊዞሩ፣ ወደኋላ ሊታጠፉ ወይም ሊቆሙ ይችላሉ።

አሽከርካሪዎችም ጥንቃቄ በማድረግ ጠቃሚ ሚና አላቸው፦ ፍጥነትዎን ይቀንሱ፣ ንቁ ሁኑ፣ እና በተለይም ጠዋት ወደ ት/ቤት ሲደርሱ እና ከሰዓት በኋላ ከት/ቤት ሲወጡ ተማሪዎችን በጥንቃቄ መመልከት/ደህንነታቸውን መጠበቅ ያስፈልጋል።

ጥቂት ተጨማሪ ሰከንዶችን ትኩረት መስጠት ትልቅ ለውጥ ሊያደርግ ይችላል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

 
  የአውቶቡስዎን መስመር ያግኙ

ወቅታዊ የት/ቤቶች አውቶቡስ መስመር መረጃ በትምህርት ቤትዎ በይነመረብ ላይ ባለው የመረጃ ቋት ውስጥ በእያንዳንዱ MCPS ትምህርት ቤት ድረ ገጽ ላይ (በስተግራ በኩል) ይገኛል። ቤተሰቦች ስለ ት/ቤቶች የአውቶቡስ መስመር መረጃ የመጓጓዣ አገልግሎት ክፍል/Division of Transportation Services ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ። እባክዎ የት/ቤት አውቶቡስ ማቆሚያዎች፣ ሰዓት፣ እና የጊዜ ሰሌዳዎች ሊለወጡ ስለሚችሉ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የሚጠቀሙበትን የት/ቤት አውቶቡስ መስመር በመደበኛነት እየተከታተሉ ማጣራት አትዘንጉ።

ጥያቄ አለዎት? የመጓጓዣ ማናጀር ያነጋግሩ። ልጅዎ(ልጆችዎ) ወደተመደበው የአውቶቡስ ዴፖ ሲደውሉ የተማሪዎን ስምና መታወቂያ፣ የአውቶቡስ መስመር ቁጥር፣ እና ትምህርት ቤቱን መግለጽ አለብዎት።

 
  ለቀጣዮቹ ሁለት የትምህርት ዓመታት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር እየተዘጋጀ ስለሆነ እባክዎ የእርስዎን አስተያየት ያጋሩን።

MCPS የትምሕርት አመት 2027-2028 እና የትምሕርት አመት 2028-2029 የትምህርት ቤቶች ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ለማዘጋጀት እየሰራ ስለሆነ የእርስዎን አስተያየት እንዲያጋሩን እንፈልጋለን። እባክዎን ይህንን የዳሰሳ ጥናት እስከ ሴፕቴምበር 20 ድረስ ሞልተው በመላክ የእርስዎን አስተያየት ያጋሩ። 

የእርስዎ ግብረመልስ ለዝግጅት ሂደቱ ወሳኝ ነው። MCPS የትምሕርት ቤት ካለንደር በሚያዘጋጅበት ወቅት የትምህርት ፍላጎቶችን፣ የአሠራር ፍላጎቶችን፣ በስቴት ህግ መሰረት የተደነገገ የትምህርት ቤት መዘጋትን፣ አነስተኛ የሚባል የትምህርት ቀናት እና የክሬዲት ሰዓት መስፈርቶችን ማክበር፣ መጥፎና ከባድ የአየር ሁኔታ እና ሌሎች ድንገተኛ ሁኔታዎችን፣ የሰራተኞች የሙያ ቀናትን፣ እና ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበትን ቀናት MCPS የቦርድ ፖሊሲ IDA፣ የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ጋር የተጣጣሙ የግምገማ መርሃ ግብሮችን ግምት ውስጥ ያስገባል።

የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ።

 
  አሁን ማወቅ ያለብዎት — ስለ ክትባት

MCPS ለመዋዕለ ሕፃናት፣ 7ኛ እና 9ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች፣ እንዲሁም ወደ MCPS አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች የክትባት መስፈርቶች አሉት። ከልጅዎ የህፃናት ሐኪም ጋር በመነጋገር የልጅዎን የክትባት ማስረጃዎች ወቅታዊ መሆናቸውን ያረጋግጡ። ክትባት የሚያስፈልግ ከሆነ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ የትምህርት ቤት እድሜ ላላቸው ልጆች ክትባቶችን በነፃ ይሰጣል። የክሊኒኮችን ዝርዝር እዚህ ያገኛሉ። ልጅዎ ትምህርት ቤት ለመግባት ከመጀመሪያው የትምህርት ቀን ጀምሮ 20 ቀናት ውስጥ የክትባት ማረጋገጫ ማቅረብ ወይም የክትባት ቀጠሮ ሊኖረው/ሊኖራት ያስፈልጋል።

ይበልጥ ለማወቅ ከዚህ አንብቡ: English | español | 中文 | français | Português | 한국어 | tiếng Việt | አማርኛ

 
  8ኛ ክፍል ተማሪዎች ስለ ጥንካሬዎቻቸው የበለጠ ለማወቅ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመዘጋጀት ነፃ እድል ያገኛሉ።

ለብዙ ዓመታት በታየው ፍላጎት እና ከቤተሰቦች እና ከአቀንቃኞች የሚቀርቡትን ጥያቄዎች በመከተል፣ MCPS 8ኛ ክፍል ሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ በትምህርት ቀን PSAT 8/9 ያለምንም ክፍያ የመፈተን እድል ይሰጣል። PSAT 8/9 ምዘና ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ እና ለትምህርት ቤቶች ስለ ተማሪዎቹ የትምህርት እድገት ጠቃሚ መረጃዎችን ይሰጣል፣ ይህም የጥንካሬ እና ተጨማሪ እድገት የሚያስፈልጋቸውን ክህሎቶችን ያመለክታል። ውጤቶቹ ተማሪዎች ለኮሌጅ እና ለሙያ ዝግጁነት ያላቸውን የእድገት ደረጃ እንዲረዱ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲዘጋጁ ትኩረት መስጠት ያለባቸውን አውዶች ለይተው እንዲያውቁ ሊያግዙ ይችላሉ። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  MCPS የት/ቤት አውቶቡስ አሽከርካሪዎችን እየቀጠረ ነው!

የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍል ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 17፣ ከጠዋቱ 10:30 a.m.- 1 p.m. ድረስ ለአውቶቡስ አሽከርካሪዎች የሥራ ቅጥር ትርኢት እያዘጋጀ ነው። ትርኢቱ የሚካሄድበት አድራሻ የሚከተለው ነው፦ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville.

ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች በራሪ ወረቀቱ ላይ ያለውን QR ኮድ እንዲቃኙ እና MCPS Careers ድረ ገጽ ላይ መግለጫ እንዲሞሉ ይጠየቃሉ። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-740-6080 ደውለው ይጠይቁ።  

 
  ወደ ጨዋታ እያመሩ ነው? ከመሄድዎ በፊት ይወቁ!

የትምሕርት አመት 2026–2027 የመኸር (fall) ስፖርት ወቅት እየተካሄደ ነው፣ እና MCPS አትሌቲክስ ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን፣ እና አድናቂዎችን ወደየስታዲየሞቹ እንዲመጡ በደስታ ይቀበላል! ይህንን ሌላ አስደሳች የውድድር ዘመን ስንጀምር፣ እያንዳንዱን ጨዋታ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ መልካም የተወዳዳሪነት መንፈስ የሰፈነበት፣ መከባበር ያለበት እና ለሁሉም ሰው ምቹ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን። በአትሌቲክስ ዝግጅት ላይ የሚሳተፉ ከሆነ ማወቅ ያለብዎትን ነገር ተጨማሪ ያንብቡ

 

 
  የወጣቶች ታወን ሆል ለተማሪዎች መቀመጫዎችን ይመድባል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 29 ከቀኑ 6 p.m. ላይ ዓመታዊ የወጣቶች ታወን ሆል ስብሰባ ያካሂዳል (5:30 p.m. ላይ ፒዛ ይቀርባል)። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባላትን እና MCPS የተማሪዎች መሪዎች ሮክቪል በሚገኘው Council Office Building, Third Floor, 100 Maryland Avenue in Rockville በአካል በመገኘት በወጣቶች ላይ ያተኮሩ ጉዳዮችን ሲወያዩ ይቀላቀሉ ወይም በዙም ይከታተሉ። የሚሳተፉ ተማሪዎች ጥያቄዎቻቸውን እና ስጋቶቻቸውን ማቅረብ እና ከካውንቲው አመራሮች ጋር በሚደረግ ውይይት መሳተፍ ይችላሉ። የሚሳተፉ ተማሪዎች ሁለት SSL ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።ለመሣተፍ ይመዝገቡ።

 
  ከተፅእኖ ፈጣሪ ወጣት ሴቶች ጋር ሀሳብዎን ውጤታማ ያድርጉ

ተፅእኖ ፈጣሪ ወጣት ሴቶች/Girls With Impact (GWI) በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነፃ፣ በአውደመረብ ላይ፣ እስከ 10 ሳምንት የሚዘልቅ የስራ ፈጠራ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ይህ ፕሮግራም ከሃርቫርድ መሪዎች ጋር የተዘጋጀ ሲሆን ስለ ቢዝነስ እቅድ፣ ግብይይት፣ እና ስለ ፋይናንስ እውቀት ጭምር የተለያዩ ርዕሶችን የሚሸፍን ተግባራዊ ትምህርትና ስልጠና አማካኝነት ወሳኝ የቢዝነስ እና የአመራር ክህሎቶችን በመገንባት ላይ ያተኩራል።

የፎል ወቅት ስልጠናው የሚጀመረው ሴፕተምበር 28 ቀን ሲሆን ትምሕርቶች የሚሰጡት ማክሰኞ፣ 7 p.m., እሮብ፣ 4:30 p.m. ወይም እሮብ፣ 8 p.m. ይሆናል እዚህ ይበልጥ ያንብቡ:እንግሊዝኛ/English |ስፓንሽኛ/Spanish

ይመዝገቡ

 
  ማግኘት ቀጥሉ፡ የሴፕተምበር SSL እድሎች አሉ!

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤት (MCPS) ተማሪዎች በሙሉ ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያስፈልጋቸዋል። የሴፕቴምበር ወር SSL እድሎችን ዝርዝር እዚህ መመልከት ይችላሉ ። MCPS - SSL ቅጾችን አሻሽሏል፤ አዲሶቹን ቅጾች ከዚህ በታች ይመልከቱ፦

 

ለቤተሰቦች ፈጣን መመሪያዎችን በመጠቀም MCPS መልሶችን በፍጥነት ይሰጣል

ስለ MCPS ግልጽ፣ ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ መረጃ ይፈልጋሉ? ቤተሰቦች መልሶችን እንዲያገኙ፣ አስፈላጊ የትምህርት ቤት መረጃዎች እንዲደርሳቸው እና ተማሪዎቻቸውን ዓመቱን ሙሉ እንዲደግፉ ለመርዳት የተነደፈውን የእኛን ፈጣን የቤተሰቦች መመሪያ/Quick Guides for Familiesይጎብኙ።

መመሪያዎቹ ቤተሰቦች የሚጠይቋቸውን አብዛኛዎቹን ርዕሶች ይሸፍናሉ፣ ይሄውም፦ ParentVUE እና ስለ ዲጂታል መገልገያዎች፣ መጓጓዣ፣ ስለትምሕርት ውጤት አሰጣጥ፣ እና ግምገማዎች፣ የማጥናት ችሎታና ዘዴዎች፣ የትምህርት ቤት ደህንነት፣ የአእምሮ ጤና፣ የተማሪዎች ባህሪ፣ ማህበራዊ ሚዲያ እና የግል የሞባይል መገልገያዎችን የሚመለከቱ መረጃዎችን ሁሉ ያካትታል።

በስምንት ቋንቋዎችየተተረጎሙ ብዙ ግብዓቶች ይገኛሉ። አዳዲስ ግብዓቶች በተደጋጋሚ ስለሚጨመሩ ገጹን ብዙ ጊዜ ተመልሰው መመልከትዎን አለብዎት።

ይህንን ፈጣን የቤተሰብ መመሪያ ሠነድ ይቃኙ፦ MCPS Quick Guides for Families

 
  ሴፕቴምበር 18 የብሎክ ፓርቲ ምግብ፣ መዝናኛ፣ እና SSL ሰዓቶችን ያቀርባል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባል ማሪሊን ባልኮምብ/Marilyn Balcombe አርብ፣ ሴፕቴምበር 18 ከቀኑ 12:30-3 p.m. ጀርመንታውን በሚገኘው ብላክሮክ ሴንተር ፎር ዘ አርትስ፣ ወደ-ትምህርት ቤት የመመለሻ ብሎክ ፓርቲያዘጋጃሉ። አድራሻ፦ BlackRock Center for the Arts, 12901 Town Commons Drive in Germantown. ይህ እለት MCPS ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀን ነው። በዚህ ነፃ ዝግጅት ላይ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች፣ ሪሶርሶች፣ ከተማሪዎች የሚቀርቡ ትርኢቶች፣ እና ምግብ ይኖራል። የዳሰሳ ጥናት ላይ የሚገኙ እና ሞልተው የሚያቀርቡ ተማሪዎች 2.5 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያገኛሉ። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-777-7960 ይደውሉ።

 
  ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነፃ የራውንድ ሃውስ ቲያትር ትኬቶች ይገኛሉ

ቤቴስዳ የሚገኘው ራውንድ ሃውስ ቲያትር ለፕሮግራሞቹ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ነፃ ትኬቶችን ይሰጣል። በዚህ ወቅት የመጀመሪያው ትርኢት፣ የኦገስት ዊልሰን/August Wilson’sMa Rainey’s Black Bottom ፣ ከሴፕቴምበር 9 እስከ ኦክቶበር 11 ይካሄዳል። ተማሪዎች በአንድ ፕሮዳክሽን አንድ ቲኬት መጠየቅ ይችላሉ። በቲኬት ስርጭት ዝርዝሩ ውስጥ ከገቡ በኋላ፣ ለቀጣይ ፕሮዳክሽኖች ቲኬቶችን ለማግኘት እንዲመዘገቡ ማሳሰቢያዎችን ያገኛሉ።እዚህ ይመዝገቡ።

 

ማሳሰቢያዎች፦

  • ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 7 – የሰራተኞች ቀን፤ ትምህርት ቤቶችና ቢሮዎች ዝግ ናቸው
  • ሪፍሪጅሬተር ከሪኩለም፦ የትምሕርት አመት 2026-2027 የተዘጋጀውን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የትምህርት መርሃ ግብር ለማንበብ ቀላል የሆነ አጠቃላይ መረጃ በአንድ ገፅ ላይ ያገኛሉ። ይህ ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል (K-12)ያሉ ተማሪዎች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት ምን እንደሚማሩ የሚያሳይ ቀላል መግለጫ ዋና ዋና ርዕሶችን፣ ጭብጦችን፣ እና ጽሑፎችን ያካትታል።
  • FARMS ማመልከቻ: ዛሬ/አሁን ያመልክቱ! ምንም እንኳን ልጆቻችሁ ባለፈው አመት ብቁ ቢሆኑም በየትምህርት አመቱ አዲስ FAARMS ማመልከቻ መቅረብ አለበት። ተደራሽነቱ በቤተሰብ የገቢ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። በኦንላይን FARMS ማመልከቻ MySchoolApps ላይ አቅርቡ (በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎሙ ቅጾች ይኖራሉ)። ለአንድ ቤተሰብ አንድ ማመልከቻ ብቻ ማቅረብ በቂ ነው። ተጨማሪ መረጃ
  • የቅዳሜ ትምህርት ቤት፦ የተማሪዎችን በራስ መተማመን እና የትምህርት ስኬት ይገነባል! ፕሮግራሞች ቅዳሜ ከጠዋቱ 8፡30-11 a.m. ላይ K-12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ይሰጣሉ፤ እነዚህ ፕሮግራሞች በንባብ፣ በሂሳብ፣ በፈተና ዝግጅት እና STEM ማበልጸጊያ ላይ ያተኮሩ ሲሆን ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ በመሳሰሉ ነገሮች ላይ ያተኮሩ ናቸው። ሴፕቴምበር 19 በሚካሄደው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው የበለጠ ይወቁ። ትምህርቱ የሚጀምረው ሴፕቴምበር 26 ከጠዋቱ 8፡30 a.m. ነው። ክፍያ ለዓመቱ $100 (FARMS $50) ነው። ወደ መሀል ቦታዎች ነፃ መጓጓዣ ይቀርባል። 
  • ከቤት ውጪ የሚሰጥ ትምህርት ኦፕን ሀውስ/Outdoor Ed Open House፡ ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 8 ከቀኑ 6:30-8 p.m. ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች Lathrop E. Smith Center ላይ ይካሄዳል። ሰራተኞች ስለ ስሚዝ ማዕከል የፕሮግራሚንግ አጠቃላይ ገፅታ መግለጫ ይሰጣሉ፣ የካምፓስ ጉብኝት ይደረጋል፣ እና ስለ ስድስተኛ ክፍል የአካባቢ ትምህርት ፕሮግራም መረጃ እና ልምዶችን ያካፍላሉ። አድራሻ፦ The Smith Center is located at 5110 Meadowside Lane in Rockville. ተጨማሪ ይወቁ እና ለመሳተፍ ይመዝገቡ። 
  • የትምሕርት መሳሪያ ዕቃዎችን ይግዙ፤ ልገሣ ያድርጉ፡ MCPS ብራንድ ከተሰጣቸው ሸቀጦች ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ሁሉ የተማሪዎችን የምግብ ዕዳ ለመክፈል ይረዳል። ምርቶች በየጊዜው ይለወጣሉ። MCPS shop የሚለውን ይመልከቱ
  • የፋሲሊቲ አማካሪ ኮሚቴ፦ MCPS በትምሕርት አመት 2026-2027 የሚያገለግሉ የማህበረሰብ አባላትን ይፈልጋል። የኮሚቴ አባላት MCPS የትምህርት ቤት መገልገያዎችን የረጅም ጊዜ እቅድ ሲያዘጋጅ እውቀታቸውን፣ ልምዳቸውን፣ እና አመለካከታቸውን ያካፍላሉ። ማመልከቻዎች መቅረብ ያለባቸው አርብ፣ ሴፕቴምበር 4 ነው።
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools