ማርች 19, 2026
ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን! በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ፣ MCPS ጉልህ የሆኑ የአሠራር ለውጦችን እና ማሻሻያዎችን ተግባራዊ አድርጓል — ይህም ስለ ትምህርት ውጤት አሰጣጥ፣ ደህንነት (በትምህርት ቤቶች ውስጥ የፖሊስ መገኘትን ጨምሮ)፣ የተማሪዎች የስነምግባር ደንብ፣ ክፍት የምሳ ሠዓት እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለ ሞባይል ስልኮች አጠቃቀምን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሶችን የሚመለከቱ ናቸው። MCPS ለቤተሰቦች፣ ለተማሪዎች፣ እና ለትምህርት ቤት ሰራተኞች አስፈላጊ በሆኑት በእነዚህ በርካታ ጉዳዮች ላይ በተግባር ለእርስዎ እንዴት እየሰራ እንደሆነ ለማወቅ የዳሰሳ ጥናቶችን እያካሄደ ነው። የዳሰሳ ጥናቱ እዚህ ይገኛል። ይበልጥ ያንብቡ።
በተጨማሪም፣ አስተያየትዎ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ የሚያብራራውን ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ፡ English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese |አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
የጸደይ/ስፕሪንግ የእረፍት ጊዜ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችንለማግኘት አመቺ ጊዜ ነው! እነዚህን ቁልፍ የጊዜ ገደቦች ልብ ይበሉ፡
ማሳሰቢያ፦ ለመመረቅ 75 የአገልግሎት ሰዓት ማግኘት ያስፈልጋል። የአገልግሎት እድሎችን እዚህ ይፈልጉ።
MCEA እና SEIU Local 500 ጋር በመተባበር፣ MCPS ማርች 12-13 በሁለት የጎልድ ስታር ድንቅ አስተማሪዎችን እና የድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎችን በማድነቅ አክብሮት ሰጥቷል። ተጨማሪ ያንብቡ እና ቪዲዮውን ይመልከቱ።
በትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካላንደር ላይ የተደረጉ አስፈላጊ ለውጦች ከሚከተለው መልእክት ጋር አርብ፣ ማርች 13 ለቤተሰቦች በኢ-ሜል ተልኳል። ካመለጠዎት ለማረጋገጥ እዚህ ያንብቡ። ከፀደይ/ከስፕሪንግ ዕረፍት በፊት ስለ ትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ሌላ መልእክት ሊኖር ይችላል።
ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ሰኞ፣ ማርች 23 ይጀመራል። IGNITE የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካዳሚ ተማሪዎች በሂሳብ፣ በእንግሊዝኛ እና STEM ለሚቀጥለው የትምህርት አመት በራስ መተማመን እንዲኖራቸው እና ዝግጁ እንዲሆኑ ያዘጋጃቸዋል። ተማሪዎቻቸው ይበልጥ ተጠቃሚ ለሚሆኑ ቤተሰቦች ParentVUE ላይ እንዲመዘገቡ የተጋበዙበት ጥሪ ይደርሳቸዋል። ፕሮግራሙ ከጁላይ 7 እስከ ኦገስት ይካሄዳል። 6. ትምህርት የሚሰጠው ከሰኞ እስከ ሐሙስ ሲሆን በስድስት ሪጅናል ቦታዎች ይካሄዳል።
Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
የቀን መቁጠሪያያዎ ላይ ምልክት ያድርጉ እና ለአንድ ዓላማ እንቅስቃሴ ላይ ለመሳተፍ ይዘጋጁ! የመጀመሪያው የሱፐርኢንቴንደንቱ የአንድ ዓላማ እንቅስቃሴ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 ቦኸረር ፓርክ ላይ ይካሄዳል።
የተማሪዎችን የምግብ ዕዳ ለማስወገድ እንዲረዳ MCPS የትምህርት ፋውንዴሽን የመመገቢያ ፕሮግራምን ለመደገፍ የማህበረሰብ ንቅናቄ ላይ ይቀላቀሉን። ምዝገባው ከ $30 ዶላር ጀምሮ ሲሆን የሩጫ ልብስ፣ ከነቴራ/ቲ-ሸርት እና የእንቅስቃሴ ቀን ዝግጅቶችን ያካትታል። የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ!
የጌትስበርግ የመጽሐፍ ፌስቲቫል፣ለልጆች የማንበብ፣ የመጻፍ እና የመግለፅ ፍላጎታቸውን ለማሳደግ የሚጠቅሙ ፕሮግራሞች፣ ወርክሾፖች፣ እና እንቅስቃሴዎች ያሉት ሲሆን፣ ቅዳሜ፣ ሜይ 16 ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ 6 p.m. ጌትስበርግ በሚገኘው ቦኽረር ፓርክ ይካሄዳል። አድራሻ፦ Bohrer Park, 506 S. Frederick Avenue in Gaithersburg. መግቢያ እና መኪና ማቆሚያ በነፃ ነው።
ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከተመደቡበት የመኖሪያ አካባቢ ትምህርት ቤት እንዲዛወሩ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚያስችላቸው የMCPS 2026-2027 የትምህርት ቤት ምደባ ለውጥ (COSA) የዝውውር ወቅት በመካሄድ ላይ ነው። የዝውውር ጥያቄዎች እስከ ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 7 ድረስ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ።
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
MCPS የማህበራዊ ሚድያ ገጾቻችንን ይከታተሉ፦ x.com/mcps / facebook.com/mcpsmd / instagram.com/mcps_md facebook.com/mcpsespanol / x.com/MCPSEspanol / instagram.com/mcpsenespanol
ኢሜሎች እና የጽሑፍ መልእክቶች/ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
የገቢያቸው ሁኔታ ብቁ ለሚያደርጋቸው ቤተሰቦች የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድ ስታርት ምዝገባ ክፍት ነው
የትምህርት ቤቶች ቀንመቁጠርያ/ካለንዳር
የወላጆች መገልገያ/ሪሶርስ ገጽ
ዘገባዎች፤የመረጃ ገፅ/Noticas en Español
የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፎች ክምችት ይመልከቱ
MCPS TV ቪዲዮ
MCPS TV español