MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ማርች 26, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  ስለ ጸደይ/ስፕሪንግ ዕረፍት በትኩረት አንብቡ!

ቤት ውስጥ እየተዝናኑም ሆነ በአየር ማረፊያ ረጅም የደህንነት ፍተሻ ሰልፍ ላይ ሲቆዩ፣ የጸደይ እረፍት ጠቃሚ መጽሐፍ ለማንበብ በጣም ጥሩ ጊዜ ነው። ለምን ጥሩ መጽሐፍ አንቃኝም? የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ቤተሰቦች  በዚህ የጸደይ/የስፕሪንግ እረፍት ወቅት – በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ወይም በጉዞ ላይ እያላችሁ ምን እንዳነበባችሁ እንድታሳዩን እናበረታታለን! የትም ቦታ ሆናችሁ አንብቡ፣ አንብቡ። ወንበር ላይ? ቢራ እየተጎነጩ? በአልጋ ላይ? በጭንቅላትዎ? ከዚያም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ #MCPSCaughtYouReading አጋሩን/አሳውቁን። ምንባቦቹ ወደየትኛው ታሪክ እንደመሯችሁ ለማየት ጓጉተናል! እና፣ ቅዳሜ፣ ሜይ16 በጌትስበርግ በሚካሄደው የመጽሐፍት ፌስቲቫልላይ ለመገኘት ቀኑን ያስታውሱ። 

 
  ስለ ጸደይ/ስፕሪንግ የትምህርት ምዘና ለመዘጋጀት፡ ቤተሰቦች ማወቅ ያለባቸው ነገሮች

የዓመቱ መጨረሻ የትምህርት ግምገማዎች አስፈላጊ ናቸው፤ ምክንያቱም ተማሪዎቻች የሚያውቁትን፣ የሚረዱትን፣ እና ማድረግ የሚችሉትን ያመላክታሉ። የሜሪላንድ አጠቃላይ የግምገማ ፕሮግራም ወይም MCAP ፈተና፣ በሜሪላንድ የአካውንትኤብሊቲ ሲስተም የተማሪዎች የትምህርት አፈፃፀም የሚለካበት ተግባር ነው። MCAP አፈፃፀም የሜሪላንድ ትምህርት ቤት የሪፖርት ካርድ ቁልፍ አካል ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የኮከብ ደረጃ አሰጣጦችን ያካትታል። የውጭው ዓለም የተማሪዎቻችንን አፈጻጸም፣ የትምህርት ቤቶቻችንን አፈጻጸም እና እንደ ዲስትሪክት ያለንን የአፈጻጸም ብቃት የሚገመግመው እና የሚያየው በዚህ መንገድ ነው። 

ምናልባት ካመለጠዎት፣ በፈተና መርሃ ግብሩ ላይ ስለተደረጉ ለውጦች እና ተማሪዎ ለመጪዎቹ የትምህርት ምዘናዎች እንዴት መዘጋጀት እንዳለበ(ባ)ት ለመርዳት እንዲችሉ መረጃዎችን ለቤተሰቦች አጋርተናል።

 
  ጊዜው የተቃረበ ስልሆነ ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን።

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን! በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ፣ MCPS ጉልህ የሆኑ የአሠራር ለውጦችን እና ማሻሻያዎችን ተግባራዊ አድርጓል — ይህም ስለ ትምህርት ውጤት አሰጣጥ፣ ደህንነት (በትምህርት ቤቶች ውስጥ የፖሊስ መገኘትን ጨምሮ)፣ የተማሪዎች የስነምግባር ደንብ፣ ክፍት የምሳ ሠዓት እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለ ሞባይል ስልኮች አጠቃቀምን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሶችን የሚመለከቱ ናቸው። MCPS ለቤተሰቦች፣ ለተማሪዎች፣ እና ለትምህርት ቤት ሰራተኞች አስፈላጊ በሆኑት በእነዚህ በርካታ ጉዳዮች ላይ በተግባር ለእርስዎ እንዴት እየሰራ እንደሆነ ለማወቅ የዳሰሳ ጥናቶችን እያካሄደ ነው። የዳሰሳ ጥናቱ እዚህ ይገኛል። ይበልጥ ያንብቡ።

በተጨማሪም፣ አስተያየትዎ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ የሚያብራራውን ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ፡
English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese |አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

 

 
  ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

የትምህርት ቤት የመጨረሻ ቀን ሐሙስ፣ ጁን 18 ነው።

ማክሰኞ (ማርች 24)፣ የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ ሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሶስት ተጨማሪ ቀናት የተማሪዎችን ወደ ት/ቤት መምጣት ለማስቀረት ያቀረብነውን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት በውሳኔ አጽድቋል። ይህ የማካካሻ ትምህርት የሚሰጥባቸው ቀናት፣ ኤፕሪል 15 ተማሪዎች ቀደም ብሎ ከሚለቀቁበት የትምህርት ቀን ጋር ተዳምሮ፣ ዲስትሪክቱ የትምህርት ዓመቱን ቀደም ብሎ ካቀደው ጊዜ ቀደም ብሎ እንዲያጠናቅቅ እና ሁሉንም የስቴት የትምህርት ጊዜ ድንጋጌዎችን ማሟላት ያስችለዋል። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  የትምህርት ቦርድ ቨርቹዋል የትምህርት ዕቅድ አፅድቋል

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በዛሬው ስብሰባ (ማርች 26)፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 2026–2027 ከባድ የአየር ሁኔታ ቨርቹዋል የማስተማር ዕቅድ አጽድቋል፣ ይህም የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ (MSDE) መስፈርቶችን የሚያሟላ እና የመጨረሻ የማፅደቅ ውሳኔ ነው።

እቅዱ ተማሪዎች በአካል ተገኝተው በሚማሩበት ጊዜ በተሻለ ሁኔታ እንደሚማሩ የታወቀ ቢሆንም፣ በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት ት/ቤቶች ለብዙ ቀናት ተዘግተው የትምህርት መስተጓጎል በሚያጋጥምበት ወቅት ትምሕርት መቀጠል እንዳለበት ትኩረት ይሰጣል። ቢያንስ ለአራት ሰዓታት የሚቆይ ቀጥታ ማስተማር፣ ቀጣይነት ያለው የተማሪዎች አገልግሎቶችን፣ እና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች እና የኢንተርኔት ተደራሽነትን ያካትታል። አስፈላጊው ነገር፣ ይህ የበረዶ ቀናትን መተካት ማለት አይደለም — ቨርቹዋል ትምህርት መስጠት ተግባር ላይ የሚውለው ቀደም ሲል በካለንደር የተያዙት ቀናት ከተሟጠጡ እና ሊተነበዩ በሚችሉ፣ ለብዙ ቀናት በሚከሰቱ ከባድ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ወቅት ብቻ ነው።

 
  የትምህርት ቦርድ በትምህርት ቤት ወሰኖች፣ ፕሮግራሞች እና ሪጅናል ፕላን/ዕቅድ ላይ የቀረቡትን ምክረሃሳቦች አጽድቋል።

ማክሰኞ (ማርች 26) የትምህርት ቦርድ ከትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ስለ ሪጅናል ሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞች የቀረቡትን የት/ቤቶች ክልል ምክረሃሳቦች እና በትምህርት ዲስትሪክቱ ውስጥ አዲስ የሪጅናል ሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞችን በተመለከተ አዲስ አቀራረብ አጽድቋል። በሥራ ላይ እንዲውሉ የጸደቁት ምክረሃሳቦች በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት እድሎችን የማስፋት፣ አመቺ ያልሆነ የተማሪዎችን ምዝገባ ሁኔታዎችን እና ወጥነት የሌለው የት/ቤት ህንጻዎች አጠቃቀም ላይ የሚታዩትን ለመፍታት የታለሙ ናቸው። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች ከውተን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Wotton HS) የክስተት ግምገማ ውጤቶችን አቅርበዋል።

ማርች 26 የትምህርት ቦርድ መደበኛ ስብሰባ ላይ፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች ፌብሩዋሪ 9 በቶማስ ኤስ. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተፈፀመውን የተኩስ ረብሻ ተከትሎ አጠቃላይ የድህረ-እርምጃ ሪፖርት ለቦርዱ አቅርበዋል።

ሪፖርቱ በጠንካራ የደህንነት ጥበቃ ሲስተም፣ በስልጠናዎች እና በትብብር የተደገፈ በሠራተኞች እና በመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎች የተከናወነ ፈጣን እና የተቀናጀ ምላሽን በጉልህ ያሳያል። እንዲሁም የመገናኛ፣ የምላሽ ፕሮቶኮል ወጥነት እና የማቀናጀት ሂደቶችን ጨምሮ መሻሻል ያለባቸው ቁልፍ ሁኔታዎች ተለይተው ቀርበዋል። MCPS ስልጠናን ለማጠናከር፣ የግንኙነት ስርዓቶችን ለማሻሻል፣ ተማሪዎችን ከቤተሰብ ጋር የማገናኘት ሁኔታን ለማሻሻል እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሱፐርቪዥን/ክትትልን ከማሳደግ አንፃር ቀድሞውኑ እርምጃ እየወሰደ ነው። ድህረ-እርምጃ ሪፖርቱን ያንብቡ

 
  ስለ ልዩ ትምህርት አገልግሎቶች፣ የሰው ኃይል እና ድጋፍ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን

የልዩ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል ረቡዕ፣ ሜይ 6 ከቀኑ 6-7:30 p.m. ለቤተሰቦች ዌቢናር ፕሮግራም ያካሂዳል፣ ይህም በልዩ ትምህርት አገልግሎቶች፣ በሠራተኞች አደረጃጀት እና በድጋፍ አሰጣጥ ዙርያ ምን አዲስ ነገር እንዳለ— እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ — መሰጠት ባለበት አፅንኦት ላይ ያተኩራል። MCPS የልዩ ትምህርት መሪዎች ይህ ለትምህርት ቤቶች እና ለመማሪያ ክፍሎች ምን ማለት እንደሆነ አውድ ይሰጣል። ክፍለ ጊዜው በቨርቹዋል የሚካሄድ ሲሆን ከጥያቄዎችና መልሶች ጋር በአጭር አቀራረብ ይከናወናል። ተጨማሪ ዝርዝሮች፣ የስብሰባ ዙም ሊንክ/Zoom ጭምር፣ በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ይጋራሉ።

 
  ተማሪዎች፦ ለተሻለ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ያላችሁን ራዕይ አካፍሉ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምክር ቤት አባል ዊል ጃዋንዶ የተሻለ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያላቸውን ራዕይ የሚያካፍሉ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ይፈልጋሉ። ስለ ሕዝብ ፖሊሲ ​​ጉዳይ አጭር የቪዲዮ ድርሰት ያቅርቡ፤ ይህም $100 ዶላር የስጦታ ካርድ የማሸነፍ እድል እንዲኖርዎት እና ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 14 ለሚካሄደው አንድ ቀን በምክር ቤት አባልነት እንዲያገለግሉ ያስችልዎታል። የመጨረሻ ቀን፡ ረቡዕ፣ ኤፕሪል 8 ነው።ያመልክቱ

 
  ተማሪ የቦርድ አባልነት (SMOB) እጩዎች ጋር ተገናኙ፡ ልዑል ዳዊት (Leul Dawit) እና ሬሜይ ገርሜይ (Reemey Ghermay)

ለሚቀጥለው ተማሪ የቦርድ አባልነት (SMOB) በእጩነት ስለቀረቡት የበለጠ ለማወቅ ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ፡- በእጩነት የቀረቡት ተወዳዳሪዎች በኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልዑል ዳዊት እና በዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነች ሬሜይ ገርሜይ ናቸው። ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ረቡዕ፣ ኤፕሪል 22 በሚካሄደው ምርጫ ላይ ድምጽ መስጠት ይችላሉ። 

 
  ቦታዎች በፍጥነት እየተያዙ ናቸው፤ ቶሎ ይመዝገቡ!

የሱፐርኢንቴንደንቱ "Shuffle" በፍጥነት እየተቃረበ ነው! የተማሪዎችን የምግብ ዕዳ ለማስወገድ ኤፕሪል 11 ቦኽረር ፓርክ ላይ በሚካሄደው የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ቀን ይቀላቀሉን። የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ! 

ከተካሄደ በኋላ፣ የበለጠ የቤተሰብ ደስታ ጊዜ ስለሚኖር ይቆዩ! Manna Food Center እና UnitedHealthcare — A Wider Circle፣ EveryMind፣ GOCO Health እና WorkSource Montgomery — ጋር በመተባበር "Nourish & Flourish" የተሰኘ የማህበረሰብ ሪሶርስ አውደ ርዕይ ያካሄዳሉ። ይህ ነጻ እና ለቤተሰብ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ምግብ፣ የጤና ምርመራዎች፣ የአኗኗር ዘይቤ አውደ ጥናቶች፣ የተመጣጠነ አመጋገብ ግብዓቶች፣ የሥራ ቅጥር አገልግሎቶች፣ እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ያቀርባል፤ ሁሉም በተመጣጠነ አመጋገብ እና በአጠቃላይ ጤና መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ላይ ያተኮሩ ናቸው።

 
  ቦርዱ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የወሰን ጥናት በሚመለከት በቀረበው ምክረሃሳብ ላይ እርምጃ ይወስዳል።

ቦርዱ ዛሬ (ማርች 26) ባደረገው ስብሰባ ላይ የተማሪዎች ምዝገባ ቁጥር መቀነስ እና የትምህርት ቤቶች ህንጻዎች አጠቃቀም አለመመጣጠንን በተመለከተ አጠቃላይ ሪፖርት ተቀብሎ ቀጣዩን የሥራ ደረጃ አጽድቋል፣ ይህም የትምህርት ቤቶችን ውህደት እና መዘጋት ሊያስከትል የሚችል የካውንቲ አቀፍ የአንደኛ ደረጃ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የወሰን ጥናት እንዲጀመር ማድረግ ነው። 

ይህ እርምጃ የተማሪዎች ምዝገባ ማዘቅዘቅ ሁኔታዎችን፣ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስላለው አቅም እና የአሠራር ብቃት ማነስ ምላሽ ይሰጣል። ይህ ሥራ በማህበረሰቡ ውስጥ ጠንካራ ትችት ሊፈጥር ቢችልም፣ ለወደፊቱ መገልገያዎችን፣ የትምህርት ግብዓቶችን እና የተማሪዎችን ፍላጎቶች በተሻለ ሁኔታ ለማሳለጥ — ምንም አይነት የትምህርት ቤት መዘጋት ሳይወሰን በፊት — በመረጃ ላይ የተመሰረተ እና በማህበረሰብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሂደት ውስጥ የመሳተፍን አስፈላጊነት ያንፀባርቃል።

ውሳኔውን ያንብቡ.

 
  MCPS የአሜሪካን 250ኛ ዓመት በተማሪዎች የኪነጥበብ ስራዎች ያከብራል።

በዚህ ዓመት የአሜሪካን 250ኛ ዓመት ክብረ በዓል ለማክበር፣ MCPS ከእያንዳንዱ ትምህርት ቤት አንድ የተመረጠ ተማሪ የሚሳተፍበት ዲስትሪክት አቀፍ "eBook — Many Voices, One Nation" — እያዘጋጀን ነው። ተማሪዎች ኦሪጅናል ግጥም፣ ድርሰት፣ የሙዚቃ ወይም የስነ-ጽሑፍ ስራ፣ ትርኢት ወይም የስነጥበብ ስራ ማቅረብ ይችላሉ። የማስረከቢያ መመሪያዎችን ይመልከቱ እና ተጨማሪ ይወቁ።

 
  የአገልግሎት ሽልማቶችን ለማግኘት የSSL ሰዓቶችን እስከ ማርች 27 ድረስ ያስገቡ

የጸደይ/ስፕሪንግ እረፍት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ለማግኘት ምቹ ጊዜ ነው! እነዚህን ቁልፍ የጊዜ ገደቦች ልብ ይበሉ፡

  • አርብ፣ ማርች 27፡ የሽልማት ውድድር ሰነድ ለማቅረብ የመጨረሻ ቀን ነው።
    • ሲንየር ተማሪዎች፡ የክብር አገልግሎት የምስክር ወረቀት ለማግኘት 240+ ሰዓትማግኘት አለባቸው።
    • የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች፡ የሱፐርኢንቴንደንት SSL ሽልማት ለማግኘት 75 ሰዓትአገልግሎት ማጠናቀቅ አለባቸው።
    • MCPS ቅጽ 560-51 ለትምህርት ቤትዎ SSL አስተባባሪ ያቅርቡ።
  • አርብ፣ ሜይ 29፡ ሁሉም ሌሎች 2025–2026 የትምህርት አመት SSL ቅጾች መቅረብ ያለባቸው የመጨረሻ ቀን ነው።

ማሳሰቢያ፦ ለመመረቅ 75 የአገልግሎት ሰዓት ማግኘት ያስፈልጋል። የአገልግሎት እድሎችን እዚህ ይመልከቱ።

 
  ወጣቶቻችንን ለመደገፍ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመገንባት ኤፕሪል 18 ላይ ይቀላቀሉን

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአእምሮ ጤና እና የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም መከላከል የቤተሰብ መድረክ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 18 ከቀኑ 1–4 p.m. በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ይካሄዳል። አድራሻ፦ Montgomery Blair High School, 51 University Blvd. East in Silver Spring. ይህ ዝግጅት ነፃ እና ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ ለሠራተኞች፣ እና ለማህበረሰብ አባላት ክፍት ነው። የሚሳተፉ ተማሪዎች 3 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። አውደጥናቱ የሚካሄደው በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ይውሰዱ

 
  የስኮላርሺፕ እድል፡ ለሲንየር ተማሪዎች "MCABSE Awards" ተዘጋጅቷል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጥቁሮች ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ጥምረት (MCABSE) ለዓመታዊው እውቅ የአፍሪካን አሜሪካውያን ምሁራን ሽልማት የመወዳደሪያ ፅሑፎችን እየተቀበለ ነው። ሽልማቶቹ ድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለመከታተል ለሚፈልጉ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተመራቂዎች ክፍት ናቸው። ከእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንድ ተማሪ ይመረጣል። ማመልከቻ መቅረብ ያለበት አርብ፣ ኤፕሪል 10 ነው።ያመልክቱ ጥያቄ ካለዎት ወደ ቻርልስ S. ፌምስተር/Charles S. Feamster ወይም አሲላህ S. ሬዲክ/Aseelah S. Reddick ኢሜይል ይላኩ።

ለተማሪዎች ሌሎች እድሎች

  • "Girl Power Contest" ውድድር፡ 5 አመት እድሜ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጃገረዶች ክፍት ነው፣ ማን አነሳሳሽ እና ለውጥ ለማምጣት እንዴት እንደቻለች ይንገሩን? ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።
  • አስተማማኝ የቪዲዮ ውድድር "Keeping It Safe Video Contest"፡ ውድድሩ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ከ 21 ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ተማሪዎች የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች እና አስከፊ ጉዳቶች 30 ሰከንድ ቪዲዮ ፈጥረው/አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።
  • "Sober Vibes Essay Contest" የድርሰት ውድድር፡- እኩዮች ከፕሮም በፊት፣ በፕሮም ወቅት፣ ወይም በኋላ አልኮል እንዳይጠጡ አሳማኝ የሆነ ድርሰት በጽሑፍ አዘጋጅተው መወዳደር ይችላሉ። ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።
  • AAPI አርት/የስነጥበብ ውድድር/ "AAPI Art Competition": ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራሁለተኛ ክፍል (K–12) ተማሪዎች ክፍት ነው። የመጨረሻ ቀን፦ እሑድ፣ ኤፕሪል 5ነው።
  • የማህበራዊ ፍትህ ትርኢት፡- የወንጀል ፍትህ ማሻሻያ፣ በሴቶች መብቶች፣ በአካባቢ ፍትህ፣ እና የዘረኝነት ፍትህ ዙሪያ ከባለሙያ ተናጋሪዎች እና ድርጅቶች ጋር ይገናኙ። SSL ሰዓቶች ይሰጣሉ። ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 ከጠዋቱ 10:30 a.m. እስከ 1 p.m. ፣ በዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Walt Whitman High School. Feria de Justicia Social LASJ
  • ስለ እግረኞች ደህንነት የኪነጥበብ/አርት ውድድር፡ ከመዋእለ ህጻናት እስከ 5ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የእግረኞችን ደህንነት መጠበቅን በሚመለከት የኪነጥበብ/አርት ስራዎችን በማዘጋጀት እንዲወዳደሩ ይበረታታሉ። የመጨረሻው ቀን ዓርብ፣ ኤፕሪል 17 ነው።
  • NAACP የወጣቶች ስብሰባ: ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 18 10 a.m.-2 p.m. , በሪቻርድ ሞንትጎሞሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Richard Montgomery High School. ምሳ፣ ትራንስፖርት፣ እና SSL የአገልግሎት ሰዓት ይሰጣል።
 
  ማሳሰቢያ
 
  በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
©1995–2026 Montgomery County Public Schools