የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ረቡእ፣ ኤፕሪል 8 ለተማሪዎች ተጨማሪ ምግቦችን ይሰጣል።
በዚህ ሣምንት፣ በመጪው የስፕሪንግ እረፍት ምክንያት፣ MCPS የቁርስ፣ የምሣ እና የእራት ምግቦችን ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጆች እና ለ MCPS ተማሪዎች (እድሜ ሳይገድብ) ዛሬ፣ ኤፕሪል 7 እና ረቡእ፣ ኤፕሪል 8 በነፃ ይሰጣል። ከሐሙስ፣ ኤፕሪል 9 እስከ ሰኞ፣ ኤፕሪል 13 የምግብ አገልግሎት አይኖርም። ረቡእ፣ ኤፕሪል 8፣ ለሐሙስ ኤፕሪል 9 የሚያገለግል ተጨማሪ ምግብ ለቤተሰብ በከረጢት ይሰጣል። በከረጢት የሚሰጠው ተቸማሪ ምግብ የሚያካትተው ለቁርስ፣ ለምሳ እና ለእራት የሚሆን ምግብ ስለሆነ በሁሉም የምግብ ማደያ ጣቢያዎች ይገኛል። ምግቦቹ በመደርደሪያ ላይ የሚቆዩ ስላልሆነ በማቀዝቀዣ ውስጥ መቀመጥ አለባቸው። MCPS ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 14 የምግብ አገልግሎት ይጀመራል። ምግብ የሚሰጥባቸውን ቦታዎች የተሟላ ዝርዝር ለማግኘት እባክዎ ይህንን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የምግብ አገልግሎት ድረገጽ ይመልከቱ/MCPS Meals Service webpage።
ሚኒስትሪዎችን የሚያገለግሉ ሴቶች "Women Who Care Ministries" ለሣምንት መጨረሻ የሚሆኑ ምግቦችን ዓርብ፣ ኤፕሪል 10፣ ከ 11 a.m.- 6 p.m. በዚህ አድራሻ፦ Montgomery Village site located at 19642 Club House Road, Suite 620, in Montgomery VIllage ለቤተሰቦች ምግብ ይሰጣሉ።
ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።
Manna Food Center-መና የምግብ ማእከል ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 ለሣምንት መጨረሻ የሚሆኑ ምግቦችን በከረጢት ያድላል። ጊዜው እና ቦታዎቹ ዓርብ፣ ኤፕሪል 10 በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ድረገጽ - MCPS website ላይ ይገለጻል።
ኤፕሪል 8 የ "Chromebook" እና "Wireless Hotspot" ይከፋፈላል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የርቀት ትምህርትን ለማመቻቸት Chromebook ወይም mobile Wi-Fi hotspot device እንዲያገኙ ለተማሪዎች ተጨማሪ እድል ይሰጣል። ባለፈው ሳምንት ለትምህርት ቤቶቻቸው ጥያቄ ላቀረቡ ተማሪዎች፣ በዚህ ረቡእ፣ ኤፕሪል 8 ከ 1:30–4 p.m. ዲቫይሶቹን-devices መውሰድ ይችላሉ እነዚህ ዲቫይሶች-devices የሚሰጡት በቅድሚያ በቀረበ ጥያቄ መሠረት ብቻ ነው። ዲቫይሶች-devices እንዲወስዱ የተዘጋጀላቸው ተማሪዎች ከየት መረከብ እንደሚችሉ ለመንገር ከ MCPS ይገለጽላቸዋል። "Chromebooks እና mobile hotspots" ለማግኘት ተጨማሪ እድል የሚሰጠው ኤፕሪል 13 በሚሆንበት ሣምንት ውስጥ ነው። ኤፕሪል 8 ለሚደረገው ማከፋፈል ለእርስዎ ልጅ ትምህርት ቤት ጥያቄ የማቅረብ እድል ያላገኙ ከሆነ፣ እባክዎ በሚቀጥለው ዙር ለሚከፋፈለው እድል ለማግኘት ትምህርት ቤትዎን ያነጋግሩ።
እቤታችሁ የኢንተርኔት አገልግሎት ለሌላችሁ ቤተሰቦች፣ Xfinity ከራሳቸው "Wi-Fi public wireless network" በነፃ አገልግሎት እየተሰጠ ነው። እቤት ውስት ዲቫይሱን ከ Wi-Fiat ጋር ለማገናኘት ስትሞክሩ የ "Xfinity network" መታየት አለበት። የ "map of Xfinity Wi-Fi hotspots" ለመመልከት ይህንን ድረገጽ ይጎብኙ www.xfinity.com/wifi hotspot ላይ ከገቡ በኋላ ከሚገኙት-ከሚታዩት hotspots ውስጥ xfinitywifi የሚለውን ኔትዎርክ ስም ይምረጡ እና browser-መቃኛውን ያስጀምሩት። በተለይም እነዚህን ከሌላ ሰው ቤት እንኳ ለማግኘት ይቻላል።
|
|