Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Aug. 25, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች

ዛሬ ኦገስት 25/2020 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የትምህርት ቦርድ ኦገስት 31 የሚጀመረውን የመጀመሪያ ሴሚስተር የ MCPS የትምህርት ማገገሚያ እቅድ አፅድቋል። ቦርዱ ስለ እቅዱ ቁልፍ የሆኑ ጉዳዮችን በመገምገም ውይይት አድርጓል፦

  1. የኤለመተሪ እና የሁለተኛ ደረጃ መርሃግብሮች
  2. በትምህርት ላይ ስለ መገኘት እና ትኩረት ማድረግ
  3. ለሠራተኞች፣ ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ቨርቹወል ትምህርትን የሚደግፍ ቴክኖሎጂ እና ሪሶርሶች
  4. ስለ ትምህርት ዓመት ካላንዳር
  5. ለተማሪዎች የምግብ አገልግሎት
  6. አስተማሪዎች እቅድ ስለሚያዘጋጁበት ጊዜ

[የፀደቀውን የማገገሚያ መመሪያ ያንብቡ ]

እንዲሁም ቦርዱ ከአርኮላ እና ሮስኮይ ኒክስ-Arcola and Roscoe Nix የኤለመንተሪ ትምህርት ቤት ኮሚቴዎች ስለ ቨርቹወል የሙሉ ቀን መርሃግብር ልምዳቸውን በዚህ ሠመር በፈጠራ ካላንዳር ያዘጋጁ ት/ቤቶች ስለሆኑ-Innovative Calendar Schools የነበራቸውን ተሞክሮ አዳምጧል። የቦርዱን ስብሰባ ለመከታተል ያልቻሉ ከሆነ፣ ውይይቱን እዚህ ይመልከቱ

ኦገስት 6 ረቂቅ እቅዱን ለቦርድ ካቀረብን ወዲህ፣ በሺዎች ከሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች፣ ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት ግብረመልስ አግኝተናል። ይህንን ግብረመልስ የማበረሰባችንን ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ለማሟላት በርካታ ማስተካከያዎችን ለማድረግ እና እቅዳችንን ለማዳበር ተጠቅመንበታል። በትምህርት ቦርድ የፀደቀው እቅድ የሚያተኩረው ለፎል ሴሚስተር (ኦገስት 31/2020 እስከ ጃኑወሪ 29/ 2021) ብቻ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። የጤና ሁኔታዎች የሚፈቅዱ ከሆነ፣ ከሁለተኛው ሴሚስተር ጀምሮ በአካል ትምህርት ለመስጠት ኖቬምበር ላይ ውሳኔውን እንደገና ለማጤን እና አስተያየቶችን ለማቅረብ MCPS ከአካባቢ እና ከስቴት መሪዎች ጋር በጋራ ይሠራል።

መታወቅ ያለባቸው ቁልፍ ነገሮች፦

  • ትምህርት የሚጀመረው 31/2020 ነው።
  • የተማሪዎች የጊዜ ሠሌዳ እሮብ፣ ኦገስት 26 በ "ParentVUE እና StudentVUE" ላይ ይታያል። በተጨማሪ፣ የጊዜ ሠሌዳው ሪፖርት ማድረጊያ ሊንክ በኦንላይን ይፋ ይገለጻል ። ወላጆች እና ተማሪዎች ለሪፖርቱ የተማሪን መታወቂያ እና ይለፍ ቃል በመጠቀም ሎግኢን ማድረግ አለባቸው።
  • ለኤለመንተሪ ተማሪዎች፣ የትምህርት ቤት ቀን 8:45 a.m. ይጀመራል እና 3:15 p.m. ይጠናቀቃል። ለሁለተኛ ደረጃ (ሰከንደሪ ስኩል) ተማሪዎች የትምህርት ቤት ቀን የሚጀመረው 8:45 ሲሆን 3:30 p.m. ይጠናቀቃል።
  • የቴክኖሎጂ እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ስርጭት ፎል እስከሚጠናቀቅ ይቀጥላል። ርእሰመምህራን ዝርዝሮቹን በቀጥታ ለትምህርት ቤቶቻቸው ማህበረሰቦች ይፋ ያደርጋሉ።
  • የፎል የምግብ አገልግሎት ሰኞ፣ ኦገስት 31 ይጀመራል። የጣቢያዎቹን ዝርዝር እና የ FARMS ማመልከቻ ከዚህ ማግኘት ይችላሉ
  • ይህንን ይመልከቱ ለወላጅ ጠቃሚ ቼክሊስት እና የወላጅ እና/ወይም የተማሪ webinar ለመሣተፍ ይመዝገቡ
  • ከልጅዎ ትምህርት ቤት እና ከአስተማሪዎች የሚላኩ ጠቃሚ መልእክቶችን ዘወትር ይከታተሉ-ይመልከቱ።
  • ለቨርቹወል የፎል አትሌቲክስ ወቅት ምዝገባ አሁን ክፍት ነው፣ የሚድል ስኩል ምዝገባ ኦገስት 28 ክፍት ይሆናል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፎል ወቅት የሚጀመረው ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 14 ሲሆን እስከ ዓርብ፣ ኦክቶበር 16 ይካሄዳል። የሚድል ስኩል የፎል ወቅት የሚጀመረው ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 22 ሲሆን እስከ ሐሙስ፣ ኦክቶበር 8 ይቀጥላል። ተማሪዎች በየትምህርት ቤቶች ድረገጽ ላይ በሚገኙ የምዝገባ በይነመረብ-ሊንክ ላይ የምዝገባ ሒደት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

ለ MCPS ተማሪዎች በሙሉ የወደፊት ትልማቸው የሠመረ እንዲሆን የሚያዘጋጃቸው ትምህርት ለመስጠት የምናደርገው ጥረት ፅኑ አቋማችን ነው። ተማሪዎች በሚያመቻቸው መንገድ ከፍተኛ ጥራት ያለው የትምህርት ተሞክሮ እንደሚያገኙ እንደምናረጋግጥ የማገገሚያ እቅዳችን አቅጣጫ ይሰጣል። ከአዲሱ የትምህርት ምህዳር ጋር እየተጣጣመ እንዲሄድ የማገገሚያ እቅዱ በተደጋጋሚ ክለሳ ይደረግበታል። የማገገሚያ መመሪያ እና ስለ 2020-2021 የትምህርት ዓመት ወቅታዊ መግለጫ ለመመልከት ይህንን በይነመረብ Fall 2020 Recovery website ይጎብኙ።

ስለትብብርዎ እናመሰግናለን። አብረን እየሥራን፣ ለልጆቻችን ይህ ስኬታማ የትምህርት ዓመት እንደሚሆን እናረጋግጣለን።

ከሰላምታ ጋር

Montgomery County Public Schools