Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Nov. 06, 2020


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ | Português


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች

ዛሬ ከሠዓት በኋላ (ኖቨምበር 6)፣ የትምህርት ቦርድ ስለ MCPS የትምህርት ማገገሚያ እቅድ እና በፈረቃ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ሁኔታዎችን ለመነጋገር ስብሰባ አድርጓል። ስብሰባው እየተካሄደ ሳለ የቀጥታ ስርጭቱን ለመመልከት ያልቻሉ ከሆነ፣ አቀራረቡን እዚህ መመልከት ይችላሉ እና በፓወር ፖይንት የቀረበውን እዚህ ለማየት ይችላሉ።

በኦክቶበር 27 እንደገለጽንላችሁ፣ MCPSበፈረቃ በአካል ተገኝተው ለመማር የሚያስችል የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄ መቆጣጠሪያ ስልት "health metrics grid" አዘጋጅቷል (hyperlink)። የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄ ስልቱ የተዘጋጀው ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ኃላፊዎች ጋር ምክክር በማድረግ ሲሆን ከበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC) መመሪያ ጋር የተጣጣመ ነው። እነዚህ የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄ ስልቶች ከተጠበቁ፣ MCPS በተለያየ ፈረቃ በአካል ተገኝቶ የመማር እቅዱን ከጃኑወሪ 12/2021 ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል በልዩ ትኩረት  የተለዩ ስፔሻል የትምህርት ፕሮግራሞች ፣ አንዳንድ ሙያ ነክ የቴክኖሎጂ ትምህርት ፕሮግራሞች ላይሰንስ ለማግኘት በእጅ መሠራት ያለባቸው፣ እና ሌሎች የስፔሻል ተማሪ ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት የሚያሻቸው ናቸው። የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄ ስልቱ እየተሟላ ከቀጠለ፣ከፌብሩወሪ 1/2021 ጀምሮ በርካታ ቡድኖች በፈረቃ በአካል ተገኝተው የመማር ሒደቱ ይጀመራል ፣ የሁለተኛ ሴሚስተር መረጀመሪያ ማለት ነው።

ለሁለተኛ ሴሚስተር የቀረበውን ሙሉውን የጊዜ ሠሌዳ ንድፈሃሳብ እና የፈረቃ ቡድኖችን እዚህ ይመልከቱ።

በዚህ እቅድ ወደፊት መግፋት የምንችለው የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄ ስልቶቹ ከተሟሉ ብቻ መሆኑን አበክሬ ለመግለጽ እፈልጋለሁ። በዲሰምበር ወር በአካል ተገኝተው መማር-ማስተማር እንድንጀምር እንደሚፈልጉ ከበርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሰምተናል። በዜና አውታሮች እንደሰማችሁት፣ በካውንቲያችንም ሆነ በስቴቱ በጠቅላላ የወረርሽኙ ስርጭት እየጨመረ መሄዱን እና በዚህ ወቅት ያሉት ቁጥሮች የተማሪ ቡድኖችን በአካል ተመልሶ ለመማር የሚያስደፍሩ አይደለም። ከካውንቲያችን የጤና ኃላፊዎች እና ሌሎችም የካውንቲያችን መሪዎች ጋር በጋራና በቅርበት መሥራታችንን እንቀጥላለን። ተማሪዎቻችንን ጤንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ በፍጥነት ወደ ህንጻዎቻችን ተመልሰው እንዲማሩ ለማድረግ ያለንን ከፍተኛ ፍላጎት ይረዱናል። ከስቴቱ የጤና ኃላፊዎች፣ ከገቨርነሩ ጽ/ቤት፣ እንዲሁም  ከስቴት የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት መመሪያ አግኝተናል።

ወደ ትምህርት ቤት ሕንፃዎች በአስተማማኝነት መመለስ

በሠመር ወቅት እንደተገለጸው ተማሪዎችም ሆኑ ሠራተኞች ወደ ትምህርት ቤት በሚመለሱበት ጊዜ በትምህርት ቤት ሕንፃዎች ውስጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ የተለየ ይሆናል። ተማሪዎች እና ሠራተኞች ይጠበቅባቸዋልየፊት መሸፈኛዎችን እንዲጠቀሙ፣ አካላዊ ርቀት እንዲጠብቁ፣ እና አዘውትረው እጃቸውን እንዲታጠቡ ይጠበቅባቸዋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በርካታ ሪሶርስ እንዲሟላ በህንጻዎች ላይ ንጹሕ አየር እንዲኖር እና እንደአስፈላጊነቱ ሲስተሙን ለማሻሻል በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስት አድርጓል።

የወላጆችን ፍላጎት ለማወቅ የሚደረግ ዳሰሳ

በኖቨምበር 11፣ ልጆቻቸው በተለይ ቨርቹወል ትምህርት ላይ እንዲቆዩ ይፈልጋሉ? ወይስ በፈረቃ በአካል እና ቨርቹወል ትምህርት በተጓዳኝ እንዲማሩ ይፈልጋሉ? የትኛውን አሠራር እንደሚመርጡ ለማወቅ ወላጆች አጫጭር መጠይቆችን እንዲሞሉ ይጠየቃሉ። ሁለቱም አማራጮች ተማሪዎች አትሌቲክስ እና ከከሪኩለም ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች ላይ በአካል እንዲሳተፉ ይፈቅዳሉ። ለተማሪያቸው MCPS መጓጓዣ እንዲያቀርብ ይፈልጉም እንደሆነ ለማወቅ ወላጆችን እንጠይቃለን።

በአካል ተገኝተው እንዲማሩ ለሚመርጡ ወላጆች የማሳወቂያ ጊዜ ሠሌዳ

የወላጆች ቅድመ ምርጫ የዳሰሳ መስኮት ከተዘጋ በኋላ፣ እንደየአካባቢው በአካል ተገኝቶ የመማር ፍላጎት ትንተና ይደረጋል። መረጃው ለትምህርት አቀራረብ የሚያገለግሉ ሞዴሎችንና የሞዴሎቹን ቦታዎች ለመንደፍ/ለማዘጋጀት የሚያገለግል ከመሆኑም ሌላ በአካል ተገኝተው መማርን ለሚመርጡ ወላጆች የማሳወቂያ መርሃግብር ይከናወናል። ቤተሰቦች የሚመርጡት ቨርቹወል ብቻ የመማር ሞዴል ወይም በአካል/ቨርቹወል በተጓዳኝነት እንዲማሩ የትኛውንም ሞዴል የሚመርጡ ቢሆን ትምህርት ቤቶች መሣሪያ በመሆን የተማሪዎችን ፍላጎት ለሟሟላት የሚያመች ዲዛይን ይሠራሉ። በተጨማሪም ትምህርት ቤቶች ያዘጋጁትን ንድፍ ሞዴሎች ለወላጆች የሚገልጹ ከመሆኑም በላይ በአካል ተገኝተው እንዲማሩ ለመረጡት ወላጆች መርሃግብሩን ያረጋግጡላቸዋል። ይሄ የግንኙነት ሒደት የሚጀመረው የትምህርት ቤት ሠራተኞች በአካል የመመለስ እቅድ መሠረት ጃኑወሪ ላይ ሲመለሱ ይሆናል።

የማስተማሪያ ሞዴሎች

ወደ ሕንጻዎች ከተመለስን በኋላ እንዴት ትምህርት እንደሚሰጥ፣ ለተማሪዎች የተለየ እንደሚሆን፣ በኮቪድ ምክንያት የሚደረጉ ገደቦችና የሠራተኞች ተደራሽነት አንድ ላይ እንደሚታይ መገንዘብ ያስፈልጋል። MCPS በአካል የሚሰጥ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እንዲኖሩ ለማድረግ እና በተሟላ ጤንነት መማር - ማስተማርን ለማከናወን በትጋት እየሠራ ነው። በአካል የሚሰጥ ትምህርት በቀጥታ ድጋፍ መስጠትን፣ በተጓዳኝ የቨርቹወል እና በአካል መማር-ማስተማርን ወይም ክፍል ውስጥ ሙሉ በሙሉ በአካል ተገኝቶ መማርን በጣምራ ያካተተ ነው።

በወላጅ ቅድመ ምርጫ ቅኝት  ውጤት ላይ በመመርኮዝ፣ ተማሪዎች የተለያዩ አስተማሪዎች ሊኖራቸው የሚችልበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፤ በየሳምንቱ በአካል እና ቨርቹወል ትምህርቶችን እያፈራረቁ የመማር ሁኔታ፣ ወይም በአካባቢ ትምህርት ቤት የማይመደቡበት ሁኔታም ሊኖር ይችላል። ውጤቱ በዚህ መልክ ሊሆን የሚችለው ወላጆች በአካል ተገኝቶ ስለመማር በሚያደርጉት ምርጫ እና በቂ ሠራተኞችን ከማግኘት አኳያ ነው። በአካል የማስተማር - መማር ተሞክሮዎች በቀጥታ በአካል ድጋፍ ማድረግን፣ በትምህርቱ ላይ ለማተኮር መሠማራት እና ማስተማርን ያካትታሉ።

የልዩ ትምህርት ምዘና ማዕከላት

ዲሴምበር 3፣ ቤተሰቦች ከሰኞ እስከ ዓርብ በቀጠሮ ድጋፍ ለማግኘት እንዲችሉ በ "Hallie Wells፣ Sligo እና Julius West middle schools" የልዩ ትምህርት ምዘና ማዕከላት ይከፈታሉ። እነዚህ የምዘና ማዕከላት ለስፔሻል ትምህርት ጀማሪዎች እና መቀጠል የሚችሉትን ብቁ መሆናቸውን ለመለየት በሚደረግ የአካል ትምህርት እና ስነልቦናዊ ምዘናዎች ላይ ቤተሰቦች በቀጥታ እንዲሳተፉ እድል ይሰጣል።

ኮቪድ - 19 የሠራተኛ ፖርታል

MCPS ጤንነትና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ፣ ሥልጠናን፣ እንዴት መተግበር እንደሚቻልና/ወይም አኮሞዴሽኖችን ወይም እረፍትን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ከስቴት ሕግ፣ ከፌዴራል ሕግና ከ CDC መመሪያ ጋር የተቆራኘ የመገናኛ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል የሠራተኛ ፖርታል ያስጀምራል።

ቦርዱ በአካል ስለመመለስ ማዕቀፉ ላይ ኖቨምበር 10 ጊዜያዊ እርምጃ እንደሚወስድ የሚጠበቅ ሲሆን፥ በመጪው ዲሰምበር 3 በማጠቃለያ ዕቅድ ላይ ድምጽ ይሰጣል። የትምህርት ቦርድም ከጃኑወሪ 7/2021 ጀምሮ በአካል ወደሚደረጉ ስብሰባዎች ይመለሳል።

ለበርካታ ተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ቨርቹወል መማር በጣም አዳጋች እንደሆነ እና ትምህርት ለመስጠት፣ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እና አገልግሎት ለመስጠት ተማሪዎቻችንን እና ሠራተኞች ወደ ህንጻዎች እንዲመለሱ ማድረግ በጣም ወሳኝነት አለው። ይህን የምናደርገው ያለምንም ስጋት እና ምክንያታዊ በሆነ አኳኋን ነው። ኮቪድ-19 ወደፊት ላልታወቀ ያክል ጊዜ ከእኛ ጋር ስለሚቆይ የተማሪዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት እንዴት ማከናወን እንዳለብን በአንክሮ ማሰብ አለብን። በእነዚህ ውስብስብ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ስንሰራ ለምታደርጉልን ድጋፍና ትብብር እናመሰግናለን። በቀረበው የእቅድ ንድፍ ላይ የሚኖራችሁን ሃሳብ እና ግብረመልስ ከእኛ ጋር ለማጋራት እባክዎ ይህንን በይነመረብ ይጎብኙ፦ www.mcpssubmitfeedback.org

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools