September 21, 2021


የኮቪድ-19 ፈጣን ምርመራ ይጀመራል፤ የኳራንቲን ፖሊሲ ተሻሽሏል

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፡-

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ተማሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ እና ኳራንቲን ሂደት ጠቃሚ ወቅታዊ መረጃ እነሆ!
እነዚህ ለውጦች የተደረጉት በሴፕቴምበር 16 ደብዳቤ ላይ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHHS) ዳይሬክተር ዶ/ር ሬይመንድ ክሮዌል (Dr. Raymond Crowel) እንደተነገረው ፈጣን ምርመራ በመኖሩ የተሻሻለ መመሪያ ስለወጣ ነው።በዚህ ጊዜ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ውስጥ ፈጣን ምርመራዎች በመኖራቸው፣ የታመመ(ች) ተማሪ ለ ኮቪድ-19 ምርመራ ፖዚቲቭ ካልሆነ(ች) ወይም የተጋላጭነት ደረጃ ሁኔታ ካልተረጋገጠ በስተቀር የ ኮቪድ-19 ምልክቶችን ለሚያሳይ ግለብ የቅርብ ንክኪ ቢኖራቸውም ኳራንቲን መቆየት የለባቸውም።

የተማሪዎቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ደህንነት እየጠበቅን በሚቀጥሉበት ጊዜያት እነዚህ ማስተካከያዎች የኳራንቲን ማግለልን እንደሚቀንሱ ተስፋ እናደርጋለን። ቤተሰቦች ወቅታዊ ሂደቶችን እንዲያገናዝቡ የሚያግዙ ጠቃሚ ሪሶርሶች በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋሉ።ስለ ትምህርት ቤት ምርመራ እና የኳራንቲን መረጃ ከዚህ በታች ተጠቃሎ ቀርቧል፦

ፈጣን ምርመራዎች አሁን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ

ትምህርት ቤቶች ሴፕቴምበር 13 ፈጣን ምርመራ (antigen) ወስደዋል፣ እና በትምህርት ቀን አንድ ተማሪ የኮቪድ -19 ምልክቶችን ሲያሳይ ወይም ስታሳይ እነዚህ ጥቅም ላይ ይውላሉ። የትምህርት ቤቱ የጤና ሰራተኞች ምልክቱ ከታየበ(ባ)ት ተማሪ ላይ ትንሽ የአፍንጫ ፈሳሽ ይወስዳሉ፤ እና ውጤቱ ከ 15-20 ደቂቃዎች ውስጥ ይታወቃል።

ፈጣን ምርመራ ለማድረግ ወላጆች/አሳዳጊዎች ፈቃድ መስጠት አለባቸው

 ቤተሰቦች በብዙ ቋንቋዎች ኦንላይን የሚገኘውን የስምምነት ቅጹን መሙላት ወይም ከት/ቤታቸው የወረቀት ቅጂዎችን ጠይቀው መሙላት ይችላሉ። በተማሪ ፋይል ላይ የስምምነት ቅጽ ከሌለ፣ ወላጆች የቃል ፈቃዳቸውን  እንዲሰጡ ይጠየቃሉ፤ እና የትምህርት ቤቱ የጤና ሰራተኞች ስለ ምርመራ ውጤቱ ከተጨማሪ መረጃ ጋር ወደ ቤት ይልካሉ።
ቤተሰቦች ለኮቪድ-19 የማጣሪያ ምርመራዎች የስምምነት ቅጽ አስቀድመው ካስገቡ፣ ተጨማሪ እርምጃ አያስፈልግም። MCPS ለማጣራት ምርመራ ፕሮግራም የተቀበሉትን የፈቃድ ቅጾች እንደ ፈጣን ምርመራ ፈቃድ ይቀበላል። ሁለቱም የዘፈቀደ የማጣሪያ ምርመራ መርሃ ግብር እና ፈጣን ምርመራ በአንድ ቅጽ ተጣምረዋል።

በፈጣን ምርመራ ኔገቲቭ ውጤት ያለው ወይም ያላት ተማሪ-የቅርብ ንክኪ ያላቸው ኳራንቲን አይቆዩም፤ ነገር ግን ይህ ሁኔታ በተከታታይ የ PCR ምርመራ ላይ የተመረኮዘ ይሆናል።
የ ኮቪድ-19 ምልክቶች ያለበ(ባ)ት ተማሪ የምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ ከሆነ ተማሪው(ዋ) የ PCR ምርመራን እንዲከታተል ወይም እንድትከታተል ይመከራል።

  1. የ PCR ምርመራ ውጤቶችን በሚጠብቁበት ጊዜ ንክኪ ወይም ግንኙነት ያላቸውን ማግለል አያስፈልጋቸውም።
  2. PCR ምርመራ ውጤት ኔገቲቭ ከሆነ፣ የቅርብ  ንክኪ ያላቸው ኳራንቲን አያስፈልጋቸውም።
  3. PCR ምርመራ ውጤቱ ፖዚቲቭ ከሆነ፣ ክትባት ያልወሰዱ የቅርብ ንክኪ ያላቸው ኳራንቲን ያስፈልጋቸዋል።

ወላጆች ለልጆቻቸው ፈጣን ምርመራ እንዲደረግ ካልተስማሙ ከልጁ ወይም ከልጅቱ ጋር ያልተከተቡና የቅርብ ንክኪ ያላቸው ምልክት ከታየበ(ባ)ት ልጅ ጋር የተረጋገጠ  የኮቪድ-19 ተጋላጭ ካልሆነ(ች) ወይም የንክኪ ሁኔታ ካልተረጋገጠ በስተቀር ኳራንቲን እንዲቆዩ አያስፈልግም። DHHS እስከዛሬ ባሉት ፈጣን ምርመራዎች መሠረት “ይህ ሁኔታ ብዙ ጊዜ ይከሰታል ብለው እንደማይጠብቁ” አመልክተዋል።

በፈጣን ምርመራ ውጤቱ ፖዚቲቭ የሆነ ምልክት የታየበ(ባ)ት ተማሪ-ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ክትባት ያልወሰዱ  ተማሪዎች ለ 10 ቀናት ኳራንቲን መቆየት አለባቸው

የኮቪድ-19 ምልክቶች ያጋጠመው ወይም ያጋጠማት ተማሪ ፈጣን የምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ ሆኖ ከተገኘ፣ ምልክቱ ካለበ(ባ)ት ተማሪ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው ክትባት ያልወሰዱ ተማሪዎች ለ 10 ቀናት እንዲገለሉ ይገደዳሉ። ከተረጋገጠ የ ኮቪድ-19 ሁኔታ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ኳራንቲን የቆዩ ክትባት ያልወሰዱ ተማሪዎች ሙሉውን የ 10 ቀናት ራስን ማግለል ማጠናቀቅ አለባቸው፤ እና ሙሉውን 10 ቀናት ከማጠናቀቃቸው በፊት ምርመራ ወስደው መመለስ አይችሉም።

የዘፈቀደ የማጣሪያ ምርመራዎች የሚቀጥሉ ሲሆን ከ 6ኛ ክፍል በላይ ይዘልቃሉ

ለግለሰብ ተማሪዎች የኮቪድ-19 የማጣሪያ ምርመራ ከቅድመ ሙአለህፃናት-6ኛ ክፍል የተጀመረ በመሆኑ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ሁሉም ክፍሎች ይስፋፋል። እነዚህ የዘፈቀደ የተማሪዎች ናሙና ሳምንታዊ ምርመራዎች ናቸው፤ እና የወላጅ/አሳዳጊ ፈቃድ ያስፈልጋል። ተመሳሳይ የስምምነት ቅጽ ለናሙና ምርመራ እና ለፈጣን ምርመራዎች ለሁለቱም ጥቅም ላይ ይውላል፣ ስለዚህ ቤተሰቦች ለእያንዳንዱ ልጅ አንድ ቅጽ ብቻ መፈረም አለባቸው።

የ ኮቪድ-19 ምርመራ ትምህርት ቤቶችን ክፍት አድርገን ለመቀጠል እና ጤንነትን ለመጠበቅ ይረዳናል

ምርመራ ትምህርት ቤቶች ክፍት እንዲሆኑ እና ደህንነትን ለመጠበቅ እንዲሁም የ ኮቪድ-19 ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ የሚረዳን አስፈላጊ የመከላከያ ስልት ነው። ይህ ስትራቴጂ ለሠራተኞች አስገዳጅ ክትባቶች፣ ጭምብሎች፣ የእጅ መታጠብ፣ ከቤት ውጭ ቦታዎችን አጠቃቀም ከፍ ማድረግ፣ እና ህመም በሚኖርበት ጊዜ ቤት መቆየት፣ ተማሪዎችን በሳምንት አምስት ቀናት በትምህርት ቤት እንዲማሩ ለማድረግ የተማሪዎችን እና የሠራተኞችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል። ሁሉም ወላጆች/አሳዳጊዎች ለልጃቸው ነፃ የ ኮቪድ-19 ምርመራ የስምምነት ቅጽ እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ። 

የአካባቢያዊ ሁኔታዎች ከተለወጡ የ DHHS የጤና ባለሙያዎች ምክሮቻቸውን ማስተካከል ሊያስፈልጋቸው ስለሚችል MCPS መመሪያቸውን መከተሉን ይቀጥላል። በዚህ ሁኔታ MCPS ፕሮቶኮሎቻችንን ለማሻሻል ዝግጁ እንሆናለን።
Montgomery County Public Schools

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ

 Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools