የእሁድ ቀን የማህበረሰብ መልእክት

ጃኑወሪ 9፣ 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ያለፈው ሳምንት በማህበረሰባችን ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ በጣም ፈታኝ ነበር። የኮቪድ-19 መመሪያ መሻሻል፣ የአውቶቡስ የሰው ሃይል እጥረት እና መጥፎ የአየር ሁኔታ በመማር ማስተማር እና በትምህርት ቤት ስራዎች ላይ መስተጓጎል አስከትሏል። ለነዚህ መስተጓጎሎች የሚዳርጉ ሁኔታዎች ከአቅማችን በላይ ሲሆኑ፣ ስለእነዚህ ተግዳሮቶች ከማህበረሰቡ ጋር በመነጋገር እና ምላሻችንን በማብራራት የተሻለ ስራ መስራት ነበረብን። ይህ ሁኔታ በሰራተኞቻችን፣ በተማሪዎቻችን እና በማህበረሰብ አባላት ላይ ላደረሰው ያልተመቻቸ ሁኔታ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

የተማሪዎቻችን እና የሰራተኞቻችን ጤንነት እና ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ እነሆነ ይቀጥላል። በአካል መማር የተማሪዎቻችንን ትምህርታዊ፣ማህበራዊ እና ስሜታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ምርጡ መንገድ እንደሆነ ስለምናምን የት/ቤቶቻችን ህንፃዎች ክፍት ሆነው እንዲቆዩ ለማድረግ ቅድሚያ እንሰጣለን። ማንኛውንም ትምህርት ቤት ወደ ቨርቹወል ትምህርት መቀየር - ለአጭር ጊዜም ቢሆን - የመጨረሻ አማራጭ ይሆናል፤ እና ውሳኔ የሚደረገው ባለው የተጣራ መረጃ እና በአገር አቀፍ፣ በስቴት እና በአካባቢ የጤና ባለሙያዎች መመሪያ ላይ የተመሰረተ ይሆናል።

የዚህ መልእክት ዋነኛው ዓላም የተማሪዎቻችንን፣ የሰራተኞቻችንን እና የቤተሰቦችን ጤንነት እና ደህንነት ለማረጋገጥ ምን አይነት እርምጃዎችን እንደምንወስድ ይገልፃል። የትምህርት ቤቶችን ወቅታዊ ተግባራት፣ እና ትምህርት ቤቶችን ወደ ቨርቹወልትምህርት ለማሸጋገር የሚታሰብበትን ጊዜና ሁኔታ ለማብራራት ነው። ይኼውም የሚከተሉትን መረጃዎች ያካትታል፦

  • KN-95 ጭንብል እና ፈጣን የምርመራ ኪት ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ማሰራጨት፤
  • ከበሽታ መቆጣጠሪያ ማእከል (CDC) በተሻሻለው መመሪያ ላይ በመመርኮዝ ለሰራተኞች አዲስ ራስን የማግለል እና ኳራንቲን ሂደቶች፣ እና
  • የአውቶቡስ አገልግሎትን እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎችን እንደገና መጀመርን ጨምሮ ስለ ት/ቤቶች አሠራር ወቅታዊ መረጃ፣
  • ስለ ትምህርት ቤቶች አሠራር ለመወያየት መጪው የማህበረሰብ ውይይት፣ እና
  • ትምህርት ቤቶችን ክፍት ስለማድረግ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንድናደርግ እንዴት እንደሚረዱን።

ብዙ ቤተሰቦች በአሁኑ ጊዜ ከወረርሽኙ ተፅእኖ ጋር እየታገሉ እንዳሉ አውቃለሁ፣ እና የራሴን ቤተሰብም ይጨምራል፥ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የወሰድኩት የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ ነበር። ይልቁንም፣ ምልክቶቼ ቀላል ናቸው፣ እና እኔ ራሴን ነጥዬ ከቤት እየሰራሁ ነው። አንድ ላይ፣ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ማለፍ እንደምንችል እርግጠኛ ነኝ። ማህበረሰባችን ጠንካራ በመሆኑ ለተማሪዎቻችን ያለን ቁርጠኝነትም የማይናወጥ ነው። ለ MCPS፣ ለተማሪዎቻችን እና ለትጉህ ሰራተኞቻችን ስለምታደርጉት ድጋፍ እናመሰግናለን።

ከአክብሮት ጋር

Monifa B. McKnight, Ed.D.
Interim Superintendent of Schools
ሞኒፋ ቢ. ማክነይት ዶ/ር
ተጠባባቂ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት

KN-95 ጭምብል ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች
ባለፈው ሳምንት ሁሉም ሰራተኞች KN-95 ጭንብል ተቀብለዋል፣ እና በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ለሁሉም ተማሪዎች KN-95 ጭንብል እናቀርባለን። እነዚህ ጭምብሎች ከሌሎች ጭምብሎች የበለጠ ከፍተኛ የመከላከል ጥንካሬ አላቸው፣ እና ተማሪዎች እና ሰራተኞች በ MCPS ፋሲሊቲዎች ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ጭምብሎችን መጠቀም ስለሚጠበቅባቸው ሳይዘናጉ ዘወትር ጭምብል እንዲያደርጉ አጥብቀን እናበረታታለን።
ፈጣን የምርመራ ኪት ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች
ተማሪዎች እና ሰራተኞች በዚህ ሳምንት ወደ ቤት የሚወስዱት ፈጣን የምርመራ ኪቶች ይቀበላሉ። ተማሪዎች እነዚህን ምርመራዎች እቤት ውስጥ እንዲያደርጉ ወላጆች እንዲረዷቸው እና የልጃቸው ምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ ወይም ኔገቲቭ እንደሆነ የ MCPS COVID-19 ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ በመጠቀም ሪፖርት እንዲያደርጉ አበክረን እንጠይቃለን። (መረጃውን በኤሌክትሮኒክ ማስተላለፍ ካልቻሉ ወደ ልጅዎ ትምህርት ቤት መደወል ይችላሉ።) እባክዎ እስከ መጪው አርብ፣ ጃንዋሪ 14 ድረስ በት/ቤቶች የሚሰራጩትን ፈጣን የምርመራ ኪቶች ሲጠቀሙ ሁሉንም ውጤቶች ማለትም ፖዚቲቭ እና ኔገቲቭ ሁለቱንም ሪፖርት ያድርጉ።. እባክዎ ከትምህርት ቤት ያልተሰጡ የተማሪዎች እና የሰራተኞች ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶችና ምርመራዎችን ሁሉ ማሳወቅዎን ይቀጥሉ። ማንኛውም የምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ የሆነ(ች) ተማሪ ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤት ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ቀናት ወይም ምልክቱ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ ለ10 ቀናት በቅድሚያ የታወቀው የትኛውም ቢሆን ራሱ(ሷ)ን ማግለል ይጠበቅበ(ባ)ታል።

በአሁኑ ጊዜ ቨርቹወል ትምህርት ላይ የሚገኙ አስራ አንድ ትምህርት ቤቶች
ባለፈው ሳምንት ወደ 14 ቀናት ቨርቹወል ትምህርት የተሸጋገሩ 11 ትምህርት ቤቶች አሉ።
ብዙ ቤተሰቦች በሚደርሳቸው መረጃ መሰረት እቅድ ማውጣት ስለሚኖርባቸው፣ እነዚህ 11 ትምህርት ቤቶች በዚህ ሳምንት ቨርቹወል ትምህርት ላይ ይቆያሉ። ከማክሰኞ ጃንዋሪ 18 ጀምሮ በአካል ወደ ት/ቤት ይመለሳሉ። ፈጣን የምርመራ እቃዎች በዚህ ሳምንት በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ይሰራጫሉ፣ ሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ፈጣን ምርመራ ወስደው ውጤቱን እስከ መጪው አርብ ጃኑወሪ 14 ድረስ እንዲያሳውቁ እናበረታታለን።

ወደፊት ወደ ቨርቹወል ትምህርት ሊያሻግሩ የሚችሉ ሁኔታዎች
ወደፊት፥ የትኛውም ትምህርት ቤት በጤና ምክንያት ወይም በሥራ ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገር ካለበት ለመወሰን MCPS ከጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) ጋር በመተባበር ትምህርት ቤቶችን እንደየሁኔታቸው በተናጠል ተግባራዊ ምክንያቶቻቸውን በመገምገም ይሰራል። ከግምት ውስጥ የሚገቡት ነገሮች ፖዚቲቭ መሆናቸው የተረጋገጡ ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን ቁጥር መጨመር፣ በኳራንቲን ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ብዛት፣ ከኮቪድ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የቀሩ ሰራተኞች ብዛት፣ እና በትምህርት ቤት ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ደረጃ ይታያል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአውቶቡስ መጓጓዣ
ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዙ የአውቶቡስ ሹፌሮች የሰው ሃይል እጥረት ተግዳሮቶችን ምላሽ ለመስጠት መስራታችንን ስንቀጥል፣ መስተጓጎልን ለመቀነስ የሚከተሉትን እርምጃዎች እንወስዳለን።

  • የተወሰኑ መስመሮችን እና ተፅእኖ ያረፈባቸውን ትምህርት ቤቶች ወቅታዊ መረጃ በዚህ ገጽ እና MCPS homepage ይመልከቷል። ስለ እያንዳንዱ ቀን ዝርዝር በቀዳሚው ምሽት 7: 00 pm ላይ ይለጠፋል፣ ሆኖም ግን በየቀኑ ጠዋት ተጨማሪ ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ።
  • በልዩ ሁኔታ መስተናገድ ያለባቸውን ተማሪዎች የሚያገለግሉ መስመሮች ቅድሚያ ያገኛሉ።
  • አንድን ትምህርት ቤት የሚያገለግሉ በርካታ የመጓጓዣ መስመሮችን ለመንዳት ያሉትን ሰራተኞች መጠቀም እንቀጥላለን።
  • እንዲሁም መስመሮችን ለመሸፈን ያሉትን የመጓጓዣ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን እና ሱፐርቫይዘሮችን እንጠቀማለን።
በተጨማሪም፣ በትራንስፖርት ዲፓርትመንት ውስጥ ሁለቱንም የአጭር እና የረዥም ጊዜ የሰው ሃይል እጥረትን ለማሟላት ብዙ የምልመላ ስልቶችን እና ሌሎች አማራጮችን እየቃኘን ነው።
ስለ ትዕግስትዎ በጣም እናመሰግናለን። ይህንን ያመልክቱ።

ስለ ኮቪድ-19 ምላሽ ቨርቹወል የማህበረሰብ ውይይት
ከማህበረሰባችን ጋር ቀጣይነት ያለው ውይይት መደረግ እናለበት እናምናለን እናም በዚህ እሮብ ጃንዋሪ 12 ከቀኑ 6፡30 pm እስከ 8፡00 pm ቨርቹዋል የማህበረሰብ ውይይት እናዘጋጃለን።
ተጨማሪ ዝርዝሮች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በወቅታዊ መረጃነት ይቀርባሉ።

የተሻሻለ ራስን ስለማግለል/ኳራንቲን የሰራተኞች መመሪያ

  • የክትባት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በኮቪድ-19 መያዛቸውን የተመረመሩ ወይም በኮቪድ-19 የተጠረጠሩ ሰራተኞች ምልክቱ ከታየበት ቀን ጀምሮ ወይም ምንም ምልክት ሳይኖር የምርመራው ውጤት ፖዚቲቭ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ 5 ቀናት በቤት ውስጥ መቆየት አለባቸው።
  • ከ5ኛው ቀን በኋላ፣ ግለሰቡ(ቧ) ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት ሳይጠቀም/ሳትጠቀም ምንም አይነት ምልክት ከሌለ፣ ግለሰቡ(ቧ) ለተጨማሪ 5 ቀናት ከሌሎች ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ጭንብል መጠቀምን በተመለከተ የ MCPS እና የ MSDE መመሪያዎች ላይ በተገለጸው መሰረት ተስማሚ የሆነ ጭምብል እስካደረጉ ድረስ ወደ ትምህርት ቤት ሊመለሱ ይችላሉ።
  • ግለሰቡ(ቧ) ከሌሎች ጋር በሚሆንበት/በምትሆንበት ጊዜ ጭምብል ማድረግ የማይችል ወይም የማትችል ከሆነ(ች)፣ ቢያንስ ለ 10 ቀናት በቤት ውስጥ መቆየት አለባቸው።

ወደፊት የቫይረሱን ስርጭት ወይም መስፋፋትን በተመለከተ በማህበረሰብ ደረጃ ያለው መረጃ እየቀነሰ ከመጣ ለተማሪዎች የኳራንቲን ቀናት ቁጥር ሊቀንስ ይችላል።

ለሰራተኞች የተሻሻለ ኳራንቲን ሁኔታ መመሪያ
እነዚህ የኳራንቲን መመሪያዎች ተግባራዊ የሚደረጉት በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ እና ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰራተኞች፣ ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆኑ አዋቂዎች Pfizer ክትባት ከ5 ወራት በፊት የወሰዱ ወይም ከ6 ወራት በፊት Moderda ክትባት የወሰዱ እና booster ያልወሰዱ ወይም የመጀመሪያ ደረጃ J&J ተከታታይ ክትባት ከ2 ወር በፊት ለወሰዱ እና booster ያልወሰዱ፤ ወይም ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ ኮቪድ-19 ህመም ላላጋጠማቸው ሠራተኞች ነው።

  • ከመጨረሻው የቅርብ ንክኪ በኋላ እነዚህ ሰራተኞች ቢያንስ ለ 5 ቀናት በቤት ውስጥ መቆየት አለባቸው።
  • ከ5ኛው ቀን በኋላ ግለሰቡ(ቧ) ምንም አይነት የሕመም ምልክት ባይታይበ(ባ)ትም ግለሰቡ (ባ) እንዲመረመር ይበረታታል እና ለተጨማሪ 5 ቀናት ከሌሎች ጋር በሚሆንበት/በምትሆንበት ጊዜ ተስማሚ የሆነ ማስክ/ጭምብል አድርገው ወደ ስራ ሊመለሱ ይችላሉ።
  • ግለሰቡ(ቧ) ከሌሎች ጋር በሚሆንበት/በምትሆንበት ጊዜ ጭምብል ማድረግ የማይችል/የማትችል ከሆነ፣ ቢያንስ ለ10 ሙሉ ቀናት በቤት ውስጥ መቆየት አለባቸው።
  • ግለሰቡ(ቧ) በማንኛውም ጊዜ የሕመም ምልክቶች ከታየበ(ባ)ት፣ እቤት ውስጥ መቆየት፣ መመርመር እና ከላይ ያሉትን ራስን የማግለል መመሪያዎች መከተል አለባቸው።

በኮቪድ-19 መያዙ(ዟ) ከተረጋገጠ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሌሎች ሰራተኞች ሁሉ ራሳቸውን ማግለል አያስፈልጋቸውም። ወደፊት፣ የቫይረሱ ስርጭት ወይም መከሰትን በተመለከተ በማህበረሰብ ደረጃ ያለው መረጃ እየቀነሰ ሲሄድ ለተማሪዎች የለይቶ ማቆያ ቀናት ቁጥር ሊቀንስ ይችላል።

በአካል ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ማክሰኞ ጃንዋሪ 18 ከቆመበት መቀጠል ይችላሉ።
ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ሁሉም በአካል ተገኝተው የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከማክሰኞ ጃንዋሪ 18 ጀምሮ ሊቀጥሉ ይችላሉ። ሁሉም ተሳታፊዎች በት/ቤቱ የሚሰጠውን ፈጣን ምርመራ ጨርሰው ውጤቱን ከአርብ ጃንዋሪ 14 በኋላ እንዲያቀርቡ ይጠበቅባቸዋል። ማንኛውም ተመልካች ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች ላይ እንዲገኝ አይፈቀድም። እነዚህ እንቅስቃሴዎች በየእለቱ የሚገመገሙት በህብረተሰብ ጤና ሳይንስ እና መረጃ ላይ በመመስረት ነው፣ እና ለኦሚክሮን ቫሪያንት (Omicron variant) ከሚሰጠው ምላሽ አንጻር በሚቀጥለው ወር ሊለወጡ ይችላሉ።

እንዴት መርዳት እንደሚችሉ
የተማሪዎቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ እና የተሟላ መረጃ እንዳለን ለማረጋገጥ የእርስዎን እገዛ እንፈልጋለን። እንዴት መርዳት እንደሚችሉ እነሆ!

  1. በሲስተሙ የተሰጡ ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቶችን ሪፖርት ማድረግ
    እባክዎ በዚህ አርብ ጃንዋሪ 14 ከትምህርት ቤቶች የሚሰራጩትን ፈጣን የምርመራ ኪቶች ሲጠቀሙ ሁሉንም ውጤቶች ፖዚቲቭ እና ኔገቲቭ ሁለቱንም ውጤት ያሳውቁ። እባክዎ ከትምህርት ቤት ያልተሰጡ ሁሉንም የተማሪዎች እና የሰራተኞች ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶችና ምርመራዎችን ማሳወቅዎን ይቀጥሉ። መረጃውን ሪፖርት ማድረግ የሚችሉት ይህን ኤሌክትሮኒክስ ቅጽ በመጠቀም ነው።
  2. የሕመም ምልክቶች ካላቸው ልጆችን በቤት ያቆዩ።
    ምርመራ ማድረግ ተማሪዎች ህመማቸውን ወደሌሎች እንዳያስተላልፉ መደረግ ያለበት አስፈላጊ እርምጃ ነው። እባክዎ ሲታመሙ እቤት ያቆዩዋቸው እና ለኮቪድ-19 ተጨማሪ ጥንቃቄ ያድርጉ።
  3. በት/ቤት ምርመራ ለማድረግ ስምምነትዎን ይግለጹ።
    ወላጆች በትምህርት ቤት ለሚሰጥ የኮቪድ ምርመራ ፈቃድ መስጠት አለባቸው እና ይህን ቅጽ በመሙላት ሊያረጋግጡ ይችላሉ። ለተጨማሪ ዝርዝሮች፣ እባክዎ የእኛን "Say Yes to the Test" ድረ ገጽ ይጎብኙ

ማህበራዊ-ስሜታዊ ጤንነት እና ደህንነት
ይህ ወቅት በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ላሉ በርካታ ሰዎች አስቸጋሪ ጊዜ ነው። ወረርሽኙ ለብዙዎች የጭንቀት ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል፣ እና በወረርሽኝ ማእበል ተከበን በምናልፍበት ወቅት MCPS ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና ቤተሰቦችን ለመደገፍ ሪሶርሶችን ለማቅረብ ቁርጠኛ ነው። ትምህርት ቤቶች ካውንስለሮች እና ሳይኮሎጂስቶች ይኖራሉ፣ ስለዚህ ሁሉም ሰራተኞች ድጋፍ እና ሪሶርሶችን ለማግኘት የሰራተኛ እርዳታ ፕሮግራምን እንዲያነጋግሩ ይበረታታሉ።

ጠቃሚ መረጃዎች

 

 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools