ሐሙስ፥ ማወቅ ያለብዎት መልእክት / ጥር 27

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 27፣ 2022 ማወቅ ያለብዎት አስር ነገሮችን እነሆ። በማግሬደር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተፈፀመውን የሽጉጥ ጥቃት ተከትሎ ስለሚወሰዱት ቀጣይ እርምጃዎች፣ ስለ KN-95 ጭምብሎች መረጃ፣ ለ10 ቀን ወደ ቨርቹወል ትምህርት የሚሸጋገሩ ትምህርት ቤቶች ዝርዝር፣ በትምህርት ቤት ውስጥ PCR ምርመራ መስፋፋት፣ ስለ 2022-2023 የትምህርት ካለንደር እና ሌሎችንም ያካትታሉ።

  1. ሠላም እና ደህንነት ቀዳሚ ተግባራችን እንደሆነ ይቀጥላል።

አርብ ጃንዋሪ 21፣ በማግሬደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተኩስ ጥቃት ክስተት እንደነበረ ይታወቃል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሸሪፍ ጽ/ቤት እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእሳት አደጋ መከላከል ጽ/ቤት፣ ፈጣን ምላሽ በመስጠት የማህበረሰባችንን ደህንነት ለመጠበቅ ላደረጉት ቁርጠኝነት እና ድጋፍ እናመሰግናለን።

በሚቀጥሉት ወራት፣ የ MCPS አመራር ከትምህርት ቤት ሰራተኞች፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ የካውንቲ ባለስልጣኖች፣ የማህበረሰብ አጋሮች እና ሌሎችም ጋር በመተባበር

  1. ሁሉንም የትምህርት ቤት ደህንነት እና ሠላም የማስጠበቅ ተሞክሮዎችን አጠቃላይ ግምገማ እናካሄዳለን፣
  2. በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የፖሊስ መገኘትን በተመለከተ በቀጣይነት የነበሩትን ስጋቶች እንፈታለን፣
  3. ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ማህበራዊ-ስሜታዊ ድጋፍ ይሰጣል፣
  4. በትምህርት ቤት የደህንነት ሰራተኞችን እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ አሰጣጥ ሂደቶች እና ስልጠናዎች ይገመገማሉ፣
  5. ለሰራተኞች የተሻሻለ የደህንነት ስልጠና ተግባራዊ ይደረጋል፣ እና
  6. ስለ ቀጣይ ጥረታችን በግልፅ እንወያያለን።

 

በማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተከሰተውን ክስተት ተከትሎ ጊዜአቸውን፣ ተሰጥኦአቸውን እና ወሳኝ ድጋፎችን ላደረጉ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ የማህበረሰብ አባላት እና ብዙ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት MCPS ለማህበረሰቡ ስላደረጉት ሰፊ ድጋፍ እናመሰግናለን።

  1. አራት የ MCPS ትምህርት ቤቶች ከጃንዋሪ 29 ጀምሮ ወደ ቨርቹወል ትምህርት ይሸጋገራሉ።

በርካታ ቁልፍ ነገሮች እና ከብዙ ባለድርሻ አካላት ቡድን የተሰጡ አስተያየቶች ከተገመገሙ በኋላ አራት ትምህርት ቤቶች እና እንዲሁም በዌስትኦቨር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኦቲዝም ፕሮግራም ለ 10 ቀናት ወደቨርቹወል ትምህርት እንዲሸጋገሩ ተደርጓል። ጠቅላላ የትምህርት ቤት ማህበረሰብን ጤንነት እና ደህንነት ለመጠበቅ፣ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ከጃንዋሪ 31 እስከ ፌብሩዋሪ 9 ባለው ጊዜ ውስጥ በቨርቹወል ትምህርት ይሳተፋሉ። እሮብ ፌብሩዋሪ 10 በአካል ወደ ት/ቤት ይመለሳሉ።

የትምህርት ቤቶቹ ዝርዝር፦

Harmony Hills ES
ሀርሞኒ ሒልስ ኤለመንተሪ ት/ቤት
Loiederman MS
ሎይንደርማን መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

Pine Crest ES
ፓይን ክረስት ኤለመንተሪ ት/ቤት
Wheaton Woods ES
ዊተን ውድስ ኤለመንተሪ ት/ቤት

  1. በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች በሚዘጉባቸው ቀናት MCPS ቨርቹወል ትምህርት ለመስጠት እያቀደ ነው።

 በተቻለ መጠን ተማሪዎች የመማር መስተጓጎል የሚያጋጥማቸው እንዲቀንስ ማድረግ አስፈላጊ ነው፣ ስለዚህ የመጀመሪያ እቅዳችንን ለመሥራት የእርስዎን አስተያየት እንጠይቃለን። እባክዎ ይህን የዳሰሳ ጥናት በመሙላት የእርስዎን ሃሳብ ያካፍሉን። በዚህ ጉዳይ ላይ በሚቀጥሉት ቀናት የበለጠ መረጃ ይኖረናል።

English /  español  /  中文  /  français /  Português /  한국어 /  tiếng Việt /  አማርኛ

  1. ለሁሉም ሰራተኞች እና ለተማሪዎች KN95 ጭንብል መስጠት ይቀጥላል።

ለትናንሽ ልጆች የሚሆኑ KN95 ጭምብሎች በዚህ ሳምንት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መድረስ ጀምረዋል። MCPS እነዚህን ጭምብሎች ለቀሪው የትምህርት አመት ገዝቶ ማሰራጨቱን ይቀጥላል። ተማሪዎች እና ሰራተኞች ጭንብል በሚያስፈልግበት የ MCPS መገልገያዎች ውስጥ ጭምብላቸውን እንዲለብሱ አጥብቀን እናበረታታለን።

ለፊት መሸፈኛ በ MCPS የሚከፋፈሉ KN95 ማስኮች መስፈርቶችን የሚያሟሉ ስለሆነ ለዚህ አገልግሎት ተቀባይነት አላቸው። በ MCPS እየተከፋፈሉ ያሉት ጭምብሎች በጥሩ ሁኔታ የተሠሩ ከመሆናቸውም በላይ በርካታ ንብርብሮች አሏቸው፣ ለጥሩ ምቾት የተነደፉ ስለሆነ የደህንነት/የጤና አደጋዎችን አያስከትሉም።

  1. በት/ቤቶች PCR ምርመራ ይበልጥ ይስፋፋል

ኮቪድ-19 ን ለመዋጋት አንዱ ወሳኝ የመከላከያ ዘዴ በትምህርት ቤት ውስጥ የዘፈቀደ PCR ምርመራ ማድረግ ነው። MCPS ተጨማሪ ምርመራ የሚያደርጉትን መጠቀም ጀምሯል። ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ፣ 20/20 Gene Systems ቢያንስ በስድስት ትምህርት ቤቶቻችን ምርመራ ይጀምራል፣ ወደፊት ተጨማሪ የማስፋፊያ እቅድም ይዘናል። ይህ ሌላ የተለየ ምርመራ አድራጊ ስለሆነ፣ ወላጆች መጀመሪያ ለ CIAN ምርመራ አድራጊ ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ ለዚህኛው በተለይ ፈቃድ መስጠት አለባቸው። ይህን አዲስ አቅራቢ የሚጠቀሙ ትምህርት ቤቶች እንዴት ለምርመራ መስማማት እንዳለብዎት መረጃ ይሰጣሉ።

እባክዎ ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ከትምህርት ቤት ያልተሰጡ ምርመራዎችን በሚመለከት ሁሉንም ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶች ሪፖርት ማድረግዎን ይቀጥሉማንኛውም የምርመራ ውጤት ፖዚቲቭ የሆነ(ች) ተማሪ ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤት ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ቀናት ወይም ምልክቱ ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ (በቅድሚያ የታወቀው የትኛውም ቢሆን) ለ 10 ቀናት ራሱ(ሷ)ን ማግለል ይጠበቅበ(ባ)ታል።

  1. ኳራንቲን ላይ ሳይሆኑ ነገር ግን በኮቪድ-19 ምክንያት ስጋት ኖሯቸው ወደ ትምህርት ቤት መምጣት ለማይችሉ ተማሪዎች እንደየሁኔታው የትምህርት አቅርቦቱን እናሰፋለን።

በዚህ አማራጭ ላይ ፍላጎት ያላቸው ቤተሰቦች የልጃቸውን ትምህርት ቤት ማነጋገር አለባቸው እና ከት/ቤት የቀሩበት ጊዜ በምክንያት እንደሆነ ይቆጠራል። ይህኛው አማራጭ እስከ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 11 ድረስ ተራዝሟል።

  1. ተመልካቾች በ MCPS ፋሲሊቲዎች ውስጥ ለሚካሄዱ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች ከሚይዙት አቅም እስከ 25 በመቶ ይቀበላሉ።

ከቅዳሜ ጃንዋሪ 29፣ 2022 ጀምሮ ተመልካቾች በ 25 በመቶ አቅም ለአትሌቲክስ ዝግጅቶች እና ሌሎች ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ወደ MCPS ተቋማት መግባት/መምጣት ይችላሉ። ተመልካቾች በሙሉ ሁል ጊዜ ጭምብል ማድረጉን መቀጠል አለባቸው።

  1. የሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለ 2022-2023 የትምህርት ዓመት የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያዎችን አጽድቋል።

በተለመደው የትምህርት አመት አቆጣጠር፣ ትምህርት የመጀመሪያው ቀን ሰኞ ኦገስት 29፣ 2022 ይሆናል፣ እና የትምህርት መጨረሻው ቀን አርብ ጁን 16፣ 2023 ይሆናል። የተለመደው የትምህርት ዓመት አቆጣጠር 182 የትምህርት ቀናት አሉት።
2022–2023 የተለመደው የትምህርት ዓመት አቆጣጠር/ካላንደር

አርኮላ እና ሮስኮ አር. ኒክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች (Arcola and Roscoe R. Nix elementary schools) ለሚከተሏቸው የፈጠራ ትምህርት ቤቶች ካላንደር (innovative schools calendar)፣ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ረቡዕ ጁላይ 6፣ 2022 ይሆናል፣ እና ትምህርት የሚጨርሱበት ቀን አርብ ጁን 16፣ 2023 ይሆናል። የኢኖቬቲቭ ትምህርት ቤት ካለንደር 210 የትምህርት ቀናት አሉጥ
2022–2023 የምርምርና ፈጠራ የትምህርት ዓመት ካለንደር = Innovative School Year Calendar

  1. የትምህርት ቦርድ እስከ ፌብሩዋሪ 7 ድረስ በተማሪ ዲሲፕሊን ፖሊሲ ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎችን በተመለከተ አስተያየቶችን ይቀበላል።

ይህ ማሻሻያ የተደረገው የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ JGA፣ የተማሪ ዲስፕሊን/ስነምግባር፣ የስነምግባር ጣልቃገብነት ፍልስፍናን የሚያድስ፣ ትምህርታዊ፣ ፍትሃዊ፣ እና በፍትሃዊነት የሚተገበር እና ግልጽ፣ ተገቢ እና በ MCPS ውስጥ ያለውን የተማሪ የስነምግባር ህግጋት የሚጥስ የተማሪዎች ባህሪን ችግር ለመፍታት የታለመ ነው።
የበለጠ ግንዛቤ ይውሰዱ እና ግብረመልስ ይስጡ

  1. በዚህ ሳምንት እስካሁን ሁሉም የአውቶቡስ መስመሮች በተሟላ ሁኔታ መሥራት ችለዋል።

በዚህ ሳምንት የ MCPS ትራንስፖርት ዲፓርትመንት የአውቶቡስ መስመሮች ምንም የተጓደለ ሰራተኛ አልነበረም። በ MCPS የትራንስፖርት መምሪያ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች የአውቶቡስ ሹፌሮችን መመልመል፣ መቅጠር እና ማሰልጠን እንደቀጠሉ ናቸው። በአጠቃላይ በዲስትሪክቱ ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት ሰራተኞች ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች እየቀነሱ ናቸው።

 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools 

 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools