banner

ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 24 መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

ፌብሩዋሪ 24, 2022

የተወደዳችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰቦች
በትምህርት ካላንደር ላይ የአሁኑን/ከዚህ ቀጥሎ ስላለው የትምህርት ዓመት ላሳውቃችሁ እፈልጋለሁ። ጃኑወሪ 3፣ 4፣ 7 እና 20 የነበረው የቅርብ ጊዜ መጥፎ የአየር ሁኔታ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በአጠቃላይ ለአራት ቀናት ትምህርት ቤቶችን እንዲዘጉ አስገድዷቸዋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የ 2021–2022 ትምህርት ቤት ካለደር ኖቬምበር 2021 ከምስጋና ቀን "Thanksgiving" በፊት ያለውን እሮብ ስርዓት-አቀፍ በዓል እንዲሆን ተሻሽሏል። ይህም MCPS ጃንዋሪ ላይ ከታቀደው በሜሪላንድ ስቴት ከሚፈለገው ዝቅተኛው 181 የትምህርት ቀናት በአንድ ቀን ብልጫ ትምህርት እንዲሰጥ ያደርጋል። ስለዚህ ከአራቱ ት/ቤቶች ከሚዘጉባቸው ቀኖች አንዱን ማካካስ ስለማያስፈልግ በእኛ የትምህርት ቀን መቁጠሪያ መጨመር ያለበት ሶስት የትምህርት ቀን ይሆናል።
ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ MCPS የ 2021–2022 የማካካሻ ቀናትን ለማሳወቅ ይፈልጋል። በስቴት የሚፈለጉትን የትምህርት ቀናት ማሟላታችንን ለማረጋገጥ MCPS የሚከተሉትን በእቅድ የተያዙ የማስተካከያ ቀናት ይጠቀማል።

  • አርብ፣ ኤፕሪል 1፣ 2022፣ ለመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለመምህራን የሙያ ቀን ሆኖ ለደረጃ አሰጣጥ እና ሪፖርት ለማዘጋጀት የተያዘ ሲሆን፣ ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን ይሆናል።
  • በተጨማሪም የ 2021–2022 የትምህርት አመት የሚከተሉትን ለማካተት ቢያንስ በሁለት ተጨማሪ ቀናት ይራዘማል።
    • ሐሙስ፥ ጁን 16፣ 2022
    • ዓርብ፣ ጁን 17/2022*

*አርብ ጁን 17፣ 2022 የትምህርት ቀን ሲሆን የመጨረሻው የትምህርት ቤት ቀን ይሆናል፤ ይህም ተማሪዎች ከመደበኛው ሠዓት በቅድሚያ የሚለቀቁበት ቀን ይሆናል ማለት ነው።   210 ቀናት የትምህርት ካሌንደር ያላቸው የኢኖቬቲቭ ትምህርት ቤቶች፣ ኤፕሪል 1, 2022 ከሁሉም ትምህርት ቤቶች ጋር የማካካሻ ቀን የሚኖራቸው ሲሆን በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት ሰኞ ሰኔ 13፣ 2022 የትምህርት አመቱ ያበቃል።
ረቡዕ፣ ጁን 15፣ 2022 ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀን ተብሎ የታቀደው አሁን ሙሉ የትምህርት ቀን ይሆናል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት የት/ቤት ህንጻዎች በሚዘጉባቸው ቀናት የተሣለጠ ቨርቹወል ትምህርት ለመስጠት እንዲያመች ተዘጋጅቶ የቀረበውን እቅድ የትምህርት ቦርድ ፌብሩዋሪ 1, 2022 አፅድቋል። በተለምዶ የበረዶ ቀናት ዋጋ ያላቸው እና አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ናቸው። መጥፎ የአየር ሁኔታ በሚያጋጥመን ጊዜ፣ ከዚህ እቅድ ውጪ በተጨማሪ የት/ቤቶች መዘጋት የሚያስፈልግ ከሆነ፣ MCPS ከስቴቱ ቢያንስ የ 180 የትምህርት ቀናት ውስጥ እንዲቀነስ ሊጠይቅ ይችላል። መደበኛ ቀናት እንዲቀነሱ ከመጠየቃቸው አስቀድሞ ብቁ ለመሆን፣ የት/ቤት ስርአቶች የተመደቡትን የማካካሻ ቀናት ተጠቅመው የተስተጓጎሉትን ጊዜያት ለማካካስ ግልፅ የሆነ ጥረት ማሳየት አለባቸው።

ተልእኳችን የተማሪዎች መማር ቢሆንም፣ ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር የተማሪዎቻችን እና የሰራተኞቻችን ደህንነት እንዲጠበቅ ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከባድ የአየር ሁኔታን በቅርበት መከታተል እና በትምህርት ካላነደር ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ማንኛውንም ተጽእኖ ማሻሻያ ማድረጉን ይቀጥላል። ስለ MCPS ትምህርት ቤት ካለንደር የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን ድረገጻችንን ይመልከቱ፦ http://www.montgomeryschoolsmd.org

ከአክብሮት ጋር
Monifa B. McKnight, Ed.D.
Interim Superintendent of Schools
ሞኒፋ ቢ ማክነይት (ዶ/ር)
ተጠባባቂ የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools