ሐሙስ፣ ማርች 10 መታወቅ ያለባቸው መልእክቶች

ሐሙስ፣ የማርች 10 አምስት ጉዳዮች እነሆ! ከአሁን ወዲያ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች እና መገልገያዎች ጭምብሎችን መጠቀም በፍላጎት አማራጭ መሆኑን ማሳሰቢያ፣ የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ዳሰሳን ስለማጠናቀቅ ማሳሰቢያ፣ የኮቪድ-19 የቤት መመርመሪያ መሣሪያ አጠቃቀም መረጃ፣ የኮቪድ-19 ክትባቶች እና ምርመራዎች አሁንም አስፈላጊ ስለመሆኑ እና ስለ ቅድመ መዋእለ ህፃናት (Prekindergarten) እና ሄድ ስታርት (Head Start) ምዝገባ መረጃዎችን ያጠቃልላል።

  1. በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች እና መገልገያዎች ውስጥ ማስክ ከአሁን ወዲያ በፍላጎት የሚደረግ አማራጭ ነው።

የትምህርት ቦርድ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ ጭምብል/ማስክ መጠቀምን አማራጭ እንዲሆን ማርች 8 ውሳኔ ሰጥቷል። ይህ ለውጥ ወዲያውኑ ተግባራዊ ይሆናል።  አሁን ተማሪዎች እና ሰራተኞች ጭምብል ለመጠቀም ወይም ላለማድረግ እንደግል ምርጫቸው ማድረግ ይችላሉ። "ጭምብል ባደርግም ባላደርግም እኔ ብቻ ነኝ"። ደግ ይሁኑ! የእኔን ማስክ መጠቀም ወይም ያለመጠቀም ምርጫን ያክብሩ! ለእያንዳንዱ ግለሰብ ጭምብል የመጠቀም/አለመጠቀም ምርጫ በጎ አስተሳሰብን፣ አክብሮትን እና መገንዘብን ለማጠናከር የምንጠቀምበት መልእክት ነው።
ከሪቺ ፓርክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Ritchie Park Elementary School) ርእሰ መምህር የተላለፈው ቪዲዮ ይህንን መልእክት አጋርቷል።

  1. የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ዳሰሳን እስከ ማርች 31 ድረስ ያጠናቅቁ

ቤተሰቦች፦ ትምህርት ቤቶቻችን እና የትምህርት ዲስትሪክቱ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ የዘር እና የስርአት አቀፍ ችግርን ለመፍታት በቀጣይነት እንዴት እንደምንሰራ በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት የእናንተን እገዛ እንፈልጋለን። ይህን የዳሰሳ ጥናት ከማርች 31 በፊት እንዲሞሉ እናበረታታዎታለን። ሞባይል ወይም ኮምፒውተር መጠቀም ይችላሉ። ስለ MCPS ፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ከዚህ የበለጠ ይወቁ። ጥናቱ የማንም ስም የማይገለፅበት ከመሆኑም በላይ በሰባት ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
በሚከተሉት ቋንቋዎች የተዘጋጀ የቤተሰብ ደብዳቤ
Englishespañol  /  中文  /  français /  Português한국어tiếng Việt አማርኛ

  1. የኮቪድ-19 ፈጣን የቤት ውስጥ መመርመሪያ ኪት እየተሰራጨ ነው።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክስ ስኩልስ (MCPS) ፈጣን የኮቪድ-19 መመርመሪያ ኪቶችን እስከ ማርች ድረስ ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች በየሶስት ሳምንቱ ማሰራጨቱን ይቀጥላል። የሚቀጥለው ማርች 21 በሚውልበት ሳምንት ለማሠራጨት ታቅዷል። እነዚህ ኪቶች የኮቪድ-19 ተፅእኖን ለመቀነስ እየተካሄደ ባለው ጥረት ወሳኝ አካል ናቸው።
ምርመራውን በትክክል ለመጠቀም እንዲረዳዎት እና መቼ እንደሚጠቀሙባቸው ለማወቅ የሚከተሉትን መገልገያዎች ይጠቀሙ።
ቪዲዮ፡ የኮቪድ-19 ፈጣን መመርመሪያ መሣሪያ አጠቃቀም መመሪያ
በዚህ ድረገጽ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ፤ በራሪ ወረቀቶች ላይ ያለውን መመሪያ ያንብቡ።
Englishespañol  /  中文  /  françaisPortuguês한국어tiếng Việtአማርኛ 
(ማሳሰቢያ፦ እነዚህ ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ የሚከናወኑ ፈጣን መመርመሪያዎች ናቸው፡ እባክዎ ከመጠቀምዎ በፊት በመሳሪያዎቹ እሽግ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ያንብቡ)

  1. የኮቪድ-19 ምርመራ እና ክትባቶችን መውሰድ ጠቃሚነታቸው ይቀጥላል።

ምርመራ፡ በትምህርት ቤት የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጠቃሚ ዘዴ ነው። MCPS በት/ቤት ውስጥ በዘፈቀደ እና ምልክቶች ለሚታይባቸው ተማሪዎች ፈጣን የኮቪድ ምርመራ ያደርጋል። ወላጆች ለዚህ ምርመራ ይህን ቅጽ በመሙላት ፈቃድ መስጠት አለባቸው። ስለ ት/ቤት የኮቪድ-19 ምርመራ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ
ክትባቶች፡ 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው ግለሰቦች የኮቪድ-19 ክትባት ለመውሰድ ብቁ ናቸው። ነፃ፣ደህንነቱ የተጠበቀ፣ እና የተዘጋጀ ነው። ክትባቱ እራስህ(ሽ)ን ለመጠበቅ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማህበረሰብህ ውስጥ እንዳይስፋፋ ለማድረግ ልትወስዷቸው ከምትችሏቸው በጣም አስፈላጊ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ነው። እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ.

  1. የቅድመ መዋለ ህፃናት/ሄድ ስታርት ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።

ለ 2022-2023 የትምህርት ዓመት የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድ ስታርት ምዝገባ አሁን ክፍት ነው። ልጆች በሴፕቴምበር 1, 2022 ወይም ከዚያ በፊት 4 አመት እድሜ የሚሞሉ መሆን አለባቸው፣ እንዲሁም ቤተሰቦች ለማመልከት በገቢ አቅም ረገድ ብቁ መሆን አለባቸው። ቤተሰቦች ልጆቻቸውን በኦንላይን ማስመዝገብ ይችላሉ። በተጨማሪም፣ በአካል ማስመዝገብ ለሚፈልጉ ቤተሰቦች እስከ ማርች 31 ድረስ በስራ ቀናት፣ ቅዳሜ እና እሁድ የምዝገባ ቦታዎች ክፍት ናቸው። ስለ ብቁነት መመሪያ፣ አስፈላጊ ሰነዶች እና እንዴት እንደሚመዘገቡ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ 240-740-4530 ይደውሉ ወይም  MCPS ድረገጽ ይጎብኙ



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools