ሐሙስ፣ ማርች 17 ማወቅ ያሉብን ነገሮች

 

ሐሙስ፣ማርች 17 መታወቅ ያለባቸው ሰባት ነገሮችን እነሆ! ስለ ኮቪድ-19 ማሳሰቢያ፣ ስለ አይምሮ ጤንነት እና የቀውስ ምንጮች መረጃ፣ የፀረ ዘረኝነት ኦዲት ጥናትን ስለማጠናቀቅ ማሳሰቢያ፣ ስለ ቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና የሄድ ስታርት ምዝገባ፣ ስለመጪው RespectFest ዝግጅት መረጃ እና ከትምህርት ቤት ውጭ ስለሚከናወኑ ተግባራት መረጃዎችን ያካትታሉ።

 1. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስላላበቃ በጥንቃቄ ይጠበቁ።
  የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC) በሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ አንጻር ኮቪድ-19  ያለበት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን አረጋግጧል። ይህም የሆነው በትምህርት ቤቶች እና በካውንቲው ውስጥ በተደረጉት ከፍተኛ የክትባት፣ የምርመራ እና ሌሎች የመከላከል ጥረቶች ምክንያት ነው። የኮቪድ-19 Omicron ወረርሽኝ ከገባ በኋላ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየቀነሰ ሄዷል። ይህም ሆኖ ወረርሽኙ ስላላለቀ ነቅተን ራሳችንን ከበሽታው መጠበቅና መጠንቀቅ አለብን።

የኮቪድ-19 ምርመራ እና ክትባቶችን መውሰድ ጠቃሚነታቸው ይቀጥላል።

  1. ክትባቶችእድሜአቸው 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ግለሰቦች የኮቪድ-19 ክትባት ለመውሰድ ብቁ ናቸው። ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በነፃ የሚሰጥ ነው። ክትባቱ እራስን ለመጠበቅ እና ኮቪድ-19 በማህበረሰብ ውስጥ እንዳይስፋፋ ለማድረግ ሊወስዷቸው ከሚችሏቸው በጣም አስፈላጊ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
  2. በት/ቤቶች ውስጥ ምርመራ MCPS በት/ቤት ውስጥ ምልክት ለሌላቸው ተማሪዎች እና የበሽታው ምልክት ለሚታይባቸው ተማሪዎች ፈጣን ምርመራ ያደረጋል። ወላጆች ለዚህ ምርመራ ፈቃድ መስጠት አለባቸው ይህን ቅጽ በመሙላት ስለ ት/ቤት የኮቪድ-19 ምርመራ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ
  3. በቤት ውስጥ ምርመራ ስለማድረግMCPS ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ መሳሪያዎችን በየሶስት ሳምንቱ እስከ ማርች ድረስ ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ማሰራጨቱን ይቀጥላል። የሚቀጥለው ማርች 21 በሚውልበት ሳምንት ለማሠራጨት ታቅዷል። ምርመራውን በትክክል ለማድረግ እና መቼ እንደሚጠቀሙበት ለማወቅ እንዲረዳዎ የሚከተሉትን ምንጮች ያገናዝቡ።

VIDEO: Directions for use of COVID-19 rapid test kit
Learn more at this website and review the flyers:
Englishespañol  /  中文  /  françaisPortuguês한국어tiếng Việtአማርኛ 
(ማሳሰቢያ፦ እነዚህ ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ የሚከናወኑ ፈጣን መመርመሪያዎች ናቸው፡ እባክዎ ከመጠቀምዎ በፊት በመሳሪያዎቹ እሽግ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ያንብቡ)

 1. ጭንብል፡ ቢሆንም ባይሆንም የምጠቀምበት እኔ ነኝ
  ከማርች 8 ጀምሮ በ MCPS ትምህርት ቤቶች እና መገልገያዎች ማስክ መጠቀም አማራጭ ፍላጎት ነው። አንዳንዶች አዲሱን የጭንብል አተቃቀም ፖሊሲ ሲቀበሉ ሌሎች ደግሞ ይሄ ለውጥ በመደረጉ ምክንያት ሊያስጨንቃቸው እንደሚችል መረዳት ቀላል ነው። ማስክ ባደርግም ባላደርግም፣ እኔ ብቻ ነኝ ጭንብል መጠቀም የግለሰብ ምርጫ እንደሆነ እና አንዳችን የሌላውን ምርጫ ማክበር እንዳለብን ማሳሰብ እንወዳለን።
  MCPS ይህን መልእክት በፖስተሮች፣ በራሪ ወረቀቶች እና ሌሎች ጠቃሚ የመረጃ ስርጭቶችን በመጠቀም እያስረዳን የግለሰቦችን ምርጫቸውን መቀበል እንዳለብን እናበረታታለን።
  1. አስገራሚው ነገር፡ ተማሪዎች ጭምብል ባለመጠቀማቸው ስጋት ሊኖርባቸው ይችላል
  2. ከፊት ጭንብል ስለማውለቅ በጉልበተኝነት የሚያሾፉትን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል
  3. ጉልበተኝነት እና ትንኮሳ ሪፖርት የሚደረግበት የ MCPS ቅፅ
  4. ስለ ጉልበተኝነት እና ትንኮሳ የ MCPS መረጃ
 1. የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ዳሰሳን እስከ ማርች 31 ድረስ ያጠናቅቁ
  እናበረታታለን ዳሰሳውን እንዲሞሉ, ክፍት ስለሆነ እስከ ማርች 31። ሞባይል ስልክ ወይም ኮምፒውተር መጠቀም ይችላሉ። ስለ MCPS ፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ከዚህ የበለጠ ይወቁ። ጥናቱ የማንም ስም የማይገለፅበት ከመሆኑም በላይ በሰባት ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

በሚከተሉት ቋንቋዎች የተዘጋጀ የቤተሰብ ደብዳቤ
Englishespañol  /  中文  /  français /  Português한국어tiếng Việt አማርኛ

 1. የቅድመ መዋለ ህፃናት/ሄድ ስታርት ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።

ለ 2022-2023 የትምህርት ዓመት የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድ ስታርት ምዝገባ አሁን ክፍት ነው። ልጆች በሴፕቴምበር 1, 2022 ወይም ከዚያ በፊት 4 አመት እድሜ የሚሞሉ መሆን አለባቸው፣ እንዲሁም ቤተሰቦች ለማመልከት በገቢ አቅም ረገድ ብቁ መሆን አለባቸው። ቤተሰቦች ልጆቻቸውን በኦንላይን ማስመዝገብ ይችላሉ። በተጨማሪም፣ በአካል ማስመዝገብ ለሚፈልጉ ቤተሰቦች እስከ ማርች 31 ድረስ በስራ ቀናት፣ ቅዳሜ እና እሁድ የምዝገባ ቦታዎች ክፍት ናቸው። ስለ ብቁነት መመሪያ፣ አስፈላጊ ሰነዶች እና እንዴት እንደሚመዘገቡ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ 240-740-4530 ይደውሉ ወይም MCPS ድረገጽ ይጎብኙ

 1. RespectFest በታዳጊ ወጣቶች የፍቅር ጓደኝነት ላይ የሚፈጠር ጥቃትን ስለመከላከል መወያየት

Respect Montgomery's አመታዊ ዝግጅት ሲሆን፥ RespectFest ከማርች 21-27 የአንድ ሳምንት የኦንላይን እንቅስቃሴዎችን ያካሂዳል፣ ይህም እሑድ ማርች 27 ከ1-4 p.m. በዊተን Wheaton ማህበረሰብ መዝናኛ ማእከል በአካል የሚደረግ ዝግጅት ነው። ተማሪዎች እና ወላጆች ስለ ፍቅር ጓደኝነት ጥላቻ፣ ጥቃት፣ እና መከላከል ይማራሉ። ተማሪዎች የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ

 1. ስለ አእምሮ ጤንነት እና ቀውስ የድጋፍ መርጃዎች/ሪሶርሶች በኦንላይን ይሰጣሉ

የአእምሮ ጤነት እና የቀውስ ድጋፍ መርጃዎችን ለሚፈልጉ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች MCPS የቀጥታ ኦንላይን መረጃዎች አሉት። እያንዳንዱ ትምህርት ቤት ካውንስለር፣ የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስት፣ የተማሪ ሰራተኛ እና የትምህርት ቤት ነርስን ያካተተ የተማሪ ድጋፍ ቡድን አለው።
መገልገያዎች/ሪሶርሶች:

  1. የአእምሮ ጤንነት መርጃዎች/ሪሶርሶች ወይም የቀውስ ድጋፍ
  2. Student Psychological Services (Guide to School Psychologists Español | Français | 中文 | tiếng Việt | 한국어 | አማርኛ)
  3. የሰራተኞች ድጋፍ ፕሮግራም
 1. በክፍል ውስጥ ትምህርት በማይኖርበት ጊዜ ማድረግ ያለብዎትን ነገሮች እየፈለጉ ነው?

ትምህርት በማይሰጥባቸው ቀናት MCPS በአካል፣ ቀጥታ እና በጥያቄ ለኤለመንተሪ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የሚኖራቸውን እድሎች ዝርዝር አዘጋጅቷል። ከእነዚህ ተግባራት መካከል አንዳንዶቹ ከ MCPS ጋር ግንኙነት የላቸውም። በቀረቡት ፕሮግራሞች ላይ ፍላጎት ካሎት፣ እባክዎን እነዚህን ድርጅቶች በቀጥታ ያግኙ።
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools