ውድ የ MCPS ወላጆች፣ አሳዳጊዎች እና የማህበረሰብ አባላት፡-

እርስዎ እና አብረው ያሉ ልጆችዎ ጥሩ የስፕሪንግ ዕረፍት እንዳሳለፉችሁ፣ትንሽ ማረፍ እንደቻላችሁ እና እርስበርሳችሁ ነፃ ጊዜ እንዳሳለፉችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ብዙዎቻችን የስፕሪንግ ዕረፍት በጣም በፍጥነት እንዳለቀ የሚሰማን ቢሆንም፣ ሌሎች ደግሞ ወደ ተለመደው የትምህርት ቀናት እና ቀኖቻችንን የሚሞሉ ፕሮጄክቶች፣ ስፖርቶች ወይም ጥናቶች ለመመለስ በጣም ይጓጓሉ። እያንዳንዱ ቤተሰብ ልዩ ነው።

ከቤተሰብ ደስታ ጋር፣ የበአል አከባበር እና ጉዞ እንዲሁም በካውንቲያችን እየጨመረ ካለው ቁጥር ጋር ተዳምሮ በኮቪድ የመያዝ አደጋ ሊጨምር እንደሚችል እናውቃለን። ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ እና ትምህርት ቤቶቻችንን በተቻለ መጠን ከኮቪድ-ነጻ ማድረግ አለብን። እባክዎን ልጅዎ እንዲመረመር/እንድትመረመር፣ ውጤቱን እንዲያሳውቅ - እንድታሳውቅ እና ከታመመ(ች) ቤት እንዲቆይ - እንድትቆይ ያበረታቱ። እንደ ሁልጊዜው፣ ከጥንቃቄ የተነሳ ጭምብል ለማድረግ የመረጡትን ውሳኔአቸውን ያክብሩ።

የአእምሮ ጤንነት ጉዳይ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ወደ መማሪያ ክፍሎች እና ወደ ትምህርት ቤቶች ሲመለሱ፣ ለህብረተሰባችን ደህንነት ምን ያህል ዋጋ እንደምንሰጥ እንድታውቁ እፈልጋለሁ! ለእኔ ትኩረት የምስጥበት ጉዳይ ነው። የትምህርት ስርአታችንም ትኩረት የሚያደርግበት ጉዳይ ነው። የትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰብ አባላት የአእምሮ ጤንነታቸውን በትምህርት ቤት፣ እንዲሁም በቤት ውስጥ ጊዜ ወስደው እንዲንከባከቡ እፈልጋለሁ።

ይህ የትምህርት አመቱ የመጨረሻ ክፍለ ጊዜ ነው። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ሁሉም ሰው ያለው ለተማሪዎቻችን እና ለቤተሰቦች ነው - ማህበረሰባችን በማህበራዊ፣ ስሜታዊ እና በአካዳሚክ እንዲበለጽግ የሚያስፈልጉትን ድጋፎች ማድረግ እንፈልጋለን።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ፣ የተማሪዎቻችንን ጮክ ያለ ድምፅ በግልፅ ሰምቻለሁ፡ እንደ ሳም እና ሂማንሹ (Sam and Himanshu) የመሣሰሉ ተማሪዎች በትምህርት ቦርድ ፊት ቀርበው እኛን እንደ ትልቅ ሰው፣ ለደህንነት ቅድሚያ እንድንሰጥ ጠይቀዋል። ተማሪዎች ያጋጠማቸውን ሚስጥራዊ ተግዳሮቶችን ለማን ማካፈል እንደሚችሉ፣ እንዲተማመኑባቸው እና ከአስፈላጊ ሪሶርሶች ጋር እንዲያገናኙዋቸው አዋቂዎችን ሲጠይቁ እሰማለሁ። ተማሪዎች በትምህርት ቤት ውስጥ የሚቆዩበትን ጊዜ እንዴት እንደምናዋቅር በተለየ መንገድ እንድናስብ እንደሚጠይቁን ተረድቻለሁ። ተማሪዎች ለመረጋጋት ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። ራሳቸውን ለማጠናከር እንዲችሉ ባልተዋቀረ ሁኔታ ተጨማሪ እድል እንዲሰጣቸው ጠይቀውኛል።

ተማሪዎቻችን የአእምሮ ደኅንነታቸውን በሚመለከት ቅድሚያ መስጠት ሲያስፈልግ ብቻቸውን አይደሉም። ሰራተኞችም እራሳቸውን እንዲንከባከቡ የሚያስችላቸውን ሚዛን መጠበቅ ያስፈልጋቸዋል። ተማሪዎቻችንን በተሻለ ሁኔታ ማገልገል ይፈልጋሉ፣ ይህም ከእነሱ የሚጠበቀውን አሟልቶ ለማቅረብና በቂ ዝግጅት ለማድረግ ጊዜ ይፈልጋል። ጤንነትን ለማጎልበት የአዋቂዎችን ትኩረት ማድነቅ አለብን።

ምንም እንኳን የአእምሮ ጤንነት እና የማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነት ጉዳይ በታሪክ በትምህርት ቤቶች የተለመደ ቢሆንም፣ በኮቪድ-19 ምክንያት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። እና እኛ ሁኔታውን ለመቆጣጠር በመቻላችን ኩራት ይሰማናል፡-

  • ማህበራዊ-ስሜታዊ ስርዓተ-ትምህርት እኔ የምመራበት ነው።
  • የመድብለ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ስርዓት የሚሸጋገሩትን ጨምሮ ተጨማሪ አማካሪዎች ያስፈልጋሉ።
  • በሁሉም ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የወላጅ ማህበረሰብ አስተባባሪዎች እና የተማሪ ደህንነት ቡድኖች ይኖራሉ።
  • ፍትሃዊ የተሐድሶ ድጋፎችን በአሰልጣኞች እና በተጨማሪ የሰራተኞች ስልጠና ማስፋፋት።

 

እስካሁን እየሠራንበት ነው፡-

  • በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ማህበራዊ ሰራተኞችን መቅጠር እና መመደብ።
  • በእኔ ውስጥ ያለውን የማህበራዊ-ስሜታዊ ስርአተ ትምህርትን መሪ ሃሳብ ለተጨማሪ ትምህርት ቤቶች መናኘት።
  • የፍትሃዊ ተሐድሶ ድጋፎችን በአሰልጣኝነት እና በተጨማሪ የሰራተኞች ስልጠና ማስፋፋት።
  • ብዙ የስነ-ልቦና ባለሙያዎችን እና ካውንስለሮችን ወደ ትምህርት ቤቶች ለመቅጠር አዳዲስ መንገዶችን ማሰስ።
  • በየዕለቱ በትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የጤናማ ቁመና እድሎች እንዲኖሩ ስልቶችን መቀየስ።
  • ጥንቃቄ መደረግ ያለባቸው ቦታዎችን እና ልምዶችን ማስፋፋት።

በትምህርት ቤታችን ህንፃዎች ውስጥ ያሉ ሰዎች በሙሉ እዚያ የሚገኙት የተማሪዎቻችንን ስኬት ለማረጋገጥ ነው። ወደ ትምህርት ቤት የመጨረሻዎቹ ሳምንታት ስንቃረብ፣ ልጅዎ መጨነቅ፣ መረበሽ፣ስጋት፣ ትንሽ ግራ መጋባት እና እንዲያውም ጉጉት የሚሰማው/የሚሰማት ከሆነ - እነዚህ ሁሉ የተለመዱ ስሜቶች ናቸው። ነገር ግን፣ አንድ ልጅ እነዚህን ስሜቶች በጤናማ ሁኔታ ማስተናገድ እንደማይችል/እንደማትችል ከተሰማዎት፣ እባክዎን የልጅዎን ትምህርት ቤት ያነጋግሩ፣ የትምህርት ቤት ካውንስለሮቻቸውን ወይም ሌላ የሚያምኑት አዋቂ ሰው እንዲያነጋግሩ አበረታቷቸው፣ እና የሚፈልጉትን እርዳታ እንዲያገኙ እናግዛቸዋለን።

ሁሉም የማህበረሰባችን አባላት ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ በራስ የመተማመን እና የደህንነት ስሜት እንዲሰማቸው እና የመማር እድል እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚቻልባቸውን ምርጥ መፍትሄዎች ለማግኘት ከእርስዎ ጋር ለመስራት እጓጓለሁ። በተከታታይ በመጪ የማህበረሰብ ውይይቶች ልጆቻችንን ለመደገፍ በጋራ መስራት እንደምንችል በተጨማሪ መስማት እቀጥላለሁ።

ከአክብሮት ጋር

Monifa B. McKnight, Ed.D
Interim Superintendent of Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools