ሐሙስ፣ ኤፕሪል 21 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኤፕሪል 21 መታወቅ ያለባቸው ቁምነገሮችን እነሆ!
ከጊዚያዊ ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ማክኬይት (Interim Superintendent Dr. McKnight) ስለ አእምሯዊ ጤንነት እና የደህንነት ቁመና፣ መጪው የማህበረሰብ ተሳትፎ ሁነቶች፣ የሠመር ፕሮግራም ምዝገባ እና ሌሎችም ጠቃሚ መልእክቶች ተካተዋል።

 1. ከስፕሪንግ እረፍት እንኳን በደህና ተመለሳችሁ

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ ጊዜያዊ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክኪንግ (Interim Superintendent Dr. Monifa B. McKnight) ስለማህበረሰብ ደህንነት አስፈላጊነት ደብዳቤ ልከዋል። ትምህርት ቤቶች ቀሪውን የትምህርት ኣመት በተሟላ ጤንነት ማጠናቀቅ እንዲችሉ የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ማህበራዊ-ስሜታዊ ጤንነት ለመደገፍ MCPS ያለውን ሪሶርስ እና ይበልት እየሰራበት መሆኑን ጭምር ያካተተ ነው።

 1. ክትባ ይውሰዱ በማኅበረሰባችን ውስጥ የሚሰራጨውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጥንቃቄ ማድረግ እና ክትባት መውሰድ አስፈላጊ ነው።

5 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው ግለሰቦች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ይችላሉ። ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በነፃ የሚሰጥ ነው። MCPS ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 30፣ የክትባት ክሊኒኮችን ያስተማግዳል፤ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ቀጣይ የክትባት እድሎችም አሉት። በ MCPS ድረገጽ እና DHHS ድረገጽ ላይ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 1. ሜይ 2 ቀኑን ያስታውሱ፡ ከትምህርት ቤት ውጪ ስለ ጤንነት ትኩረት የሚሰጥበት ቀን ነው

ዲስትሪክት አቀፍ ለጤና ትኩረት የሚሰጥበት ቀን በመሆኑ፣ ተማሪዎች በአካላዊ፣ አእምሯዊ እና ስሜታዊ ደህንነት ላይ በሚያተኩሩ ከትምህርት-ቤት-ውጪ በሚከናወኑት በርካታ እንቅስቃሴዎች ላይ እንዲሳተፉ እናበረታታለን። እንቅስቃሴዎቹ የአካል ብቃት፣ ዮጋ፣ ዳንስ፣ ስነጥበብ እና ሙዚቃን ያካትታሉ። ቨርቹወል እና በአካል የመሣተፍ እድሎች ይኖራሉ። ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎን የ OST ድረ-ገጽ ይጎብኙ። የ MCPS ሰራተኞችም በርካታ ተመሳሳይ እድሎች ስለሚኖራቸው በቅርቡ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።

 1. ከዶክተር ማክኒት (Dr. Monifa B. McKnight) ጋር በሚካሄደው የኤፕሪል 27 ቀጣይ ዝግጅት ላይ ከ 200 በላይ የማህበረሰብ አባላት ይሳተፋሉ

tableከሦስቱ ዝግጅቶች የመጀመሪያው፣ "ሁላችን በአንድ ላይ" የተሰኘ ተማሪዎቻችንን የማስቀደም መርሃግብር የተካሄደው ረቡዕ፣ ኤፕሪል 20 በጌትስርበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር። ኤፕሪል 27 እና ሜይ 7 ሁለት ተጨማሪ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ። እነዚህ ሁነቶች የሚካሄዱት ቤተሰቦችን፣ ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና ማህበረሰቡን በማሰባሰብ MCPS ተማሪዎቹን እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማገልገል እንደሚችል ስለ ዲስትሪክቱ ጥንካሬዎች፣ ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች እና ያሉትን እድሎች ለመወያየት ነው።
ዝግጅቶቹ የሚከናወኑት፦

 • እሮብ፣ ኤፕሪል 27፣ 19፡30 p.m., Walter Johnson High School cafeteria, 6400 Rock Spring Drive, Bethesda
 • ቅዳሜ፣ ሜይ 7, 11 a.m., Paint Branch High School cafeteria, 14121 Old Columbia Pike, Burtonsville

እንዲመዘገቡ እናበረታታለን። የተወሰነ የ MCPS አውቶቡስ መጓጓዣ ይቀርባል።

 1. ለአብዛኛዎቹ የ MCPS የሠመር ፕሮግራሞች ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።

MCPS በዚህ ሠመር ለአንደኛ ደረጃ፣ ለመካከለኛ ደረጃ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነፃ ፕሮግራሞችን ይሰጣል። ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የክሬዲት ኮርሶች እና የተራዘመ ትምህርት (ELO) Title I አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፕሮግራም ጁን፣ ጁላይ እና ኦገስት ላይ ይሰጣሉ። በአጠቃላይ በአካል ተገኝተው መማር ያለባቸው ፕሮግራሞች ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ይከናወናሉ። በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች በካውንቲ እና በከተማ አስተዳደር ኤጀንሲዎች እንዲሁም በውጭ አገልግሎት ሰጪዎች የሚደገፉ ከሰዓት በኋላ የሚካሄዱ ፕሮግራሞች ይኖራሉ። እዚህ የበለጠ ይወቁ፣ ወይም የሠመር ፕሮግራሞች ድረገጽ ይጎብኙ።

 1. ስለህፃናት ሻምፒዮና ዝግጅት ሐሙስ፣ ኤፕሪል 28 የቀጥታ ሥርጭት ይመልከቱ።

ለ 2022-2023 የ MCPS የአመቱ ምርጥ መምህር ማን ይሆናል? 6፡30 p.m. በሚጀመረው መርሃ ግብር ላይ እውቅና የሚያገኙት ሦስት የመጨረሻ እጩዎች ናቸው።

 • ኢርማ ናጃሮ (Irma Najarro)፣ በዋሽንግተን ግሮቭ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአራተኛ ክፍል የመድብለ ቋንቋ መምህር
 • ማይክል ኤድዋርድስ (Michael Edwards)፣ በጁሊየስ ዌስት መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የስድስተኛ ክፍል የአለም ጥናቶች እና አለምአቀፍ ሰብአዊነት መምህር
 • ጆናታን ደን (Johnathan Dunn) በሼርዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመዘምራን አሰልጣኝ/አስተማሪ ናቸው።

ይህንን የታላቅ ዝግጅት ማስታወቂያ በ MCPS ድረ-ገጽ MCPS YouTube ቻናል ወይም በኬብል MCPS-TV (Comcast 34፣ Verizon 36፣ RCN 88) መመልከት ትችላላችሁ።Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools