ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ማህበረሰብ፡-

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት (DHHS) ዲፓርትመንት መመሪያዎች ጋር ለማጣጣም ስለ ኮቪድ-19 የማሳወቅ ሂደት ላይ ለውጥ አድርጓል።

በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC) እናየሜሪላንድ የጤና መምሪያ በተሰጠው መመሪያ መሰረት (MDH)፣ ከአሁን በኋላ በትምህርት ቤቶች እና በልጆች እንክብካቤ ፕሮግራሞች ውስጥ የአጠቃላይ ንክኪ ግንኙነቶችን ዱካ ማፈላለግ አስፈላጊ አይደለም።

ቫይረሱ በአካባቢያችን እና በመላ አገሪቱ እየተሠራጨ ባለበት ወቅት ይህ ለውጥ ሊደረግ የቻለው የ COVID-19 ስርጭትን የሚቀንሱ ክትባቶችን በመውሰድ እና የጤና መመሪያዎችን ለመከተል ባደረግነው ጠቃሚ የክትትል ውጤት ምክንያት ነው።

ይህም ከሜይ 2፣ 2022 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

  1. MCPS ከአሁን በኋላ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ተማሪዎች ወይም የስራ ባልደረቦች ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦች በመለየት ወይም በግል ማሳወቅ አይኖርበትም።
  2. በተናጠል ለትምህርት ቤቶች በበሽታው የተያዙ ፖዚቲቭ ጉዳዮችን ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ እንደአግባቡ በመማሪያ ክፍል፣ ወይም በትምህርት ቤት ደረጃ መልዕክቶች ይላካሉ።
  3. ዕለታዊ ሁኔታዎች በትምህርት ቤት የኮቪድ-19 ዳሽቦርድ ላይ ሪፖርት መደረጉ ይቀጥላል።

ከካውንቲው የጤና ጥበቃ አጋሮቻችን ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን እና ተለይቶ በታወቀ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ የንክኪ ፍለጋ ተግባር እናካሂዳለን፤ ተጨማሪ የማስወገጃ ስልቶችን ለት/ቤቱ ማህበረሰብ እናሳውቃለን፣ ይኼውም በጣቢያው ላይ ወይም በቤት ውስጥ ጭንብል መጠቀም እና PCR ወይም ፈጣን ምርመራ ማድረግን ያጠቃልላል። የተማሪዎችን፣ የሰራተኞችን እና የማህበረሰቦችንን ጤንነት እና ደህንነት ለማረጋገጥ በወረርሽኝ የሚያዙትን (ፖዚቲቭ) ቁጥር መጨመር/አለመጨመር ሁኔታዎችን እየተከታተልን ስልታችንን እናስተካክላለን።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ

Montgomery County Public Schools 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools