ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦
የ2022-2023 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሳምንት የትምህርት ቆይታ በጣም በቶሎ አልፏል። ብዙ አስደሳች የሁኑ ነገሮች አሉ እና ለዚህም በጣም አመሰግናለሁ። በየክፍሎቻችን ውስጥ አስደሳች እና ታስቦበት/ዝግጅት የተደረገበት ትምህርት በክፍሎሽ ውስጥ ጥልቅ ተሳትፎ፣ እና ሰራተኞች እና ተማሪዎች ለአዲሱ ዓመት በይበልጥ ዝግጁ ሲሁኑ ተመልክቻለሁ። የኮቪድ-19 ደመና እያሽቆለቆለ በመጣ ቁጥር በትምህርት ብቃታችን ላይ ትኩረታችንን ስንቀጥል እና ስናሰፋ በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ እንደዚህ ያለ አዎንታዊ ጉልበት ማየት መንፈስን የሚያድስ ነው።
ለዚህ አዲስ አመት፣ ሁሉንም ቢሮዎች እና ተግባራትን በመወከል መላው የአመራር ቡድን በዚህ ሳምንት ሁሉንም ማለት ይቻላል ትምህርት ቤቶቻችንን ጎብኝቷል። በየእለቱ የተመለከትነውን እንገመግማለን፣ መሻሻል ያለባቸውን ወይም አፋጣኝ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ቦታዎችን እንለያለን። ተለይተው የወጡ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራን ነው። አዎ፣ መሠራት ያለበት ሥራ እያለ፣ በመጀመሪያዎቹ የትምህርት ቀናቶቻችን የምናከብራቸው/የምንደሰትባቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ አስደናቂ ሰራተኞች አሉን፣ እያንዳንዱ አውቶቡስ ሲሰራ ቆይቷል፣ የቴክኒክ ስርዓቶቻችን ጤናማ ናቸው እና ሁሉም ፕሮግራሞቻችን እና ተግባሮቻችን የተማሪዎቻችን እና የሰራተኞቻችን የደህንነት ፕሮግራሞችን ጨምሮ በመካሄድ ላይ ናቸው። በጋራ፣ በዚህ የትምህርት አመት በሚኖረን አቅም በጣም ተስፋ እናደርጋለን።
ይህ ከተባለ፣ ስለ ደህንነት ጉዳዮች ሁላችንንም ማስታወስ እፈልጋለሁ። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ በሞንትጎመሪ መንደር ከሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንዲት ልጅ ከትምህርት ቤቷ አውቶቡስ ስትወጣ በመኪና ተመታች። ለሕይወት አስጊ ያልሆነ ጉዳት አጋጥሟታል እናም ለእሷ እና ለቤተሰቧ ሃዘን ይሰማናል። ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ተጠንቀቅ እና ህጎቹን አውቀን መቀጠል እንዳለብን ለማስታወስ ያገለግላል። አውቶቡስ ሲቆም መብራቱ ብልጭ ድርግም ይላል እና የማቆሚያው ምልክት/ክንፍ እና የማቆሚያ ምልክቶች ሲውጡ መቆም አለብዎት። የቆመ የትምህርት ቤት አውቶብስን በማለፍ በጉዞዎ ላይ የሚቆጥቡት ምንም ያህል ጊዜ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ወይም የህይወት መጥፋት ዋጋ አይተካም። ይህንን መረጃ ለጎረቤቶችዎ እና ለጓደኞችዎ እንዲያካፍሉ እጠይቃለሁ ።
ከትምህርት ቤት ሰራተኞች ጋር ተገናኝቻለሁ፣ ከልጆቻችሁ ጋር ምሳ ላይ ተቀምጫለሁ፣ ክፍል ውስጥ ሆኜ ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ተማሪዎች ጋር ተነጋግሬያለሁ፣ መማር እና ማስተማርን በተግባር አይቻለሁ። ተማሪዎቻችን በጣም የተወደዱ እና በመመለሳቸው በጣም ደስተኞች ናቸው።
እንደገለጽኩት፣ የአመራር ቡድኑ የኦፕሬሽን ቢሮዎቻችን እና ሌሎችንም ጨምሮ በአውቶቡስ መማቆያዎች፣ በምግብና ስነ-ምግብ ማዕከላችን የትምህርት ቤት ጉብኝቶችን አድርጓል። እኛ "አሁን ሁላችንም አንድ ላይ ነን፣ ሁላችንም ለተማሪዎቻችን፣ ሰራተኞቻችን እና ማህበረሰባችን" ።
ከመልካም ወዳጅነት ጋር
ዶክተር ሞኒፋ ቢ ማክናይት/Dr. Monifa B. McKnight
Superintendent of Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org