የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት ወቅታዊ የት/ቤት ተጠያቂነት ሪፖርት ካርድ አውጥቷል/Accountability Report Card

በዚህም መሠረት 92% የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በስቴት ኮከብ ደረጃ 3 ወይም ከዚያ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡ ሲሆን/
5 ኮከቦችን ያስመዘገቡ ትምህርት ቤቶች 43% ናቸው።

ማርች 10

የተከበራችሁ ወላጆችና አሳዳጊዎች፦

ሐሙስ ማርች 9፣ የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) በሜሪላንድ ስቴት ውስጥ ስላሉት እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የስቴት ሪፖርት ካርድ ይፋ አድርጓል። —የሜሪላንድ ሪፖርት ካርድ—በስቴቱ ውስጥ የሚገኝ እያንዳንዱን ትምህርት ቤት ስኬት ለመለካት እና መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች ለመለየት የተነደፈ ሲሆን ከዚህ ቀደም የሜሪላንድ ሪፖርት ካርድ ይፋ የተደረገው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት 2019 ነበር።

chart

የሜሪላንድ የሪፖርት ካርድ የተነደፈው የሚከተሉትን ጨምሮ የትምህርት ቤቶችን ስኬት በተለያዩ መንገዶች ለመለካት ነው፣

  1. በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነጥበብ እና በሂሳብ የስቴት ፈተና/ምዘናዎች
  2. ለድህረ-ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ዝግጁነት
  3. የእንግሊዘኛ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸውን የማዳበር ብቃት
  4. የምሩቃን ብዛት መጠን
  5. የሜሪላንድ ትምህርት ቤቶች ዳሰሳ ጥናት
  6. ሥር የሰደደ ከትምህርት መቅረት
  7. በደንብ የተሟላ ሥርዓተ ትምህርት ተደራሽነት እና ክሬዲት የሚያገኙ ተማሪዎች።

በእነዚህ የአፈጻጸም መመዘኛዎች ላይ በመመስረት፣ ስቴቱ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት በመቶኛ ደረጃ፣ በአጠቃላይ የተገኙ ነጥቦችን በመቶኛ እና ከ1 እስከ 5 ኮከቦች ባለው የኮከብ ደረጃ ይሰጣል።

ምንም እንኳን የሜሪላንድ የሪፖርት ካርድ በርካታ የተለያዩ የምዘና ዘርፎችን የሚጠቀም ቢሆንም፥ የተማሪዎች የአካዳሚክ ስኬት እና እድገት ግን የሚለካው በአንድ የመረጃ ነጥብ ላይ ብቻ ነው፣ ይኼውም፦ የሜሪላንድ አጠቃላይ ግምገማ ፕሮግራም (MCAP) የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነ ጥበብ/ሊተርሲ እና የሂሳብ ፈተናዎች/ምዘና ነው።

የሜሪላንድ ሪፖርት ካርድ ጠቃሚ መረጃ የሚሰጥ ቢሆንም ከ 160,000 በላይ ለሆኑ ተማሪዎቻችን እድገትና ስኬት ያለው መረጃ እና እይታ ውስን ነው። ትምህርት ቤትን ማሻሻል ቀድሞውንም የአካባቢ ኃላፊነት ነው። ማን የትምህርት ጉጉት እንዳለው፣ እና ማን የእኛን እርዳታ እንደሚፈልግ ስለ ተማሪዎቻችን ይበልጥ የምናውቀው እኛ ነን።

ለምሳሌ፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የበለጠ ዝርዝር እና የት/ቤት ስኬትን በዝርዝር ሪፖርት የሚሰጠውን ፍትሃዊ ተጠያቂነት ሞዴል"Equity Accountability Model" ይጠቀማል። ፍትኃዊ የአካውንቴብሊቲ ሞዴል በርካታ እና ዘወትር የሚካሄዱ ምዘናዎችን የተማሪዎችን እርምጃ (እየተሻሻሉ መሄድ)፣ ስለ ተማሪዎች ስኬት ልዩነት/አለመጣጣም መቀነስ እና ማስወገድ ልዩ ትኩረት በመስጠት ትምህርት ቤት የሁሉንም ተማሪዎች ፍላጎት ያሟላ እንደሆን ለመወሰን ይጠቅማል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪ ስኬት ስትራቴጂ ዘርፈ ብዙ እና የተማሪዎችን ፍላጎት ለማሟላት የተነደፈ ነው። ተመራቂዎቻችን በኮሌጅ፣ በስራ፣ በማህበረሰብ እና በህይወት ስኬታማ ለመሆን ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools

 

MCPS የሜሪላንድ ሪፖርት ካርድ ድረገጽ ይመልከቱ፦ website
*ከቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እስከ 2ኛ ክፍል ብቻ የሚያገለግሉ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮከብ ደረጃ አይሰጣቸውም።*
*የሪፖርት ካርድ በቻይንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ኮሪያንኛ፣ ስፓኒሽኛ እና ቬትናምኛ ቋንቋዎች በዚህ በይነመረብ ላይ ይገኛል፦https://reportcard.msde.maryland.gov/ *



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools