በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ት/ቤቶች ሠላም፣

ደህንነት እና ጤነኛ ቁመና ያለንን ቁርጠኝነት ትምህርት ቤቶቻችን እና ተማሪዎቻችን - አሁን ሁላችንም በአንድ ላይ ከቤተሰቦች ጋር በመተባበር እናከናውናለን። ወቅታዊ መረጃ፦

Friday, Feb. 24

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶቻችን ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ፍትሃዊ እና ስኬታማ ትምህርት ቤቶች እንዲሆኑ ያለንን ቁርጠኝነት የሚዘረዝር አጠቃላይ ስለ ት/ቤቶች ደህንነት ማስጠበቂያ ስልቶች አሉት። ይህንን ቁርጠኝነት ለመደገፍ፣የትምህርት ስርዓታችን ተከታታይየአፋጣኝ፣ የአጭር ጊዜ እና የረዥም ጊዜ የደህንነት አጠባበቅ ስልቶችን በመተግበር ላይ ነው።

ይህንን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ትብብር ወሳኝ በመሆኑ MCPS ከሰራተኞች፣ ከተማሪዎች፣ ከወላጆች እና ከሰፊው ማህበረሰብ ጋር በቅርበት እየሰራ ነው። ይህም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰባችንን ፍላጎቶች ለማሟላት ካለን "ሁላችንም በአንድ ላይ" ከሚለው ቀጣይነት ካለው አካሄድ ጋር ይጣጣማል። ማዕቀፉ በትብብር፣ በታለመላቸው ግብዓቶች፣ ቀጣይነት ባለው ክትትል እና ተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ ነው።

የእኛ ስልቶች/ስትራቴጂዎች

የአጭር ጊዜ/አፋጣኝ
ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 25፣ ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር፣ Fentanyl Family Forum በአሁኑ ጊዜ በማህበረሰባችን ውስጥ ብዙ ወጣቶችን እየጎዳ ያለውን ገዳይ የሆነ ህገ-ወጥ ፈንተንየል መዘዝ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በ ኖርዝዉዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቤተሰቦች ውይይት መድረክ ያስተናግዳል። በጃኑዋሪ ወር፣ MCPS የመጀመሪያውን የ Fantanyl መዘዝ በሚመለከት የቤተሰብ ውይይት መድረክ/ፎረም በክላርክስበርግ ህለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Clarksburg High School) አስተናግዷል።

ተጨማሪ የአጭር ጊዜ/ፈጣን ስልቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የት/ቤቶች ደህንነትን በሚመለከት ቀጣይነት ያለው የተማሪዎች፣ የሰራተኞች እና የቤተሰብ መልዕክቶችን ማጋራት።
  • የወቅቱን የት/ቤቶች ደህንነት በሚመለከት ሊሻሻሉ የሚገቡ ጉዳዮችን በተመለከተ የባለድርሻ አካላትን የተለያዩ አመለካከቶችን ለመስማት ተከታታይ ክፍለ ጊዜዎችን ማዘጋጀት/ማስተናገድ
  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ደህንነትን በሚመለከት የተማሪዎች የደህንነት አማካሪ ቡድን ማቋቋም።

የተማሪዎች መፀዳጃ ክፍል ክትትልና ቁጥጥር እቅድ

የት/ቤት መጸዳጃ ቤቶች ለተማሪዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ ቦታ መሆን አለባቸው። እንደ አደንዛዥ እፅ እና ትምባሆ መጠቀም የተከለከለ ስለሆነ የስነምግባር ደንባችንን የሚጥሱ ተግባራት የሚከናወኑበት ቦታ መሆን የለበትም። የት/ቤት ሰራተኞች በትምህርት ቀን፣ በትምህርት ክፍለ ጊዜያት እና በምሳ ሰአት መካከል የእይታ ክትትል እና የመጸዳጃ ቤት ፍተሻ በተደጋጋሚ ያደርጋሉ።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣የግል አጠቃቀም እና ደህንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀምን በማመጣጠን ክፍት እንደሚሆኑ ለማረጋገጥ በመጸዳጃ ቤት በሮች ላይ መቆለፊያዎች እየተገጠሙ ነው። ትምህርት ቤቶች በክፍት ሠዓት እና ክፍል ውስጥ በማይሆኑባቸው ጊዜዎች ለምሳሌ ከትምህርት ቤት ሰዓት በፊት፣ ከትምህርት በኋላ እና በምሳ ሰአት የተወሰኑ የመጸዳጃ ቤቶችን ተደራሽነት ሊገድቡ ይችላሉ።

የአጭር ጊዜ

የአጭር ጊዜ ስልቶች የተማሪ ደህንነት ላይ ተፅእኖ ያላቸውን የተወሰኑ ልምዶችን፣ ፖሊሲዎችን እና ሂደቶችን መገምገም እና መመርመርን ያካትታሉ። እነዚህ ስልቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ

  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪ የስነምግባር ህግን መከለስ።
  • በተወሰኑ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተማሪ ባጆችን መጠቀም/መሞከር።
  • የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰርን (CEO) 2.0 የመግባቢያ ሰነድ (MOU) መገምገም።
  • ከድንገተኛ አደጋ ዝግጁነት ጋር ግንኙነት ላላቸው ሰራተኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና መስጠት
  • የተማሪዎችን በትምህርት ላይ የመገኘት ልምምዶች ግምገማ ማድረግ።

የረዥም ጊዜ

የረጅም ጊዜ ስትራቴጂዎች ከላይ የተጠቀሱትን ስትራቴጂዎች ውጤታማነት ቀጣይነት ያለው ክትትል ማድረግ እና በሚቀጥለው የትምህርት ዓመት መጀመሪያ ላይ MCPS የት/ቤቶች ደህንነት ማዕቀፍ ትግበራን ያጠቃልላል፣ ይህም የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • ደረጃውን የጠበቀ የደህንነት መገልገያዎችን በሁሉም ህንጻዎች ማስቀመጥ
  • የተማሪዎች በትምህርት ላይ የመገኘት ልምምዶችን ማሻሻል
  • የተማሪ የስነምግባር ህግን ማሻሻል
  • CEO 2.0 MOU የትምህርት ቤት እና የዲስትሪክት ፍላጎቶችን ማሟላት እንደሚቀጥል ማረጋገጥ።
  • የደህንነት ጥበቃን በሚመለከት የዲስትሪክት ሰራተኞች ስልጠና እና የተማሪ ኮሚቴዎችን መጨመር
  • በአመታዊ የሰራተኞች ስልጠና ላይ ስለ ድንገተኛ ሁኔታ እና ደህንነት ሞጁል መጨመር.

ሁሉም በአንድ ላይ አሁን

MCPS ሁሉም ተማሪዎች ለመማር እና ለማደግ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አመቺ የሆነ ትምህርት የሚቀስሙበት አካባቢ እንዲኖራቸው ለማድረግ ቁርጠኛ ነው። ሁሉም ሰራተኞች ስለ ት/ቤቶች ደህንነት የማስተዋወቅ እና ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ፣አመቺ እና አካታች/አቃፊ የትምህርት ቤት አውድ እንዲፈጠር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው። ትምህርት ቤቶቻችን፣ ተማሪዎቻችን እና የእኛ ሀላፊነት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስራ ነው። በአንጻሩ በትምህርት ቤት ንብረት ውስጥ አደንዛዥ እጾችን መጠቀም፣ የጦር መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት እና ሁከት መፍጠር የመሳሰሉትን ተቀባይነት የሌላቸውን ባህሪያት ለማውገዝ በትምህርት ቤት እና በቤት ውስጥ ስለሚጠበቅ መልካም ስነምግባርን በሚመለከት ቤተሰቦች ከልጆቻቸው ጋር የመነጋገር ሃላፊነት አለባቸው። እነዚህ ድርጊቶች በትምህርት ቤቶቻችንም ሆነ በአካባቢያችን ምንም ቦታ የላቸውም።

የስፕሪንግ ወቅት እና የትምህርት አመት መጨረሻ መቃረቡን በጉጉት እየተጠባበቅን ሳለ ተማሪዎቻችንን፣ቤተሰቦቻችንን እና ማህበረሰባችንን በት/ቤት የተማሪዎቻችንን ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የምንከታተላቸውን እርምጃዎች ማሳወቅ እንቀጥላለን።

የዕቅዱን እና የጊዜ ሰሌዳውን ሌሎች ዝርዝሮችን እዚህ ይመልከቱ:- https://www.montgomeryschoolsmd.org/departments/security/plan.aspx

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools