ሰኞ፣ ኤፕሪል 22 አሁን በተመሣሣይ ሰአት የሚሰጥ የትምህርት ቀን ነውይኼውም ተማሪዎች ያመለጣቸውን ትምህርት ማካካሻ ቀን ይሆናል። ተማሪዎች ራሳቸውን ችለው እንዲያጠናቅቁ ከተመደበላቸው የቤት ሥራ ጋር ወደ ቤታቸው ይላካሉ።

በዲጅታል ኮሙኒኬሽን በይነመረብ የሚሰጥ ትምህርት ቀጥታ አስተማሪ ቆሞ እያስተማረ(ች)ች ሳይሆን ወይም ቴክኖሎጂ ሳይጠቀሙ ተማሪዎች በትምህርት ላይ የሚሳተፉበት ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችን እና የቤት ስራዎችን ይገልጻል። ተማሪዎች በእለቱ ትምህርት ላይ መገኘታቸውን ለማረጋገጥ የተሰጣቸውን የትምህርት ቤት ስራዎችን ማጠናቀቅ አለባቸው። ማናቸውም አዳጋች ወይም ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ቢከሰቱ ለተማሪዎች የተሰጣቸውን የትምህርት ቤት ሥራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጣቸዋል።

ትምህርት ቤቶች ማርች አጋማሽ ላይ በዲጅታል ኮሙኒኬሽን በይነመረብ ስለሚሰጥ የትምህርት እቅዶቻቸው ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ያጋራሉ፣ይህም መገልገያ ሪሶርሶችን/ግብዓቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ እና የተሰጣቸውን የት/ቤት ሥራ ስለ ማጠናቀቅ ተጨማሪ መመሪያዎችን ያካትታል። 

2023-2024 የትምህርት አመት ውስጥ —ጃኑዋሪ 16፣ ጃኑዋሪ 17፣ እና ጃኑዋሪ 19 በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ሶስት የትምህርት ቀናት ት/ቤቶች ዝግ ነበሩ። ጃንዋሪ 16፣ ጃንዋሪ 17፣ እና ጃንዋሪ 19 የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) ከባድ የአየር ሁኔታ የሚከሰቱባቸውን ቀናት እና የሰራተኞች የሙያ ማዳበር ትምህርት ቀናትን ጨምሮ የተወሰኑ ቀናትን በቨርቹዋል የትምህርት ቀናት የመጠቀም ኃላፊነት ለትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ተሰጥቷል።

2023-2024 የትምህርት አመት ቀን መቁጠሪያ/ካላንደር ማንኛውም ተጨማሪ የት/ቤቶች መዘጋት የሚከሰት ከሆነ ተጨማሪ የትምህርት ማካካሻ ቀናትን እቅድ ውስጥ በማስገባት ለሁለት የአደጋ ጊዜያት ትምህርት ቤቶች እንደሚዘጉ ያመለክታል። ሰኞ፣ ኤፕሪል 22 ለትምህርት ማካካሻ ተለይተው ከተያዙት ቀናት አንዱ ነው።

እለቱ ለመምህራን የሙያ ማዳበር ትምህርት ቀን ሲሆን በራስ ጥረት የሚማሩበት እና እቅድ የሚያዘጋጁበት እለት ይሆናል። ቴሌ ዎርክ/ሥራ ይፈቀዳል። በተጨማሪም፤ መምህራን ሚዛናዊ በሆነ የማስተማር እና የመማር ማዕቀፍ ላይ በማተኮር በዲጅታል ኮሙኒኬሽን በይነመረብ የሙያ ማበልፀግ ትምህርት ሞጁል ላይ ለመሳተፍ ጊዜ ይኖራቸዋል። ለሰራተኞች በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ተጨማሪ መረጃ ይተላለፋል። 

*ማሳሰቢያ፦ ኢኖቬቲቭ የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ ለሚከተሉ ትምህርት ቤቶች፣ የአርኮላ እና የሮስኮ R. ኒክስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቀን መቁጠሪያ ሰኞ፣ ኤፕሪል 22, 2024 አልተቀየረም። ለተማሪዎች ትምህርት የሌላቸው ቀን ሲሆን ለአስተማሪ ሰራተኞች የሙያ ማዳበር ትምህርት ቀን ይሆናል።   


ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org