መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሀሙስ ኖቨምበር 16 2023

1. የወላጅ-አስተማሪ ኮንፈረንስ ዝግጅት 

ይዘጋጁ! የተማሪዎ የወላጅ-መምህር ኮንፈረንስ በዚህ ወር የሚደረግ ስለሆነ MCPS ከዚህ ዝግጅት ምርጥ ቁምነገሮችን እንድታገኙ ይፈልጋል። የእርስዎ ተማሪ በትምህርት ቤት፣ በአካዳሚክ እና በማህበራዊ ጉዳዮች እንዴት እየሰራ(ች) እንደሆነ ከአስተማሪ(ዎች) ጋር ለመነጋገር እና ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ለወላጅ-አስተማሪ ኮንፈረንስ እንዴት እንደሚዘጋጁ ከዚህ በታች ያሉትን መመሪያዎች ይመልከቱ። 

2. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) 2ኛ ምዕራፍ/Phase Two የትምህርት አመት ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ለማዳበር አስተያየትዎን ያካፍሉን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የ2024–2025 የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ በማዘጋጀት ላይ ስለሆነ ዲስትሪክቱ በሁለት ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎች ላይ ከቤተሰቦች፣ ከተማሪዎች፣ከሰራተኞች እና ከማህበረሰብ አባላት ተጨማሪ ግብረመልስ ይፈልጋል። ይህ ግብረመልስ፣ የዳሰሳ ጥናት #2፣ የዲስትሪክቱን ትምህርታዊ ዝግጅቶች እና ተግባራዊ ፍላጎቶችን ለማራመድ በመዳበር ላይ ያለውን ሁለተኛውን ምዕራፍ ይወክላል። 

የቀን መቁጠሪያ ቅኝት:

English  /  español  /  中文  /  françaisPortuguês한국어tiếng Việt  /  አማርኛ

3. በትምህርት ላይ መገኘት እና መከታተል ፋይዳ አለው፡ ሰኞ፣ ኖቬምበር 20 እና ማክሰኞ፣ ኖቬምበር 21 የትምህርት ቀናት ናቸው።

ሰኞ፣ ኖቬምበር 20 እና ማክሰኞ፣ ኖቬምበር 21 ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት የትምህርት ቀናት መሆናቸውን MCPS ለወላጆች/ለተንከባካቢዎች ያሳስባል። በሁለቱም ቀናት ጠቃሚ የማስተማር እና የመማር ሥራዎች የሚከናወኑ ሲሆን ከምስጋና/Thanksgiving እረፍት በፊት ተማሪዎች ከእኩዮቻቸው ጋር ለመገናኘት የሚችሉበት ጥሩ አጋጣሚ ነው። እባክዎን ልጅዎ/ልጆችዎ ትምህርት ቤት እንዲገኙ ለማድረግ የተቻለዎትን ጥረት አድርጉ። ልጆቻችሁ በመደበኛነት ትምህርት ቤት መገኘት እንዳይችሉ እንቅፋት ካጋጠማቸው፣ እባኮትን በትምህርት ቤት ውስጥ የታመነ(ች) አዋቂ ሰው ለምሳሌ፦ የትምህርት ቤት ካውንስለር ወይም የተማሪ ሰራተኛ ያነጋግሩ።

4. ማሳሰቢያ፡ የኮቪድ ምርመራ ኪቶች ይገኛሉ 

የኮቪድ-19 የቤት መመርመሪያ ኪቶች ከረቡዕ፣ ኖቬምበር 22 በፊት ለሰራተኞች እና ለተማሪዎች ይሰጣሉ።ጉዞዎች እና ትልቅ ማህበራዊ ስብሰባዎች የመሣሰሉ የበዓል እንቅስቃሴዎች ኮቪድ-19 ለመሳሰሉ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች የመጋለጥ እድልን ስለሚጨምሩ ሁሉም ሰው የቤት ውስጥ መመርመርያ እንዳለው ማረጋገጥ እንፈልጋለን። የምርመራ ኪት ካገኙ፣የአገልግሎት ማብቂያ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን በዚህ የኮቪድ ምርመራ ሠንጠረዥ ላይ መመልከት እንዳለብዎት ያስታውሱ።

 

5. ዝግጅቶች እና ልዩ ልዩ እድሎች

ስለ ሥራ ማስኬጃ ባጀት ግንዛቤ ያግኙ እናም ድምጽዎን ያሰሙ! 

እሮብ፣ ኖቬምበር 29 ከቀኑ 7 p.m., ላይ MCPS en Español ገጽ ስለ MCPS የስራ ማስኬጃ በጀት በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ። ጥያቄዎችን ለመመለስ የአስተዳደር እና የበጀት ቢሮ ዳይሬክተር ኢቮን አልፎንሶ-ዊንዘር/Ivon Alfonso-Windsor ይገኛሉ። 

ፎል የቲያትር ፕሮዳክሽን በመካሄድ ላይ ነው

በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የፎል ወቅት የቲያትር ዝግጅቶች መጋረጃ እየተከፈተ ነው። እስከ 2024 መጀመሪያ ድረስ የሚካሄዱትን ምርጥ ትርኢቶች ለማየት አሁኑኑ ያቅዱ። ይበልጥ ያንብቡ

የሽልማት መስጫ ወቅት በመካሄድ ላይ ስለሆነ ዛሬውኑ እጩዎችን ይጠቁሙ! 

እውቅና ሊሰጠው/ሊሰጣት የሚገባ ሰራተኛ፣ አስተዳዳሪ ወይም አስተማሪ አለ? ልዩ ብቃት ያላቸው ሰራተኞችን፣ መምህራንን እና አስተዳዳሪዎችን እውቅና ለመስጠት እጩዎችን ለበርካታ ሽልማቶች ለመጠቆም ክፍት ነው። 

6. ብሩህ ጊዜያት/Bright Spots 

ብሔራዊ የተለማማጅነት ሳምንት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)፣ ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ከሞንትጎመሪ የሥራ ግብረኃይል፣ እና ከሜሪላንድ የሌበር ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር በተማሪዎች እና በንግድ ማህበረሰብ ላይ ያተኮረ ብሔራዊ የስልጠና ሳምንት  ሁለት ዝግጅቶችን አስተናግዷል። በ 2019 የጸደቀው የወጣቶች ስልጠና ፕሮግራም የሚከፈልባቸው ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የወጣቶች የሥራ ልምምዶች ለመፍጠር የተነደፈ ሲሆን ይህም ተማሪዎች ከፍተኛ ችሎታና ክህሎት ባላቸው፣ በከፍተኛ ሁኔታ እድገት ባላቸው ዘርፎች ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያዘጋጃቸው ነው።  

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ለተደረገላቸው መልካም ነገር ምላሽ ይሰጣሉ እና ምስጋና ያቀርባሉ 

የ MCPS ተማሪዎች እና ሰራተኞች ከምስጋና/ታንክስጊቪንግ እረፍት በፊት ያሉትን ቀናት ለማክበር፣ በማገልገል እና ለአካባቢያቸው ማህበረሰቦች በመስጠት ያሳልፋሉ። ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ የሰልፎችን ትርኢት እና ፌስቲቫሎችን፣ ምግብ እና አልባሳትን ከማዳረስ እና ከአረጋውያን ጋር ያሳለፉትን ጊዜ በዲስትሪክቱ ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትን በጨረፍታ ይመልከቱ። 

የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎችን ማክበር

የዊንተር ፎል የስፖርት ወቅት እየተካሄደ ስለሆነ የፎል ወቅት ሻምፒዮና የውድድችን ዙር ይመልከቱ። 

አንዳንድ ፍንጭ በጨረፍታ፡ 

  • ኖርዝዉድ አትሌቲክስ ብሔራዊ የአሸናፊነት ክብር አግኝቷል

  • ፑልስቪል የስቴት ስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸንፏል

  • የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አበረታች/cheerleading ቡድን 2A የስቴት አሸናፊ ሆኗል

  • አልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - የወንዶች 4A ስቴት አገር አቋራጭ ሻምፒዮና

  • የዊንስተን ቸርችል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 4A ስቴት የመጨረሻ እጩ ተወዳዳሪ በመሆን አጠናቋል

  • ዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - የልጃገረዶች አገር አቋራጭ ቡድን ወደ 4A የስቴት አገር አቋራጭነት ተሸጋግሯል 

የኤዲሰን ተማሪዎች ለአሜሪካ ቻይንኛ ትምህርት ቤት የኮምፒውተር ላቦራቶሪ ለግሰዋል

በቶማስ ኤዲሰን ሁለተኛ ደረጃ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተማሪዎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (ITF) የኔትወርክ ኦፕሬሽን ፕሮግራም ለአሜሪካ ቻይንኛ ትምህርት ቤት የኮምፒውተር ላብራቶሪ ለግሷል። ትምህርት ቤቱ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ለሚገኙ የቻይና ማህበረሰቦች ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል (K-12) ተማሪዎች ጥብቅ ትምህርታዊ ተሞክሮዎችን በመስጠት ላይ ያተኩራል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

MCPS የዘገባ ማእከልንየቅርብ ጊዜዎቹን ዜናዎች እና መረጃዎች፣ የፎተግራፍ ክምችት/ጋለሪዎች እና ቪዲዮዎችን ይመልከቱ።ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)