MCPS ባለ ብዙ ደረጃ የትምህርት ቤት ደህንነት/ሰላም እቅድ ለትምህርት ቦርድ ያቀርባል

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

ት/ቤቶቻችን ሰላማዊ/ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው፣ እና በMontgomery County Public Schools፣ ይህ የትምህርት ዓመት ሰላማዊ/ደህንነቱ የተጠበቀ እና ለሁሉም ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ጎብኝዎች አዎንታዊ መሆኑን ለማረጋገጥ እየሰራን ነው።

ከቅርብ ጊዜያት በፊት፣ በርካታ ትምህርት ቤቶቻችን ስዋስቲካን የሚያሳዩ/የሚወክሉ የግድግዳ ላይ ስሁፎችን/ስዕሎችን እና በአንዳድ ሁኔታዎች ፀረ-LGBTQን+ ቋንቋን ጨምሮ የጸረ-ሴማዊ እና የፖለቲካ ይዘት ያለው የንብረት ውድመት ሰለባዎች እንደነበሩ ማስታወስ ጠቃሚ ነው። እነዚህ የጥላቻ ድርጊቶች በተማሪዎቻችን፣ ሰራተኞቻችን እና ቤተሰቦች ላይ ሊያደርሱት የሚችሉትን ጉዳት እና ጭንቀት እንገነዘባለን። እነዚህ ድርጊቶች ህገወጥ ብቻ አይደሉም— ማህበረሰባችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ፣ የፍርሃትና የመከፋፈል ድባብን የሚፈጥሩ ናቸው። በዚህ በፖለቲካ እና በስሜት በሚነዱበት ወቅት፣ ትርጉም ያላቸው ውይይቶችን ማድረግ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ፣ ለዚህ ባህሪ ከፍተኛ ትኩረት ለመስጠት በጋራ መቆም እና ይህን መሰል ከፋፋይ ድርጊቶችን ከህይወታችን ለማስወገድ በጋራ መረባረብ ከመቸውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ነው። 

ደህንነት በከፍተኛ ሁኔታ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደመሆኑ፣ የዲስትሪክቱ አመራሮች በመጪው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን ለመደገፍ የታቀዱ የደህንነት እርምጃዎችን የሚመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ማክሰኞ ኦገስት 20 ለትምህርት ቦርድ አቅርበዋል። ይህ መልእክት ከዚያ ፕረዘንቴሽን የተገኙ መረጃዎችን እና ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እና ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነትን ወደ ትምህርት ቤቶቻችን እና ወደ ቢሮዎቻችን ለማምጣት የተሰሩ ሌሎች ጠቃሚ ስራዎችን ያጋራል።

ባለ ብዙ ደረጃ እቅዱ አራት ዋና ዋና ክፍሎችን ያካትታል፡

  1. ለስኬት የሚረዱ ቅድመ ሁኔታዎች
  2. የአስቸኳይ ሁኔታ ዝግጁነት
  3. መሰረተ ልማቶች
  4. የሰው ሀይል ማቅረብ እና ስልጠና መስጠት

ለስኬት የሚረዱ ቅድመ ሁኔታዎች

በየአመቱ የሚከለሰው የMCPS የተማሪ የስነምግባር ህግ ለእነዚህ ለሚጠበቁ ነገሮች ማዕቀፍ ያቀርባል። ለመጪው የትምህርት ዘመን፣ ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከተማሪዎች የመከባበር ባህል ሞጁል/Student Culture of Respect Module ጎን ለጎን ከተማሪ የሚጠበቁ ነገሮች ሞጁልን/Student Expectations Module ያጠናቅቃሉ። ይህ እያንዳንዱ ተማሪ እኛ እንዲያሳዩ የምንጠብቀውን ባህሪ እና በMCPS የተማሪ የስነምግባር ህግ ላይ በተቀመጠው/በተገለጸው መሰረት የስነ ምግባር ጉድለት የሚያስከትለውን ውጤቶች እንዲረዳ/እንድትረዳ ያግዛል።

ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን ለመቀነስ እና በትምህርት ላይ እንዲያተኩሩ፣ ተማሪዎች በMCPS አውታረ መረብ ላይ የማህበራዊ ሚዲያ ሳይቶችን/ገጾችን ማግኘት/መጠቀም አይችሉም። በተጨማሪም፣ በግል የሞባይል መሳሪያዎች ላይ የወጣውን ወቅታዊ ፖሊሲያችንን እየገመገምን እና በተለያዩ/በበርካታ ትምህርት ቤቶች ውስጥ “ቀኑን ሙሉ ተንቀሳቃሽ ስልክን አለመጠቀም/Away All-Day ” የሚል የተንቀሳቃሽ ስልክ ፖሊሲን እየሞከርን ነው። ይህ እርምጃ/እቅድ ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን ለመቀነስ፣ በማናቸውም የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በመጠቀም ማስፈራራትን፣ ትንኮሳ መፈጸምን/cyberbullying ለመከላከል እና የተማሪዎችን ተሳትፎ ለማሻሻል ያለመ ነው።

በተጨማሪም ባለፈው ዓመት በአምስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተሞከረውን የተማሪ መለያ (የተማሪ መታወቂያ) ፕሮግራምን እያስፋፋን ነው። በኖቬምበር 2024፣ ይህ ፕሮግራም በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል።

የአስቸኳይ ሁኔታ ዝግጁነት

እያንዳንዱ ትምህርት ቤት ከስርዓት አቀፍ የደህንነት እና የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር (OSSEM) ቢሮ ጋር በመተባበር የትምህርት ቤት የድንገተኛ አደጋ ዕቅዶቹን በየዓመቱ ያዘምናል። እነዚህ እቅዶች ሰራተኞች እና ተማሪዎች ከድንገተኛ አደጋዎች በፊት፣ በድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ እና ከድንገተኛ አደጋዎች በኋላ ሊወስዷቸው የሚገቡ እርምጃዎችን ይዘረዝራሉ። በተጨማሪም ትምህርት ቤቶች በድንገተኛ አደጋ ጊዜ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች የሚደረጉ ልምምዶች ላይ ይሳተፋሉ፣ እናም ዝግጁነታችንን ለማረጋገጥ ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር በቅርበት መስራታችንን እንቀጥላለን።

መሰረተ ልማቶች

ሁሉም የMCPS አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የደህንነት ካሜራዎች ተገጥሞላቸዋል። በተጨማሪም፣ የወጣቶችን የሚተኑ/ወደጭስነት የሚለወጡ ነገሮችን የማጨስ/vaping ወረርሽኝን ለመከላከል MCPS ከስምምነት የተገኙ ገንዘቦችን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መጸዳጃ ቤቶች ውስጥ ቬፕን የሚጠቁሙ መሣሪያዎችን ለመግጠም ይጠቀማል።

የሰው ሀይል ማቅረብ እና ስልጠና መስጠት

ለ2024–2025 የትምህርት ዘመን ሰባት ተጨማሪ የደህንነት/የጥበቃ ረዳቶች ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመድበዋል። እንዲሁም ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች የሚሰጡ ስልጠናዎችን እየጨመርን/እያሳደግን ነው። የትምህርት ቤታችን የደህንነት/የጥበቃ ሰራተኞች ሁከት እንዳይባባስ የመከላከያ/የማርገቢያ ዘዴዎችን እና አወንታዊ የት/ቤት አካባቢን/ድባብን ለመፍጠር የሚረዱ ምርጥ ልምዶችን ጨምሮ ልዩ ስልጠናዎችን ማግኘታቸውን ይቀጥላሉ።

ተጨማሪ የደህንነት እርምጃዎች/እቅዶች

ጥላቻን አድሎአዊነትን እና ጉልበተኝነትን/ማስፈራራትን መጋፈጥ

በዚህ ዓመት፣ ዲስትሪክቱ ጥላቻን አድሎአዊነትን እና ጉልበተኝነትን/ማስፈራራትን ለመጋፈጥ የተደራሽነት እርምጃ/እቅድ ጀምሯል። ዓላማው ለሁሉም የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ አባላት የመግባባት፣ የትምህርት እና የወደፊቱን በማሰብ እርምጃዎች የሚወሰዱበት አካባቢብን/ድባብን መፍጠር ነው። ይህ ጥረት ጥላቻ-አድሎአዊነት እና ጉልበተኝነት/ማስፈራራት የሚገለጽባቸውን የተለያይዩ መንገዶችን ለመግለጽ እና ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ወላጆች እነዚህን ጎጂ ባህሪያትን እንዲያውቁ/እንዲለዩ ለመርዳት ግልጽ የሆኑ ትምህርታዊ ግብዓቶችን/መገልገያዎችን ለማቅረብ ዓላማ ያደረገ ነው። በተጨማሪም፣ ዘመቻው እንደዚህ ዓይነት ክስተቶችን ካዩ ወይም ካጋጠሞት ውጤታማ በሆነ መልኩ ምላሽ ስለመስጠት ተግባራዊ መመሪያን ያስተላልፋል።

የትምህርት ቤት የአዕምሮ ጤና እና የማህበራዊ-ስሜታዎ ድጋፍ

የተማሪ ደህንነት፣ የአዕምሮ ጤና እና የማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነት ለተማሪ ስኬት መሰረታዊ ነገሮች ናቸው። ይህንንም ለማሳካት፣ በMCPS ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የግለሰብ ተማሪ ፍላጎቶችን ቅድሚያ ሊሰጠው ከሚገባው ጀምሮ በቅደም ተከተል ለይቶ ለማስቀመጥ እና አግባብነት ያለውን የጣልቃ ገብነት እና የድጋፍ ደረጃን ለመስጠት የተዘጋጀ የተማሪ ደህንነት ቡድን/Student Well-Being Team አለው። እነዚህ ቡድኖች የትምህርት ቤት አማካሪዎችን፣ የስነ-ልቦና ባለሙያዎችን፣ የተማሪ ፐርሶኔል ሰራተኞችን፣ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃ የሙሉ ጊዜ/ቋሚ ማህበራዊ ሰራተኞችን/ሶሻል ወርከሮችን ያካትታሉ። በተጨማሪም፣ የባህሪ ጤናን ለመደገፍ ወደነበረበት የመመለስ ዘዴዎች ስፔሻሊስቶች/ባለሙያዎች በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተመድበዋል/ተሰማርተዋል። በዚህ ዓመት፣ MCPS በ101 አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ቀጥተኛ የቴራፒ ህክምና አገልግሎቶችን ለመስጠት ከThrive Behavioral Health፣ ከSheppard Pratt እና Jewish Social Service Agency (JSSA) ጋር በመተባበር እየሰራ ነው። የMCPSን ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ዘዴ በመጠቀም፣ በMCPS ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ተማሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ እና የውጭ የአእምሮ ጤና አቅራቢዎችን ማግኘት ይችላል።

በተጨማሪም፣ MCPS ዲስትሪክት አቀፍ፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ፣ የተቀናጀ የአእምሮ ጤና ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ከጄድ ፋውንዴሽን ጋር በመጀመሪያዎቹ የሶስት-ዓመት የትምህርት ቤቶች ቡድን ውስጥ ለመሳተፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመረጡ 15 የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ውስጥ አንዱ ነው። ሲጠናቀቅ፣ ይህ ማዕቀፍ ፍላጎቶችን ለመገምገም፣ የአገልግሎቶችን እና የድጋፎችን ተፅእኖ ለመለካት፣ እና በዲስትሪክት እና በትምህርት ቤት ደረጃ ተጠያቂነትን ለማቅረብ መረጃን የሚጠቀም የእድገት/የመሻሻል ሞዴል ሆኖ ያገለግላል።

ይህንን ስራ ስለሚመራው መረጃ የበለጠ ይረዱ/ይማሩ

በ2023–2024 የትምህርት ዘመን፣ በተማሪ የመረጃ ስርዓታችን ሲነርጂ በኩል በድምሩ 4,424 ክስተቶች ሪፖርት ተደርጓል። ከእነዚህ ውስጥ 726ቱ (16%) የተማሪዎችን ደህንነት ሊጎዳ የሚችሉ ወሳኝ ክስተቶች ተብለው ተመድበዋል። እነዚህ ክስተቶች እንደ የጦር መሳሪያዎች፣ የቦምብ ስጋቶች፣ ድብድብ/ግጭት፣ ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እና ያለፈቃድ ወደሌላ ሰው ንብረት መግባት የመሳሰሉ ምድቦችን አካትተዋል።

ከተዘገቡት ክስተቶች ውስጥ 3,698ቱ (84%) በተማሪ ደህንነት ላይ ቀጥተኛ ስጋት የማይፈጥሩ ወሳኝ ያልሆኑ ክስተቶች እንደነበሩ መገንዘብ ጠቃሚ ነው። ወሳኝ ያልሆኑ ክስተቶች ምሳሌዎች እንደ ትናንሽ እንስሳት ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ መግባት ወይም ጊዜያዊ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ያሉ ቀላል ጉዳዮችን ያካትታሉ። ምንም እንኳን እነዚህ ክስተቶች ወሳኝ ክስተቶች ባይሆኑም የት/ቤት ስራዎችን ሳያስተጓጉሉ መፈታታቸውን ለማረጋገጥ በሰነድ ተመዝግበው ይያዛሉ።

የተማሪዎቻችንን ደህንነት እና ስኬት ለማረጋገጥ በጋራ በምንሰራበት ጊዜ ከMCPS ጋር ለሚያደርጉት ቀጣይነት ያለው ትብብር እና በMCPS ላይ ላለዎት እምነት እናመሰግናለን።

ለትምህርት ቦርድ የቀረበውን ፕረዘንቴሽን በቪዲዮ እዚህ ጋር እና ጥቅም ላይ የዋሉ ስላይዶችን እዚህ ጋር ይመልከቱ።

M. Brian Hull, Chief Operating Officer Montgomery County Public Schools


መገልገያዎች


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org