የትምህርት ቦርድ ፌብሩዋሪ 19 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት በጊዜያዊነት አጽድቋል፣ 2025-2026 የትምህርት ቤቶች የቀን መቁጠሪያ (ካላንደር) ቴክኒካዊ ማሻሻያዎችንም አጽድቋል፣ እንዲሁም በትምህርት አመት 2026 አስፈላጊ የሆነ የትምህርት መመሪያ ፖሊሲ ላይ ያለውን አቋም ገምግሟል። ቦርዱ የተማሪዎችን አመራር እና ስኬት እውቅና ሰጥቷል፣ ለተማሪ የቦርድ አባልነት (SMOB) የእጩነት ኮንቬንሽን፣ የፓትሪሺያ B. ኦኔል የተማሪዎች የስነጥበብ ጋለሪ መክፈቻ፣ እና የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወር እውቅና መስጠት፣ የብሔራዊ የትምህርት ቤት ካውንስለሮች ሳምንት፣ በታዳጊዎች የፍቅር ጓደኝነት መካከል የሚነሳ ግጭትን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር፣ እና የሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት የሚዘከርበት ወር እውቅና መስጠት፤ እንዲሁም በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ያሉ የተማሪዎች እና የማህበረሰብ አጋሮች የፈጠራ ሥራዎችን፣ ቁርጠኝነት እና ተጽዕኖን ፈጣሪነትን በማረጋገጥ አክብሮት ሰጥቷል።
የበጀት አመት FY 2027 የሥራ ማስኬጃ ባጀት | 2025–26 የትምህርት ቤት ቀን መቁጠርያ (ካለንደር) | ስለ ፖሊሲ ማሻሻል | SMOB #49 እጩ ተወዳዳሪዎች | ክብረ በዓላት | የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወር | የሕዝብ ትምህርት የላቀ አገልግሎት ሽልማቶች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ የበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀትን በጊዜያዊነት ተቀብሏል፣ ይህም በዋና ዋና የሥራ ክፍሎች ፍላጎቶች እና አስፈላጊ የተማሪዎች አገልግሎቶች ላይ የሚያተኩር $3.78 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ነው። በጀቱ ከሰራተኞቻችን ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን በማክበር $139.7 ሚሊዮን ዶላር ያካተተ እና ለልዩ ትምህርት ትልቅ ትኩረት የተሰጠበት ነው።
ይህ ጊዜያዊ በጀት ለግምገማ ወደ ካውንቲው ሥራ አስፈፃሚ እና የካውንቲ ካውንስል የሚቀርብ ሲሆን፣ ቦርዱ ጁን 25, 2026 የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል። ዋናዎቹ መጪ ቀናት የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
ማርች 13, 2026፡ የካውንቲው ስራ አስፈፃሚ ስለ በጀት ዓመት 2027 የበጀት እቅዶችን ይፋ ያደርጋል
ኤፕሪል 2026: የካውንቲ ካውንስል የበጀት ምምክር ችሎት ይካሄዳል
ሜይ 21, 2026፡ የካውንቲ ካውንስል በካውንቲው የበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት ላይ የውሳኔ እርምጃ ይወስዳል
ጁን 25, 2026፡ የትምህርት ቦርድ ስለ ባጀት ጉዳይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል
ስለ በጀት ዓመት 2027 በጀት እና ቀጣይ እርምጃዎች የበለጠ ለማወቅ የትምህርት ቦርድን ስብሰባ ይመልከቱ።

ቦርዱ የትምህርት አመት 2025–2026 የቀን መቁጠሪያ (ካላንደር) ቴክኒካዊ ማሻሻያዎችን አጽድቋል። አርብ፣ ማርች 20, 2026፣ ለሙያዊ እድገት ትምህርት የማይሰጥበት ቀን ስለሚሆን ከአየር ሁኔታ ጋር ለተያያዙ የት/ቤቶች መዘጋት እንደ ማካካሻ ቀን አይውልም።
ስቴቱ በአሁኑ ጊዜ ቢያንስ 180 የትምህርት ቀናት እንዲኖሩ ይፈልጋል። ከአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ ምክንያት ት/ቤቶች ተዘግተው ስለነበረ ለተማሪዎች የመጨረሻው የትምህርት ቀን ይስተካከላል። የተመደቡት የትምህርት ማካካሻ ቀናት ጁን 18፣ ጁን 22፣ ጁን 24 እና ጁን 25, 2026 ናቸው።
በተጨማሪም፣ ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 23 በአየር ሁኔታ ምክንያት የትምህርት ቤቶችን መዘጋት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ጁን 26 ትምህርት የሚሰጥበት ቀን ይሆናል።
የተሻሻለውን የቀን መቁጠሪያ (ካላንደር) ለማየት ማሻሻያዎቹን/amendments ይመልከቱ።
የትምህርት ቦርዱ 2026 የፖሊሲ ዝግጅት ስብሰባ ላይ የተካተቱ በርካታ ቁልፍ ረቂቅ ሕጎችን ገምግሟል። ቦርዱ ለተማሪዎች፣ ለሠራተኞች፣ እና ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ ለመሟገት የሚከተሉትን አቋሞች ወስዷል፦
HB 1192 / SB 645: የስቴት የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች ቦርድ – አባልነት እና ፈቃድ መስጠት – ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) አስተርጓሚዎችን በሚመለከት ትምህርት – ተኮር የፈቃድ መደብ ለማቋቋም የሚደረጉ ማሻሻያዎች ላይ ድጋፍ መስጠት። የተጠየቁት ማሻሻያዎች አሁን ያሉትን ሰራተኞች በሥራቸው እንዲቆዩ ለማድረግ ግልጽ የሆኑ የሽግግር ድንጋጌዎችን፣ ብቃትን በእኩልነት የማሻሻል ሁኔታ ማመቻቸት እና የቅጥር እንቅፋቶችን ለመቀነስ እና የተማሪዎችን የአገልግሎት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የታለመ በቂ የትግበራ ጊዜን ያካትታሉ።
HB 704 / SB 586: የማህበረሰብ ብቁነት ማስፋፊያ ፕሮግራም – ከማሻሻያ ጋር ድጋፍ መስጠት (በቂ የትምህርት ቤት በጀት ድጋፍ)። ቦርዱ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ጠይቋል፣ የቀረበው $10 ሚሊዮን ዶላር ስቴት አቀፍ ብቁነትን ለመሸፈን በቂ እንዳልሆነ እና MCPS ተጨማሪ ግብዓቶችን ማቅረብ እንደማይችል መግለጽ።
HB 807: የመምህራን ዝግጅት ፕሮግራሞች – የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪ ብቃት – ማሻሻያ በማድረግ ድጋፍ መስጠት (ማቀንቀን)። ቦርዱ የተማሪዎችን ስብጥር በተሻለ ሁኔታ ለማንፀባረቅ "እንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪ" የሚለውን ሁሉንም ማጣቀሻዎች "ብዝሃ ቋንቋ ተማሪ" በሚለው እንዲተካ ይጠይቃል።
HB 490 / SB 311: ትምህርት – ብሉ ፕሪንት የሜሪላንድ የወደፊት እቅድ – ክለሳ – በቴክኖሎጂ ሪፖርት ማድረግን በማስወገድ፣ የማካካሻ ትምህርት የገንዘብ ድጋፍ መስጠት እና እጥረትን ለመቅረፍ የመምህራን ፈቃድ አማራጮችን በማስፋፋት የአስተዳደር ሸክምን ለመቀነስ የቀረቡ ክለሳዎችን መደገፍ። ረቂቅ ህጉ ለጣምራ ምዝገባ እና ለማጠቃለያ አገልግሎቶች ማመቻቸትን/flexibility አለው፣ እና ለርዕሰመምህራን ብሔራዊ የቦርድ የምስክር ወረቀት መስፈርቶችን ለአምስት ዓመታት ያራዝማል።
SB 646: የፐብሊክ ስኩልስ ሲስተም ኮንትራቶች – የተከለከሉ ድንጋጌዎች – ተገቢ ያልሆኑ ውሎችን በማስወገድ እና በመሻር የውል ድርድሮችን ለማቀላጠፍ ድጋፍ መስጠት፣ ከኮንትራክተሮች ጋር በሚደረጉ ስምምነቶች ውስጥ ለትምህርት ስርዓቱ የተሻለ ጥበቃ መኖሩን ማረጋገጥ።
HB 936: የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ – የአካባቢ የምግብ ግዥ – በአካባቢው ከሚገኙ እርሻዎች እና የተለያዩ የምግብ አይነት አቅራቢዎች የምግብ ግዥን በተወሰነ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ድጋፍ መስጠት። ይህ MCPS ሊያከናውናቸው የሚችል ግቦችን እንዲተልም እና ከፍተኛ የአሠራር ስልት በመቀየስ የአካባቢ ምግብ አቅርቦት ዕቅዶችን ማዘጋጀት ያስችለዋል።
የአካባቢን የራስ ገዝ አስተዳደር መጠበቅ – ቦርዱ የአካባቢን ውሳኔ የመስጠት ሥልጣኑን ለመጠበቅ በባጀት ያልተደገፉ የአስተዳደር መስፈርቶችን ለመከላከል በርካታ ግዴታዎችን ይቃወማል፤ ከእነዚህም ውስጥ፡
HB 948 (የውጤት አሰጣጥ ሩብሪክስ) – ይህ ረቂቅ ሕግ የተወሰኑ የውጤት አሰጣጥ ደንቦችን ይከለክላል፣ ይህም የአካባቢውን የውጤት አሰጣጥ ፖሊሲዎች እና የአካዳሚክ አስተዳደር ነፃነትን ይጥሳል።
HB 943 / SB 592 (የፋይናንስ ሊተርሲ መመረቂያ መስፈርት) – ቦርዱ የፋይናንስ እውቀትን ከፍ አድርጎ የሚመለከት ቢሆንም፣ የአካባቢውን የሥርዓተ ትምህርት flexibility የሚገድቡ በስቴት የተደነገጉ የመመረቂያ መስፈርቶችን ይቃወማል።
HB 755 እና HB 525 (የተማሪ የግል የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ አጠቃቀም ፖሊሲዎች)– ቦርዱ ለሁሉም የሚስማማ አንድ አይነት የስቴት ፖሊሲ ግዴታን ከመከተል ይልቅ በተማሪ የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ አጠቃቀም ፖሊሲ ላይ የአካባቢ ቁጥጥርን ለማስጠበቅ ይፈልጋል።
SB 375 (የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልጠና ፕሮግራም መስፈርት) – ቦርዱ የዚህን አይነት የሥልጠና ፕሮግራም አስገዳጅ ባህሪ ይቃወማል፣ ምክንያቱም የሙያ እውቀት ፍላጎት በአካባቢው መወሰን እንዳለበት ያቀነቅናል።
የእነዚህን ረቂቅ ህጎች ዝርዝር ውይይት ፌብሩዋሪ 19 ቀን በተካሄደው ስብሰባ ላይ ማየትይችላሉ።
ፌብሩዋሪ 11 ቀን፣ 400 በላይ የሚሆኑ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪ ተወካዮች በዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የቦርድ አባል (SMOB) እጩ የመምረጥ ኮንቬንሽን ላይ ተሰብስበው ነበር፣ በዚያም የዲስትሪክቱ 49ኛ የቦርድ አባል ለመሆን የተደረገው ፉክክር ሞቅ ያለ ነበር። ከስምንት ችሎታ ካላቸው እጩዎች መካከል ልኡል ዳዊት/Leul Dawit (ከኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) እና ሬሜይ ገርሜይ/Reemey Ghermay (ከዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) የመጨረሻ እጩዎች ሆነው ተመርጠዋል፣ እያንዳንዳቸውም ከተማሪ አስተዳደር፣ ከማህበረሰብ ተነሳሽነት እና ከስቴት የተማሪ ድርጅቶች አስደናቂ የአመራር ልምዶችን የቀሰሙ ናቸው። ተማሪ የቦርድ አባል (SMOB) ምርጫ ረቡዕ፣ ኤፕሪል 22 ይካሄዳል።
የመጨረሻ እጩ ተወዳዳሪዎችን በተግባር ያሳዩትን ደስታ፣ንግግሮች፣ እና ማስታወቂያዎችን ለማየት ተቀርጾ የቀረበውን ቪዲዮ ይመልከቱ!
ፓትሪሺያ B. ኦኔል የተማሪዎች የስነጥበብ ጋለሪ መክፈቻ
የቦርድ አባላት የፓትሪሺያ B. ኦኔል የተማሪዎች የስነጥበብ ጋለሪ በይፋ መከፈቱን አብስረዋል። ወደ ቦርድ ቢሮ የሚመጡ ጎብኚዎች በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የተዘጋጁ የፈጠራ ሥራዎችን በማየት ይደሰታሉ። ፓትሪሺያ ኦኔል ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 23 ዓመታት ቁርጠኛ አገልግሎት ያበረከቱ እና ለእያንዳንዱ ተማሪ ፍትሃዊነትን፣ የተመቻቸ እድልን እና የትምህርት ልህቀትን ለማሳየት የነበራቸውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያከብር መግለጫ ወጥቷል። የመጀመሪያው የቤተዝዳ-ቼቪ ቼዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኪነጥበብ ስራዎችን የሚያሳይ ሲሆን፣ የተማሪዎችን ድምጽ፣ ፈጠራ፣ እና ስኬት ከፍ በማድረግ ዘላቂ የአገልግሎት ድርሻቸውን በመቀጠል የነበራቸውን ጥልቅ እምነት ያንፀባርቃል። በአካል መጎብኘት አይቻልም? ጋለሪውን በኦንላይን እያስሱ እነዚህን ልዩ የተማሪ ፈጠራዎች ይቃኙ።
የአፍሪካን አሜሪካን ታሪክ የሚዘከርበት ወር

የቦርዱ ምክትል ፕሬዝዳንት ብሬንዳ ዎልፍBrenda Wolff የጥቁር አሜሪካውያንን ልዕልና ቅርስና ውርስ በትምህርት ቤቶቻችን እና በማህበረሰቦቻችን ውስጥ ፍትሃዊነት እና እኩልነት ቀጣይነት ያለው ትኩረት መሆኑን በማንፀባረቅ የአፍሪካን አሜሪካን የታሪክ ወር መከበሩን አብስረዋል። ቦርዱ አገልግሎታቸው አካታችነትን እና ተሳትፎን የሚያጠናክር መሪዎችን አክብሮት ከመስጠት አኳያ መዋቅራዊ አለመመጣጠንን እውቅና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በጉልህ ተመልክቷል። ብራንደን ኮንዌይ/Brandon Conway እና ቤንጃሚን ሉዊስ/Benjamin Lewis ከበርተንስቪል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ኒኮላስ ባሴይ/Nicholas Bassey ከ MCCPTA እና የሮክቪል ከንቲባ ሞኒክ አሽተን/Monique Ashton የትምህርት ፍትሃዊነትን እና የማህበረሰብ ተሳትፎን ለማሳደግ ላሳዩት ቁርጠኝነት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ብሔራዊ የትምህርት ቤት ካውንስለሮች ሳምንት

የቦርድ አባል ካርላ ሲልቬስትሬ/Karla Silvestre ለብሔራዊ የትምህርት ቤት ካውንስለሮች ሳምንት እውቅና ሰጥተዋል። ይህ ጊዜ የሚዘከረው የትምህርት ቤት ካውንስለሮች የትምህርት ስኬትን፣ የሙያ እቅድ ማዘጋጀትን እና የተማሪዎችን ደህንነት በመደገፍ ረገድ የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና በጉልህ የሚታይበት ነው። ቦርዱ ሚሪያም ፔስካ/Miriam Peska፣ ዶ/ር ጄኒፈር ጆንስ/Dr. Jennifer Jones፣ ስቴፋኒ ፓውል/Stephanie Powell፣ ዴቢ ቬላዝኬዝ/Debbie Velazquez እና ዶ/ር ካረን ዲ. ክሪውስDr. Karen D. Crews በሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ ላበረከቱት እና ላሳዩት አመራር እና አጠቃላይ የትምህርት ቤት የካውንስሊንግ ወይም የምክር አገልግሎቶችን ለማጠናከር ላሳዩት ቁርጠኝነት አክብሮት ሰጥቷል።
ስለ ታዳጊ ወጣቶች የፍቅር ጓደኝነት ጊዜ ጥቃት የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር

የቦርዱ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን/Grace Rivera-Oven ታዳጊ ወጣቶች በፍቅር ጓደኝነት ጊዜ ስለሚደርስባቸው ጥቃት የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን በማስመልከት ለወጣቶች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ጤናማ እና አክብሮት የተሞላበት ግንኙነትን ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት በመስጠት አስገንዝበዋል። "Choice Respect Montgomery" መስራች ዳኛ ማሪኤልሳ በርናርድ/Judge Marielsa Bernard፤ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የልዩ ተጎጂዎች ክፍል ኃላፊ ዴቢ ፌይንስቴይን/Debbie Feinstein፤ እና የማህበረሰብ ብሪጅስ ዋና ዳይሬክተር ሻነን ባቢ-ቶማስ/Shannon Babe-Thomas፣ ታዳጊዎችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ ግንኙነቶችን ለመገንባት የሚያስፈልጋቸውን እውቀት፣ የተለያዩ ግብዓቶችን እና ድጋፍ በማስታጠቅ ላሳዩት አመራር እና አቀንቃኝነት በትኩረት አክብሮት ተሰጥቷቸዋል።
የስራ ሙያ እና የቴክኖሎጂ ትምህርት ወር

የቦርድ አባላት ጁሊ ያንግ እና ላውራ ስቱዋርት የሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት (CTE) ወርን እውቅና ሰጥተዋል፣ CTE ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ለኮሌጅ፣ ለስራ እና ለዕድሜ ልክ ስኬት በማዘጋጀት ረገድ ያላቸውን ተጽእኖ በትኩረት እውቅና እና አክብሮት ሰጥተዋል። ቦርዱ የዎርክሶርስ ሞንትጎመሪ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አንቶኒ ፌዘርስቶን/Anthony Featherstone፤ ከሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ዶ/ር አን ካዴሚያን/Dr. Anne Khademian፤ ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ ዶ/ር ጄርሜይን ዊሊያምስ/Dr. Jermaine Williams፣ CTE ፋውንዴሽን ስቲቨን ቦደን/Steven Boden፤ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትብብር ቦርድ ተወካዮችና የትምህርት ቤት መሪዎችን ዶ/ር ኢሪና ላግራንጅ/Dr. Irina LaGrange የኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር፣ እና የቤቴዝዳ-ቼቪ ቼዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠባባቂ ርዕሰ መምህር የሆኑትን ሚስተር ኬቨን ዲ. ያተስ/Mr. Kevin D. Yates አክብሮትና እውቅና ሰጥቷል። የጋራ አመራራቸው እና ትብብራቸው ትርጉም ያለው የሙያ ፈለጎችን ያሰፋል እንዲሁም ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የሥራ ግብረኃይል እድሎችን ያጠናክራል።

የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበትን ወር ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በተገኙ ሶስት ተከታታይ አነቃቂ ዝግጅቶች ያክብሩ፦ ቀደምት አባቶች ያስተጋቡት ድምፅ የስኮትላንድ A.M.E. ጽዮን ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ቅርስ እና የጥቁሮችን የትምህርት መሠረት ይዳስሳል። ታሪካዊ ቅርስን መፍጠርካርቨር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እና የማህበረሰባቸውን እሴቶች በማራመድ ከአግላይ ሥርዓት የተላቀቁ ተማሪዎችን አክብሮት መስጠት። የወደፊቱ መሪ ለመሆን የሮክቪል ከተማ ከንቲባ ሞኒክ አሽተን/Monique Ashton ስለ አመራር፣ ተገቢ ውክልና፣ እና ለቀጣዩ ትውልድ በሮችን ስለ መክፈት ይናገራሉ። ታሪክን ለማክበር፣ ስኬቶችን እውቅና ለመስጠት፣ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲን ያለፈ፣ የአሁኑን፣ እና የወደፊት ሁኔታ የሚቀርጹ እሴቶችን ለማበረታታት እና ለማነቃቃት ከእኛ ጋር ይቀላቀሉን።

የትምህርት ቦርድ በካውንቲው ውስጥ ባለው የትምህርት ልምድ ላይ ዘላቂ የሆነ አዎንታዊ ተጽዕኖ የፈጠሩ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን፣ እና የንግድ ማህበረሰቦችን እውቅና ለመስጠት 2026 ለሕዝባዊ ትምህርት የላቀ አገልግሎት ሽልማት የእጩዎችን ጥቆማ እየተቀበለ ነው። ሽልማቶቹ የሚቀርቡት በሚከተሉት ምድቦች ነው።
የቢዝነስ አጋር
የማህበረሰብ አጋር
የት/ቤት አገልግሎት በጎ-ፈቃደኛ
የተማሪ አገልግሎት ሽልማት
እጩዎችን እስከ ሰኞ፣ ማርች 9 5 p.m. ድረስ መጠቆም ይቻላል።
የእጩዎች ጥቆማ ማቅረቢያ ቅጾች፦ English | español | français | 中文 | Portuguese | 한국어 | tiếng Việt | አማርኛ
| ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 23 | ጸደይ/ስፕሪንግ የፋሲሊቲዎች እና የት/ቤቶች ክልል ውይይት #1 (5:00 p.m.) |
| ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 24 | የልዩ ማህበረሰብን ጉዳይ የሚመለከት ኮሚቴ (12:00 p.m.)
ስፕሪንግ/ጸደይ የፋሲሊቲዎች እና የት/ቤቶች ክልል ውይይት #2 (5:00 p.m.) |
| ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 26 | የፖሊሲ ማኔጅመንት ኮሚቴ (3:00 p.m) |
በህዝባዊ የውይይት መድረኮች እና አስተያየት በመስጠት ከእኛ ጋር ይሳተፉ።
Facebook፣ Instagram፣ Bluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org