ሜይ 5 ቀን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በትምህርት አመት 2026 የላቀ የትምህርት አገልግሎት ያበረከቱትን የአክብሮት እውቅና የመስጠት ሥነ ስርአት አክብሯል፤ በዚህ ስነ ስርአት ላይ የተማሪዎቻችንን፣ የሰራተኞቻችንን እና የማህበረሰብ አጋሮቻችንን አስደናቂ ተጽእኖ አድንቋል። ቦርዱ ሜይ 7 ባካሄደው የሥራ ክፍለ ጊዜ 2026–2027 የተፋጠነ የሂሳብ ትምሕርት ሞዴል ወቅታዊ መረጃ አግኝቷል። ይህ ከ 3ኛ እስከ 5ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የላቀ ደረጃ ያለው፣ በየግላቸው የሚሰጡ ፈተናዎችን ለማቅረብ የተነደፈ ሞዴል --ሲሆን በአንድ ላይ ከታጨቀ "ኮምፓክትድ ሒሳብ"/“compacted math” ወደ ክላስተር ቡድን ሽግግርን ያካትታል። ቦርዱ በተጨማሪም የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም በተመለከተ ፖሊሲ IGS ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ገምግሟል፣ እንዲሁም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን፣ የውሂብ ግላዊነትን እና የአካዳሚክ ታማኝነትን በመልካም ሥነ ምግባር ስለ መጠቀም ግልጽ የሆኑ መመሪያዎችን አስቀምጧል፣ እንዲሁም በፈጠራ እና በሰብአዊ አጠቃቀም መካከል ሚዛናዊ እንዲሆን አፅእኖት ሰጥቷል። በተጨማሪም፣ ቦርዱ የዲስትሪክቱን የፖሊሲ አወጣጥ ሂደት የበለጠ ግልፅ እና ለቤተሰቦች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ የታለመ የፖሊሲ BFA ማሻሻያዎችን ተወያይቷል።
የላቀ የትምህርት አገልግሎት እውቅና | የሂሳብ ሥርዓተ ትምህርት | ፖሊሲ IGS | ፖሊሲ BFA |

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እና MCPS የትምሕርት አመት 2026 የላቀ የትምህርት አገልግሎት ያበረከቱትን ክብርና እውቅና ለመስጠት ከእኛ ጋር እንድትሆኑ ይጋብዟችኋል። በዚህ አነቃቂ ምሽት ትምህርት ቤቶቻችንን ለመቀየር ከልባቸው ጠንክረው ለሰሩት ተማሪዎችን፣ አስተማሪዎችን እና አጋሮችን እውቅና ተሰጥቷል።
በሥነ ስርአቱ ላይ የትምሕርት አመት 2026–2027 የአመቱ ምርጥ መምህር ሚሼል ኤሊ/Michelle Elie ላሳዩት ልዩ አመራር እና ጥልቅ የሆነ የሙያ ፍቅር፤ ከአመቱ ምርጥ የህግ አውጪ ተወካይ ግሬግ ዊምስ/Greg Wims፣ የሌጋሲ ሽልማት አሸናፊ ጄሚ ዳርቪሽ/Jamie Darvish እና የአመቱ ምርጥ የድጋፍ አገልግሎት ሰራተኛ ኦስካር አልቫሬንጋ/Oscar Alvarenga እና የማህበረሰብ አጋር አሸናፊ ዶናልድ ዊሊያምስ/Donald Williams ጋር አክብሮት እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል። የዚህን የምርጥ ምሽት የአሸናፊዎችን ዝርዝር በሙሉ እንዲመለከቱ እና ዋና ዋና ነገሮችን እንዲያዩ እንጋብዝዎታለን።
በዚህ ሳምንት MCPS ስለ አዲሱ የሂሳብ ሥርዓተ ትምህርት እና የተፋጠነ ሞዴል ከ 2026–2027 የትምህርት አመት ጀምሮ እንዴት እንደሚተገበር ተጨማሪ መረጃዎችን ለቦርዱ አቅርቧል። ቦርዱ በቅርቡ ያፀደቀውን Amplify Desmos የትምህርት መርሃ ግብር ተከትሎ፣ ዲስትሪክቱ 4ኛ እና 5ኛ ክፍል አሁን ያለውን “compacted math” ሞዴል ለማስወገድ አቅዷል። በምትኩ፣አሁን የላቀ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች 3ኛ እስከ 5ኛ ክፍል "ክላስተር ቡድን" አማካኝነት ከክፍል ደረጃ በላይ የከሪኩለም ይዘት እንዲያገኙ እና ሥርዓተ ትምህርቱ ሲጠቃለል ብዙ ጊዜ የሚታየው የክህሎት ክፍተት እንዳይኖር ማረጋገጫ ይሆናል። በዚህ ሞዴል፣ ተማሪዎች ከእኩዮቻቸው ጋር ሆነው በየክህሎት ደረጃቸው የሚመጥን የተለየ ትምህርት እና ጥልቅ ክህሎት ማበልጸጊያ እያገኙ ይቀጥላሉ።
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች 2026–2027 ከመገባደዱ በፊት ለቤተሰቦች እና ለትምህርት ቤቶች ደረጃ በደረጃ መመሪያ እንደሚዘጋጅ ገልፀዋል።
ስለ አዲሱ የሂሳብ ትምህርት ዘርፍ የበለጠ ይወቁ።
ቦርዱ ፖሊሲ IGS፣ ስለ ትምህርታዊ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ከማህበረሰብ የተሰጡ አስተያየቶችን ገምግሟል። ይህ ፖሊሲ ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ደህንነቱ በተጠበቀ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ስለ መጠቀም ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቷል። የተደረጉት ቁልፍ ማሻሻያዎች የተማሪዎችን የውሂብ ግላዊነት መጠበቅ እና ስለ AI የውሂብ ቋትን ጨምሮ ዋና ዋና የማህበረሰብ ስጋቶችን ይዳስሳሉ። የተሻሻለው ፖሊሲ መምህራን በክፍል ውስጥ ዋና ውሳኔ ሰጪዎች ሆነው እንደሚቀጥሉ እና ጤናማ የአእምሮ እድገትን ለመደገፍ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች "ከስክሪን ነፃ" ጊዜ እንዲኖራቸው ይደነግጋል።
የሚቀጥለው ምንድነው፡ ቦርዱ ይህንን ፖሊሲ ሜይ 21, 2026 የመጨረሻ ድምጽ በመስጠት ለማፅደቅ ቀጠሮ ይዟል።
አተገባበር፦ ከፀደቀ በኋላ፣ ዲስትሪክቱ ሁሉንም AI መሳሪያዎች በጥንቃቄ እያጣራ AI ያመነጫቸውን የተሳሳቱ መረጃዎች ለመለየት የሚያስችል የሰራተኞች ስልጠና ይሰጣል።
ቦርዱ በተጨማሪም MCPS ኦፊሴላዊ ደንቦቹን እንዴት እንደሚያዘጋጅ እና እንደሚያሻሽል የሚቆጣጠርበትን ፖሊሲ BFA ላይ የተደረጉ ለውጦችን ገምግሟል። እነዚህ ማሻሻያዎች የሚያተኩሩት ከዲስትሪክቱ ውሳኔዎች ጀርባ ያለውን "እንዴት" እና "ለምን" የሚለውን እሳቤ ለሕዝብ ግልጽ ለማድረግ ነው።
ስለ ታቀዱት ለውጦች ቁልፍ የሆኑ ፍንጮች፡
ትርጉም ያለው የማህበረሰብ ድምጽ፦ ከ 200 በላይ የማህበረሰብ አባላት ለሰጡት አስተያየት ምላሽ ለመስጠት፣ ቦርዱ ከማህበረሰቡ የተሰጡት ግብረመልሶች ግብዓት የአንድን ፖሊሲ የመጨረሻ ስሪት እንዴት እንደሚለውጠው በትክክል ለማሳየት ቁርጠኛ ነው።
ውጤቶችን መፈተሽ፦ አዳዲሶቹ ድንጋጌዎችና ፖሊሲዎች ዲስትሪክቱ በትክክል እየሰራ መሆኑን ለመከታተል እና ግቦች ካልተሳኩ ፈጣን እርምጃ መውሰድን ይደነግጋሉ።
ለክትትል ቀላል ነው፦ የተሻሻለው ሂደት የትኞቹ ፖሊሲዎች እየተገመገሙ እንደሆነ ለማየት እና ታሪካዊ ለውጦችን ለማግኘት ለወላጆች ቀላል ያደርገዋል።
ሰኞ፣ ሜይ 11 ልዩ የቦርድ የሥራ ስብሰባ (12:00 p.m.)
ሐሙስ፣ ሜይ 14 ልዩ የቦርድ የሥራ ስብሰባ (12:30 p.m)
የኮሙኒኬሽን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ የቦርድ አድቫይዘሪ ኮሚቴ (6:30 p.m)
ማክሰኞ፣ ሜይ 19 ልዩ አገልግሎት የሚያስፈልጋቸው ማህበረሰብ ኮሚቴ (9፡00 a.m.)
ፊስካል ማኔጅመንት ኮሚቴ (5፡30 p.m.)
ሐሙስ፣ ሜይ 21 የቦርድ የሥራ ስብሰባ (4፡00 p.m.)
በህዝባዊ የውይይት መድረኮች ላይ አስተያየት በመስጠት ይሳተፉ።
Facebook፣ Instagram፣ Bluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org