የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ጁን 4 ባካሄደው የሥራ ክፍለ ጊዜ ለበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት $3.72 ቢሊዮን ዶላር አጽድቋል። ቦርዱ የሪጅናል የፋይናንስ ጫናዎችን በመጋፈጥ፣ የአሠራር እውነታዎችን እና የትምሕርት አሰጣጥን ለማስቀጠል ያለውን ጥልቅ ቁርጠኝነት በማመጣጠን ባሳለፈው የመጨረሻ የበጀት ውሳኔ $36 ሚሊዮን ዶላር ክፍተት በማቻቻል ወስኗል። በአስቸጋሪ የበጀት ቅነሳ ሁኔታዎች፣ በጀቱ ዋና ዋና የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን ለማካሄድ/ለማስቀጠል እና የትምህርት ቤቶችን የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እና የኮሌጅ ናቪጌተሮችን ጨምሮ በቀጥታ ለተማሪዎች አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን ያከናውናል። ከፋይናንስ እቅድ ባሻገር፣ ቦርዱ የሶስተኛ ሩብ ዓመት የአካዳሚክ አፈፃፀምን ገምግሟል፣ እየተሻሻለ የመጣውን MCPS አትሌቲክስ ገጽታ ተወያይቷል፣ ለቀጣዩ የትምህርት ዓመት "Leveling Up" ስልቶችን ዘርዝሯል፣ እንዲሁም የተማሪዎችን የስክሪን አጠቃቀም ጊዜ እና የማህበረሰብ ተሳትፎን በተመለከተ አዲስ የአሠራር ሁኔታን አስተዋውቋል።
የበጀት አመት FY 2027 አጠቃላይ በጀት | የሦስተኛ ሩብ ዓመት Q3 አካደሚክ አፈጻጸም | MCPS አትሌቲክስ & ታይትል IX | ከፍተኛ ደረጃ ለማደግ ማሻሻል | አዲስ ቢዝነስ
ቦርዱ ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የበጀት ዓመት 2027 $3.72 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት አጽድቋል። ዲስትሪክቱ ካቀረበው የመጀመሪያ ጥያቄ $36 ሚሊዮን ዶላር እጥረት ቢኖርበትም፣ መጨረሻው የፀደቀው በጀት የክፍል ትምህርትን ባለበት ደረጃ ለመቀጠል፣ ወሳኝ የተማሪዎችን ድጋፍ ለመጠበቅ እና በተቻለ መጠን የቅነሳ ተጽእኖን ለመገደብ ቅድሚያ ተሰጥቷል።
የበጀት ቅነሳው 415 የሥራ መደቦች ላይ ተጽዕኖ ቢኖረውም፣ በአሁኑ ጊዜ 159ቱ ክፍት ናቸው፣ ስለዚህ ተጽዕኖ የሚደርስባቸው ሠራተኞች ያለፍላጎት በሚደረገው የዝውውር ሂደት ወደ ሌሎች የሥራ መደቦች ሊመደቡ ይችላሉ። የዲስትሪክቱ መሪዎች የዲስትሪክቱን ዋና ተልዕኮ ማለትም የማስተማርን ዋና ተልእኮ በመጠበቅ የረጅም ጊዜ የፋይናንስና በጀት መረጋጋትን ለማስጠበቅ አስቸጋሪ ውሳኔዎችን ማድረግ አስፈላጊ መሆናቸውን አፅንዖት ሰጥተዋል።
ዋና ዋና የሥራ መዋቅሮችን መጠበቅ በተመለከተ፡ የተፀደቀው በጀት በተማሪዎች የስነ አእምሮ ጤና እና የማስተማር ዘርፎች ላይ ኢንቨስትመንቶችን በመቀጠል የትምህርት ቤት የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን፣ የትምህርት ድጋፍ ሰራተኞችን፣ የኮሌጅ እና የሙያ ዝግጁነት ሥራ መደቦችን እና የትምህርት ቤት ደህንነት የሥራ መደቦችን ጨምሮ ቁልፍ ድጋፎችን ይጠብቃል።
ሙሉውን የበጀት ዝርዝሮችን ውሳኔ ያንብቡ
ጁን 4 የቦርድ ስብሰባ እና የበጀት ውሳኔ አሰጣጥ ይመልከቱ
ቦርዱ የሶስተኛ ሩብ ዓመት የትምህርት አፈጻጸም መረጃ ገምግሟል፣ ይህም የትምህርት ዓመቱ ሊጠናቀቅ እየተቃረበ ሲሄድ ወሳኝ መለኪያዎችን ያንፀባረቀ ነው።
ይህ ወቅታዊ መረጃ በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሊተርሲ ትምህርት (literacy) እድገት፣ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሂሳብ ትምህርት መሻሻል እና ጠንካራ የኮርስ አፈጻጸም መኖሩን ያመለክታል። በተቃራኒው፣ MCPS የተማሪዎችን የአፈጻጸም መረጃ በመጠቀም የትምህርት አሰጣጥን ለማጠናከር እና የትምህርት እድሎችን ክፍተቶች ለመዝጋት 6ኛ ክፍል የሂሳብ ትምሕርት ትኩረት የሚሰጠው የድጋፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል።
SY 2025–2026 የትምህርት አፈፃፀም፡ የሶስተኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት ያንብቡ
ቦርዱ ስለ MCPS አትሌቲክስ ወቅታዊ መረጃ አግኝቷል፣ ይህም የተማሪዎችን ተሳትፎ፣ ታይትል Title IX ቀጣይነት እና STUNT እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስግኔቸር እግር ኳስን ጨምሮ የአትሌቲክስ እድሎችን ለማስፋት የታቀደ ነው።
ሰራተኞቹ የጂምናስቲክን እንቅስቃሴ ማቆምን በተመለከተ የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ጭምር ገምግመዋል፤ ይህም የተሳትፎ መቀነስ፣ የአሰልጣኞች እጥረት እና የረጅም ጊዜ የዘላቂነት ስጋቶችን የሚጠቅስ ነው።
ይህ ለቤተሰቦች ምን ማለት ነው፡ MCPS የወደፊት የፕሮግራም አቅርቦቶችን ሲገመግም እና በዲስትሪክቱ ውስጥ ፍትሃዊ የአትሌቲክስ እድሎችን ለማመቻቸት እየሰራ ስለሆነ ጂምናስቲክን ጨምሮ የአትሌቲክስ ፕሮግራሞች 2026–2027 የትምህርት አመት ላይ ይቀጥላሉ።
ጁን 4 የቀረበውን የአትሌቲክስ ወቅታዊ መረጃ ይመልከቱ
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት የታቀዱ ቁልፍ ተነሳሽነቶችን አጠቃላይ አቅጣጫ አቅርበዋል፤ ይህም የትምህርት ልህቀትን እና የአሠራር ማሻሻያዎችን ለማምጣት የታለመ ነው። ክለሳዎቹ እና ማሻሻያዎቹ ይበልጥ የሚያተኩሩት፦
የቀረበው ምክረ ሃሳብ የአካዳሚክ ውጤቶችን፣ የአሠራር ቅልጥፍናን፣ እና የቤተሰብ ተሳትፎን ለማሻሻል የረጅም ጊዜ ጥረቶችን እንደ ወደፊት ስትራቴጂክ ዕቅድ አካል አድርጎ ዘርዝሯል።
ስለወደ ቀጣይ ደረጃ ማሻሻል የቀረበውን ያንብቡየቦርድ አባል ጁሊ ያንግ/Julie Yang ለአንደኛ እና ለመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች የዲጂታል መሳሪያዎችን አጠቃቀም አጠቃላይ ግምገማ የሚመለከት አዲስ የውሳኔ ሀሳብ አስተዋውቀዋል። ለመጀመሪያው የቦርድ ግምገማ እና ለወደፊት እርምጃ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ፦ የተማሪዎችን ትኩረት፣ እንቅልፍ፣ እና አካላዊ ጤንነት ለመጠበቅ ዘመናዊ የዲጂታል መሳሪያዎችን ከተለምዶአዊ የማስተማሪያ ዘዴዎች ጋር ማመጣጠን አስፈላጊ መሆኑን ያንፀባርቃል።
የውሳኔ ሀሳቡ ወደፊት በሚደረግ የድምጽ አሰጣጥ ከፀደቀ፣ MCPS እስከ ማርች 2027 ድረስ ለቦርዱ መደበኛ የግምገማ ሪፖርት እንዲያቀርብ ይመራዋል።
ስለ መዋእለ ህጻናት እስከ ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች (K-8) ስክሪን የማያ ገጽ ጊዜ ውሳኔ ሰነድ ያንብቡ
ቦርዱ ከጁላይ 1, 2026 እስከ ጁን 30, 2027 ድረስ ለሚቆየው የኮሙኒኬሽን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አማካሪ ኮሚቴ አዲስ አባላት እንዲሾም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አጽድቋል።
ኮሚቴው MCPS እና ቦርዱ ወሳኝ በሆኑ የዲስትሪክት ተነሳሽነቶች ላይ ከቤተሰቦች ጋር እንዴት መገናኘት እንዳለባቸው በጥራት የማካሄድ ኃላፊነት አለበት። ለቀጣዩ የትምህርት አመት፣ ዋና ትኩረታቸው በመጪው የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የወሰን ጥናት ዙሪያ ላይ ያተኮረ ሁሉን አቀፍ የግንኙነት እቅድ ማዘጋጀት እና ተግባራዊ ማድረግ ይሆናል።
ስለ አማካሪ ኮሚቴ የውሳኔ ሰነድ ያንብቡ
ሐሙስ፣ ጁን 25 የቦርድ መደበኛ ስብሰባ (ከሰዓት በኋላ 4፡00 p.m.)
ማክሰኞ፣ ጁን 30 የፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ (ከሰዓት በኋላ 3፡00 p.m.)
ሰኞ፣ ጁላይ 6ተማሪ የቦርድ አባል/SMOB የቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት ይከናወናል (4፡00 p.m.)
በህዝባዊ የውይይት መድረኮች ላይ አስተያየት ለመስጠት ይሳተፉ።
Facebook፣ Instagram፣ Bluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org