አበይት ጉዳዮች
ኦክቶበር 9, 2025
|
|
ለፕሮግራም ትንተና፣ እና ለድንበር ጥናት ስብሰባዎች ይቀላቀሉን
MCPS ለእያንዳንዱ ተማሪ የመኖሪያ አካባቢያቸው የትም ቢሆን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ፕሮግራሞች እና የመማር እድሎችን እንዲያገኙ ለማድረግ አስፈላጊ እና የተቀናጁ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው። የአካዳሚክ ፕሮግራም ትንተና እና የድንበር ጥናቶች የተለያዩ ጥረቶች አይደሉም፣ ነገር ግን MCPS ትልቅ ቁርጠኝነት ያለው እቅድ በመንደፍ እና ግብዓቶችን በተገቢው ሁኔታ እና በፍትኃዊነት በማመቻቸት ተማሪዎች ጠንካራ ትምህርቶችን እንዲያገኙ እና ለወደፊታቸው ዝግጁ እንዲሆኑ ማስቻል ነው። የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ቀደም ሲል በሪጅን 5) እና ኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ቀደም ሲል በሪጅን 6) ክልላቸው/ሪጅናቸው ይቀየራል። ይበልጥ ያንብቡ።
የድንበር ጥናት አማራጮች የሚቀርቡባቸው ስብሰባዎች በመካሄድ ላይ ናቸው
ኦክቶበር ላይ በሚካሄዱት ቨርቹዋል ወይም በአካል በመገኘት የወሰን ጥናት አማራጮች የሚቀርቡባቸው ስብሰባዎች ላይ ይሳተፉ። እነዚህ የመረጃ ውይይት የሚደረግባቸው የህዝብ ስብሰባዎች ስለ ቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደገና መክፈት፣ ስለ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መክፈት፣ እና 2027-2028 የትምህርት አመት የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስለሚስፋፋበት ሁኔታ ተጣርቶ የቀረበ የድንበር አማራጮችን ይመረምራሉ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
የትምህርት ቤቶቻችን ህንፃዎች ጠንካራ እውነቶች—እና እንዴት እንደምናስተካክላቸው
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች እጅግ በጣም ጥሩ እንዲሆኑ ይጠበቃል—ምቹ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ እና አካታች መሆን አለባቸው። ነገር ግን ማህበረሰባችን በብዙ የትምህርት ቤት ህንጻዎች ሁኔታ ተበሳጭቷል፣ እና ሱፐርኢንተንደንት ቶማስ W. ቴይለር (ዶ/ር) እውነታውን ለመጋፈጥ እና አዲስ ትልም ለመቅረጽ ጊዜው አሁን ነው ይላሉ።
ሰኞ፣ ኦክቶበር 13፣ ከቀኑ 6 p.m. ሱፐርኢንተንደንቱ ወደፊት ስላሉ ተግዳሮቶች እና ትምህርት ቤቶቻችንን ለመጠገን እና ለማዘመን የሚያስፈልገውን እቅድ ያቀርባሉ። በቀጥታ ስርጭት የሚያቀርቡት የበጀት አመት 2027 ካፒታል በጀት እና 2027-2032 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራምን (CIP) በቀጥታ ይመለከታል። በይነመረብ ላይ www.montgomeryschoolsmd.org ወይም MCPS-TV (Comcast 34፣ Verizon 36፣ RCN 88) መመልከት ይችላሉ።
የሕዝብ አስተያየት መስጫ እድሎች፦ ኦክቶበር 23፣ ኦክቶበር 28፣ እና ኖቨምበር 6 (ካስፈለገ)በሚደረጉ የትምህርት ቦርድ ስብሰባዎች ላይ የማህበረሰብ አስተያየቶች ይቀርባሉ። እንዲሁም ሱፐርኢንተንደንቱ CIP የማህበረሰብ አስተያየትና ውይይት የሚቀርብባቸውን ክፍለ ጊዜዎች ኦክቶበር 21 (በአካል) እና ኦክቶበር 22 (ቨርቹዋል)የሚያስተናግዱ ሲሆን—ዝርዝሩ በቅርቡ ይወጣል።
እንዳያምልጥዎት—ከባድ እውነቶች ለማስተካከል እቅድ የሚያሟሉበት ወቅቱ አሁን ነው።
|
|
|
ትምህርት ቤቶቻችንን ማጠናከር፦ የበፊት ዳራ መፈተሽ እና የመለያ ባጅ ማሻሻል
MCPS ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ መስጠቱን ሲቀጥል የዳራ ፍተሻ፣ የጣት አሻራ፣ እና ባጅ በማጣራት ረገድ ወደፊት እየገሰገሰ ነው። ባለፈው ሳምንት ቡድናችን የዋልተር ጆንሰን ክለስተር ትምህርት ቤቶችን ጎብኝቷል፤በዚሁ መሠረት MCPS ሂደቱን እስከ ዲሴምበር አጋማሽ ድረስ ለማጠናቀቅ በትጋት መሥራቱን ይቀጥላል። ከዚህ በታች በድጋሚ ማጣራት የተደረገላቸውን ሰራተኞች ብዛት የሚያመለክት የእስካሁን አፈጻጸማችንን ይመለከቷል።
ሜትሪክ/Metric |
ቫልዩ/Value |
እስከ ዛሬ እንደገና ማጣራት የተደረገላቸው ጠቅላላ ሠራተኞ ብዛት |
3,399 |
% የተጠናቀቀ የትምህርት ቤት ሠራተኞች |
32% |
# የተጠናቀቀ የትምህርት ቤቶች ብዛት |
77/211 |
|
|
|
የትምህርት ቦርድ (BOE) በሕዝብ አስተያየት ሂደት ላይ ለውጥ አድርጓል
ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ተሳትፎን ለማበረታታት በሚደረገው ጥረት የትምህርት ቦርድ የህዝብ አስተያየት መስጫ ሂደቱን ለማሳለጥ በመመሪያው ላይ ማሻሻያ አድርጓል። ከኦክቶበር 16 የስራ ክፍለ ጊዜ ጀምሮ፣ በምዝገባ ወቅት የህዝብ አስተያየት ለመስጠት የተመዘገቡት የመጀመሪያዎቹ 20 ግለሰቦች ለመናገር ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ደቂቃ ይሰጣቸዋል። የምዝገባ ሂደቱ ከተዘጋ በኋላ የሚቀር የህዝብ አስተያየት መስጫ ጊዜ ካለ በስብሰባው ቀን የመክፈቻው ክፍለ ጊዜ መጀመሪያ ከመድረሱ 15 ደቂቃ በፊት ቦርዱ ሰራተኞች ዘንድ በመመዝገብ እንደአመጣጣቸው ቅደም ተከተል በመጀመሪያ የመጣ ቅድሚያ እድል ያገኛል። ለበለጠ መረጃ የቦርዱን የማህበረሰብ ተሳትፎ ድረ ገጽ ይጎብኙ፦
|
|
|
ዛሬ ለነጻ እና ለዋጋ ቅናሽ ምግብ (FARMS) ማመልከትን እንዳይረሱ!
የምግብ ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ዛሬውኑ በኦንላይን ያመልክቱ!2025-2026 የትምህርት አመት ለነጻ እና ለዋጋ ቅናሽ ምግብ (FARMS) ፈቃድ የሌላቸው ተማሪዎች ከዛሬ፣ ኦክቶበር 9, 2025 ጀምሮ፣ወደሚከፈልበት ደረጃ ስለሚሸጋገሩ ለምግብ እንዲከፍሉ ይደረጋሉ። ልጆቻችሁ ያለፈው አመት ብቁ ቢሆኑም እንኳ በየትምህርት አመቱአዲስ FAARMS ማመልከቻ መሞላት አለበት። ከቀዳሚው የትምህርት አመት የተማሪ ምግብ ጥቅማ ጥቅሞች የሚቀጥሉት ለመጀመሪያዎቹ 30 የስራ ቀናት ወይም አዲስ የብቁነት ፈቃድ እስኪወሰን ድረስ ብቻ ነው። ቤተሰቦች በትምህርት አመቱ በማንኛውም ጊዜ ማመልከት ይችላሉ።
የፌደራል የገቢ ደረጃዎችን የሚያሟሉ ቤተሰቦች ለነጻ የትምህርት ቤት ምግብ ብቁ ናቸው፣ ነገር ግን ይህንን ጥቅማጥቅም ለማግኘት ማመልከት አለባቸው። በአንድ ቤተሰብ ለሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች የሚያስፈልገው አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ፣ የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት መምሪያን ድረ ገጽ ይጎብኙ፦ Department of Food and Nutrition Services website
በእነዚህ 60 ትምህርት ቤቶች የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁርስ እና ምሳ ያለምንም ክፍያ ያገኛሉ፣ እና ቤተሰቦች በሌላ ትምህርት ቤት የሚማር/የምትማር ስም ዝርዝር ውስጥ ያልተገለጸ ተማሪ ከሌላቸው በስተቀር FARMS ማመልከቻ ማስገባት አያስፈልጋቸውም።
|
|
|
የዊንተር/የክረምት አትሌቲክስ ምዝገባ አሁን ተከፍቷል
ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዊንተር/የክረምት አትሌቲክስ ምዝገባ ሰኞ፣ ኦክቶበር 13 እኩለ ቀን ላይParentVue እና ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ሰኞ፣ ኦክቶበር 27 ይከፈታል። ስለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አትሌቲክስ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ይመልከቱ፦
boys’ and girls’ basketball, cheerleading, corollary bocce, boys’ and girls’ indoor track, pompons, boys’ and girls’ swimming and diving, and coed wrestling የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስፖርት የወንዶች እና የሴቶች ቅርጫት ኳስ ያካትታል። ተጨማሪ መረጃ
|
|
|
ከልብ መንዳት
ሁጎ “አሌክስ” ካርሪዮን/Hugo “Alex” Carrion ወደ ሁለት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ጠዋት ማለዳዎችን በተመሳሳይ ሁኔታ ይጀምራል፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ስለሆኑ ወደ አውቶቡሱ ሲሳፈሩ፣ ብዙዎች በዊልቼር የሚቀመጡ፣ አንዳንዶች መናገር የማይችሉ፣ ናቸው እና ሁሉንም “መላእክት” ይላቸዋል። መጀመሪያ አመጣጡ ከቦሊቪያ ሲሆን፣ ካሪዮን ከ19 ዓመታት በላይ MCPS የአውቶቡስ ሹፌር በመሆን አገልግሏል። ለዓመታት ከተማሪዎች ጋር የመሰረተው ትስስር ዘላቂ እና ጥልቅ ነው። የካርዮን ርህራሄ የመጣው ከግል ጉዞው እና ከባህላዊ ግንዱ ነው።
ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
በዲጂታል አለም ውስጥ የቤተሰብዎን ደህንነት ይጠብቁ
የትምህርት ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት በኦክቶበር እና በኖቬምበር መጀመሪያ ላይ ሀሙስ፣ 6-7 ፒ.ኤም ነፃ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ዌቢናር ተከታታይ ፕሮግራም ያቀርባል። በዲጂታል አለም የቤተሰብዎን ደህንነት ለመጠበቅ ቀላል እና ጠቃሚ ስልቶችን ይማሩ።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
|
አሁን ያውቃሉ፡ የእግረኛ ደህንነት
ወደ ትምህርት ቤት፣ ወደ አውቶቡስ ፌርማታ፣ ወይም በከተማ አካባቢ፣በእግር የሚጓዙ ከሆነ እዚህ ራስዎን ለመጠበቅ የሚረዳዎት ሰባት ቀላል ምክሮች አሉ። ያስታውሱ፦ ንቁ መሆን አለብዎት፣ ግራና ቀኝ ሁለቱንም በኩል መንገዶችን መመልከት እና መንገድ በሚያቋርጡበት ጊዜ ስልክዎን እንዳያዩ ማስወገድ እርስዎን ከአደጋ ይጠብቃል።
Watch in Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
|
|
|
EdTalk: Making Space for Art Premieres Oct. 10
አዲሱ EdTalk ክፍል፣ የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ጁሊ ያንግ በግሌንስቶን ሙዚየም የማህበረሰብ ተሳትፎ ስራ አስኪያጅ ፍራንሲስካ ሞራጋ ሎፔዝ እና በኢማጊኔሽን ስቴጅ ዋና የስነ ጥበባት ፕሮግራሚንግ ኦፊሰር ጆአን ላምፓርተር በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለኪነጥበብ “ቦታ” መስጠት እና ከባህላዊ የምህርት ክፍለጊዜ ውጪ ለተማሪዎች ጥበባትን የመዳሰስ አስፈላጊነት ላይ ውይይት አድርገዋል። ትዕይንቱ በፖድካስት የሚተላለፍ ስለሆነ አርብ፣ ኦክቶበር 10 ከቀኑ 12:01 a.m. ላይ (በዚህ ሊንክ) ይመለከቷል።
|
|
|
ቤተሰቦች፡ ሕገ መንግሥታዊ መብታችሁን እወቁ
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ሁሉም ልጅ - የስደት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን - ተቀባይነት ያለው፣ የሚከበርበት፣ ሰብአዊ ክብሩ የተረጋገጠበት፣የሚከበርበት እና የሚወደድበት ቦታዎች ናቸው እና በዚህ መርኅ ይቀጥላሉ። ዲስትሪክቱ ቀጣይነት ባለው ቁርጠኝነት ሁሉም ቤተሰቦች ደህንነት እና ድጋፍ እንዲሰማቸው ለማድረግ፣ MCPS ለቤተሰቦች የተለያዩየስደተኞች ድጋፎች እና ሪሶርሶች/መገልገያዎች አሉት።
ህገመንግስታዊ መብትዎን እወቁ
|
|
|
መጀመሪያ ተዘጋጅ የተሰኘ ፖድካስት በኦንላይን ብዝበዛ ላይ ያተኩራል/First PREPARE Podcast Focuses on Online Exploitation
የፖድካስት ማንቂያ ደወል/Podcast alert! የሜሪላንድ የትምህርት ቤት ደህንነት ማእከል (MCSS) PREPARE ፖድካስት የመጀመሪያውን ክፍል በኦንላይን ስለሚደረግ ብዝበዛ ከቲም እና ታሚያ ውድስ ጋር Do It for James Foundation ጀምሯል። PREPARE ፖድካስት የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ መፍትሄዎችን፣ ምርጥ ልምዶችን፣ እና እውነተኛ ታሪኮችን ያጋራል።እዚህ አድምጡ/Listen.
|
|
|
ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
-
Omega Psi Phi Achievement Week ፕሮግራም የስኮላርሺፕ ማመልከቻዎችን ለማቅረብ ክፍት ነው። ፕሮግራሙ ለጥቁር አሜሪካውያን የህይወት ኑሮን ለማሻሻል አስተዋጾ ላደረጉ አፍሪካዊ አሜሪካዊ ወንድ ሲንየር ተማሪዎች ክፍት ነው። ማመልከቻ እዚህ ይገኛል። ማመልከቻው መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ኦክቶበር 24 ነው። ይህ ውድድር ከስኮላርሺፕ ሽልማቶች ጋር የድርሰት ፅሁፍ ውድድርንም ያካትታል። የድርሰት ጽሑፍ የሚቀርብበት ቀነገደብ ዓርብ፣ ኦክቶበር 31 ነው። ተጨማሪ መረጃ
-
2026 Regeneron Science Talent Searchማመልከቻ ለማቅረብ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች አሁን ክፍት ነው። የሀገሪቱ አንጋፋ STEM ውድድር ሲንየር ተማሪዎች የወደፊቱ ከፍተኛ የሳይንስ ተማሪ ተብለው ለመሰየም እና $250,000 ዶላር ከፍተኛ ሽልማት እንዲያሸንፉ ለማበረታታት ኦሪጅናል የምርምር ውጤት እንዲያቀርቡ ይጋብዛል። በኦንላይን የሚቀርብ ማመልከቻ ድርሰቶችን፣ ስለተማሪዎች እና ስለ ምርምራቸው ጥያቄዎችን፣ ከመምህራን እና ከአማካሪዎቻቸው የተሰጡ አስተያየቶችን፣ እና ዋናውን የጥናት ወረቀት ማካተት አለበት። የመጨረሻው ቀን ሐሙስ፣ ኖቬምበር 6 ነው።
-
ይናገሩ፣ ህይወትን ያድኑ፡ Montgomery County State's Attorney's Office ታዳጊዎች የኦፒዮይድ አላግባብ መጠቀምን ወይም ከመጠን በላይ መውሰድ እና በታዳጊ ወጣቶች መካከል ያለውን የፈንታኒል አደጋ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታዳጊዎች ኦሪጅናል ቪዲዮ ፈጥረው እንዲያዘጋጁ ለህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያ የሚቀርብ ውድድር ያስተናግዳል። በውድድሩ በመሳተፍ 10 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ለሚችሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ክፍት ነው። የሚቀርብበት ቀን እሁድ፣ዲሴምበር 7 ነው።
|
|
|
|
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛ በአሥር (10) የመዝናኛ ማእከሎች “የክለብ መዝናኛዎችን” አዘጋጅቷል
አዲሱ የትምህርት አመት በተጠናከረ ሁኔታ እየቀጠለ ነው፣ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛ ማዕከል ተማሪዎች ንቁ፣ ማህበራዊ፣ እና ከክፍል ውጪ ለሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች እየረዳቸው ነው። ታዋቂው "ክለብ አድቬንቸር/Club Adventure" ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም በ 10 የካውንቲ የመዝናኛ ማእከላት ይካሄዳል። ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጀ መርሃ ግብር ስለሆነ በአስተማማኝ እና ምቹ የልጆች መዝናኛ አካባቢ በወር $75 በመክፈል የአዋቂዎች ክትትል የሚደረግላቸው እንቅስቃሴዎችን ያካሄዳል።ለምዝገባ ይህን በይነመረብ ይጠቀሙ፦ ActiveMONTGOMERY
|
|
|
የኪድ ሙዚየም ትምህርት ቤቶች ዝግ በሚሆኑበት ጊዜ "KID Museum" አለልዎት
KID ሙዚየም ትምህርት ቤቶች በሚዘጉበት ቀናት ካምፖች አሉት። የቀን ካምፖች ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 5ኛ ክፍል ተማሪዎች አርብ፣ ኦክቶበር 17 እና ሰኞ፣ ኦክቶበር 20. ከጠዋት 9 am. እስከ 4 p.m ክፍት ናቸው። ኪድ ሙዚየም/KID Museum የሚገኝበት አድራሻ፦ 3 Bethesda Metro Center in Bethesda. ለመሣተፍ ክፍያ ይኖራል።።በተጨማሪ ተማሩና ኣመልክቱ።
|
|
|
ግንኙነትዎ ይቀጥል
|
|
ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
|
|