አበይት ጉዳዮች
ኦክቶበር 30, 2025
|
|
|
|
የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ፤ትምህርት ቤትዎን ለማሻሻል ያግዙ!
MCPS በትምህርት፣ በኮሙኒኬሽን ሁኔታ፣ እና በትምህርት ቤት እና በዲስትሪክቱ ስላላቸው አጠቃላይ እርካታ ልምዳቸውን እና ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ ወላጆችን/ተንከባካቢዎችን ይጋብዛል። የትምህርት አሰጣታችንን በማሻሻል እና ትምህርት ቤቶቻችን እና ዲስትሪክታችን ለሁሉም ተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች የበለጠ ተቀባይነት ያለው ቦታ እንዲሆን ማድረግ እንፈልጋለን።
የዳሰሳ ጥናቶቹ አሁን በሚከተሉት ስምንት ቋንቋዎች ይገኛሉ፦
English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese |አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
የዳሰሳ ጥናቱ የልጅዎን የተማሪ መታወቂያ ቁጥር ይጠይቃል። የልጅዎን መታወቂያ ቁጥር ParentVue ከፍተው የተማሪ መረጃ ላይ ጠቅ በማድረግ ማግኘት ይችላሉ። የሚሰጡት ምላሽ በሚስጥራዊነት ይጠበቃል፤የተማሪ መታወቂያው የሚያስፈልግበት ምክንያት ምላሾቹን ከትክክለኛው ትምህርት ቤት ጋር የሚገናኙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳናል።
|
|
|
በዚህ የሣምንት መጨረሻ ሠዓትዎን ወደኋላ መመለስ እንዳይረሱ!
ወደ መደበኛ ሰዓት ስለምንመለስ፣ በዚህ እሁድ፣ ኖቨምበር 2 ሰዓትዎን አንድ ሰዓት ወደኋላ መመለስ እንዳለብዎት አይርሱ። አጭር ቀናት እና ጨለማ ምሽቶች ስለሚሆኑ፣ ንቁ መሆን እና ደህንነትን መጠበቅ አስፈላጊ ነው።
ስለ ደህንነት ማሳሰቢያዎች፦
-
በመንገድ ላይ ንቁ ይሁኑ፥ እና እግረኞችን እና ብስክሌተኞችን ይጠንቀቁ።
-
የመኪናዎ የፊት መብራቶች በትክክል መሥራታቸውን ያረጋግጡ።
-
የጭስ መውጫዎች እና የካርቦን ሞኖክሳይድ ማስጠንቀቂያዎችን ይፈትሹ፤ አስፈላጊ ከሆነ ባትሪዎችን መተካት አለብዎት።
የሠዓት ጊዜ ለውጥ በሚደረግበት ወቅት ደህንነትን ስለመጠበቅ ተጨማሪ ምክሮችን ለማግኘት የሚከተለውን ይጎብኙ፦
|
|
|
አሁን ማወቅ ያለብዎት፦ ስለ አደንዛዥ እፅ መከላከል
አንዳንድ ጊዜ ወላጆች አስቸጋሪ ውይይቶችን ማድረግ ያስፈልጋቸዋል…
ከአደንዛዥ ዕፅ፣ ከአልኮልና፣ ከትምባሆ ነፃ ሆኖ ለመኖር መምረጥ አንድ ወጣት ሊያደርጋቸው ከሚችላቸው ምርጥ ውሳኔዎች አንዱ ነው። እነዚህ አደንዛዥ ንጥረ ነገሮች …
-
ጤናን ይጎዳሉ።
-
ሚዛናዊነትን ያዛባል።
-
ሙሉ አቅምን ከማሳካት ይከለክላል።
ወላጆች፣ ውይይት ማድረጋችሁን ቀጥሉ፣ ከልጆቻችሁ ወደፊት የሚጠበቅባቸውን በግልጽ አስቀምጡ እና ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ስጡ።
ይበልጥ ያንብቡ።
Watch in Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
|
|
|
የካፒታል በጀት የማህበረሰብ ውይይት መድረኮች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች ተዘጋጅተዋል።
ለበጀት ዓመት (FY) 2027 የካፒታል በጀት እና FY 2027-2032 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) በስድስት ዓመታት ውስጥ $2.7 ቢሊዮን ዶላር ተጠይቋል። ሆኖም ግን፣ የተጠየቀው የበጀት መጠን የዲስትሪክቱ መገልገያዎች ከሚፈልጉት ወጪ ውስጥ ግማሽ ያህሉን ብቻ ይሸፍናል። በመጪዎቹ የሕዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች ይቀላቀሉን።
|
|
|
ኖቨምበር 8 የሚከበረው የአእምሮ ጤና እና ደህንነት አውደ ርዕይ እንዳያመልጥዎት!
MCPS ኖቨምበር 3-8 በሚካሄደው 2025 የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት (MHAW) ላይ ይሳተፋል። ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 8 ከጠዋቱ 10 a.m.-2 p.m. በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚካሄደው የአእምሮ ጤና እና ደህንነት አውደርዕይ እንዳያመልጥዎት።
አድራሻ፦ Gaithersburg High School, 101 Education Blvd /in Gaithersburg። ይህ የነፃ ዝግጅት ለሰራተኞች፣ ለተማሪዎች፣እና ለቤተሰቦች ክፍት ነው፣ አውደ ጥናቶችን፣ የማህበረሰብ አጋሮች ስለአይምሮ ጤና እና ደህንነት የሚያጋሩትን መረጃዎች፣ የተማሪዎች መድረክ፣ እና ዳንስ፣ ዙምባ እና ዮጋ ያካትታል። RSVP/ለመሳተፍ ይመዝገቡ.
|
|
|
ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት ማበልጸጊያ እድሎች መኖራቸውን ይወቁ።
በኖቬምበር እና ዲሰምበር ወር፣ የተፋጠነ እና የበለፀገ ትምህርት ቢሮ ቤተሰቦች ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የትምህርት ማበልጸጊያ እድሎችን እንዲያውቁ ለመርዳት አራት ክፍሎች ያሉት ተከታታይ የዌቢናር ዝግጅት ያካሄዳል። ቤተሰቦች እንዴት እንደሚሰራ በተሻለ ሁኔታ እንዲያውቁ ለመርዳት የባለተሰጥኦ እና ጎበዝ ተማሪዎችን የመለየት ሂደት በሌላ ክፍለ ጊዜ ይካሄዳል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
|
|
|
MCPS አውቶቡስ መንዳት ይፈልጋሉ?
MCPS ሐሙስ፣ ኖቨምበር 13 ከጠዋቱ 10:30 a.m.-12:30 p.m. የአውቶቡስ አሽከርካሪዎችን እና ረዳቶችን ለመቅጠር የሥራ አውደ ርዕይ አዘጋጅቷል። አውደ ርዕዩ የሚካሄደው በሮክቪል በሚገኘው የመጓጓዣ አገልግሎቶች ዲቪዚዮን (DOTS) በሚከተለው አድራሻ ነው፦ Division of Transportation Services (DOTS), 16651 Crabbs Branch Way in Rockville ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-740-6080 ይደውሉ። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
እዚያው በቦታው የሚከናወኑ የመግቢያ ዝግጅት እና የፋይናንስ እርዳታ "Financial Aid" አውደ ጥናቶች
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪዎች ረቡዕ፣ ኖቨምበር 5 እና ሐሙስ፣ ኖቨምበር 6 ላይ ከበርካታ የሜሪላንድ ኢንድፐንደንት ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቦታው በሚደረግ የኮሌጅ መግቢያ ዝግጅት ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ተማሪዎች ለመመዝገብ የትምህርት ቤታቸውን የኮሌጅ እና የሙያ ስራ አማካሪ እንዲያነጋግሩ ይጠየቃሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
በተጨማሪም፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች ለኮሌጅ የትምህርት ክፍያ የሚያግዙ አማራጮችን እንዲያውቁ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የገንዘብ ድጋፍ አውደ ጥናቶችን/financial aid workshops እያዘጋጁ ናቸው። ወላጆች በማንኛውም ትምህርት ቤት በመገኘት በፋይናንስ አውደ ጥናት ላይ መሳተፍ ይችላሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
|
|
|
ስሚዝ ሴንተር ኖቨምበር 15 የማህበረሰብ አገልግሎት ቀን ያስተናግዳል።
"The Lathrop E. Smith Environmental Education Center’s (Smith Center)" የላትዝሮፕ ኢ. ስሚዝ የአካባቢ ትምህርት ማዕከል (ስሚዝ ሴንተር) አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ቀን ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 15 ከጠዋቱ 9 a.m.-1 p.m. ይካሄዳል። ለረጅም ጊዜ የስሚዝ ማዕከል ደጋፊ እና አስተዋፅዖ አበርካች ለሆነችው ሜሪ ሃዋርድ የተሰየመው ይህ ቀን አዋቂዎች እና ቤተሰቦች MCPS ሰራተኞች እና ወዳጆች በመተባበር ማዕከሉን ለማሻሻል እድል ይሰጣል። ቀለም መቀባት፣ የማገዶ እንጨት ርብራብ ማዘጋጀት፣ እና ለተማሪዎች የመዝናኛ እድሎችን ማስፋትን ጨምሮ የተለያዩ የክህሎት ተግባራት ይኖራሉ። የሚሳተፉ ተማሪዎች የአገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፣ ነገር ግን ከአዋቂ ሰው ጋር መሆን አለባቸው። ይመዝገቡ/RSVP.
|
|
|
የዊንተር (የክረምት) ጃኬት እርዳታ በመሰብሰብ ላይ ነው
የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድ ስታርት ቢሮዎች ለተቸገሩ ተማሪዎች አዳዲስ ጃኬቶችን እንዲለግሱ እየጠየቁ ነው። ለትናንሽ ልጆች ኮፍያ፣ ጓንት፣ እና ቦት ጫማዎች ያስፈልጋቸዋል። መጠናቸው 4፣ 5፣ እና 6 የሆነ የወንዶች እና የሴቶች ጃኬት ልብስ ልገሳ በጣም ያስፈልጋል። የተጠቆሙ ጃኬት ልብሶች Head Start/Pre-K Amazon wish list ላይ ሊገኙ ይችላሉ።
የጃኬት ልብሶቹን በዚህ አድራሻ መላክ ይቻላል፦ Rocking Horse Road Center, 4910 Macon Road, Room 141 in Rockville. እቃዎቹ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 9 a.m.–5 p.m., በአካል ማድረስ ወይም በኦንላይን ማዘዝ እና በቀጥታ ወደ ሮኪንግ ሆርስ ሮድ ሴንተር " Rocking Horse Road Center" በማምጣትለሊሳ ኮሎንማስረከብ ይችላል።
|
|
|
ባህል እና ማህበረሰብን መዘከር
አመታዊው የላቲን ዳንስ ውድድር ሰኞ፣ ኖቨምበር 24 ከቀኑ 7 p.m. ላይ በስትራትሞር የሙዚቃ ማዕከል ይካሄዳል። ይህ ታዋቂ ዝግጅት የላቲን ጭፈራዎችን የሚያቀርቡ በርካታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዳንስ ቡድኖችን ያካትታል። የቲኬቶች ዋጋ $15 ዶላር ሲሆን ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 1 ላይ ለሽያጭ ይቀርባል።
|
|
|
ትምህርት ቤቶቻችንን ማጠናከር፦ የበፊት ዳራ መፈተሽ እና የመለያ ባጅ ማሻሻል
MCPS ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ መስጠቱን ሲቀጥል የዳራ ፍተሻ፣ የጣት አሻራ፣ እና ባጅ በማጣራት ረገድ ወደፊት እየገሰገሰ ነው። ባለፈው ሳምንት፣ ቡድናችን የቤቴስዳ-ቼቪ ቼዝ ትምህርት ቤቶችን ክላስተር ጎብኝቷል፣ እና MCPS ሂደቱን እስከ ዲሰምበር አጋማሽ ድረስ ለማጠናቀቅ ትክክለኛ መንገድ ላይ እንደሚገኝ ተመልክተናል። ከዚህ በታች በድጋሚ ማጣራት የተደረገላቸውን ሰራተኞች ብዛት የሚያመለክት የእስካሁን አፈጻጸማችንን ይመለከቷል።
ሜትሪክ/Metric |
ቫልዩ/Value |
እስከ ዛሬ እንደገና ማጣራት የተደረገላቸው ጠቅላላ ሠራተኞ ብዛት |
4,903 |
% የተጠናቀቀ የትምህርት ቤት ሠራተኞች |
46% |
# የተጠናቀቀ የትምህርት ቤቶች ብዛት |
117/211 |
|
|
ማሳሰቢያ
-
የሳይበር ደህንነት ዌቢናሮች፦ ኦክቶበር 30 እና ኖቨምበር 6 ከሠዓት በኋላ 6-7 p.m. በመሳተፍ ስለ ቤተሰብዎ ደህንነቱ የተጠበቀ የኦንላይን አጠቃቀም የበለጠ ይወቁ።
-
የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የክረምት/ዊንተር አትሌቲክስ፦ ምዝገባ አሁን ክፍት ስለሆነParentVue ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ያገኛሉ። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስፖርት የወንዶች እና የሴቶች ቅርጫት ኳስ ያካትታል።
-
ከቤት ውጭ የሚሰጥ ትምህርት ያግዙ!: ከቤት ውጪ የሚካሄድ የስድስተኛ ክፍል ፕሮግራም ላይ የሚያግዙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ይፈለጋሉ። ተጨማሪ መረጃ
-
"Choose Respect Video Contest"/አክብሮትን መምረጥ የቪዲዮ ውድድር ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው፣ ይህ ውድድር ታዳጊዎች በወጣቶች መካከል ስለ ፍቅር ጓደኝነት ጥቃት ግንዛቤ ለማዳበር የሚረዳ ኦሪጅናል ቪዲዮ እንዲፈጥሩ ያበረታታል። ቪዲዮዎቹ በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ሊሆኑ ይችላሉ፤ እና 50-70 ሰከንድ ርዝመት ሊኖራቸው ይገባል። ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ያስገኛል። የመጨረሻው ቀነገደብ እሁድ፣ ፌብሩዋሪ 15, 2026 ነው።
-
በግልጽ ይናገሩ፤ ሕይወት ያድኑ፦ በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች የኦፒዮይድ/ፌንታኒል አላግባብ መጠቀምን እና ከመጠን በላይ የመውሰድን አደጋዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ኦሪጅናል ቪዲዮ በመፍጠር ሕይወት አድን ትምህርት ሰጪ የሆነ ማስገንዘቢያ ያቅርቡ። የመጨረሻው ቀን እሑድ፣ ዲሰምበር 7 ነው።
-
BOLT Leadership Academy ቦልት የአመራር አካዳሚ፦ ይህ ፕሮግራም የአመራር አቅማቸውን በማዳበር እና የአስተዳደር ክህሎት ለማጠናከር ለሚፈልጉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች እና ሶፎሞር ተማሪዎች ክፍት ነው።
-
በጥንካሬ ራስን መከላከል፦ ይህ ዝግጅት MoCo EmpowHER አማካይነት የተዘጋጀ ሲሆን ስለ ደህንነት፣ በራስ መተማመን፣ እና ራስን የመከላከል ግንዛቤ መስጠት ላይ ያተኮረ ነው። ይመዝገቡ/Register.
|
|
|
|
Gobble፣ Gobble፣ Join the YMCA B-CC Turkey Chase
ሐሙስ፣ኖቨምበር 27 ወይም ኖቨምበር 24-30 በሚካሄደው ቨርቹዋል YMCA Bethesda-Chevy Chase እና Bethesda Chevy Chase Rotary ስፖንሰር በሚደረገው 43ኛው አመታዊ "Turkey Chase Charity Race"ውድድር ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን እና የማህበረሰብ አጋሮችን እንዲቀላቀሉ ተጋብዘዋል። ከዝግጅቱ የሚገኘው ገቢ ለሠመር ካምፕ የሚሰጥ የትምህርት ዕድል፣ ለወጣቶች ፕሮግራሞች ተደራሽነት፣ ለአረጋውያን የጤና አገልግሎት መስጠት እና በደርዘን የሚቆጠሩ የአካባቢው ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል። እንዴት እንደሚሳተፉ የርስዎ ምርጫ ቢሆንም፣ ሁሉም ሰው የዚህ ማህበረሰብ ባህል አካል በመሆን እና በመሮጥ፣ በመራመድ፣ በመዋኘት፣ ወይም ብስክሌት በመንዳት እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ ይችላል! ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ። |
|
|
በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
-
ግንኙነቶችን መገንባት እና የሙያ ፈለጎችን መገንባት፦ 170 በላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ኮሌጅ የጀርመንታውን ካምፓስ አመታዊ የወጣቶች አመራር ጉባኤ ላይ ተሰብስበው ነበር፤ በዚህም ቀን በመማር፣ በአመራር እና በግንኙነት ላይ ያተኮረ ዝግጅት ተካሄዷል።
-
የከበሮ ድምፅና/የእንቅስቃሴ አወራረድ፡- ኦክቶበር 25 አስራ ሁለት የሙዚቃ ባንዶች በዚህ አመት በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው የሙዚቃ ማርች ባንድ ትርኢት ላይ ተሳትፈዋል።
-
"Big Bows and High Toes"፡- ኦክቶበር 25 በተካሄደው 37ኛው አመታዊ የቺርሊዲንግ ውድድር ላይ ከ 25 የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ቡድኖች አስደናቂ የሆኑ ዝግጅቶችን አቅርበዋል።
-
ከርዕሰ መምህሩ ዴስክ፡ "የሚያደርጉትን ነገር ለምን እንደሚወዱ"፡ኦክቶበር ብሔራዊ የርዕሰ መምህራን ወር ነው! የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ርእሰ መምህራን ስለ ርዕሰ መምህርነት ሥራቸው የሚወዱትን ነገር እንዲያካፍሉን ጠይቀናቸው—ምን እንደሚሉ እነሆ።
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
|
|