የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ መለያ አርማ

ኖቨምበር 6, 2025

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

የመጀመሪያውን ሩብ አመት መዝግበናል— ወደ ሁለተኛው ሩብ አመት ደርሰናል!

ፈጣኑን 2025-2026 የትምህርት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመትን አጠናቀናል፣ በዚህም ተማሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን በእያንዳንዱ እርምጃ ጠንክረው ሲሰሩ ቆይተዋል። ከክፍል ትምህርት እስከ የማህበረሰብ ተሳትፎ፣ ከዚያም እስከ አትሌቲክስ ሜዳዎች የተለያዩ ዝግጅቶች፣ተማሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን አንፀባራቂ ሆነዋል። ሁለተኛውን ሩብ ዓመት ስንጀምር፣ በዚሁ ፍጥነት ለመቀጠል ጓጉተናል—ምን እንዳሳካን እና ወደፊት ትምህርት ቤቶቻችን ምን እንደሚጠብቃቸው እነሆ! 

ትምህርት ቤቶቻችን በስቴት የሪፖርት ካርድ አመዘጋገብ ላይ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል፤ 95.5% ወይም ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡት ሶስት ኮከቦችን አግኝተዋል።

2035 ላይ ወደ አራት ወይም ከዚያ በላይ ለማስመዝገብ እየተጓዝን ነው።

ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ በተለቀቀው 2024–2025 የሜሪላንድ የትምህርት ቤቶች ሪፖርት ካርድ መሠረት፣ MCPS ጠንካራ የትምህርት እድገት ማሳየቱን ይቀጥላል። በአፈጻጸም ግምገማው ውስጥ ከተካተቱት 200 የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ 95.5% የሚሆኑት ሶስት ኮከቦች ወይም ከዚያ በላይ ደረጃ አግኝተዋል፣ ይህም ከስቴት አቀፍ አማካይ 86% ውጤት በእጅጉ ይበልጣል። በዚህ ዓመት፣ 53.5% የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች 4-ኮከብ ወይም 5-ኮከብ ደረጃ (ከፍተኛውን ደረጃ) አግኝተዋል፣ ይህም 2023-2024 የትምህርት አመት ውጤት ጋር ሲነጻጸር 3.5 በመቶኛ ጠንካራ የተሻለ ውጤት ጭማሪ አሳይቷል። ይበልጥ ያንብቡ።

መግለጫውን ያንብቡ.

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች እድገት እያሳዩ ናቸው፡ የእድገት እና የአስቻይ ሁኔታ ታሪክ

በመላው ካውንቲ ውስጥ፣ ትምህርት ቤቶች MCPS ስትራቴጂካዊ እቅድን ወደ ተግባር እየለወጡ ሲሆን፣ 2035 የትምህርት አመት ላይ ሁሉም ትምህርት ቤቶች 4 ኮከቦች ወይም ከዚያ በላይ እንደሚያስመዘግቡ ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው እየሠሩ ናቸው። በዚህ ዓመት ከተገኙት የስኬት ታሪኮች መካከል የሮዝሞንት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የዊሊያም ኤች. ፋርኳኸር መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይገኙበታል። ሮዝሞንት እና ፋርኳኸር ከሶስት ወደ አራት ኮከቦች ሲሸጋገሩ፣ ዋትኪንስ ሚል ደግሞ ከሁለት ወደ ሶስት ኮከቦች ተሸጋግሯል። ይበልጥ ያንብቡ።

አሁን ማወቅ ያለብዎት፡ ስለ ወላጅ-አስተማሪ ኮንፈረንስ

የወላጅ-መምህር ኮንፈረንሶች ከኖቨምበር 24-25 የሚካሄዱ ሲሆን ከልጅዎ አስተማሪ ጋር ስለ ልጅዎ የትምህርት ሁኔታ - ስለ ትምህርትም ሆነ ስለ ማህበራዊ መስተጋብር ሁኔታ - ለመነጋገር ጥሩ አጋጣሚ ነው። ለመዘጋጀት እንዲረዳዎት መጠየቅ የሚችሏቸውን ጥያቄዎች እና ምክሮችን ለማግኘት በተጨማሪ ያንብቡ። 

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

የሪፖርት ካርዶች ኖቨምበር 7 ይወጣሉ

ለመጀመሪያው የማርክ መስጫ ወቅት የሪፖርት ካርዶች ParentVueላይ ኖቨምበር 7 ከቀኑ 5 p.m. ላይ ይወጣሉ።

ParentVue ላይ የሪፖርት ካርዶችን እና የአሁን የትምህርት ግስጋሴን ሁኔታ ለማወቅ ደረጃ በደረጃ ማድረግ ያለብዎት አቅጣጫ እነሆ። ለመጀመሪያዎቹ ሶስት የማርክ መስጫ ወቅቶች የሪፖርት ካርዶች ከሁሉም ተማሪዎች ጋር ወደ ቤት ይላካሉ፤ የአመቱ የመጨረሻ ሪፖርት ካርድ ወደ ተማሪዎች ቤት በፖስታ ይላካል። በመጀመሪያው ሩብ ዓመት፣ ወላጆች የሪፖርት ካርዶችን እስከ ኖቨምበር 12 ድረስ እንደሚደርሳቸው መጠበቅ ይችላሉ። ተጨማሪ ያንብቡ።

አስፈላጊ ማሳሰቢያ፦ የአየር ንብረት ሁኔታ ዛሬውኑ ቅኝት ያድርጉ እና ትምህርት ቤትዎን ያሻሽሉ!

MCPS በትምህርት፣ በኮሙኒኬሽን ሁኔታ፣ እና በትምህርት ቤት እና በዲስትሪክቱ ስላላቸው አጠቃላይ እርካታ ልምዳቸውን እና ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ ወላጆችን/ተንከባካቢዎችን ይጋብዛል። የትምህርት አሰጣታችንን በማሻሻል እና ትምህርት ቤቶቻችን እና ዲስትሪክታችን ለሁሉም ተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች የበለጠ ተቀባይነት ያለው ቦታ እንዲሆን ማድረግ እንፈልጋለን። 

የዳሰሳ ጥናቶቹ አሁን በሚከተሉት ስምንት ቋንቋዎች ይገኛሉ፦
English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese |አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

የዳሰሳ ጥናቱ የልጅዎን የተማሪ መታወቂያ ቁጥር ይጠይቃል። የልጅዎን መታወቂያ ቁጥር ParentVue ከፍተው የተማሪ መረጃ ላይ ጠቅ በማድረግ ማግኘት ይችላሉ። የሚሰጡት ምላሽ በሚስጥራዊነት ይጠበቃል፤የተማሪ መታወቂያው የሚያስፈልግበት ምክንያት ምላሾቹን ከትክክለኛው ትምህርት ቤት ጋር የሚገናኙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳናል።

MCPS የትምህርት ቤቶችን ስኬት የሚደግፉ የተሻጋሪ ተግባራት ቡድኖች

እያንዳንዱ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ የራሱ ጥንካሬዎችና ተግዳሮቶች አሉት፣ እና ለሁሉም የሚስማማ አንድ አይነት መፍትሔ የለም። ለዚህም ነው ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር MCPS ተሻጋሪ-ተግባራዊ ቡድኖችን ያስጀመሩት፦ በትምህርት ቤቶች ላይ ያተኮሩ የትምህርት አቀራረብ ሁኔታዎችና ዓይነቶችን የሚመለከቱ ባለሙያዎችን ያቀፈ ቡድን ሲሆን፤ ከትምህርት ቤቶች እና ክለስተሮች ጋር በቀጥታ አብረው በመሥራት ማስተማርን፣ መማርን፣ እና የትምህርት ቤት ስራዎችን ለማራመድ እና ለማጠናከር የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣሉ።

እነዚህ ቡድኖች በአመራር፣ በፍትሃዊነት፣ በልዩ ትምህርት፣ በብዝሃ ቋንቋ ትምህርት፣ በሊተርሲ፣ በሂሳብ፣ በሰው ኃይልና በደህንነት ዘርፍ ልዩ ባለሙያዎችን ያካትታሉ። ይህንን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ እነዚህ የትብብር ቡድኖች ትምህርት ቤቶች ጠንካራ የድጋፍ ስርዓቶችን እንዲገነቡ እና በዲስትሪክቱ ውስጥ ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲፈጥሩ እንዴት እየረዱ እንደሆነ ለማየት ከዚህ ጋር የቀረበውን ቪድዮ ይመለከቷል።

የትምህርት ቤት ማሻሻያ እቅዶችን አሁን በኦንላይን ያገኛሉ።

የትምህርት ቤት ማሻሻያ ዕቅዶች (SIPs) እድገትን ለመከታተል፣ ትምህርትን ለማጠናከር፣ እና ለሁሉም ተማሪዎች ውጤቶቻቸውን ለማሻሻል ትኩረት የተደረገባቸው፣ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ፍኖተ ካርታዎች ናቸው። ትምህርት ቤቶች በጣም አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ እንዲያተኩሩ የሚያደርጉ የማሰላሰል፣ የትብብር፣ እና የእድገት መሳሪያዎች ናቸው፤ ይህም እያንዳንዱ ተማሪ በትምህርት እና በእውቀት እንዲበለጽግ የሚረዳ ነው።

ለሁሉም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች SIP አሁን በሶስት ቦታዎች በኦንላይን ይገኛል፦

ይበልጥ ያንብቡ።

የሪፍሪጅሬተር ከሪኩለም "Refrigerator Curriculum" የሁለተኛ ሩብ አመት የትምህርት ማቴሪያሎችን አሁን ማግኘት ይችላሉ።

የሪፍሪጅሬተር ከሪኩለም "Refrigerator Curriculum" — ለሁለተኛው ሩብ ዓመት የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፣ ኖቨምበር 4 ጀምሮ — በኦንላይን ያገኛሉ። ይህ ሥርዓተ ትምህርት ተማሪዎች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ጊዜ ምን እንደሚማሩ የሚያመላክት ባለ አንድ ገጽ አጠቃላይ መግለጫ ነው። እነዚህ መመሪያዎች ቤተሰቦች ስለ ቁልፍ የትምህርት ጭብጦች እና ጽሑፎች እንዲያውቁ፣ በተማሪዎቻቸው ትምህርት ላይ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እና ካስፈለገም ጽሑፉ ከሃይማኖታዊ አመለካከቶች ጋር የሚጋጭ ከሆነ አማራጭ የትምህርት ስራዎችን እንዲጠይቁ ይረዷቸዋል።

ቤተሰቦች፡ መብታችሁን ማወቅ አለባቸው

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ሁሉም ልጅ — የስደት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን — ተቀባይነት ያለው፣ የሚከበርበት፣ ሰብአዊ ክብሩ የሚጠበቅበት፣እና የሚወደድበት ቦታዎች ስለሆኑ በዚህ መርኅ ይቀጥላሉ። የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡ MCPS ለትምህርት ቤት ሰራተኞች መከተል ያለባቸውን ስለ ፕሮቶኮል መመሪያ አሰራጭቷል። ዲስትሪክቱ አሁን ለክለቦች፣ ለሕፃናት እንክብካቤ፣ እና ለአትሌቲክስ የመሳሰሉ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎችን የሚደግፉ ሰራተኞችን እና ሌሎች አዋቂዎችን ለመርዳት ተጨማሪ መመሪያ እየሰጠ ነው። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

የመጀመሪያ ሩብ አመት፦ ጠንካራ ተሳትፎ ነበር — እየተሻሻልንበት እና ምን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አመላካች ነው።

እስከ ሴፕቴምበር 30 ድረስ ያለውን የተማሪዎችን መረጃ በተመለከተ የመጀመሪያው ሪፖርት ተማሪዎች ምን ያህል ጊዜ በትምህርት ቤት እንደሚገኙ እና እንዴት MCPS አዎንታዊ ባህሪን እንደሚደግፍ ጠቋሚ መረጃ ይሰጣል። እነዚህ የመጀመሪያ ውጤቶች የዓመቱን የመጀመሪያዎቹን አምስት ሳምንታት — ወደ 24 የትምህርት ቀናትን — የሚሸፍኑ ሲሆን መበረታታ ያለባቸውን ተግባራት እና አንዳንድ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን ዘርፎች ያመለክታሉ።

በአጠቃላይ፣ MCPS ውስጥ የትምህርት ክትትል ተሳትፎ መጠን 94.9% ጠንካራ ሆኖ ተገኝቷል፣ በአብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶችም የክትትል መጠኑ ያለማቋረጥ እየጨመረ መጥቷል። በተጨማሪ በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት እየተሻሻለ የመጣውን የውሂብ መጠን ያንብቡ።

MCPS የማህበረሰባችንን ታላቅነት ማክበር

እናም ይህ የሚያመለክተው ባለፉት ጥቂት ወራት፣ የተማሪዎቻችንን፣ የሰራተኞቻችንን፣ የትምህርት ቤቶቻችንን እና የአጋሮቻችንን አስደናቂ ስራ ከፍ ማድረጋችንን ነው። ከተግባራዊ ትምህርት እና ዓለም አቀፍ የልምድ ልውውጥ እስከ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ደህንነት፣ ፈጠራ፣ እና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ባለሥልጣናት ጉብኝቶች፣ የእኛን ምርጥ ማንነት ያጎላሉ። የትምህርት ዓመቱን በጠንካራ ሁኔታ እንድንጀምር ያነሳሱንን አንዳንድ ሁኔታዎች ወደ ኋላ መለስ ብለን እንመልከት

SNAP ላይ የተደረጉ ለውጦች የትምህርት ቤት ምግቦችን የሚነካው እንዴት ነው?

"Supplemental Nutrition Assistance Program (SNAP)" ስር በቀጥታ ነፃ ምግብ እንዲያገኙ የተፈቀደላቸው ተማሪዎች 2025-2026 የትምህርት አመት ለቀሪው ጊዜ የምግብ ጥቅማጥቅሞችን ማግኘታቸውን ይቀጥላሉ። አዲስ SNAP ጥቅማጥቅሞችን የማግኘት መብት ያላቸው ተማሪዎች ማመልከቻዎቻቸው ሲጠናቀቁ በዚህ የትምህርት ዓመት ለነፃ የትምህርት ቤት ምግቦች ብቁ ይሆናሉ። ከሥራ የተባረሩ ወላጆች/አሳዳጊዎች ልጆቻቸው ነፃ እና ቅናሽ ዋጋ ያለው ምግብ እንዲያገኙ እዚህ ማመልከት ይችላሉ። ይበልጥ ያንብቡ።

ቦርዱ እስከ ኖቨምበር 10 ድረስ በካፒታል ማሻሻያ ዕቅድ ላይ የህዝብ አስተያየት ይቀበላል

የትምህርት ቦርዱ የማህበረሰብ አባላት በሱፐርኢንቴንደንቱ የቀረበው የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) ላይ አስተያየት እንዲሰጡ እየጋበዘ ነው። እስከ ሰኞ፣ ኖቨምበር 10 እኩለ ቀን ድረስ የሚቀርቡ አስተያየቶች "BoardDocs" ላይ ለሁሉም የቦርድ አባላት እና የአመራር ሰራተኞች ይሰራጫሉ። ቪዲዮ ወይም የጽሑፍ አስተያየቶችን እንዴት ማስገባት እንደሚቻል ተጨማሪ ያንብቡ።

መጪው ስለ ድንበር ጥናት ውይይት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራሞች ትንታኔ ክፍለ ጊዜ እንዳያመልጥዎት ይሳተፉ።

MCPS የማህበረሰቡ አባላት በትምህርት ቤቶች የማካለል ጥናቶች እና በአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትንተና በሚመለከት በተከታታይ በሚደረጉ የተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎች ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል። መቼ እና የት እንደሚካሄዱ ይመልከቱ። 

አስፈላጊነቱ ምንድነው?
የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትንተና ድረ-ገጽ

ኖቨምበር 8 የሚከበረው የአእምሮ ጤና እና ደህንነት አውደ ርዕይ እንዳያመልጥዎት!

MCPS ኖቨምበር 3-8 በሚካሄደው 2025 የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት (MHAW) ላይ ይሳተፋል። ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 8 ከጠዋቱ 10 a.m.-2 p.m. በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚካሄደው የአእምሮ ጤና እና ደህንነት አውደርዕይ እንዳያመልጥዎት። አድራሻ፦ Gaithersburg High School, 101 Education Blvd /in Gaithersburg። ይህ ነፃ ዝግጅት ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ክፍት ሲሆን አውደ ጥናቶችን፣ የማህበረሰብ አጋሮች የሚያጋሩትን ስለ አእምሮ ጤና እና ደህንነት መረጃዎች፣ የተማሪዎች መድረክ እና ዳንስ፣ ዙምባ እና ዮጋን ያካትታል። RSVP/ለመሳተፍ ይመዝገቡ.

ለትምህርት ቤቶቻችን ደህንነት ቅድሚያ መስጠት

ባለፈው ሳምንት፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክክ ስኩልስ (MCPS) ቡድኖች አልበርት አንስታይን፣ ሮክቪል፣ እና ኮ/ል ዛዶክ መግሩደር ትምህርት ቤቶችን ከለስተር ጎብኝተዋል። እስከ ዲሰምበር አጋማሽ ድረስ የሠራተኞችን የበፊት ታሪክ ማጣራት፣ የጣት አሻራ፣ እና የባጅ ሂደትን ለማጠናቀቅ በትክክለኛ መንገድ ላይ እንደሚገኙ ተመልክተዋል። ከዚህ በታች እስካሁን ድረስ ስለተከናወነው ሂደት ወቅታዊ መረጃ ይገኛል፣ ይህም እንደገና ማጣሪያ ያጠናቀቁ ሠራተኞችን ቁጥር የሚያንፀባርቅ ነው።

ሜትሪክ/Metric

ቫልዩ/Value

እስከ ዛሬ እንደገና ማጣራት የተደረገላቸው ጠቅላላ ሠራተኞ ብዛት

5,506

% የተጠናቀቀ የትምህርት ቤት ሠራተኞች

52%

# የተጠናቀቀ የትምህርት ቤቶች ብዛት 

132/211

በተጨማሪም፣ 608 የትራንስፖርት አገልግሎት ዲቪዥን (DOTS) ሰራተኞች ኖቨምበር 3፣ እንደገና ማጣራት የተደረገላቸው ስለሆነ DOTS ሰራተኞች ቁጥር ወደ 54% ደርሷል።

ማሳሰቢያ

  • የካፒታል በጀት፡ የበጀት ዓመት (FY) 2027 የካፒታል በጀት እና 2027–2032 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) ለስድስት ዓመታት $2.7 ቢሊዮን ዶላር ጠይቋል። በመጪዎቹ የሕዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች ይቀላቀሉን። ከኖቬምበር 4 የትምህርት ቦርድ የስራ ክፍለ ጊዜ የተወሰዱትን የውይይት ስላይዶች ይመልከቱ። 

  • ለቤተሰብ የሳይበር ደህንነት፦ በተከታታይ ከሚቀርበው የዌቢናር ውይይት ፕሮግራም የመጨረሻው ሐሙስ፣ ኖቨምበር 6 ከቀኑ 6-7 6-7 p.m. ይካሄዳል።

  • የስራ ቅጥር አውደ ርዕይ፡ የአውቶቡስ ሹፌር ወይም የአውቶቡስ አስተናጋጅ ለመሆን ፍላጎት ያለው ሰው ያውቃሉ? ሐሙስ፣ ኖቨምበር 13 ከጠዋቱ 10:30 a.m.-12:30 p.m. ድረስ ይምጡና ይጎብኙን። አውደ ርዕዩ የሚካሄደው ሮክቪል በሚገኘው የመጓጓዣ አገልግሎት ዲቪዥን (DOTS) መሥሪያ ቤት ነው። አድራሻ፦ Division of Transportation Services (DOTS), 16651 Crabbs Branch Way in Rockville ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-740-6080 ይደውሉ።

  • የስሚዝ ማዕከል የማህበረሰብ አገልግሎት ቀን፡ ይህ ዝግጅት ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 15 ከጠዋቱ 9 a.m.-1 p.m. ይካሄዳል። ቅብ መቀባት፣ የማገዶ እንጨት መፍለጥ እና ተማሪዎችን የሚያዝናኑ እድሎችን ማስፋትን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት ይከናወናሉ። ይመዝገቡ/RSVP

  • የትምህርት ማበልጸጊያ እድሎች፦ የተፋጠነ እና የበለፀገ ትምህርት ቢሮ ቤተሰቦች ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ (K-12ኛ ክፍል) ላሉ ተማሪዎች የትምህርት ማበልጸጊያ እንዲማሩ የሚያግዙ ሁለት ተጨማሪ የበይነመረብ ዌቢናሮች አሉት።

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2025 Montgomery County Public Schools