የክረምት የአየር ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ፡ የማጽዳት ሂደት እና አስፈላጊ ማሳሰቢያዎች
አርብ፣ ጃኑዋሪ 30 ክፍተኛ ቅዝቃዜ ያዘለ ኮዱ ቀይ ስለሆነ– ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ይሆናሉ።
አንዳንድ የህፃናት እንክብካቤ ጣቢያዎች ክፍት ይሆናሉ | የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ተጨምረዋል።
ዕቅድ ለማዘጋጀት ዓላማ፦ MCPS ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 2 ሁለት ሰዓት ዘግይቶ የመክፈት ሁኔታ እንደሚኖርም ይገመታል። ይህንን ሁኔታ በተመለከተ፦ የካውንቲ እና የስቴት ሰራተኞች መንገዶችን ከበረዶ ክምር የማጽዳት ሁኔታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ለሚያደርጉት የእግር ጉዞ አስተማማኝ መሆኑ ሁኔታው ታይቶ ለውጥ ሊደረግ ይችላል። ስለ ሰኞ የሥራ ሁኔታ እሁድ፣ ፌብሩዋሪ 1 ከቀኑ 4 p.m. በኋላ ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃ እናጋራለን።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ ቀደም ብሎ የተጋራውን ሙሉ መልእክት ለማግኘት፣ ይህንን ሊንክ/አገናኝ ይመልከቱ።
አንዳንዶች ለምን ወደ ቨርቹዋል ትምህርት አንሸጋገርም? ብለው ጠይቀዋል
በዚህ ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ቨርቹዋል ትምህርት አንሸጋገርም። MCPS ለእያንዳንዱ ተማሪ አንድ ለ አንድ የርቀት ትምህርት መስጫ መሳሪያዎች የሉትም፣ ይህም የትምህርትን ፍትሃዊ ተደራሽነት ይገድባል። በተጨማሪም፣ በዚህ ጊዜ መዘጋት ብዙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ከአዳዲስ አስተማሪዎች ጋር አዳዲስ ኮርሶችን በሚጀምሩበት አዲስ ሴሚስተር መጀመሪያ ላይ የተገጣጠመ ስለሆነ ለአጭር ጊዜ ወደ ቨርቹዋል ትምህርት የሚደረግ ሽግግር ተግባራዊ የማይሆን እና መሰናክል ይሆናል። በመጨረሻም፣ MCPS በአሁኑ ጊዜ በመንግስት የተፈቀደለት የቨርቹዋል ትምህርት እቅድ የለውም፣ በዚህም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ወደ ቨርቹዋል ትምህርት እንዳንሸጋገር ያደርገናል።

MCPS እሁድ ቀን ከወረደው ከባድ የበረዶ ክምርና የበረዶ ማእበል የማገገሙን እንቅስቃሴ ይቀጥላል። ቡድኖቻችን ያለመታከት እየሰሩ ቢሆንም፣ ቀጣይነት ያለው የቅዝቃዜ ሁኔታ ት/ቤቶችን እና ቢሮዎችን እንደገና ለመክፈት እጅግ በጣም አስቸጋሪ እና ፈታኝ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።
ደህንነት በእኛ በኩል ፍጹም ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንደገና ለመክፈት መንገዶች፣ የአውቶቡስ ማቆሚያዎች፣ የትምህርት ቤት መገልገያዎች እና የእግር ጉዞ መንገዶች ግልጽ እና በቀላሉ ለመንቀሳቀስ ምቹ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብን።
ከፍተኛ የቅዝቃዜ ሁኔታ የተለመደውን የመንገድ መጥረግ ውጤታማነትን ገድቧል፣ ይህም ከተጠረገም በኋላ —በእግረኛ መንገዶች እና በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ላይ እንደገና የሚያዳልጥና አደጋን ያስከትላል። ቅዳሜና እሁድ ላይ የሁኔታውን መሻሻል በቅርበት እንከታተላለን።
ብዙዎቻችን ከቤቶቻችን ባንወጣም፣ የጥገና ቡድኖቻችን የተወሰኑ የመገልገያ መሣሪያዎችን ይዘው ከእሁድ እለት ጀምሮ ውጭ መንገዶችን ለማስተካከል እየታገሉ ናቸው። የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን ከማጽዳት ጀምሮ በእጅ የእግረኛ መንገዶች ላይ ጨው መነስነስ ድረስ፣ ወደ ትምህርት ቤቶቻችን ለመመለስ ደህንነታቸው የተጠበቀና ምቹ እንዲሆን ለማድረግ ያለመታከት እየሰሩ ናቸው። በዚህ ተግባር ጥረት እያደረጉና እየታገሉ ያሉትን ቡድኖቻችንን ከካውንቲ አጋሮቻችን ጋር ከልብ እናመሰግናለን። ማህበረሰባችን ወደ መደበኛ ሁኔታ እንዲመለስ ለማድረግ በዚህ ከባድ የአየር ሁኔታ ውስጥ ሌት ተቀን ጠንክረው ሲሰሩ ቆይተዋል። ይህ ብርቱ ሥራ እየተካሄደ ባለበት ሁኔታ የትምህርት ቤተሰቦች እና ሠራተኞቻችንን ስለሚያሳዩት ትዕግስትና ግንዛቤ እናደንቃለን።
መንገዶችን እና ት/ቤቶችን የማጽዳት ጥረቶችን የፎተግራፍ ክምችት ይመልከቱ፦
የህፃናት እንክብካቤ አቅርቦት
በዚህ ወቅት፣ አንዳንድ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተቋማት የህፃናት እንክብካቤ አገልግሎቶችን በመስጠት ሊደግፉ ይችላሉ። የተደራሽነት ሁኔታው እንደየቦታው ይለያያል፦ በረዶ እና የበረዶ ክምር ማስወገድ፣ ወደ ህንፃው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለመድረስ መቻል፣ የህንጻዎቹ ሲስተሞች ሙሉ በሙሉ በትክክል የመሥራት ሁኔታ፣ እና የሰራተኞች መገኘት፣ MCPS ሰራተኞች እና የልጆች እንክብካቤ አገልግሎት ሰጪው ድርጅት ሰራተኞች የመገኘት ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው። ቤተሰቦች አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥ እና የስራ ሰዓቶችን ሁኔታ ለማረጋገጥ የህፃናት እንክብካቤ አገልግሎት ሰጪዎቻቸውን በቀጥታ ማነጋገር አለባቸው።
|