አበይት ጉዳዮች
ፌብሩዋሪ 5, 2026
|
|
MCPS በቅርቡ በተከሰተው የክረምት የበረዶ ማእበል ምክንያት በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ላሳያችሁት ትዕግስት እና ጽናት ቤተሰቦችን፣ ተማሪዎችን እና ሠራተኞችን ልባዊ ምስጋና ማቅረብ ይፈልጋል። በተለይ ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሕንጻ አገልግሎት ሠራተኞችን፣ አጠቃላይ የጥገና፣ የትራንስፖርት እና የምግብ አገልግሎት ቡድኖችን ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ማመስገን እንፈልጋለን። ወደ መደበኛው ሁኔታ እስክንመለስ የነብረውን ሁኔታ ስለተረዳችሁን እና ታግሳችሁን ስለቆያችሁ እናመሰግናለን።
|
|
|
|
በበረዶ ቀናት የተቋረጡትን የትምህርት ቀናት ስለማካካስ
በቅርቡ በተፈጠረው የክረምት የበረዶ ማዕበል ምክንያት፣ MCPS አራት የትምህርት ቀናትን ማካካስ አለበት። ሁለት ትምህርት-ነክ ያልሆኑ ቀናት ወደ ትምህርት ቀናት ይቀየራሉ፡ አርብ፣ ማርች 20 እና ሐሙስ፣ ጁን 18፣ ይህም ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን እና አዲሱ የትምህርት አመት የመጨረሻ ቀን ይሆናል። ማርች 20 የኢድ አልፈጥር በዓልን የሚያከብሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ለመቅረት ይፈቀድላቸዋል።
ሌሎች የማካካሻ ቀናትም እየታሰቡ ነው፣ ነገር ግን ገና ምንም አይነት ውሳኔ አልተሰጠም። MCPS አንዳንድ የትምህርት ቀናትን ስለ መሰረዝ ለስቴቱ ጥያቄ ያቀርባል። ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እያለ፣ ዲስትሪክቱ የትምህርት ቀናትን የማካካስ እቅዱን ያሻሽላል እና የተሻሻለውን የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ለቤተሰቦች ያጋራል።
|
|
|
አዲስ የማርክ መስጫ ወቅት፣ አዲስ እርምጃ፡ የተማሪዎን ስኬት ይከታተሉ።
ሦስተኛው የማርክ መስጫ ወቅት በይፋ የተጀመረው ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 3 ነው። አዲስ ሴሚስተር ሲጀመር፣ ቤተሰቦች በማርክ መስጫ ወቅት እና በሁለተኛው ሴሚስተር ወቅት ሁሉም ሰው የተማሪዎችን የትምህርት እድገት በተመለከተ ተመሳሳይ ገጽ ላይ እንዲሆን ለማድረግ ግንኙነት የመፍጠር እድል አላቸው። ስለ ጠንካራ ጅምራችን እና ቁልፍ ቀናትን የሚመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት እዚህ ያንብቡ።
|
|
|
ሱፐርኢንቴንደንቱ ስለ ውድዋርድ፣ እና ስለ ውተን የድንበር ጥናት ምክረ ሀሳቦችን አቅርበዋል
የትምህርት ቦርድ ዛሬ (ፌብሩዋሪ 5) ባካሄደው የሥራ ክፍለ ጊዜ፣ ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር ስለ ቻርለስ W. ውድዋርድ እና ቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የወሰን ምክረ ሃሳቦችን አቅርበዋል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
MSDE ለኮሌጅ እና ለስራ ጠቃሚ የሆነ የሂሳብ ትምህርትን እንዴት እያጠናከረ እንደሆን?
የትምህርት ቦርዱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ (ፌብሩዋሪ 5) በሚያካሂደው የሥራ ክፍለ ጊዜ ስለ ሂሳብ ትምህርት ፖሊሲ እና ተግባር ይወያያል። በእርግጠኛነት ይመልከቱ። የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ ተማሪዎች ለኮሌጅ እና ለሙያ እንዴት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው የሚያስገነዝብ የሂሳብ ትምህርት ፖሊሲ አውጥቷል። አንደኛው ክፍል ተማሪዎች በየዓመቱ ማወቅ የሚያስፈልጋቸውን ከቅድመ መዋእለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል (PreK-8) የሂሳብ ትምህርት ደረጃ መስፈርት ያመለክታል። ዛሬ ማታ ከቀኑ 6:30-7:45 p.m. በሚደረገው ዙም ስብሰባ (Zoom meeting) ላይ የበለጠ ለማወቅ ተጨማሪ መረጃያግኙ፦
|
|
|
የጥቁሮች ታሪክ ወር መዘከሪያ
በጥቁሮች ታሪክ መዘከሪያ ወር የትምህርት ቦርድ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጥቁሮችን ታሪክ ኃይል፣ ጽናት፣ እና ዘላቂ ተሻጋሪነትን እውቅና በመስጠት ሲያከብር ኩራት ይሰማዋል። ትምህርት፣ አመራር፣ እና ማህበረሰብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰባሰቡት ፖቶማክ በሚገኘው የስኮትላንድ ጽዮን ቤተክርስቲያን "Scotland A.M.E. Zion Church" ሲሆን በዚህ ቦታ ላይ የትምህርት ዕድል መሰረት ተጥሏል። ተጨማሪ ያንብቡ እና አባቶች ያስተጋቡትን ድምፅ ይመልከቱ።
እንዲሁም፣ የአርጋይል መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ጄምስ አልሪች "principal James Allrich of Argyle Middle School" ስለ ታሪክ ተወራሽነት፣ ስለ አመራር፣ እና አገልግሎት ያቀረቡትን በተጨማሪ ይመልከቱ።
|
|
|
በሠመር ወቅት ጉዞ ለማድረግ አቅደዋል? የመኸር (ፎል) የስፖርት ልምምዶች የሚጀምሩት ኦገስት 12 አካባቢ ነው
የሙቀት መጠኑ አጥንት ውስጥ የሚገባ ቅዝቃዜ ቢኖረውም፣ አንዳንዶች ስለ ሠመር ዕረፍት ጊዜ ማቀድ ጀምረዋል! የመኸር (ፎል) የስፖርት ልምምዶች ረቡዕ፣ ኦገስት 12 ሊጀምሩ እንደሚችሉ ያስታውሱ። ልምምዶች ከተጀመሩ በኋላ ቡድኖች ከሰኞ እስከ ቅዳሜ እስከ ወቅቱ መጨረሻ ድረስ ወጥ የሆነ ልምምድ ማድረግ ይችላሉ። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
አሁን ማወቅ ያለብዎት፦ ስለ ተማሪ አገልግሎት ትምህርት
በሜሪላንድ ተማሪዎች ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት እንደሚያስፈልጋቸው ያውቃሉ? የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት ኃላፊነትን፣ በቡድን መሥራትን፣ እና አመራርን የመሳሰሉ ክህሎቶችን ለመገንባት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ ነው። ተማሪዎች ከአምስተኛ ክፍል በኋላ በሠመር ወቅት ከተፈቀደላቸው ድርጅቶች ጋር በፈቃደኝነት በመሥራት ወይም በትምህርት ቤት በሚካሄዱ ተግባራት ላይ አገልግሎት ለመስጠት በመሳተፍ የተማሪ አገልግሎት ሰዓት ማጠራቀም መጀመር ይችላሉ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
|
|
|
|
|
ማሳሰቢያ
|
|
|
|
|
ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
-
MoComCon 2026፦ MoComCon የስነጥበብ ውድድር ላይ በመሳተፍ የጥበብ አድናቂነት ፍቅርዎን ይግለጹ። የዚህ አስቂኝ ኩመካ፣ የልብወለድ ግራፊክስ እና አድናቂዎች በዓል ጭብጡ ኦርጅናል ገጸ-ባህሪን መፍጠር/መሳል እና ማሳየት ነው። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 9ነው።
-
HBCU Fair፡ ለዚህ ዝግጅት ይመዝገቡ፣አርብ፣ ፌብሩዋሪ 13 The Universities at Shady Grove, 9630 Gudelsky Drive in Rockville. MCPS በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት ቀደም ብሎ ተማሪዎች የሚለቀቁ ወይም ት/ቤት የመዘጋት ሁኔታ ካጋጠመው፣ እነዚያ የትምህርት ቀናት ወደ ቨርቹዋል የትምህርት ቀን ይዛወራል።
-
አክብሮትን ይምረጡ የተሰኘ የቪድኦ ውድድር/"Choose Respect Video Contest" ለመለስተኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ይህ ውድድር በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች የፍቅር ጓደኝነት ጥቃትን በተመለከተ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ኦርጅናል ቪዲዮ ፈጥረው/ቀርጸው እንዲያቀርቡ የተዘጋጀ ውድድር ነው። ቪዲዎችን የሚያዘጋጁት በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ያስገኛል። የመጨረሻው ቀን እሑድ፣ ፌብሩዋሪ 15 ነው።
-
ሠመር ራይዝ "Summer RISE"፦ የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 17 ድረስ ክፍት ነው። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሶፎሞር ተማሪዎች እና ለጁኒየር ተማሪዎች ክፍት የሆነው ይህ ፕሮግራም ተማሪዎች በኢንዱስትሪ ምርጫዎቻቸው መሰረት ቢያንስ ከጁን 22 እስከ ጁላይ 24 ባለው ጊዜ ውስጥ 50 ሰዓታት አገልግሎት መስጠት ከሚችሉባቸው የሙያ አስተናጋጆች ጋር ይመደባሉ።
-
የጌትስበርግ የመጽሐፍ ፌስቲቫል የግጥም ውድድር፦ የዘንድሮው ጭብጥ "ሰብአዊነት ምንድን ነው?" በተሰኘ ርዕስ የሚቀርብ ነው። የሚሳተፉ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ መሆን አለባቸው። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 20ነው።
-
ስልክ ያቁሙ፣ ትኩረት ይስጡ፦ በሚል ርዕስ የእግረኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ትምህርት ሰጪ የሆነ 30 ሰከንድ ቪዲዮ ያዘጋጁ። በእግር ስትጓዙ፣ መኪና፣ ወይም ብስክሌት ስትነዱ በስልክዎ ላይ ሳይሆን በአካባቢዎ ዙሪያ ላይ ማተኮር አስፈላጊመሆኑን ይገንዝቡ። በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። Macbook Air ወይም በመቶዎች የሚቆጠሩ የስጦታ ቪዛ ካርድ ማሸነፍ ይችላሉ። መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 28ነው።
-
ኮንግሬሽናል የሥነ ጥበብ ውድድር "Congressional Art Competition"፦ 8ኛው ኮንግሬሽናል ዲስትሪክት ውስጥ ለሚኖሩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሁሉ ክፍት ነው። የመወዳደሪያ ግብአቶች በኦንላይን መቅረብ አለባቸው። አሸናፊው የፈጠራ ውጤት በዩ.ኤስ ካፒቶል ህንፃ "U.S. Capitol Building" ውስጥ ለአንድ አመት በመላ አገሪቱ ካሉ ሌሎች ኮንግሬሽናል ዲስትሪክቶች የተውጣጡ የፈጠራ ስራዎች ጋር ተቀምጦ ይታያል። መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን ሰኞ፣ ማርች 30ነው።
-
አስተማማኝ የቪዲዮ ውድድር "Keeping It Safe Video Contest"፡ ውድድሩ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ከ 21 ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ተማሪዎች የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች እና አስከፊ ጉዳቶች 30 ሰከንድ ቪዲዮ ፈጥረው/አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋብዛል። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ ማክሰኞ፣ ማርች 31ነው።
-
"Sustainability Poster Contest"፡ ሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች በዚህ አመታዊ ውድድር ላይ የኢነርጂ ቁጠባ፣ የቆሻሻ ቅነሳ፣ እና ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ግንዛቤን ለማሳደግ መሳተፍ ይችላሉ። አዲሱን የዲጂታል አርት ይመልከቱ! የመጨረሻ ቀነገደብ፦ አርብ፣ ኤፕሪል 3ነው።
|
|
|
በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
ስለ ወደፊቱ መዘጋጀት፡ በሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት ወር፣ MCPS በአሥራ ሁለት 12 የሙያ ክላስተሮች ውስጥ የሚያቀርባቸውን 51 ፕሮግራሞች እውቅና ይሰጣል። ተማሪዎች በኢንዱስትሪዎች ተቀባይነት ያላቸው የምስክር ወረቀቶችን፣ የኮሌጅ ክሬዲት፣ የስራ ተለማማጅነት፣ እና የስራ ልምድ የማግኘት እድል ይኖራቸዋል።
የሜሪላንድ ስቴት ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባልነት (SMOB) የመጨረሻ ተወዳዳሪ፡ በፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሶፎሞር ተማሪ የሆነችው Lorena Wu የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ የተማሪ አባል ለመሆን የትምህርት አመት 2026-2027 የመጨረሻ እጩዎች አንዷ ሆና ተመርጣለች።
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|