MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS አርማ

አበይት ጉዳዮች

ኦገስት 20, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 

ታላቁ ቀን ተቃርቧል! በዚህ ሳምንት፣ መምህራንና ሰራተኞች ወደ ትምህርት ቤቶቻችን ተመልሰዋል፣ የመማሪያ ክፍሎችን እያዘጋጁ፣ ትምህርቶችን እያቀዱ እና ለአዲሱ የትምህርት አመት ተማሪዎችን ለመቀበል እየተዘጋጁ ናቸው። በሚቀጥለው ሳምንት፣ ኮሪደሮቻችን በተማሪዎቻችን ኃይልና ደስታ ይሞላሉ — ሰኞ፣ ኦገስት 24 በሚካሄደው የሽግግር ቀን እና ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 በሚካሄደው ለሁሉም ተማሪዎች የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ለመገናኘት በጉጉት እንጠብቃለን።

 
  ደህንነቱ ወደተጠበቀ የትምህርት ዓመት በመጓዝ ላይ፡ የትምሕርት ቤት አውቶቡስ መስመሮች እና የደህንነት ምክሮች

የትምሕርት ቤት አውቶቡስ መስመሮች የመጓጓዣ አገልግሎት ክፍል ድረ ገጽ ላይ ወይም በትምህርት ቤትዎ ድረ ገጽ ፊት ለፊት በትምህርት ቤት የመረጃ ቋት ውስጥ ተለጥፈዋል። እባክዎን አውቶቡሶች በትራፊክ መጨናነቅ፣ መድረሻ እና ከት/ቤት በሚለቀቁበት ጊዜ በሚፈጠር መጨናነቅ ምክንያት ዘግይተው ሊደርሱ እንደሚችሉ ያስታውሱ። ጥያቄ አለዎት? የመጓጓዣ ማናጀር ያነጋግሩ። ልጅዎ(ልጆችዎ) ወደተመደበው የአውቶቡስ ዴፖ ሲደውሉ የተማሪዎን ስምና መታወቂያ፣ የአውቶቡስ መስመር ቁጥር፣ እና ትምህርት ቤቱን መግለጽ አለብዎት።

አዲስ የትምህርት ዓመት ሲጀመር፣ ተማሪዎች ወደ አውቶቡሶች ሲገቡና ሲወጡ የሚጠበቅባቸውን ነገሮች እንዲሁም በአውቶቡስ ውስጥ መከተል ያለባቸውን ሥነ-ሥርዓትና ባህሪ ተማሪዎችንና ቤተሰቦችን ስለ ትምህርት ቤት የአውቶቡስ ደህንነት ማሳሰብ አስፈላጊ ነው። MCPS በየቀኑ ከ 100,000 በላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተማሪዎችን የሚያገለግሉ ከ 1,200 በላይ የአውቶቡስ መስመሮች አሉት። የተማሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ፣ የትምህርት ቤት አውቶቡሶችን ስለማሽከርከር እና ስለ ሜሪላንድ ህግ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት በተጨማሪ ያንብቡ

 
  የመጨረሻው ቆጠራ ተጀምሯል!
  • ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢቶች ቅዳሜ ይካሄዳሉ፦ ኦገስት 22 የትምህርት አመት 2026–2027 በሚጀመርበት ስድስት የሪጅናል ትርኢቶቻችን ላይ እንገናኝ። ቤተሰቦች ስለ ትራንስፖርት፣ ስለ ቴክኖሎጂ፣ ስለ ልዩ ትምህርት፣ ስለ ብዝሃ ቋንቋ አገልግሎቶች፣ ስለ አእምሮ ጤና እና ሌሎች ማዕከላዊ ቢሮዎች ላይ የሚገኙ እውቀት ያላቸውን MCPS ሰራተኞችን በቀጥታ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ድጋፍ ሊሰጧቸው ይችላሉ! ትምህርት ቤትዎን እና በአቅራቢያዎ ወደ ት/ቤት የመመለሻ ትርኢት የሚካሄድበትን ቦታ ያግኙ፦
    • አልበርት አንስታይን፣ ከጠዋቱ 9 a.m.– እስከ ቀትር (አልበርት አንስታይን፣ ቤቴስዳ-ቼቪ ቼዝ፣ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ ኖርዝዉድ፣ ዋልት ዊትማን ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
    • ፔይንት ብራንች፣ ከጠዋቱ 9 a.m.– እስከ ቀትር (ጄምስ ሁበርት ብሌክ፣ ፔይንት ብራንች፣ ሼርውድ፣ ስፕሪንግብሩክ ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
    • ዊተን፣ ከቀኑ 3–6 p.m. (ጆን ኤፍ. ኬኔዲ፣ ዋልተር ጆንሰን፣ ዊተን/ቶማስ ኤዲሰን፣ ቻርለስ W. ውድዋርድ ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
    • ሪቻርድ ሞንትጎመሪ፣ ከቀኑ 1–4 p.m. (ዊንስተን ቸርችል፣ ሪቻርድ ሞንትጎመሪ፣ ሮክቪል፣ ቶማስ S. ውተን ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
    • ጌትስበርግ፣ ከጠዋቱ 9 a.m.– እስከ ቀትር (ጌትስበርግ፣ ኮሎኔል (ዛዶክ ማግሩደር፣ ኩዊንስ ኦርቻርድ፣ ዋትኪንስ ሚል ክላስተር ትምህርት ቤቶች)
    • ሴኔካ ቫሊ፣ ከቀኑ 3–6 p.m. (ክላርክስበርግ፣ ደማስከስ፣ ኖርዝዌስት፣ ፑልስቪል፣ ሴኔካ ቫሊ ክላስተር ትምህርት ቤቶች)

ነፃ ክትባቶች በፔይንት ብራንች፣ ጌትስበርግ፣ እና ሴኔካ ቫሊ ት/ቤቶች ይሰጣሉ። ለነፃ ክትባቶች ብቁ ለመሆን የተማሪዎች የክትባት ማስረጃዎች ያስፈልጋሉ። ቤተሰቦች ስለ ነፃ የክትባት ግብዓቶች እና ቦታዎችን በአልበርት አንስታይን፣ በዊተን፣ እና በሪቻርድ ሞንትጎመሪ የመረጃ ጠረጴዛዎች ላይ ማግኘት ይችላሉ።

  • የሽግግር ቀን፡ ሰኞ፣ ኦገስት 24 ሁለተኛው አመታዊ የሽግግር ቀናችን ነው። ወደ መዋእለ ህጻናት፣ 6ኛ ክፍል፣ 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች፣ እንዲሁም በማንኛውም ክፍል ወደ MCPS አዲስ ለሚገቡ አንዳንድ የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች የመጀመሪያው ሙሉ ቀን ይሆናል። ከርዕሰ መምህራንና ከመምህራን ጋር ይገናኛሉ፣ ሕንፃዎችን ይጎበኛሉ፣ የዕለት ተዕለት ተሞክሮዎችን ያያሉ፣ ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር ይገናኛሉ፣ እንዲሁም ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 ይፋዊ የመጀመሪያ የትምህርት ቤት ቀን ከመጀመሩ በፊት የማህበረሰብ ስሜት መገንባት ይጀምራሉ። ስለ ሽግግር ቀን የበለጠ ይወቁ፦ እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish
  • ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 ለሁሉም ተማሪዎች በሁሉም ክፍሎች የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀን ነውእንኳን ደህና መጣችሁ!
  • ከመጀመሪያው ደወል ጀምሮ እስከ መጨረሻው ከት/ቤት የመሰናበቻ ደወል ድረስ ሞባይል ስልክ መጠቀም አይፈቀድም፦MCPS ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ለትምሕርታቸው ትኩረት እንዲሰጡ እና እርስ በርስ እንዲገናኙ የሚያግዝ አዲስ የሞባይል ስልክ ደንብ ተግባራዊ ያደርጋል። የግል ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በሙሉ በትምህርት ቀን ውስጥ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች— ከመጀመሪያው ደወል ጀምሮ ተማሪዎች እስከሚለቀቁበት የመጨረሻ ደወል ድረስ - በተማሪዎች እጅ እንዳይቀመጡ ይደረጋል። ይህ የትምህርት ሥራ መስተጓጎሎችን ይቀንሳል፣ ተማሪዎች በመማር ላይ በትኩረት እንዲሳተፉ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ያግዛል ተብሎ ይታመናል።
  • ለቤተሰብ ተስማሚ የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር፦ ለትምሕርት አመት 2026-2027 አዲስ የተዘጋጀው ይህ የቀን መቁጠሪያ መደበኛውን የቀን መቁጠሪያ በቀላል እና ተደራሽ በሆነ ቅርጸት ይተካል። ተማሪዎች ትምህርት ቤት ሲሆኑ፣ ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን ሲኖራቸው፣ እንዲሁም የክረምት/ዊንተር እና የጸደይ/ስፕሪንግ ዕረፍት ሲኖራቸው፣ ቤተሰቦች አስቀድመው እንዲያቅዱ እና የማየት ችግር ላለባቸው ተጠቃሚዎች ሁሉ የማንበብ ሁኔታን ለመርዳት በጨረፍታ ለማየት ቀላል ተደርጓል። 
 
  የሚፈልጉትን ለማግኘት ቀላል ሆኗል!

የሴንትራል ሰርቪስ ዋናው የመረጃ ቋት ተሻሽሏል፣ ይህም ተጠቃሚዎች የሚፈልጉትን እንዲያገኙ ቀላል አድርጎላቸዋል፣ ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና የስራ ፈላጊዎች ተዛማጅ ግብዓቶችን እንዲቃኙ አዳዲስ መተግበሪያዎችን እና የቅኝት ዘዴዎችን ቀላል ያደርጋል። የዲስትሪክቱን በብዛት ተደራሽ የሆኑ መገልገያዎችን ትንታኔዎች፣ የተሻሻለ የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር እና የዜና አምድ እና የመረጃ ክፍል የአዲሱ ቅንብር አካል ናቸው። ይህ የመረጃ ቋት ገጽ የማሻሻል ትግበራ በትምህርት ዓመቱ ውስጥ MCPS ድረ ገጹን ለማደስ የተከናወነ ሰፊ ስርዓት አቀፍ ተነሳሽነት መኖሩን ያመለክታል።

 
  ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

ሌላ የትምህርት ዓመት ለመጀመር አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶናል! በጉጉት ይጠብቁ፤ ዘንድቶ እጅግ አስደሳች የትምሕርት ዓመት ይሆናል! ኦገስት 17፣ ሱፐርኢንቴንደንት ቴይለር ስለ MCPS ዋና ተልዕኮ፡ ማስተማር፡ ለቤተሰቦች መረጃ የሚሰጥ መልእክት በኢሜል አስተላልፈዋል።

ጥቂት ፍንጮችን እነሆ፡

  • የሚጠበቁ ነገሮች ግልፅነት። የትምሕርት ውጤት አሰጣጥ የበለጠ ግልጽ እና ወጥነት ያለው ይሆናል። በተጨማሪም የትምህርት ሥራዎችን ዘግይቶ መሥራት፣ ረዘም ያለ ጊዜ አኮሞዴሽን፣ መቅረት/አለመገኘት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ግልጽ የሆኑ መስፈርቶች አሉ።
  • የትምሕርት ምዘናዎች/ግምገማዎች ተማሪዎች የሚያውቁትን፣ የሚረዱትን፣ እና ማድረግ የሚችሉትን መረጃ ይሰጡናል። ቤተሰቦች የትምህርት ምዘና/ግምገማ የቀን መቁጠሪያ ይሰጣቸዋል፣ ይህም ምን እንደሚደረግ አስቀድመው ማየት እና ማቀድ ያስችላቸዋል።
  • ሪፍሪጅሬተር ከርኩለም ተማሪዎች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት ምን እንደሚማሩ የሚያሳይ ቀላል፣ አንድ ገጽ የሥርዓተ ትምህርት መግለጫ፣ ዋና ዋና ርዕሶችን፣ ጭብጦችን እና ጽሑፎችን ጭምር ማጋራታችንን እንቀጥላለን።
  • ጥሩ የጥናት ልምድ ይገንቡ። በቤት ውስጥ ለመማር መደበኛ ጊዜ እና ቦታ ያዘጋጁ እና በዚያ ቀን በትምህርት ቤት ስለተማረ(ች)ው ነገር ተነጋገሩ/ይጠይቁ። ከትምህርት ቤት የሚላኩ መልእክቶችን እና ስራዎችን ዘወትር በመደበኛነት ይከታተሉ። ከአስተማሪዎች እና ልጅዎን ከሚደግፉ ሌሎች አዋቂ ሰዎች ጋር አዘውትረው ይገናኙ።
  • ግንኙነትዎን ይቀጥሉ። ስለ ኦፊሴላዊ MCPS መተግበሪያዎች እና እንዴት ማግኘትና መጠቀም እንደሚችሉ ይወቁ።
 
  የመጀመሪያ ቀን ምርጥ ፎቶ ላኩልን!

ልዩ ሁኔታዎችን በማጋራት የመጀመሪያውን የትምህርት ቀን ደስታ እንድናበስር ያግዙን! ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ እና ትምህርት ቤቶች የሚወዷቸውን የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ፎቶዎች ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። የተመረጡ ፎቶዎች ከማክሰኞ ጠዋት ጀምሮ በዲስትሪክቱ ድረ ገጽ እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይጋራሉ። ፎተግራፎችን በኢሜል ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መላክ ይችላሉ፦ Facebook, Instagram ወይም X እንዲሁም በስፓንሽኛ ማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎቻችን ላይ፣ Facebook Instagram እና Xመላክ ይቻላል።

 
  ስለ ቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School መተማመንን ይኑርዎት እና ክህሎቶችን ያሳድጉ

ልጅዎ በቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School (ጆርጅ B. ቶማስ፣ Sr. የትምሕርት አካዳሚ) በራስ መተማመንን እና የትምህርት ስኬትን እንዲያዳብር/እንድታዳብር ያግዙ። ፕሮግራሞች ቅዳሜ ጠዋት ላይ ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራሁለተኛ (K-12ኛ) ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚሰጡ ሲሆን በንባብ፣ በሂሳብ፣ በፈተና ዝግጅት እና ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ የመሳሰሉ STEM ክህሎት ማበልጸጊያዎች ላይ ያተኩራሉ።

ቤተሰቦች እንዲያስመዘግቡ እና ስለ ፕሮግራሙ እንዲያውቁ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ሴፕቴምበር 19 ይካሄዳል። የመጀመሪያው የማስተማር ክፍለ ጊዜ ሴፕቴምበር 26 ከጠዋቱ 8፡30-11 a.m. ይካሄዳል።

  • ክፍያ፦ $85/በዓመት ($40 FARMS ለተፈቀደላቸው) ማሳሰቢያ፦ ክፍያዎች ከሴፕቴምበር 1 በኋላ ወደ $100 የሚያድግ ሲሆን/ FARMS ለሚያገኙ $50 ይሆናል።
  • መጓጓዣ፦ ወደ መሀል ቦታዎች መጓጓዣ ነፃ MCPS የአውቶቡስ መስመሮች አሉ።
  • ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ለምዝገባ፦ saturdayschool.orgይመልከቱ
 

የተማሪዎችን የምግብ ዕዳ ለመክፈል እና Rep MCPS ከመደብር ለመግዛት ያግዙ!

የተማሪዎችን የምግብ ዕዳ ለመክፈል (እና MCPS ያለዎትን ድጋፍ ለመግለጽ!)፣ አሁን MCPS የሚፈልጋቸውን እቃዎች መግዛት ይችላሉ። ወቅቶች ሲለዋወጡ፣ በኦንላይን መደብር ውስጥ ያሉት ምርቶችም እንዲሁ ስለሚለዋወጡ፣ በየጊዜው መላልሰው ይመልከቱ።የመደብሮችን ዝርዝር ይመልከቱ

 
  ማሳሰቢያዎች፦
  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍል መርሃ ግብሮች፦ አሁን StudentVue እና ParentVue ላይ ይገኛሉ።
  • FARMS ማመልከቻዎን እስካሁን አላቀረቡም?: ዛሬውኑ ያመልክቱ! ምንም እንኳን ልጆቻችሁ ባለፈው አመት ብቁ ቢሆኑም በየትምህርት አመቱ አዲስ FAARMS ማመልከቻ መቅረብ አለበት። በኦንላይን FARMS ማመልከቻ MySchoolApps ላይ አቅርቡ (በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎሙ ቅጾች ይኖራሉ)። በአንድ ቤተሰብ ለሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች የሚያስፈልገው አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው። ተጨማሪ መረጃ
  • የመገልገያ ሕንፃዎች አማካሪ ኮሚቴ፦ MCPS ለትምህርት አመት 2026-2027 በዚህ ኮሚቴ ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበረሰብ አባላትን ይፈልጋል። የኮሚቴ አባላት MCPS የትምህርት ቤት መገልገያዎችን የረጅም ጊዜ እቅድ ሲያዘጋጅ እውቀታቸውን፣ ልምዳቸውን፣ እና አመለካከታቸውን ያካፍላሉ። ፍላጎት ካለዎት፣ እስከ አርብ፣ ሴፕቴምበር 4 ድረስ ማመልከቻ ያስገቡ።
  • የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስፖርት ምዝገባ፡ በዚህ ዓመት አዲስ የወጣ ስለሆነ፣ የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች MCPS የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አትሌቲክስ ለመሳተፍ ብቁ ናቸው። የወንዶችና የሴቶች ወጣቶች ሶፍትቦል እና ኮድ ክሮስ ካንትሪ "softball and coed cross country" በመኸር ወቅት የሚካሄዱ ስፖርቶች ናቸው። ወቅታዊ የቅድመ-ተሳትፎ የአካል ብቃት ምርመራ (MCPS Form SR-8) ፋይል በማድረግ ParentVue ላይ ይመዝገቡ።
  • የጨዋታ መሪ ይሁኑ፡ የሜሪላንድ የህዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአትሌቲክስ ማህበር መሪዎችን ማህበረሰብ ይቀላቀሉ እና የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስፖርቶችን ሥነ ሥርዓት በመጠበቅ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወቱ፣ እና በወጣት ተማሪዎች-አትሌቶች ህይወት ላይ ለውጥ ያመጣሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools