MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS አርማ

አበይት ጉዳዮች

ሴፕተምበር 17, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 

የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ማሳሰቢያ፡ አርብ፣ ሴፕቴምበር 18 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቅበት ቀን ነው። ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 21 ትምህርት የማይሰጥበት ቀን ነው፤ ለተማሪዎችና ለመምህራን ትምህርት አይኖርም።

 

ስለ ወደፊቱ ማቀድ፡ ሁለት ምዕራፎች፣ ለመሳተፍ በርካታ እድሎች ይኖራሉ

40 ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ MCPS የተማሪዎች ምዝገባ ቁጥር እየቀነሰ ነው። በዚህም ምክንያት፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው በላይ ቦታ ሲኖራቸው፣ ሌሎች ማህበረሰቦች ግን አሁንም በማደግ ላይ ናቸው። ይህ ማለት ትምህርት ቤቶቻችንን እና የተለያዩ ተቋሞቻችንን እንዴት እየተጠቀምንባቸው እንዳለ በሰፊው እና በጥልቀት የምንመረምርበት፣ እንዲሁም ለሁሉም ተማሪዎች የተሻለ የወደፊት ዕጣ ፈንታን የምናቅድበት ጊዜ አሁን ነው ማለት ነው። 

የዚህ ሥራ አካል እንደመሆኑ መጠን፣ MCPS   አንዳንድ የመጀመሪያ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋት ወይም ለማጣመር ማጤን ይኖርብናል ማለት ነው። አሁን የምንጀምረው፤ ውሳኔ የመስጠት ማዕቀፉን እንዲሁም ሊታሰብባቸው የሚገቡ ማዕቀፎችን እና ጉዳዮችን በተመለከተ፣ መረጃዎችን በጥንቃቄ በመገምገምና ከማህበረሰቡ ጋር ትርጉም ያለው ተሳትፎ በማድረግ ነው።

ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት እና ጥምረት የሚደረጉ ውይይቶች ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ ለሰራተኞች፣ እና ለማህበረሰቦች አስቸጋሪ እንደሚሆን እንገነዘባለን። በእያንዳንዱ ውሳኔ ላይ የተማሪዎችን ፍላጎት ማዕከል በማድረግ፣ ይህንን ሥራ በጥንቃቄ፣ በግልጽነት፣ እና በርህራሄ ለመወጣት ሙሉ በሙሉ ቁርጠኞች ነን። ስለሚቀጥሉት እርምጃዎች የበለጠ ይወቁ

 
  አስተያየትዎን ለመስጠት የመጨረሻ ዕድል ነው!

2027-2028 እና 2028-2029 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ዝግጅት ላይ አስተያየትዎን ለመስጠት፣ ይህንን የዳሰሳ ጥናት እስከ ሴፕቴምበር 20 ድረስ ሞልተው ይመልሱ።

 
  አንድ ፈጣን ሚስጥራዊ ማመልከቻ — ለቤተሰብዎ ተጨማሪ ድጋፍ

ጥቂት ደቂቃ ሊሰጡት የሚገባ አንድ የትምህርት ቤት ቅጽ እነሆ። ቤተሰብዎ ለነጻ እና በቅናሽ ዋጋ ለሚቀርቡ ምግቦች (FARMS) ብቁ ሊሆን የሚችል ከሆነ፣ ማመልከቻ ያቅርቡ! ምንም ዓይነት መጥፎ አመለካከት ወይም ማመንታት አያስፈልግም። የተማሪ ብቁነት በሚስጥራዊነት የሚጠበቅ ነው።

ከሁሉም በላይ፣ በቤትዎ ውስጥ ያሉ ሁሉም MCPS ተማሪዎች በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ቢማሩም እንኳ፣ ለሁሉም በአንድ ማመልከቻ ብቻ ማቅረብ በቂ ነው። ባለፈው የትምህርት ዘመን ማመልከቻ አቅርበው ከነበረ፣ ለዚህኛው የትምህርት ዘመን አሁንም ሌላ ማመልከቻ መሙላት ያስፈልግዎታል።

በፍጥነት የሚሞላ ነው። ሚስጥራዊ ነው። እናም ይህ ለቤተሰብዎ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። ዝም ብለው ማሳለፍ የለብዎትም፤ ጥቂት ደቂቃዎችን ወስደው መስፈርቶቹን የሚያሟሉ መሆንዎን ያረጋግጡ።

FARMS ያመልክቱ፤ ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ። ማመልከቻውን ለመሙላት እርዳታ ይፈልጋሉ? ይህንን ደረጃ-በ-ደረጃ የተዘጋጀ መመሪያ እና MySchoolApps ቪድኦይመልከቱ እና ረቡዕ፣ ኦክቶበር 7በፊት ማመልከቻውን ሞልተው ያቅርቡ። 

 
  ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እቅድ እያወጡ ነው? የማዕከል/የሴንተር ፕሮግራሞችን ይቃኙ

MCPS፣ በትምህርት ዘመን 2027–2028 ወደ 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች "ሴንተር ፕሮግራም" (Center Program) የማመልከቻ ሂደት፣ መስፈርቶች እና የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚያስችል ቨርቹዋል (virtual) የመረጃ ልውውጥ ስብሰባ ሴፕቴምበር 23 ያካሄዳል።

የሚካሄደው፦

  • ረቡዕ፣ ሴፕተምበር 23 ቀን 7 p.m.:እንግሊዝኛ/ English (ASL እና አማርኛ/Amharic፣ ቻይንኛ/Chinese እና ፈረንሳይኛ/French) | 8 p.m.,ስፓንሽኛ/ Spanishቀጥታ የማስተርጎም አገልግሎት ይሰጣል።

8ኛ ክፍል ተማሪዎች ቤተሰቦች፤ በአካባቢዎ በሚገኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሚገኙት ከመደበኛ ትምህርት ውጪ የሆኑ እንቅስቃሴዎች፣ አትሌቲክስ እና የማህበራዊ ግንኙነት እድሎች በተጨማሪ፣ በሪጅኑ የሚሰጡትን ልዩ የማዕከል/የሴንተር ፕሮግራሞች መመልከት ይችላሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

 
  የበለፀገ፣ የተፋጠነ፣ እና ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች የሚሰጡ የትምህርት እድሎችን ይቃኙ።

ቤተሰቦች በዚህ የመኸር/ፎል ወቅት በሚካሄደው የተፋጠነ እና የበለጸገ ትምህርት (AEI) የቤተሰብ ዌቢናር ተከታታይ ዝግጅት ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ባለ አራት ክፍል ተከታታይ ቨርቹዋል የትምሕርት ማበልጸግ እና የተፋጠነ እድሎችን፣ ተሰጥኦ እና ችሎታ ያላቸው ተማሪዎችን መለያ፣ የግንዛቤ (ኮግኒቲቭ) ችሎታ ፈተና (CogAT) እና የወላጅ አቀንቃኝነት በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ለቤተሰቦች መረጃ እና ግብዓቶች ይሰጣሉ። ይበልጥ ለማወቅ በሚከተሉት ቋንቋዎች ያንብቡ፦ English / Spanish /አማርኛ/Amharic / Chinese / French / Korean / Portuguese / Vietnamese

 
  MCPS ለከፍተኛ ደረጃ ትምህርቶች ተደራሽነትን ለማስፋት በአገር አቀፍ አውታረ መረብ ይሳተፋል።

MCPS፣ ለላቁ የትምህርት ኮርሶች ተደራሽነትን ለማስፋት እና ተማሪዎች አቅማቸውን በተጨማሪ እንዲገነዘቡ ለመርዳት፣ በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ 20 በላይ የትምህርት አስተዳደር አካላት (school districts) ጋር እየተሳተፈ ነው። MCPS፣ በ "Social Mobility Leadership Network" አማካኝነት፤ እንደ Advanced Placement (AP)፣ dual enrollment እና International Baccalaureate (IB) ያሉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የላቀ የትምህርት መርሐ ግብሮች ለመደገፍ የሚያስችሉ መንገዶችን ለመዳሰስ ከ Aspen Institute Education & Society Program፣ ከ College Board እና ከሌሎች ተሳታፊ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ጋር በጋራ ይሰራል። በሶስት ዓመቱ የቡድን አባላት አማካኝነት፣ MCPS አሁን ያሉትን ጥረቶች ይገነባል፣ ዲስትሪክት አቀፍ ልምዶች እና ፖሊሲዎች ወደ ላቀ ትምህርት የበለጠ ወጥ የሆኑ መንገዶችን እንዴት መፍጠር እንደሚችሉ ይመረምራል፣ እንዲሁም ተመሳሳይ ተግዳሮቶችን ከሚያልፉ ዲስትሪክቶች ጎን ለጎን ይማራል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

 
  በቅዳሜ ትምህርት ቤት አማካኝነት በራስ መተማመንን እና የአካዳሚክ ስኬትን ያጎልብቱ

በዚህ ሳምንት መጨረሻ፣ ከዘጠኙ ቅርንጫፎቹ በአንዱ በሚካሄደው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ለመሳተፍ 'Saturday School' (George B. Thomas, Sr. Learning Academy) ይቀላቀሉ። ቤተሰቦች ስለ ፕሮግራሞቹ መረጃ ማግኘት እና ተማሪዎቻቸውን ማስመዝገብ ይችላሉ። የማጠናከሪያ/Tutoring ትምህርት ክፍለ-ጊዜዎች ሴፕቴምበር 26 ከጠዋቱ 8:30 እስከ 11 a.m. ይጀምራሉ።

ቅዳሜ ጠዋት ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል (K-12ኛ) ላሉ ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮግራሞች የሚካሄዱ ሲሆን ንባብ፣ የቋንቋ ስነ ጥበብ፣ ሂሳብ፣ የፈተና ዝግጅት፣ እና ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ የመሳሰሉ STEM ማበልጸጊያዎች ላይ ያተኩራሉ።

ክፍያ፦ $100/በዓመት (FARMS ለተፈቀደላቸው $50)
መጓጓዣ፦ ወደ መሀል ቦታዎች መጓጓዣ ነፃ MCPS የአውቶቡስ መስመሮች አሉ።
ለተጨማሪ መረጃ እና ምዝገባ: saturdayschool.org

 
  ቦርዱ የ 2027 ቁልፍ የደንብ ድንጋጌ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ይፋ አድርጓል።

የትምሕርት ቦርዱ የ 2027 የደንብ ድንጋጌ አጀንዳውን ይፋ ለማድረግ፣ ዓመታዊ የደንብ ድንጋጌ ጉባኤውን በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካሄዷል። ይህ ዝግጅት፣ ለመጪው የ 2027 የሜሪላንድ ጠቅላላ ጉባኤ (Maryland General Assembly) ስብሰባ ቦርዱ ያስቀመጣቸውን የደንቦች ድንጋጌ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች አስቀድሞ ለመመልከት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልዑካን ቡድን አባላትን እና የአካባቢ መሪዎችን በአንድ ላይ ያሰባስባል። ቦርዱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አራት ጉዳዮች፡- በቂ የትምህርት ቤት በጀት መኖሩን ማረጋገጥ፣ የአካባቢ የራስ አስተዳደር መብት እንዲጠበቅ ማድረግ፣ ብቁ የሆኑ የትምህርት ባለሙያዎችን መቅጠር፣ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የመማሪያ አካባቢን ማስፈን ናቸው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ፦ 

 
  ጥቂት ውይይቶች፣ ትልቅ ለውጥ፡ ስለ አእምሮ ጤና እና ደህንነት የቤተሰብ መመሪያ

ጥቂት ውይይቶች ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ። MCPS የአእምሮ ጤና እና ደህንነትን የሚመለከት one-pager፤ ወላጆች እና ተንከባካቢዎች የልጆቻቸውን የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ለመደገፍ የሚረዳቸው ተግባራዊ ምክሮችን ይዟል። እነዚህም የልጆችን ሁኔታ መከታተልና ለውጦችን ማስተዋል፣ ጤናማ የዕለት ተዕለት ልማዶችን መፍጠር እና መቼ እርዳታ መጠየቅ እንዳለበት ማወቅን የመሳሰሉ ጉዳዮችን ያካትታል። ይህ መመሪያ በትምህርት ቤት የሚሰጡ ድጋፎችን እና ለአስቸኳይ ሁኔታዎች የሚሆኑ መረጃዎችንም ያካተተ ሲሆን፣ ይህም ቤተሰቦች ስጋት ሲያጋጥማቸው የት መሄድ እንዳለባቸው እንዲያውቁ ያስችላቸዋል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

 
  2026 የጸደይ/ስፕሪንግ ወቅት MAP ውጤቶች የተማሪዎችን እድገት ያሳያሉ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምሕርት ቤቶች (MCPS) ተማሪዎች 2026 ጸደይ/ስፕሪንግ ወቅት በተደረገው NWEA MAP ምዘና በሂሳብ ትምህርት መሻሻል አሳይተዋል፤ በአንደኛ እና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ባሉ ሁሉም የተማሪ ቡድኖች የትምሕርት አፈጻጸም ላይ መሻሻል ታይቷል። በአጠቃላይ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሂሳብ አፈጻጸም 7.3 በመቶ ነጥብ ሲጨምር፣ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሂሳብ አፈጻጸም ደግሞ 6.3 በመቶ ነጥብ ጨምሯል። እነዚህ ውጤቶች የአካዳሚክ ብቃትን በማሻሻል ረገድ ግልጽ የሆነ መነቃቃት እና በመላው ስርዓቱ ላይ የተመዘገበ እድገት መኖሩን ያሳያሉ።

በአጠቃላይ በዲስትሪክቱ የተገኙ ተጨማሪ ውጤቶችን እና የተማሪ ቡድኖች መረጃዎችን ለማግኘት፣ ሙሉውን 2026 የጸደይ/የስፕሪንግ ወቅት MAP አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት ይመልከቱ።

 
  ለኮሌጅ ትምህርት ዝግጅት የሚረዱ አማራጮች፡ የኮሌጅ ኤግዚቢሽኖች፣ አውደ ጥናቶች እና የገንዘብ ድጋፍ/Financial Aid

MCPS, Career Council, Inc. እና College Fairs USA አርብ፣ ኦክቶበር 9 ከጠዋቱ 9:30 a.m.-12:30 p.m. ድረስ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር እና ሲንየር ተማሪዎች በአካል ተገኝተው የኮሌጅ መግቢያ መረጃዎችን የሚያገኙበት አውደ ርዕይ ያስተናግዳሉ። ቦታው፦ at the Activity Center at Bohrer Park in Gaithersburg በትምህርት ቀን በኤግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች በኦንላይን መገለጫቸውን እንዲሞሉ የሚያስችል አገናኝ ሊንክ ያገኛሉ። ለተጨማሪ መረጃ፣ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን ካውንስለር ማነጋገር አለባቸው። የአውደ ርዕዩ መግለጫ/Fair Flyer:/እንግሊዝኛ/English| ስፓንሽኛ/Spanish

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው፦ የኮሌጅ ምዝገባ እና የነፃ ትምህርት ዕድል (scholarship) ማመልከቻ ወቅት ሲጀመር፣ ስለ ኮሌጅ ማመልከቻ ሂደት እና የገንዘብ ድጋፍ (financial aid) ጥያቄዎችን ለመመለስና አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት MCPS የኮሌጅ እና የሙያ ዳሰሳ አስተናጋጆች (College and Career Navigators) ዝግጁ መሆናቸውን ያስታውሱ። ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፤ ለኮሌጅ ትምህርት ትክክለኛውን መንገድ ስለመምረጥ፣ የድርሰት ጽሁፍ ስራዎችን (essays) ስለማዘጋጀት እና ስለ 'Common App' አጠቃቀም ለቤተሰቦች መመሪያ ለመስጠት የተለያዩ በአካል የሚከናወኑ እና በኦንላይን የሚሰጡ ወርክሾፖችን እያዘጋጁ ናቸው። ምን እንደሚቀርብ ይመልከቱ እና ይቀላቀሉን!

የሞንትጎመሪ ኮሌጅም በቅርቡ የገንዘብ ድጋፍ ዝግጅቶችን ያቀርባል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.  

 
  የሠመር የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓቶች ከሴፕቴምበር 25 በፊት መቅረብ አለባቸው።

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለመመረቅ 75 ሰዓት SSL (የተማሪ አገልግሎት ትምህርት) ተሳትፎ ያስፈልጋቸዋል። በእነዚህ የሴፕቴምበር ዕድሎች የአገልግሎት ሰዓቶችን ማግኘት ቀጥሉ። ከ 6ኛ ክፍል በኋላ በ MCPS የተመዘገቡ ተማሪዎች የ SSL መስፈርትን በማጣጣት የሚያካክስ/ እፎይታ ያገኛሉ። በአካል እና ቨርቹዋል አገልግሎት ለመስጠት ያሉት እድሎች፣ማሳሰቢያዎች እና ወቅታዊ መረጃዎች በሙሉ SSL ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ

 
  ስልኮቻችሁን አስቀምጡ፤ በየዕለቱ የትምህርት አካል ሁኑ።

የትምህርት ዓመቱ እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ቤተሰቦችና ተማሪዎች ከመጀመሪያው ደወል ጀምሮ እስከ ሚለቀቁበት ደወል ድረስ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች የሞባይል ስልኮችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ከአጠገባቸው አርቀው ማስቀመጥ እንደሚጠበቅባቸው ማስታወስ አለባቸው። በሜሪላንድ ከስልክ-ነጻ ትምህርት ቤቶች የተሰኘ ህግ፣ MCPS ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በትምሕርት ትኩረት እንዲያደርጉ እና ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚያግዝ አዲስ የሞባይል ስልክ ደንብ በመተግበር ላይ ነው። ይህ የትምህርት ሥራ መስተጓጎሎችን ይቀንሳል፣ ተማሪዎች በመማር ላይ በትኩረት እንዲሳተፉ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ያግዛል ተብሎ ይታመናል።

ስልኮቻችሁን አስቀምጡ። ተገናኙ። ተፈላሰፉ/ፍጠሩ ተማሩ። መሪ ሁን(ኚ) የዕለቱ አካል ሁኑ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ፦ 

 
  ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
  • ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ብሎክ ፓርቲ፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባል ማሪሊን ባልኮምቤ/Marilyn Balcombe ይህን ዝግጅት አርብ፣ ሴፕቴምበር 18 ከቀኑ 12:30-3 p.m. ጀርመንታወን ቀጥሎ ባለው አድራሻ ያስተናግዳሉ። አድራሻ፦ BlackRock Center for the Arts, 12901 Town Commons Drive in Germantown. 
  • የወጣቶች ታወን ሀውስ፦ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ስብሰባ ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 29 ከቀኑ 6 p.m. ሮክቪል በሚከተለው አድራሻ፦ Council Office Building, Third Floor, 100 Maryland Avenue in Rockville ወይም በዙም ይካሄዳል። የሚሳተፉ ተማሪዎች ጥያቄዎቻቸውን እና ስጋቶቻቸውን ማቅረብ እና ከካውንቲው አመራሮች ጋር በሚደረግ ውይይት መሳተፍ ይችላሉ። ለመሣተፍ ይመዝገቡ
  • ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣት ሴቶች የመኸር/Fall ክፍለ ጊዜ፦ ይህ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጠው ነፃ፣ የኦንላይን፣ 10-ሳምንት የሚፈጅ የስራ ፈጠራ ፕሮግራም ሴፕቴምበር 28 በሚውልበት ሳምንት ይጀመራል። ትምህርቶች ማክሰኞ ከቀኑ 7 p.m.,፣ ረቡዕ ከቀኑ 4፡30 p.m. ወይም ረቡዕ ከቀኑ 8 p.m. ላይ ይካሄዳሉ ይመዝገቡ። የበለጠ መረጃ ያግኙ:እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish
  • Latina Legacy Conference: This event for Latina female high school students will be held from 10 a.m.-1 p.m. on Friday, Oct. 30 at 15 W. Gude Drive in Rockville. ርዕሶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ የላቲና ሴቶች ደህንነት እና የአእምሮ ጤና፤ በትምህርት ዘርፍ ያሉ ላቲና ሴቶች፤ የላቲና ሴቶች የአማካሪነት (mentorship) ተሳትፎ፤ እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህ እና የላቲና ተማሪዎች ድምፅ። ለመመዝገብ፣ ተማሪዎች እስከ ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15 ድረስ ምክትል ርዕሰ መምህራቸውን ማነጋገር አለባቸው።
  • ለአሜሪካ ያለዎትን ራዕይ ያጋሩ፡ 5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ፕሬዚዳንታዊ ንግግር በመጻፍና በማቅረብ እስከ $1,000 ሽልማት ማግኘት ይችላሉ። "ንግግሩን" ተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተመረጡ በማሰብ የበዓለ ሲመት ንግግራቸውን 2-3 ደቂቃ በሚፈጅ ቪዲዮ እንደሚያቀርቡ ያበረታታል። ለዴሞክራሲያችን ምርጥ ነው የምትሉትን አንድነትን የሚያበረታታ ራዕይ አቅርቡ።ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ መወዳደሪያው መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ አርብ፣ ኦክቶበር 30ነው።
  • BlackRock Center for the Arts የሚከናወን የዲዛይንና የግንባታ ፕሮጀክት፡ ፕሮግራሙ BlackRock Center for the Arts የአካባቢ ጥበቃን የሚያጎለብትና የአካባቢ እፅዋትንና ዛፎችን ያካተተ የመሬት ገጽታ (landscape) በመፍጠር ላይ ያተኩራል። ከኦክቶበር 3 ጀምሮ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሴኔካ ክሪክ (Seneca Creek) የውሃ ተፋሰስን ለማሻሻል የሚረዳ ፕሮጀክት በመንደፍና በመትከል ስድስት ተከታታይ ቅዳሜዎችን ያሳልፋሉ። ተማሪዎች እስከ 18 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት (SSL) ማግኘት ይችላሉ። ያመልክቱ 
 

ከዜና አምድ

  • በሊተርሲ ክህሎት የተመዘገበውን አስደናቂ ስኬት ማክበር፡ William B. Gibbs አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የላቀ ብቃት አሳይቷል! ትምህርት ቤቱ፣ ብሔራዊ ለትርፍ ያልተቋቋመ የትምህርት አውታር ዘገባ አቅራቢ "The 74" የሊተርሲ ክህሎትን (literacy) በማጎልበት ረገድ "Bright Spots Top School" (አርአያነት ያለውና የላቀ ውጤት ያስመዘገበ ትምህርት ቤት) ተብሎ እውቅና አግኝቷል።
  • በሌክዉድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስደናቂ ቀን፦ ተማሪዎች በሕይወታቸው ልዩ ከሆኑ ሰዎች ጋር ትርጉም ያለው ጊዜያትን የማሳለፍ እና ለረጅም ዓመታት የሚቆዩ ትዝታዎችን የመፍጠር ዕድል አግኝተዋል።
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools