MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS Logo

አበይት ጉዳዮች

ኦክቶበር 22, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
የትምህርት ቤት መዘጋትን በተመለከተ የሚካሄዱ ውይይቶች፦ የመጀመሪያው ዙር ተሳትፎ አሁን እየተካሄደ ነው   የትምህርት ቤት መዘጋትን በተመለከተ የሚካሄዱ ውይይቶች፡ የመጀመሪያው ዙር ተሳትፎ አሁን እየተካሄደ ነው።

MCPS ትምህርት ቤቶችን ስለመዝጋት እና ስለማጣመር/ማዋሃድ የሚያጠናው ለምንድነው? መረጃዎች ምን ያስገነዝቡናል? ውሳኔዎች የሚሰጡት እንዴት ነው? እነዚህ አስፈላጊ ጥያቄዎች ናቸው፤ ማህበረሰባችንን አንድ ላይ እያሰባሰብን ያለነውም በትክክል ለዚህ ነው። ትምህርት ቤቶቻችን የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለማወቅ፣ ጥያቄዎችን ለማንሳት፣ እንዲሁም ለተሳታፊዎቹ ፋይዳ ያላቸውን ጉዳዮች ለማጋራት፤ ለቤተሰቦች፣ ለሰራተኞች እና ለማህበረሰብ አባላት እድል የሚሰጡ የውይይት መድረኮቻችን በመካሄድ ላይ ናቸው። ለመዝጋት ወይም ለማጣመር የተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሉም፤ ምንም ዓይነት ምክረ ሐሳቦች አልቀረቡም፤ ወይም አስቀድሞ የተወሰነ ውሳኔም የለም። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ስብሰባዎች እየተካሄዱ ሲሆን፣ ይህም በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች በቀላሉ እንዲሳተፉ ለማስቻል ታስቦበት ነው። ስለ ስብሰባ ቦታዎች ማስታወሻ፦ የስብሰባ ቦታዎቹ የተመረጡት በመላው ሞንትጎመሪ ካውንቲ ያሉ ሰዎች የሚሳተፉበትን ዕድል ለመፍጠር እና በተቻለ መጠን ብዙ ቤተሰቦችን ለመድረስ ታስቦ ነው። በአንድ የተወሰነ ትምህርት ቤት ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ስብሰባ ማካሄድ፣ ያ ትምህርት ቤት ወይም ማህበረሰብ እንዲዘጋ ወይም ከሌላ ጋር እንዲጣመር/እንዲዋሃድ ታስቧል ማለት አይደለም። ለመሳተፍ፣ ሁሉንም መልሶች ማወቅ ወይም ሁሉንም ጥያቄዎች ማወቅ አይጠበቅብዎትም። ይህ አብሮ የመማር፣ የማዳመጥ እና የማቀድ ሂደት ነው፤ አሁንም ቢሆን መሣተፍ የሚችሉበት ጊዜ አለ። ይበልጥ ያንብቡ. 

እዚህ ይመልከቱ: እንግሊዝኛ/English | ስፓንሽኛ/Spanish

 
 መራራው እውነት፡ ‘ዘገምተኛ ዓመት’ ማለት ‘ከሥራ የሚታቀቡበት ዓመት’ ማለት አይደለም   መራራው እውነት፡ «ዘገምተኛ ዓመት» ማለት «ከሥራ የሚታቀቡበት ዓመት» ማለት አይደለም

MCPS ለ 2028 የበጀት ዓመት የቀረበውን የካፒታል በጀት እንዲሁም ከ 2027 እስከ 2032 ላሉት የበጀት ዓመታት የተዘጋጀውን የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) ማሻሻያዎችን ማድረግ የሚያስችለውን ሂደት ጀምሯል። 2028 የበጀት ዓመት «መደበኛ ያልሆነ» (off-year) የማሻሻያ ዑደት በመሆኑ፣ የቀረበው ሀሳብ በነባሩ የካፒታል ዕቅድ ላይ በተመረጡ ማስተካከያዎች ላይ ብቻ የሚያተኩር እንጂ፣ ሁሉንም ፕሮጀክቶች ያካተተ አጠቃላይ ግምገማ አይደለም። ነገር ግን መራራው እውነት ይህ ነው፤ MCPS እያረጁ በመጡ ትምህርት ቤቶች፣ እየቀነሰ በመጣ የተማሪዎች ቁጥር፣ እና እየጨመረ በመጣ የግንባታ ወጪ ምክንያት እጅግ አስቸጋሪ ውሳኔዎችን መጋፈጥ ይጠበቅበታል። ባሉት ውስን ሀብቶች እያደገ የመጣውን የመሰረተ ልማት ፍላጎት የት/ቤት ህንጻዎች ያሉበት ሁኔታ፣ ዲስትሪክቱ በህንጻዎቹና ተቋማቱ ላይ የሚያደርገውን ኢንቨስትመንት እንደገና ማጤን ይኖርበታል። ምንም አለማድረግ አማራጭ ሊሆን አይችልም።

ቪድኦቹ ላይ ያለውን 'መራራ እውነት' ይመልከቱ። 

 
MCPS የመጀመሪያ ደረጃ ውጤቶችን እና የመማር ሂደቱን ለማጠናከር የሚወሰዱ እርምጃዎችን ያሳውቃል   MCPS የመጀመሪያ ደረጃ ውጤቶችን እና ትምህርትን ለማጠናከር የሚወሰዱ እርምጃዎችን ያሳውቃል/ያጋራል።

እያንዳንዱ ተማሪ። እያንዳንዱ የመማሪያ ክፍል። በየቀኑ። MCPS የተማሪዎችን የትምህርት አፈጻጸም በጥልቀት ሲመረምር እና ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የሚያገኙትን ትምህርትና ድጋፍ ለማጠናክር፣ ማስተላለፍ የሚፈልገው መልእክት ይህ ነው።

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 22 የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ የትምህርት ዓመት 2026–2027 የተማሪዎችን የትምህርት አፈጻጸም በተመለከተ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት መግለጫ አድምጧል። ይህ ገለጻ በንባብ እና በሂሳብ ትምህርት የተገኙ ውጤቶችን የዳሰሰ፣ የእድገት እና የተግዳሮት ዘርፎችን የለየ፣ እንዲሁም MCPS ይህንን መረጃ በመጠቀም በመላው ዲስትሪክቱ የማስተማር እና የመማር ሂደቱን እንዴት እያሻሻለ እንደሚገኝ የሚያብራራ ነው። ይበልጥ ያንብቡ።

 
ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…   ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

ቤቨርሊ ፋርምስ፣ ሶመርሴት እና ትራቪላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በስቴት እና በሀገር አቀፍ ምዘናዎች ላሳዩት የላቀ አፈጻጸም እንዲሁም በተማሪዎች መካከል የሚታየውን የትምህርት ውጤት ልዩነት (achievement gap) ከስቴት አማካይ ውጤት አንጻር በማጥበብ ረገድ ላስመዘገቡት ስኬት እውቅና በመስጠት፣ 2026-2027 የሜሪላንድ "ብሉ ሪባን" (Blue Ribbon) ትምህርት ቤቶች ተብለው ተሰይመዋል። የሜሪላንድ "ብሉ ሪባን" (Blue Ribbon) ትምህርት ቤቶች መርሃ ግብር በመላው ስቴቱ የሚገኙ 23 አርአያነት ያላቸውን ትምህርት ቤቶች እውቅና የሰጠ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 12ቱ የመንግስት/የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ናቸው። ተጨማሪ ያንብቡ ፤ እንዲሁም ለትምህርት ቤቶቻቸው ዜናውን እንዴት እንዳበሰሩ ይመልከቱ።

 
በትምሕርት አመት 2027-2028 የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ላይ አስተያየት መስጠትዎን ያረጋግጡ   በትምሕርት አመት 2027-2028 ካለንደር ላይ አስተያየት መስጠትዎን ያረጋግጡ

MCPS የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ 2027-2028 (ካለንደር) እያዘጋጀ ስለሆነ፣ ዲስትሪክቱ ከእርስዎ ተጨማሪ አስተያየት ግብዓት ማግኘት ይፈልጋል!

ለትምሕርት ዓመት 2027-2028 በቀረበው ረቂቅ የትምህርት ቀን መቁጠሪያ ላይ አስተያየትዎን ለመስጠት ይህን ሁለተኛውን የዳሰሳ ጥናት ሞልተው ይመልሱ። የዳሰሳ ጥናቱ አርብ፣ ኖቨምበር 6 ይዘጋል። የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ።

 
ቦርዱ በሁለት ፖሊሲዎች ላይ የህዝብ አስተያየት ይፈልጋል   ቦርዱ በሁለት ፖሊሲዎች ላይ የህዝብ አስተያየት ይፈልጋል

የትምህርት ቦርድ በሁለት ፖሊሲዎች ላይ በቀረቡት ማሻሻያዎች ላይ የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይፈልጋል—ፖሊሲ IPD: ትምህርታዊ የጉዞ ፕሮግራሞች፣ የመስክ ጉብኝቶች እና የተማሪዎች ድርጅት ጉዞዎች እናፖሊሲ BLB: በይግባኝ እና በችሎት ሂደቶች ላይ ለሚደረጉት የአሰራር ደንቦች።

የህዝብ አስተያየት ፖሊሲዎች

 
ParentVue በደንብ እየተጠቀሙበት ነው?   ParentVue በደንብ እየተጠቀሙበት ነው?

ParentVUE፡ በልጅዎ ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ነገሮችን ለማወቅ እና ለመገናኘት ከሚያስችሉዎት ቀላል መንገዶች አንዱ ነው። ቤተሰቦች የልጆቻቸውን የትምህርት ውጤቶች እና የቤት ሥራዎችን ለመከታተል፣ ትምህርት ቤት መገኘታቸውን ለማረጋገጥ፣ የት/ቤት አውቶቡስ መጓጓዣ መረጃ ለማግኘት፣ የሪፖርት ካርዶችን እና የትምሕርት ውጤት ግምገማዎችን ለማግኘት፣ የኦንላይን ምዝገባዎችን ለመሙላት እና ከመምህራን ጋር በቀጥታ ለመገናኘት ይጠቅማቸዋል።

አዲሱን ParentVue app መተግበሪያ ይጫኑ፣ የትምሕርት ውጤት መዝገብ (Gradebook) እና የመተግበሪያውን አቋራጭ ምርጫዎን ያስተካክሉ፣ እንዲሁም ParentVUE በየጊዜው ይከታተሉ። በመተግበሪያው አማካኝነት በቀጥታ የወላጅ-መምህር ውይይቶችን ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። ያስታውሱ፦ እያንዳንዱ ወላጅ ወይም አሳዳጊ የራሱን ParentVUE አካውንት/account እና የይለፍ ቃል መጠቀም አለበት።

እዚህ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፦ : English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

 
EdTalk ከፍተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴንተር ፕሮግራሞችን ይቃኙ   EdTalk ከፍተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴንተር ፕሮግራሞችን ይቃኙ

«EdTalk» የቅርብ ጊዜ ዝግጅት ላይ፣ አቅራቢዋ የትምህርት ቦርድ ፕሬዚዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን (Grace Rivera-Oven) እና እንግዶቻቸው ስለ አዲሶቹ MCPS ሴንተር ፕሮግራሞች (Center Programs) ሲወያዩ ይመልከቱ። በአካባቢያቸው ለሚገኙ የተለያዩ የአራት ዓመት የአካዳሚክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልዩ ትኩረት ፕሮግራሞች (Center Programs)፣ 8ኛ ክፍል ተማሪ ያላቸው ቤተሰቦች እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ ይወቁ። EdTalk ይመልከቱ | Vea Educacion al Día

አሁን ሁሉንም EdTalk እና Educación al Día ዝግጅቶችን በአፕል ፖድካስቶች፣ Spotify ወይም የሚወዷቸውን ፖድካስቶች በሚያዳምጡበት ጣቢያ ሁሉ መስማት ይችላሉ።

 
አሁን ያውቁታል — በሙያና ቴክኒክ ትምህርት ፕሮግራም ላይ የተደረጉ ለውጦች   አሁን ያውቁታል — በሙያና ቴክኒክ ትምህርት ፕሮግራም ላይ የተደረጉ ለውጦች

በሙያ እና ቴክኒክ ትምህርት (CTE) ፕሮግራሞች ላይ ጠቃሚ ለውጦች ሊደረጉ ነው። 2027 የመኸር ወቅት ጀምሮ፣ MCPS በስቴት ከጸደቁት የሙያ እና ቴክኒክ ትምህርት (CTE) ፕሮግራሞች መካከል ቁጥራቸውን ከ 51 ወደ 37 ዝቅ ያደርጋል። አንዳንዶቹ ቀስ በቀስ ይወገዳሉ፤ ሌሎች ደግሞ ይጣመራሉ ወይም ይሻሻላሉ። እነዚህን ለውጦች ማድረግ ለተማሪዎች ከፍተኛ ክፍያ እና ተፈላጊነት ያላቸው የሥራ መስኮች የሚያዘጋጁአቸውን አዳዲስ፣ የተቀናጁ፣ እና ዘመናዊ የትምህርትና የሙያ ዘርፎችን እንዲቃኙ ትልቅ ዕድል ይሰጣቸዋል።

እንግዲያው፣ ይህ ምን ማለት ነው? አንዳንድ CTE ፕሮግራሞች በአዲሱ ስድስት የሪጅን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሞዴላችን ውስጥ ይካተታሉ፤ ይህም በመላው ካውንቲው ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸውን ፕሮግራሞች ተደራሽነት ለማስፋት ይረዳል። ፕሮግራሞቹ ከሜሪላንድ አዲሱ 14 የሙያ ዘርፎች ሞዴል ጋር ይጣጣማሉ።

ተማሪዎ ቀድም ሲል CTE ፕሮግራም ውስጥ የሚማር/የምትማር ከሆነ፣ ምንም አይስተጓጎልበ(ባ)ትም። የያዙትን ፕሮግራም ማጠናቀቅ እና የታቀዱትን የሙያ ምስክር ወረቀቶች ማግኘት ይችላሉ።

አሁን ያውቃሉ/Now You Know:English | Spanish |አማርኛ/Amharic | Chinese | French | Korean | Portuguese | Vietnamese

 
ፈጣን እና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው፤ እንዲሁም ትልቅ ጥቅም አለው፦ FARMS የምግብ ፕሮግራም ዛሬውኑ ያመልክቱ!   ፈጣን እና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው፤ እንዲሁም ትልቅ ጥቅም አለው፦ FARMS የምግብ ፕሮግራም ዛሬውኑ ያመልክቱ!

ጥቂት ደቂቃ ሊሰጡት የሚገባ አንድ የትምህርት ቤት ቅጽ እነሆ። ቤተሰብዎ ለነጻ እና በቅናሽ ዋጋ ለሚቀርቡ ምግቦች (FARMS) ብቁ ሊሆን የሚችል ከሆነ፣ ማመልከቻ ያቅርቡ! 

ከሁሉም በላይ፣ በቤትዎ ውስጥ ያሉ ሁሉም MCPS ተማሪዎች በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ቢማሩም እንኳ፣ ለሁሉም በአንድ ማመልከቻ ብቻ ማቅረብ በቂ ነው። ባለፈው የትምህርት ዘመን ማመልከቻ አቅርበው ከነበረ፣ ለዚህኛው የትምህርት ዘመን አሁንም ሌላ ማመልከቻ መሙላት ያስፈልግዎታል።

በፍጥነት የሚሞላ ነው። ሚስጥራዊ ነው። እናም ይህ ለቤተሰብዎ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። ዝም ብለው ማሳለፍ የለብዎትም፤ ጥቂት ደቂቃዎችን ወስደው መስፈርቶቹን የሚያሟሉ መሆንዎን ያረጋግጡ።

FARMS ያመልክቱ፤ ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ። ማመልከቻውን ለመሙላት እርዳታ ይፈልጋሉ? ይህንን ደረጃ በደረጃ መመሪያ በመከተል እና MySchoolApps ቪዲዮ ይመልከቱ፤ እና ማመልከቻዎን በቅድሚያ ሞልተው ያቅርቡ።

 
MCPS የአውቶቡስ ሹፌሮችን እየቀጠረ ነው   MCPS የአውቶቡስ ሹፌሮችን እየቀጠረ ነው

በትራንስፖርት ዘርፍ አርኪ የሥራ መስክ ላይ ፍላጎት አለዎት? ሮክቪል፣ 16651 Crabbs Branch Way in Rockville በሚገኘው የሼዲ ግሮቭ ትራንስፖርቴሽን ዴፖ (Shady Grove Transportation Depot) አርብ፣ ኖቨምበር 6 ቀን ከጠዋቱ a.m.-1 p.m. ድረስ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍል (Division of Transportation Services) የሚያዘጋጀው የስራ አውደ ርዕይ እንዳያመልጥዎት። በዝግጅቱ ላይ ከመሳተፋቸው በፊት፣ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች MCPS Careers ድረ-ገጽ ላይ የኦንላይን መገለጫቸውን (profile) እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-740-6080 ይደውሉ።

 
የኮሌጅ እቅድ አለዎት? የሚረዳዎት ጠቃሚ ፍንጭ፣ መሳሪያዎች እና ግብዓቶች   ኮሌጅ የመግባት እቅድ አለዎት? የሚረዳዎት ጠቃሚ ፍንጭ፣ መሳሪያዎች እና ግብዓቶች

ለኮሌጅ እየተዘጋጁ ነው? የኮሌጅ ፍለጋዎን ሲያከናውኑ፣ FAFSA ዝግጁ ይሁኑ፣ በሜሪላንድ የሚገኙ የግል ኮሌጆችንና ዩኒቨርሲቲዎችን ይዳስሱ፤ እንዲሁም ለትምህርት ማመልከቻዎች፣ ለፈተና ዝግጅት፣ ለትምህርት ጥናት ዘርፎች (majors) እና ለሙያ ምርጫ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ያግኙ።

  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪዎች ያሏቸው ወላጆች፦ 2027-2028 ለተማሪዎች የፌዴራል የገንዘብ ድጋፍ (FAFSA) ማመልከቻ ቅጽ ሞልተው ለማቅረብ አሁን ክፍት ነው። FAFSAን ከመሙላታቸው በፊት፣ ተማሪዎች እና አስተዋጽኦ አበርካቾች (ለምሳሌ ወላጅ ወይም የትዳር አጋር —አስፈላጊ ከሆነ) የFSA ID ማውጣት አለባቸው፤ ይህም መለያ ወደ FAFSA ለመግባት እና ሰነዱን ለመፈረም እንደ የተጠቃሚ ስም (username) እና የይለፍ ቃል (password) ያገለግላል። ስለ FAFSA ወይም ስለ ፋይናንሻል ኤይድ (የገንዘብ ድጋፍ) ሂደት ጥያቄዎች ካሎዎት፣ የኮሌጅ እና የሙያ መሪዎን (College & Career Navigator - CCN) ወይም የትምህርት ቤት አማካሪዎን ያነጋግሩ።
  • ለሜሪላንድ ስቴት የገንዘብ ድጋፍ ለመጀመሪያ ጊዜ እያመለከቱ ነው? በቅርብ ጊዜ ከሜሪላንድ ከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን (MHEC) በተሰጠው መመሪያ መሰረት፣ የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች በዚህ ጊዜ የMDCAPS አካውንት ማውጣት/መክፈት የለባቸውም። ተማሪዎች በሜሪላንድ የተማሪ መረጃ ስርዓት (MDSIS) በኩል አካውንት ይፈጥራሉ፣ ይህም MHEC ጃንዋሪ ወር ላይይኖራል ብሎ ይገምታል።
  • የተመዘገበ ኮሌጅ እና የስራ ወርክሾፖች፡ ብዙ አርእስቶችን የሚሸፍኑ የኮሌጅ እና የሙያ ዝግጁነት አውደ ጥናቶችን፣ ድርሰት መፃፍን፣ የገንዘብ ድጋፍን፣ የተለመዱ/Common App ምክሮችን፣ የፈተና መሰናዶን፣ በኮሌጅ መተግበሪያዎች ላይ AI መጠቀምን፣ የስራ እቅድ ማዘጋጀትን፣ NCAA ምልመላን እና ሌሎችንም ያካትታል።
  • የግል ኮሌጆች የማመልከቻ ቀናት፡ ኖቨምበር 9 ቀን፣ ለማንኛውም የሜሪላንድ የግል ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ ያለ ምንም የማመልከቻ ክፍያ ማመልከት ይችላሉ።
 
ለስቴት ሻምፒዮና የሚያደርሰው ጉዞ የሚጀምረው እዚህ ነው!   ለስቴት ሻምፒዮና የሚያደርሰው ጉዞ የሚጀምረው እዚህ ነው!

ቡድኖች የስቴት ሻምፒዮና ዋንጫን ወደ ቤታቸው የማምጣት ግብ ይዘው፣ በውድድር አመቱ ማጠቃለያ ምዕራፍ (postseason) ሲፋለሙ፣ የውድድሩ ድባብም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሟሟቀ ይሄዳል። ለማንኛውም MCPS የውድድር አመት ማብቂያ (postseason) ዝግጅት ትኬቶችዎንእዚህ ያግኙ!

ለሚከተሉት የካውንቲ ሻምፒዮናዎች ከእኛ ጋር ይሁኑ፦

  • Field hockey – ሰኞ፣ ኦክቶበር 26 አልበርት አይንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 6 p.m.
  • እግር ኳስ/Soccer – ሰኞ፣ ኦክቶበር 26 ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሴቶች 5:30 p.m. / የወንዶች 7:15 p.m.
  • ቮሊቦል – ሰኞ፣ ኖቨምበር 2 ኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 3፡30 p.m.

MPSSAA ድረ-ገጽ ላይ የሚገኘውን የስፖርት ድረገጽ በመጎብኘት፣ የሚወዷቸውን ቡድኖች እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ይከታተሉ፤ እንዲሁም የቅርብ ጊዜ መርሐ ግብሮችን፣ የውድድር ሰንጠረዦችን፣ የተጋጣሚዎችን ዝርዝር፣ ውጤቶችን እና የሻምፒዮና መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ። 

ማሳሰቢያ፦ በሪጅናል እና በስቴት ደረጃ በሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ የሚፈቀደው MPSSAA ማለፊያ ካርድ (passes) ያሏቸው ሰዎች ብቻ ናቸው። 

 
ማሳሰቢያዎች፦   ማሳሰቢያዎች፦
  • Game Changer Conference፦ 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ወንድ ተማሪዎች፣ ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 24፣ ከጠዋቱ 8 a.m.-noon (እኩለ ቀን) ድረስ፣ ጀርመንታወን በሚገኘው ሞንትጎመሪ ኮሌጅ - ጀርመንታወን ካምፓስ፣ ባዮሳይንስ ትምህርት ማዕከል (Bioscience Education Center)፣ 20200 Observation Drive በሚካሄደው ዝግጅት ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ይመዝገቡ
  • የማርቺንግ ባንድ ትርዒት፡ ቅዳሜ ኦክቶበር 24 በ 11:30 a.m በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይጀምራል። ነጻ እና ለህዝብ ክፍት የሆነ።
  • የሜሪ ሃዋርድ የአገልግሎት ቀን፡ ቅዳሜ ኦክቶበር 24 ከ 8 a.m.-1 p.m። ፕሮጄክቶቹ የአትክልት ቦታዎችን እና ድንኳኖችን ማስዋብን፣ ዱካዎችን መንከባከብን እና የግንባታ ፕሮጀክቶችን ያካትታሉ። ይመዝገቡ/RSVP.  
  • የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክረምት/ዊንተር ስፖርቶች ምዝገባ፡ ለወንዶችና ለሴቶች የቅርጫት ኳስ፣ ሰኞ፣ ኦክቶበር 26 ከቀኑ 12 ሰዓት (ቀትር) ላይ ይከፈታል።
  • የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ኤግዚቢሽን፡ ቅዳሜ ኖቬምበር 14 በጄምስ ሀበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ 10 a.m.-1 p.m። ነፃ እና ለሰራተኞች፣ ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ክፍት ነው።
 
ከመማሪያ ክፍል ውጭ   ከመማሪያ ክፍል ውጭ
  • *አዲስ* ሁሉም የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለዘንድሮው የትምህርት አመት ከትምህርት ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎቻቸው ዝርዝር ላይ የመጨረሻ ማሻሻያዎችን አድርገዋል። ዝርዝሩ እዚህ ይገኛል።
  • *አዲስ* USG Lab Crawl፦ በምህንድስና፣ በቴክኖሎጂ፣ በጤና ወይም በስነ ህይወት ሳይንስ ላይ ፍላጎት ላላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው። በተግባር ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎች እና በተግባቦት የማስመሰል ልምምዶች፣ በእነዚህ ዘርፎች መማር እና መስራት ምን እንደሚመስል ይቃኙ። ዝግጅቱ ሰኞ፣ ኖቬምበር 2 ከጠዋቱ a.m.-3 p.m. በሮክቪል ይካሄዳል አድራሻ፦ the Universities at Shady Grove, Building IV, 9631 Gudelsky Drive in Rockville. ይመዝገቡ/Register.
  • የC-SPAN 'StudentCam Documentary Competition' ዶክመንተሪ ውድድር፡ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች፣ C-SPAN በየዓመቱ በሚዘጋጀው እና ማህበረሰባችንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በጥልቀትና በሂሳዊ አስተሳሰብ እንዲያስቡ በሚያበረታታው፣ ብሔራዊ የቪዲዮ ዶክመንተሪ ውድድር (StudentCam) ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በዚህ አመት ተማሪዎች ከውድድሩ ጭብጥ ጋር የሚገናኝ ርዕስ ላይ ከአምስት እስከ ስድስት ደቂቃ የሚፈጅ የቪዲዮ ዶክመንተሪ ሠርተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፣ የውድድሩ ጭብጥም“Mr. Speaker, I Rise To …”. የመጨረሻ ቀን፡ ረቡዕ፣ ጃንዋሪ 20, 2027።
  • የቪዲዮ ውድድር፦ "ድምጽዎን ያሰሙ፣ ህይወትን ይታደጉ" - በታዳጊዎች ዘንድ እየተስፋፋ ስላለው ህገ-ወጥ ኦፒዮይድስ፣ ከመጠን በላይ ስለመውሰድ (overdose) እና ስለ ፌንታኒል (fentanyl) አደጋዎች ግንዛቤን የሚያሳድግ ኦሪጅናል የቪዲዮ ውድድር ያዘጋጁ። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት/ SSL ሰዓቶች ማግኘት ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ ለወጣ $5,000፣ ለሁለተኛ $3,000 እና ለሦስተኛ $1,000 ሽልማት ይሰጣል። የመጨረሻው ቀን ሰኞ፣ ኖቬምበር 30ነው።መወዳደሪያውን ያቅርቡ።
  • ለአሜሪካ ያለዎትን ራዕይ ያጋሩ፡ ከ5ኛ-12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች አሁን ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተመረጡ እና የመክፈቻ ንግግራቸውን በ2-3 ደቂቃ ቪዲዮ እያቀረቡ እንደሆነ እንዲያስቡ የንግግር ጥሪዎን ያቅርቡ። እስከ 1,000 ዶላር የሚደርሱ ሽልማቶችን ያሸንፉ።ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ መወዳደሪያው መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ አርብ፣ ኦክቶበር 30ነው።
  • የ Smokey Bear ፖስተር ውድድር፡የሜሪላንድ ደን አገልግሎት ለ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የእሳት መከላከል ወር Smokey Bear ፖስተር ውድድር ስፖንሰር እያደረገ ነው። ተማሪዎች "የዱር ሰደድ እሳትን መከላከል የሚችሉት እርስዎ ብቻ ነዎት!"/“Only YOU can prevent wildfires!” የሚለውን ታዋቂ መልእክት መነሻ በማድረግ ኦሪጅናል የጥበብ ሥራ ፈጥረው እንዲወዳደሩ ተጠይቀዋል። የዱር ሰደድ እሳት ደህንነትን እና የደን ጥበቃን ለመዳሰስ የመጨረሻው ቀን፦ ሰኞ፣ ኖቬምበር 2ነው።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
  • Capital Weather ከመዋእለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን፣ ስለ አየር ሁኔታ፣ ስለ ወቅቶች፣ ስለ አየር ንብረት ወይም በተፈጥሮ ተመስጠው የፈጠሯቸው ኦርጅናል ስራዎችን ለልጆች የጥበብ ማሳያ ዝግጅት እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
 

ዜና አምድ

 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools