ትምህርት ቤት ሊጀመር አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል፡ ስለ ትምህርት እንነጋገር
ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች
የትምህርት አመት 2026-2027 ሊጀመር አንድ ሳምንት ብቻ ቀረው! እርስዎም እንደኛ ጓጉተው እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ - ጥሩ የትምህርት ዓመት ይሆናል።
ባለፈው ሳምንት፣ ስለ ደህንነት እና የትምህርት ቤቶቻችንን ደህንነት ስለመጠበቅ ሁላችንም ስለምንጋራው ኃላፊነት ጽፌላችኋለሁ። በዚህ ሳምንት፣ ስለ MCPS ዋና ተልዕኮ፡- ማስተማር ወሳኝ መረጃዎችን ማካፈል እፈልጋለሁ።
ትምህርት ዋና ትኩረታችን ነው፣ ስለዚህ MCPS የመገኘቱ ምክንያት እርስዎን እና ቤተሰብዎን ለማገልገል ነው። ልጆቻችሁ በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ፣ ትምሕርታቸውን እንዲጋፈጡና፣ አዲስ እውቀት እንዲቀስሙ፣ በራስ መተማመንን እንዲገነቡ፣ ግንኙነቶችን እንዲያዳብሩ እና MCPS ለቀጣዩ ተግባር ዝግጁ እንዲሆን እንፈልጋለን። ከእኛ ጋር ስለምትተባበሩ እና ስለልጆቻችሁ እምነት ስለጣላችሁብን እናመሰግናለን።
ዛሬ የትምህርት አመቱ ከመጀመሩ በፊት ማወቅ ያለብዎትን አንዳንድ ተግባራዊ ነገሮችን ማንሳት እፈልጋለሁ።
ለአንዳንድ ተማሪዎች፣ ትምህርት የሚጀምረው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሲሆን ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ የሚደረግ ነው።
ሰኞ፣ ኦገስት 24፣ ሁለተኛው አመታዊ የተማሪዎች የሽግግር ቀን ሲሆን ይህም ለመዋዕለ ሕፃናት፣ ለስድስተኛ እና ለዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች፣ በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችን ወደ ሶስተኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች እና ለትምህርት ቤቶቻቸው አዲስ ለሆኑ ተማሪዎች የመጀመሪያው ሙሉ የትምህርት ቀን ነው። ይህ ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ከመምጣታቸው በፊት ቅድሚያ ሰጥተው እንዲዘጋጁ ታስቦ የተዘጋጀ ሙሉ የትምህርት ቀን ነው።
ይህን ያደረግነው ለምንድነው? ጥናቶች፣ የራሳችን፣ የወላጆች እና የመምህራን ተሞክሮ በግልፅ እንደሚያሳዩት፡- በተለይም ስድስተኛ እና ዘጠነኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች የሚዛወሩ ተማሪዎች ጭምር ብዙውን ጊዜ በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ ሊያዳግታቸው ይችላል። እንዲሁም በክፍላቸው ውስጥ በሌሎች ተማሪዎች ትኩረታቸውን ሳይከፋፍሉ ትርጉም ያለው የሽግግር ወቅት ያሳለፉ ተማሪዎች በአመቱ የተሻለ ውጤት እንደሚያስመዘግቡ እናውቃለን። የአዳዲስ ህንጻዎች ምደባ፣ አዲስ የጊዜ ሰሌዳዎች፣ አዳዲስ ጓደኞች፣ አዳዲስ የትምህርት ባለሙያዎች - ሁሉም ለልጆቻችን በጣም አዲስ ሊሆንባቸው ይችላል እና በሽግግር ቀናት በጥንቃቄ በተዘጋጁ እንቅስቃሴዎች ይህንን ውጥረት ለመቀነስ በተሻለ ሁኔታ መምራት እንችላለን። ይህ ወደ አዲስ ትምህርት ቤቶች ለሚሸጋገሩ ተማሪዎቻችን የተሻለ ስኬት የሚያስገኙላቸውን በራስ መተማመን እና ምቾት ለመስጠት ትልቅ እድል ነው። በሌላ አነጋገር፣ የመጀመሪያው ቀን ያለምንም ውጥረት የበለጠ ምቹ አቀባበል እንዲሆንላቸው እንፈልጋለን። እዚህ የበለጠ ይወቁ እዚህ ቪዲዮ ይመልከቱ እንግሊዝኛ / ስፓንሽኛ
የትምሕርት ውጤት አሰጣጥን የበለጠ ግልጽ እና ወጥነት ያለው እንዲሆን እያደረግን ነው።
በዚህ አመት የትምሕርት ውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት ማድረግ ላይ አንዳንድ አስፈላጊ ለውጦች ይደረጋሉ። የቤት ሥራዎች በተማሪ StudentVUE እና ParentVUE ላይ ተጠናቀው መቅረብ ያለባቸው ቀናትን እና የጊዜ ገደቦችን (ክሬዲት ለማኘት የመጨረሻው ሥራ መቅረብ ያለበት ቀን) በግልጽ ተለይቶ ይገለጻል፤ አንድም የቤት ሥራ ወይም ምዘና ከማርክ-መስጫ ወቅት ውጤት 20 በመቶ በላይ ሊይዝ አይችልም፤ የልምምድ እና የዝግጅት የቤት ሥራ 10 በመቶ በላይ ሊይዝ አይችልም፤ እና ተማሪዎች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት ብቁ ያልሆኑበትን ምዘናዎች እንደገና ለመውሰድ ወይም ለመከለስ ቢያንስ ሁለት እድሎች ይኖራቸዋል። በተጨማሪም ዘግይቶ መሥራት፣ ረዘም ያለ ጊዜ አኮሞዴሽን፣ ከትምምህርት መቅረት፣ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አጠቃቀም ዙሪያ ግልጽ የሆኑ ተጠባቂ ሁኔታዎች ይኖራሉ።
እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ
ምዘናዎች ሙከራዎች ናቸው እንጂ ማደናቀፊያ አይደሉም።
የትምሕርት ምዘናዎች ተማሪዎች የሚያውቁትን፣ የቀሰሙትን፣ እና ማድረግ ስለሚችሉት ነገር ለሁላችንም መረጃ ይሰጡናል። በተጨማሪም ልጅዎ በትምሕርት እያደገ እንደሆነ (በአካዳሚክ ደረጃ) እና ምን አይነት ተጨማሪ እርዳታ ሊፈልግ እንደሚችል ያሳዩናል። እነዚህ ነገሮች ልጆችን የሚገልጹ ወይም እያንዳንዱን የፈተና ቀን ወደ ከፍተኛ ውጥረት የሚያስከትል ክስተት ለመቀየር የታሰቡ አይደሉም። ልጅዎ እንዴት እየሰራ(ች) እንደሆነ በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎችን ለማቅረብ ቁርጠኛ ነን - ይህ አጋርነታችንን ለማጠናከር ማሻሻል እንዳለብን የምናውቀው ዘርፍ ነው።
በዚህ ዓመት፣ ለቤተሰቦች የትምሕርት ግምገማ የቀን መቁጠሪያ እናቀርባለን፣ ስለዚህ ምን እንደሚከተል ማየት እና አስቀድማችሁ ማቀድ ትችላላችሁ። ጠቃሚ ምክሮቻችን፡- የተለመዱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ያከናውኑ፣ ልጅዎ በቂ እንቅልፍና ቁርስ እንዲያገኝ ያድርጉ፣ ጥረቱን ያበረታቱት፣ እና እባክዎን ቴስት ሲኖር ወደ "ማድረግ ወይም አለማድረግ" ስጋት አትለውጡት። ስለ ትምሕርት ምዘናዎች ጥያቄዎች ካሉዎት፣ የልጅዎን አስተማሪ ለመጠየቅ አታመንቱ። እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ
ልጅዎ የሚማራቸውን/የምትማራቸውን ነገሮች ይከታተሉ።
ልጅዎ የሚማረውን/የምትማረውን ማወቅ በቀላሉ እንዲከታተሉ፣ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ እና በቤት ውስጥ እንዲማሩ ለማድረግ ይረዳቸዋል። ባለፈው የትምህርት ዓመት ተማሪዎች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት ምን እንደተማሩ፣ ዋና ዋና ርዕሶችን፣ ጭብጦችን፣ እና ጽሑፎችን ጨምሮ፣ ቀላል፣ አንድ ገጽ ያለው ጽሑፍ ለቤተሰቦች በሪፍሪጅሬተር የሚለጠፍ የሥርዓተ ትምህርት አጭር መግለጫ አቅርበናል። የትምሕርት አመት 2026-2027 በሪፍሪጅሬተር የሚለጠፍ የሥርዓተ ትምህርት አጭር መግለጫ እዚህ ተመልከቱ።
ጥሩ የጥናት ልምዶች ይገነባሉ።
ቤተሰቦች ለትምሕርት ሊያደርጉት ከሚችሏቸው ምርጥ ነገሮች እንደ አልጀብራ፣ ኬሚስትሪ፣ ወይም የዛሬ ማታ የቤት ስራ መልስ የመሳሰሉ የላቀ ይዘት እውቀት አያስፈልጋቸውም። ልጅዎን በትምህርት ለመርዳት ከሚያስችሉት ምርጥ መንገዶች አንዱ በቤት ውስጥ መደበኛ የዕለት ተዕለት የትምሕርት ትግበራዎችን መገንባት ነው።
በቤት ውስጥ ለመማር መደበኛ ጊዜ እና ቦታ ያዘጋጁ እና በዚያ ቀን በትምህርት ቤት ስለተማረ(ች)ው ነገር ተነጋገሩ/ይጠይቁ። በየጊዜው ከትምህርት ቤት የሚሰጡትን ወረቀቶችን እና የሚሰሩ ስራዎችን ይመልከቱ - ለተማሪዎች በእያንዳንዱ ክፍል ይህ ሊደረግ ይችላል። ትላልቅ ስራዎችን ወደ ትናንሽ ስራዎች በመከፋፈል ማገዝ ይችላሉ። እርዳታ ከመስጠትዎ በፊት ልጅዎ ጥያቄዎችን እንዲጠይቅ/እንድትጠይቅ እና ፕሮብሌሞችን እንዲፈታ/እንድትፈታ ያበረታቱት። የሚያደርጋቸውን/የምታደርጋቸውን ጥረቶች አወድሱ - ፍፁምነትን መጠበቅ አያስፈልግም። በተጨማሪም፡ ልጅዎን ከሚደግፉ አስተማሪዎች እና ከሌሎች አዋቂዎች ጋር አዘውትረው ይገናኙ።
ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች፣ እነዚህ የዕለት ተዕለት ተግባራት የበለጠ አስፈላጊ ናቸው። የተያያዘው መመሪያ በቤት ውስጥ IEP እና 504 ድጋፎችን ለማጠናከር፣ የራስን ጥረት ለማበረታታት፣ እና ተማሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሳቸውን ችለው መሥራት እንዲችሉ የመርዳት ሀሳቦችን ያካትታል። ምንም እንኳን አባሪ የተደረገው ልዩ ድጋፍ የሚያገኙ ተማሪዎችን በመርዳት ላይ ያተኮረ ቢሆንም፣ ይህ መመሪያ ለሁሉም ተማሪ ይሠራል። ትናንሽ ተሞክሮዎች ተዳምረው በእርግጥ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። እዚህ የበለጠ ይወቁ (ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች)።
ግንኙነት እንዳለዎት እርግጠኛ ይሁኑ
ስለ ልጅዎ ትምህርት መረጃ ለማግኘት መኳተን የለብዎትም።
MCPS ቤተሰቦች በትምህርት ዓመቱ በሙሉ ስለ ትምሕርት ውጤቶችን ለማየት/ለማወቅ፣ ስለተመደቡ የትምሕርት ስራዎች፣ ስለ ጊዜ ሰሌዳዎች፣ ከትምህርት ቤት እና ከዲስትሪክት ስለሚላክላቸው መልእክቶች፣ ስለ ምግብ እና ስለ ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ለማግኘት የሚጠቀሙባቸው ኦፊሴላዊ ዲጂታል መገልገያዎች አሉት። ስለ ኦፊሴላዊ MCPS መተግበሪያዎች እዚህ የበለጠ ይወቁ ኦፊሴላዊ MCPS መተግበሪያዎች እና ዲጂታል መተግበሪያዎች፣ እያንዳንዳቸው ምን እንደሚያደርጉ እና ለቤተሰብ ጥቅም የተዘጋጁ እያንዳንዱን መተግበሪያዎች እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ቀላል መመሪያን ይጠቀሙ።
ቴክኖሎጂ የእርስዎ ሙያ ባይሆንም ችግር የለውም። ትምህርት ቤትዎን ይጠይቁ። ግንኙነት እንዲኖርዎት መርዳት እንፈልጋለን።
አንድ ሳምንት ብቻ ቀረው!
ተቃርበናል። የሚቀጥለው ሰኞ የሽግግር ቀን ሲሆን ማክሰኞ ደግሞ ለእያንዳንዱ ተማሪ የመጀመሪያው ሙሉ የትምህርት ቀን ይሆናል። ይህንን ሁሉ ለመከታተል፣ እባክዎን ይህን ለቤተሰብ ተስማሚ የቀን መቁጠሪያ ቅጂ ያውርዱ ወይም ያትሙ።
አውቶቡሶቹ ይጓዛሉ፣ ካፍቴሪያዎች ይከፈታሉ፣ የመማሪያ ክፍሎች ይሞላሉ፣ እና አዲስ የትምህርት አመት በይፋ ይጀመራል። አስደሳች ቀናት ይሆናሉ። አስቸጋሪ ቀናትም ይኖራሉ። ምናልባት አንዳንድ ሰው ጠዋት ጫማውን ለማግኘት የሚቸገር ሊኖር ይችላል።
ትምህርት ቤት ነው። የቤተሰብ ጉዳይ ነው።
የእኛ ስራ ልጆቻችሁ ወደ ትምህርት ቤቶቻችን በር ሲገቡ የሚያውቃቸው፣ የሚያምኑበት፣ የሚያስተምሩ፣ እና እንዲያድጉ የሚያግዙ አዋቂዎች እንዲኖሩት ማረጋገጥ ነው። የእርስዎ አጋርነት ይህንን ለማድረግ የተሻለ ያደርገናል። ልጅዎን ወደ MCPS ስለላኩልን እና ከእኛ ጋር ስለተባበሩ እናመሰግናለን።
ባለፈው ሳምንት፣ ይህንን የትምህርት አመት በጣም አስተማማኝ እንዲሆን እንድታግዙን ጠይቄአችሁ ነበር።
በዚህ ሳምንት ደግሞ ጥሩ የትምህርት ዓመት እንዲሆንልን እንድታግዙን እጠይቃለሁ።
የቀረው አንድ ሣምንት ብቻ ነው በጣም ያጓጓል።
ከሠላምታ ጋር
Thomas W. Taylor, Ed.D., M.B.A.
Superintendent of Schools
ቶማስ W. ቴይለር ዶ/ር., M.B.A.
የት/ቤቶች ሱፐር ኢንተንደንት
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools
P.S. በሚመጣው የትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢት ላይ እናንተን ማየት እንፈልጋለን። በራሪ ወረቀቱን/flyer ተመልከቱ.
በራሪ ወረቀት/flyer
|