የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
 

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

 

ስለ ወደፊቱ ማቀድ፡ ሁለት ምዕራፎች፣ ለመሳተፍ በርካታ እድሎች ይኖራሉ

40 ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ MCPS የተማሪዎች ምዝገባ ቁጥር እየቀነሰ ነው። በዚህም ምክንያት፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው በላይ ቦታ ሲኖራቸው፣ ሌሎች ማህበረሰቦች ግን አሁንም በማደግ ላይ ናቸው። ይህ ማለት ትምህርት ቤቶቻችንን እና የተለያዩ ተቋሞቻችንን እንዴት እየተጠቀምንባቸው እንዳለ በሰፊው እና በጥልቀት የምንመረምርበት፣ እንዲሁም ለሁሉም ተማሪዎች የተሻለ የወደፊት ዕጣ ፈንታን የምናቅድበት ጊዜ አሁን ነው ማለት ነው። 

የዚህ ሥራ አካል እንደመሆኑ መጠን፣ MCPS አንዳንድ የአንደኛ ደረጃ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት እና ማጣመር ስለመቻላቸው ማጤን ያስፈልገዋል። አሁን የምንጀምረው፤ ውሳኔ የመስጠት ማዕቀፉን እንዲሁም ሊታሰብባቸው የሚገቡ መመዘኛዎች እና ጉዳዮችን በተመለከተ፣ መረጃዎችን በጥንቃቄ በመገምገምና ከማህበረሰቡ ጋር ትርጉም ያለው ተሳትፎ በማድረግ ነው።

ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት እና ውህደት የሚደረጉ ውይይቶች ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ ለሰራተኞች፣ እና ለማህበረሰቦች አስቸጋሪ እንደሚሆን እንገነዘባለን። በእያንዳንዱ ውሳኔ ላይ የተማሪዎችን ፍላጎት ማዕከል በማድረግ፣ ይህንን ሥራ በጥንቃቄ፣ በግልጽነት፣ እና በርህራሄ ለመወጣት ሙሉ በሙሉ ቁርጠኞች ነን።

ይህ ለምን አስፈላጊ ሆነ? ትምህርት ቤቶቻችንን እና ውስን ሀብታችንን በብቃት መጠቀም፣ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ተማሪዎች በሚፈልጉበት ቦታ ላይ በብዛት እንድናውል ያስችለናል፤ እነዚህም ጠንካራ የማስተማር ሂደት፣ ምርጥ ፕሮግራሞችን ማቅረብ እና እያንዳንዱ ተማሪ እንዲያድግና እንዲሳካለት የሚያግዙ አገልግሎቶችና ድጋፎችን ተደራሽ ማድረግ ናቸው። በጣም ትልቅ ወይም በጣም ትንሽ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች፣ በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች እጅግ ጥሩ የሆነ የትምሕርት ተሞክሮዎችን እንድናቀርብ ያግዙናል።

መታወቅ ያለበት አስፈላጊ ነገር፦ ይህ ስራ በሁለት የተለያዩ ደረጃዎች በሁለት አመት ውስጥ ይከናወናል።

በዚህ ዓመት = የመዝጋት እና የማጣመር ውሳኔዎች። ቀጣዩ ዓመት = የድንበር ውሳኔዎች።

ደረጃ 1፡ ውሂብ መረጃዎችን መገምገም እና ውሳኔዎችን መወሰን — 2026–2027
በዚህ የትምህርት አመት፣ MCPS በመላው ካውንቲው የሚገኙ የአንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ይገመግማል፤ በዚህም የተማሪዎች ምዝገባ፣ የህንጻ አጠቃቀም፣ የት/ቤት አቅም መጠን፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የፕሮግራም አወቃቀሮች እና ሌሎች ጉዳዮች ይታያሉ። ዓላማው፣ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ለትምህርት ቦርዱ እንዲዘጉ እና እንዲጣመሩ የሚገቡትን ትምህርት ቤቶችን ለይቶ መወሰን ነው።

በዚህ ምዕራፍ በመላው ካውንቲው የድንበር ወሰን ጥናት አይካሄድም።

ደረጃ 2፡ በመላው ካውንቲ የሚካሄድ የድንበር ማካለል ጥናት — 2027–2028
የመጀመሪያው ምዕራፍ ከተጠናቀቀ እና MCPS የተማሪዎቻችንን ቁጥር መጠን የሚመጥን ትክክለኛ የትምህርት ቤቶች ብዛት ከታወቀ በኋላ፣ MCPS ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላው ካውንቲው የሚካሄድ የአካባቢ ወሰን ጥናት እንዲሁም ለሚመለከታቸው መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የወሰን ማስተካከያ ሥራዎችን ይጀምራል።

የእርስዎ ድምፅ በአጠቃላይ ሂደቱ ውስጥ ወሳኝ አካል ነው። ቤተሰቦች፣ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች፣ እና የማህበረሰብ አባላት ስለ መረጃው ግንዛቤ ለማግኘት፣ ጥያቄዎችን ለማቅረብ፣ እና ስለ መለኪያ መመዘኛዎች እና ምክንያቶች አስተያየት ለመስጠት በርካታ እድሎች ይኖራቸዋል። በአካል እና ቨርቹዋል (በኦንላይን) አማራጮች የሚከናወኑ ሁለት ዙር የውይይት መድረኮች ታቅደዋል።

  • አንደኛ ዙር፦ ኦክቶበር 19–ኖቬምበር 2
  • ሁለተኛ ዙር፦ ኖቨምበር 30–ዲሰምበር 10
  • ሙሉውን የጊዜ ሰሌዳ እና የስብሰባ ቦታዎችን ከዚህ በታች ይመልከቱ። 

ይህ መጀመሪያው ነው። ለወደፊት ውይይቶች የሚከናወኑ በርካታ ሥራዎችና ዕድሎች አሉ። ደረጃ 1 እና 2 አፈጻጸም ትግበራ (መዝጋት፣ ማጣመር እና የአገልግሎት ክልል ድንበር መወሰን) 2029-2030 የትምህርት ዘመን ላይ ይጀመራል።

1ኛ ዙር

የማህበረሰብ ተሳትፎ ቀን

ዓይነት

የስብሰባ ሰዓት

የስብሰባ ቦታ

ሰኞ፣ ኦክቶበር 19

ቨርቹወል

ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 pm

ዙም (Zoom)

ሰኞ፣ ኦክቶበር 19

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ጌትስበርግ መካከለኛ/ደ/ት/ቤት Gaithersburg MS

ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 20

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ኪንግስቪው መካከለኛ ደ/ት/ቤት Kingsview MS

ሮብ፣ ኦክቶበር 21

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ሮዛ ፓርክስ መካከለኛ ደ/ት/ቤት Rosa Parks MS

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 22

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ኤ. ማሪዮ ሎይደርማን መካከለኛ ደ/ት/ቤት A. Mario Loiederman MS

ኣርብ፣ ኦክቶበር 23

ቨርቹወል

12:00-1:00 p.m.

ዙም (Zoom)

ሮብ፣ ኦክቶበር 28

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ጁሊዩስ ዌስት መካከለኛ ደ/ት/ቤት Julius West MS

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 29

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ኢስተርን መ/ደ/ት/ቤት Eastern MS

ኣርብ፣ ኦክቶበር 30

ቨርቹወል

ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m.

ዙም (Zoom)

ሰኞ፣ ኖቬምበር 2

ቨርቹወል

6:00-7:00 p.m.

ዙም (Zoom)

የቀለም ኮድ፦ አረንጓዴ = በኦንላይን የሚደረግ ቨርቹዋል ስብሰባ፤ ሰማያዊ = በአካል የሚደረግ ስብሰባ

2ኛ ዙር

የማህበረሰብ ተሳትፎ ቀን

ዓይነት

የስብሰባ ሰዓት

የስብሰባ ቦታ

ሰኞ፣ ኖቬምበር 30

ቨርቹወል

ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m.

ዙም (Zoom)

ሰኞ፣ ኖቬምበር 30

ቨርቹወል

6:00-7:00 p.m.

ዙም (Zoom)

ማክሰኞ፣ ዲሰምበር 1

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ኸርበርት ሁቨር መካከለኛ ደ/ት/ቤት Herbert Hoover MS

ረቡዕ፣ ዲሰምበር 2

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ሪጅቪው መካከለኛ ደ/ት/ቤት Ridgeview MS

ሐሙስ፣ ዲሰምበር 3

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ኒውፖርት ሚል መ/ደ/ት/ቤት Newport Mill MS

አርብ፣ ዲሰምበር 4

ቨርቹወል

ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m.

ዙም (Zoom)

ሰኞ ፣ ዲሴምበር 7

ቨርቹወል

ከቀትር 12:00 እስከ 1:00 p.m.

ዙም (Zoom)

ማክሰኞ፣ ዲሰምበር 8

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ቤንጃሚን ባንከር መ/ደ/ት/ቤት Benjamin Banneker MS

ረቡዕ፣ ዲሰምበር 9

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ሮኪ ሂል መካከለኛ ደ/ት/ቤት Rocky Hill MS

ሐሙስ፣ ዲሰምበር 10

በአካል

6:30-8:30 p.m.

ፓርክላንድ መ/ደ/ት/ቤት Parkland MS

የቀለም ኮድ፦ አረንጓዴ = በኦንላይን የሚደረግ ቨርቹዋል ስብሰባ፤ ሰማያዊ = በአካል የሚደረግ ስብሰባ

 

በዚህ አድራሻ ኢሜል አድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org