Is this email not displaying correctly? View it in your browser

mcps logo

All In Header Image

 

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

 

 

officer icon

ይሄ በ Albany, N.Y., የሚኖረው የልጄ ልጅ ኤፕሪል 2 በምዋእለ ህጻናት ክፍል ውስጥ እያለ የተነሣ ፎተግራፍ ነው። እርሱ ከሌሎች አምስት የልጅ ልጆቼ ጋር፣ New York፣ Indiana፣ እና Maine፣ እቤታቸው ሆነው ይማራሉ። እዚህ በሞንትጎመሪ ካውንቲ እንዳለው አይነት እነርሱም ተመሣሣይ ለውጥን እየተለማመዱ ናቸው። በእርግጥ፣ በአንፃራዊ ከአገሪቱ በጠቅላላ ይሄ አይነት ምስል ሊመጣ ይችል ነበር። እኔ ይህንን የቤተሰቤን ፎተግራፍ ለእናንተ ማጋራት የፈለግሁበት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ያለንበት ዓለም ሁኔታ ለእኔ ፕሮፌሽናል ልምምድ ብቻም ሣይሆን በግል ያለሁበት ሁኔታም መሆኑን ለመግለጽ ነው።

የእኔ የልጅ ልጆቼ እድለኞች ናቸው። የሚያግዟቸው ጠንካራ ሲስተሞች እና እስካሁን ድረስ ገቢ የሚያገኙ ወላጆች አሏቸው። ሁሉም ልጆች እና ቤተሰቦች በደህና ሁኔታ አይደሉም። ለሁሉም ልጆች፣ በተለይም ላልታደሉት፣ የትምህርት ቤቶቻችን ሠራተኞች በጣም ያስፈልጓቸዋል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ውስጥ በአስገራሚ ሁኔታ ህይወታቸውን ለመለወጥ የሚያስችል መሠረታዊ-አስፈላጊ ትምህርት እና አገልግሎቶችን እንሰጣቸዋለን።

ባለፈው ሣምንት፣ ከ Damon Monteleone, Todd Stillman እና Elizabeth Pierce ከሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በነዚህ ያልታሰቡ ከባድ ጊዜያት ተማሪዎቻቸውን ለማገልገል ትምህርት ቤታቸው እንዴት እየሠራ እንደሆነ በ” talkover Zoom” የመነጋገር እድል ነበረኝ። ውይይታችንን እዚህ here መመልከት ትችላላችሁ። እነርሱ እያደረጉ ያሉት ጥረት በካውንቲያችን ታስቦበት የሚደረግ እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የተሠማራበት ጥረት መሆኑን ያመለክታል-ይገልጻል።

officer icon

ከዚህ በተጨማሪ ማንነቱ(ቷ) እንዲገለጽ ካልፈለገ(ች) አስተማሪዎቻችን ባለፈው ሣምንት አንድ መልእክት አግኝቻለሁ። ስሜት የሚነካ እና እውነተኛ ስለሆነ ላካፍላችሁ እወዳለሁ።

“ባለፈው ሰኞ ማርክ መስጠት የሚያስፈልጉ አንዳንድ ፈተናዎችን ለመውሰድ ወደ Churchill በሄድኩ ጊዜ፣ ባዶ በሆነ የት/ቤት ጊቢ ሳልፍ ትምህርት ቤቱ እንዲሁ ባዶ ህንጻ ብቻ ሆኖ አየሁ። የተለመደውን የት/ቤት ይዘት አጥቷል፣ መተላለፊያ ላይ ምሣ የሚበሉ ልጆች ጫጫታ፣ ከልጆች ጋር የሚያወሩ መምህራን፣ እና የተለመደው የት/ቤት ግርግር አይታይበትም። እንደእውነቱ ከሆነ፣ ትምህርት ቤት የሚያሰኘው ህይወት የሌለው ሆኗል፣ ያንን አይነት ህንፃ አሁን የለንም። እና ያ ለሁላችንም ትልቅ እጦት ነው። በርካታ ልጆች እና ሠራተኞች እኔ ራሴንም ጭምር ይህንን በማጣታቸው እያዘኑ ናቸው።"


“ነገር ግን ወደኋላ ልመለስና፣ ሁላችንም በዚህ ዓለም አቀፍ ቀውስ ውስጥ እየተጫወትን መሆናችንን እመለከታለሁ። በልጆቻችንን ህይወት የተረጋጋ ክፍል ልንሆን እንችላለን። ማየት የሚፈልጉት አይነት የጸና እና ፍትህ ያለው መገንዘብ የሚችል አዋቂ/ጎልማሳ ልንሆን እንችላለን። ህይወት ያለው የትምህርት ልምዳቸው በእርግጠኝነት ህንጻው አለመሆኑን እና እውነተኛው ህይወት ያለው የትምህርት ክንውን እኛ ከእነርሱ ጋር ያለን ግንኙነት መሆኑን ልናሳያቸው እንችላለን።

የተማሪዎቻችንን የመማር ጥረትና ፍላጎት እንዳይደናቀፍ/ to ensure the “soul” of the learning experience is not lost for our students አሁን እያደረጉት ስላለው ጥረት እና ወደፊት ለመግፋት በሚያሳዩት ከፍተኛ ትጋት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞችን በሙሉ ለማመስገን እወዳለሁ። አስቸጋሪ ሁኔታ እየተጋፈጥን ብንሆንም፣ ተማሪዎቻችንን የሚጠቅሙ መፍትሔዎችን በመፍጠር የሚደረጉትን ጥረቶች ማየት እንዴት የሚያበረታታ ነው። አስፈላጊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ሁሉ ይህንን እናደርጋለን።

 

Superintendent Jack R. Smith
ከሱፐርኢንተንደንት ጃክ አር. ስሚዝ ዶ/ር

Important Online Resources: