የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች፡-
በነገው ቀን፣ ጁን 29/2020፣ የትምህርት ቦርድ በ MCPS የሠመር እና የፎል ትምህርት ማገገሚያ እቅዶች ላይ እያካሄደ ያለውን ውይይት ይቀጥላል። ይህንን አስፈላጊ ውይይት እንድትከታተሉ እናበረታታለን። ስብሰባው የሚጀምረው በ 3:30 p.m. ሲሆን በ MCPS ድረ-ገጽ እና በ MCPS TV (Comcast 34፣ Verizon 36፣ RCN 89) በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። ትምህርት በድጋሚ ስለሚከፈትበት ጥረት ጁላይ 14 ቦርዱ በሚያካሄደው የሥራ ስብሰባ ውይይት ይቀጥላል። ማሳሰቢያ፦ ግባችን ፋሲሊቲዎችን እና የትምህርት ቤት ህንፃዎችን እንደገና ስለሚከፈቱበት እቅድ ማእቀፍ -framework of the plan እና ሌሎችንም አስፈላጊ ጉዳዮችን በጁላይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ከማህበረሰብ ጋር መወያየትና ሃሳቦችን መጋራት ነው። ስለፎል 2020 አጠቃላይ እቅድ ለመገንባት ብዙ ጥረት በምናደርግበት ጊዜ ስለምታበረክቱት ተሳትፎ እና ስለ ትዕግስታችሁ እናመሰግናለን።
ከዚህ በታች የተገለጹት፦ ስለ ፎል 2020 ከወላጆች/ከሞግዚቶች የሚሰበሰብ የዳሰሳ ጥናት፣ ስለ ሠመር የምግብ አገልግሎት እቅድ፣ በ MCPS ፋሲሊቲዎች ስለህፃናት እንክብካቤ፣ እና ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተመጻህፍት (MCPL) የሠመር ምንባብ ፕሮግራም የመሣሠሉት ማሳሰቢያዎች እና ወቅታዊ መረጃዎች ናቸው።
ከማክበር ሰላምታ ጋር፣
Jack R. Smith, Ph.D.
Superintendent of Schools
ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)
የት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ
ፎል 2020 ዳሰሳ፦ የእርስዎ ግብረመልስ አስፈላጊ ነው!
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለፎል እየተዘጋጀ ባለው የዲስትሪክቱ የማገገሚያ እቅድ መካተት ያለባቸውን ቁልፍ ጉዳዮች በተመለከተ ከማህበረሰብ አስተያየቶችን ለማሰባሰብ የዳሰሳ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል። ይህን ዳሰሳ በሚሞሉበት ወቅት፣ የርቀት ትምህርት መቀጠልን ጭምር፣ የተቀናጀ ፊት-ለ-ፊት በአካል ማስተማር እና አንዳንድ የርቀት ትምህርቶችን በጣምራ ማካሄድ፣ እና የአካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና የተሻሻለ የጤና አጠባበቅና መከላከል መስፈርቶችን በመጠበቅ በአካል ትምህርት መስጠት የመሣሠሉትን የተለያዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ እንደምናስገባ እባክዎ ግንዛቤ ይኑርዎት።
ይህን ዳሰሳ ለመሙላት ከ 10 እስከ 15 ደቂቃ ሊወስድ ይችላል። በዚህ ዳሰሳ ላይ ያሉት ጥያቄዎች በሙሉ ግዴታ ያልሆኑ ናቸው። እርስዎ የሚሰጡት ምላሽ ይፋ የማይሆን ሲሆን የማጠቃለያ ሃሳቡ ብቻ ሪፖርት ይደረጋል። እባክዎ ዳሰሳውን ጁላይ 8፣ ከ 7 p.m. በፊት ሞልተው ይመልሱ።
የወላጅ ዳሰሳ ጥናት ይሙሉ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሠመር የምግብ አገልግሎት ፕሮግራም በነፃ ምግቦችን ይሰጣል።
ከጁላይ 6/2020 ጀምሮ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የቁርስ እና የምሣ ምግቦችን ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጆች እና ለ MCPS ተማሪዎች በሙሉ (እድሜ ሳይለይ) በካውንቲው ከ60 በላይ የ MCPS ጣቢያዎች እና ማህበረሰብን-መሠረት ያደረጉ 30 ፕሮግራሞች አማካይነት ይከፋፈላል። ምግቦቹ የሚከፋፈሉት፦ በ MCPS ጣቢያዎች ከ 10 a.m.–noon/እስከ እኩለቀን በትምህርት ቤት ጣቢያዎች ሲሆን ከ 9–10 a.m. በአውቶቡስ የማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ይከፋፈላል። ከ MCPS ትምህርት ቤት፣ ተንቀሳቃሽ ወይም በአውቶቡስ ከሚታደልባቸው ጣቢያዎች ምግቦችን ለመቀበል ተማሪዎች/ቤተሰቦች መታወቂያ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም። የምግብ ሥርጭት የሚካሄደው በሣምንት አራት ቀን ይሆናል፦ ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ እና ዓርብ። የበለጠ መረጃ ለማግኘት እና በሙሉ የጣቢያዎችን ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
በ MCPS ፋሲሊቲዎች የሚካሄድ የህፃናት እንክብካቤ
የትምህርት ቤት ህንፃዎች መዘጋታቸው የህፃናት እንክብካቤ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያስከተለውን ትልቅ ጫና እንገነዘባለን። እንደገና የሚከፈትበትን ሁኔታ ለመተግበር፥ በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት፣ በካውንቲው ወቅታዊ የጤና ሁኔታ፣ እና በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ያለመጠናቀቅ የሚገድቡ መሆናቸውን እንዲገነዘቡ እንፈልጋለን። እንዴት እና የት የህፃናት እንክብካቤ መስጫዎችን ለመክፈት እንደሚቻል እና እንደሁኔታው በሠመር ፕሮግራሞች፣ ለተማሪዎች፣ በህንፃዎቹ አቅም እየተመጠነ፣ ትምህርት ቤቶችን ፎል ላይ እደገና የመክፈት ዝግጅት ሥራን በሚመለከት ለመወሰን በመጪዎቹ ሣምንታት፥ ከአካባቢ የጤና ሃላፊዎች ጋር እና የህፃናት እንክብካቤ ሰጪዎች ጋር አብረን እንሠራለን። በሙሉ የህፃናት እንክብካቤ ሰጪዎች ከህንፃዎቹ አቅም ባነሰ ሁኔታ መመጠን እና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የመሣሠሉ የ MSDE እና ሌሎችም የስቴት እና የአካባቢ የጤና መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተመጻህፍት የሠመር ምንባብ ፕሮግራም-"MCPL Summer Reading Program" ለ MCPS ተማሪዎች በሙሉ ክፍት ተደርጓል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተመጻህፍት (MCPL) እስከ ኦገስት 31/2020 በሚካሄደው የዚህ ዓመት የሠመር ምንባብ ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ እንዲሣተፉ ተጋብዘዋል። የዚህ ዓመቱ መሪ ቃል “Imagine Your Story” የሚለው ነው። ፕሮግራሙ ለልጆች እና ለጨቅላ ወጣቶች በጣም ጥሩ መጻህፍት በማንበብ እና በደስታ፣ በቀልድ፣ በጨዋታ የሠመርን ወቅት እንዲያሳልፉ እድል ይሰጣል። ተማሪዎች ባጆችን እና ሽልማቶችን እንዲሁም የቁሳቁስ ሎተሪዎችን የማግኘት እድል ይኖራቸዋል። ይበልጥ መረጃ ለማግኘት እና ልጅዎን ለማስመዝገብ ይህንን የ MCPL ድረ-ገጽ ይጎብኙ።
|