ሀሙስ መታወቅ ያለባቸው ነገሮች መልእክት /ፌብሩዋሪ 10፣ 2022

ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 10፣ 2022 ማወቅ ያለብዎት ሰባት ነገሮች እነሆ። ይኼውም፦
ቋሚ ሱፐርኢንተንደንት መሾም፣ ስለትምህርት ቤት ደህንነት መረጃ፣ የሠላም እና የደህንነት ግምገማ፣ የፀረ ዘረኝነት ኦዲት ወቅታዊ መረጃ፣ ስለ ኮቪድ-19 ቤት ውስጥ የሚጠቀሙበት ፈጣን የምርመራ ዕቃዎች እና ሌሎችንም ያካትታሉ።

  1. የትምህርት ቦርድ ታሪካዊ በሆነ መግለጫ ቀጣዩን ሱፐርኢንተንደንት መሾሙን አሳውቋል።

ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክከኒት (Dr. Monifa B. McKnight) ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 8 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ቋሚ ሱፐርኢንተንደንት በመሆን ተሹመዋል። የትምህርት ቤቶችን ዲስትሪክት በመምራት ረገድ የመጀመሪያዋ ሴት እና ሁለተኛ አፍሪካዊት አሜሪካዊት ናቸው። ዶ/ር ማክኒት (Dr. McKnight) ከጁላይ 1፣ 2022 ጀምሮ ከጊዜያዊ ኃላፊነት ወደ MCPS ሱፐርኢንተንደንትነት ቋሚ የኃላፊነት ቦታ ይሸጋገራሉ። እርሳቸው በህዝብ ትምህርት ቤቶችአስተማሪነት እና አስተዳዳሪነት የ 23 አመት ልምድ ያካበቱ ሲሆን፣ አብዛኛውን ሲሰሩ የቆዩት በ MCPS ውስጥ ነው።

ዶክተር ማከኒይት (Dr. McKnight) ለማህበረሰቡ ያስተላለፉትን መልዕክት ያንብቡ።

  1. የሉም ወደ 10 ቀን ቨርቹወል የትምህርት ጊዜ የተሸጋገሩ የ MCPS ትምህርት ቤቶች

በሚቀጥለው ሳምንት ምንም ተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ወደ ቨርቹወል ትምህርት አይሸጋገሩም። MCPS ኮቪድ-19 በት/ቤት ስራዎች እና በአካል በመማር ላይ ያለውን ተፅእኖ መከታተል እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጊዜያዊነት ወደ በርቹወል ትምህርት መሸጋገር ያለባቸውን ትምህርት ቤቶችን መለየት ይቀጥላል።

  1. በሁሉም ትምህርት ቤቶች ውስጥ MCPS ስለ ት/ቤት ሠላም እና ደህንነት ጠለቅ ያለ ግምገማ በማካሄድ ላይ ነው

በቅርብ ሳምንታት ውስጥ፣ የዲስትሪክቱ ሰራተኞች ይህን ስራ ለማሳወቅ በሕዝብ ስብሰባዎች በርካታ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን አሳትፈዋል፥ ለትምህርት ቦርድ እና ሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ጭምር አቅርበዋል።
የቀረቡት አራት ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫዎች የሚከተሉት ናቸው፦

  • ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ የትምህርት ቤት አካባቢን መፍጠር
  • የአእምሮ ጤና እና ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነት
  • የት/ቤት ሠላም፣ደህንነት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር ፕሮግራምን ማዳበር
  • ክስተቶችን በጋራ የመከላከል ማዕቀፍ

የስራ ቡድኑ ፌብሩወሪ 24 ለሚደረገው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ውይይት የሚደረግባቸው ምክረሃሳቦችን ያቀርባል።
ይህንን ሥራ የሚመሩ ባለድርሻ አካላት የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህራን እና የአሁን የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰሮች
  • የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ካቢኔ እና የመጀመሪያ ደረጃ አመራር የከአስተዳዳሪ ሰራተኞች ማህበር
  • ከሁሉም መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 230 ተማሪዎች
  • ቀደም ሲል በሥራ ላይ የሚገኙ የአማካሪ ቡድኖች፡ የትምህርት ቤት እና የተማሪዎች ደኅንነት (RSSSW) አስተባባሪ ኮሚቴ እና የማህበረሰብ ተወካዮችን የሚያካትቱ የተማሪ ደህንነት አስፈጻሚ ቡድኖች (SWAG)፣
  • የማህበሩን አመራር ጨምሮ የሰራተኛ ማህበር ተወካዮች (MCAAP, MCEA, SEIU)፣
  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ ሰራተኞች እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ተወካዮች

እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.

  1. ስለ ፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ዳሰሳ፡ ተጨማሪ መረጃ

ፌብሩዋሪ 2፣ ዶ/ር ማክክሊት (, Dr. McKnight) በትምህርት ዲስትሪክት ውስጥ የዘር እና የስርዓት አቀፍ መሰናክሎችን ለመፍታት እየተካሄደ ስላለው ስራ እና ቁርጠኝነት ይህንን ወቅታዊ መረጃ አጋርተዋል። ከመጪው የዳሰሳ ጥናት ምን እንደሚጠበቅ የበለጠ መረጃ ለመስጠት ለቤተሰቦች ማሻሻያው ተልኳል።

    • ከ 4ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ሁሉም ከማርች 1 እስከ ማርች 31 ባለው ጊዜ ውስጥ በትምህርት ቤት ከዕድሜአቸው ጋር የሚመጥን ማንነታቸውን ይፋ በማይደረግ የዳሰሳ ጥናት ይሳተፋሉ። እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የዳሰሳ ጥናቱ የሚካሄድበትን ቀን ይወስናል።
      1. ማንኛውም ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጃቸው የዳሰሳ ጥናቱ ላይ እንዲሳተፍ/እንድትሳተፍ የማይፈልጉ ከሆነ ይህን ቅጽ መሙላት አለባቸው።
      2. ይህንን የዳሰሳ ጥናት በተሻለ ለመረዳት የሚያግዙ አንዳንድ ሪሶርሶችን እነሆ፦
        1. ሁሉም ተማሪዎች የዳሰሳ ጥናቱ ላይ ከመሳተፋቸው በፊት ማየት ያለባቸው ቪዲዮ
        2. ስለ ፀረ ዘረኝነት ኦዲት የተሰጠ አጭር መግለጫ (በ español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ)
        3. ማብራሪያ የዳሰሳ ጥናቱ ምን እንደሚመስል

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች (በ español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ)

  1. በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ፈጣን መመርመሪያዎች እየተከፋፈሉ ነው።

MCPS 190,000 ፈጣን መመርመሪያዎችን ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ያከፋፍላል። በማርች ወር ወደ ቤት ከሚላኩት 50,000 የመመርመርያ ኪት ጨምሮ ፈጣን የመመርመሪያ ኪቶች እስከ መጋቢት ድረስ ይሰራጫሉ። ሰራተኞች እና የተማሪዎች ወላጆች ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶችን በMCPS ኮቪድ-19 ሪፖርት ማድረጊያ አማካይነት ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።

  1. የትምህርት ቦርድ የ MCPS የሥራ አፈጻፀም ወቅታዊ መረጃዎችን ተቀብሏል።

ፌብሩዋሪ 8 ስብሰባ ወቅት የቦርድ አባላት ከ MCPS ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተጽእኖዎች ዙሪያ ያቀረቡትን ሪፖርት አድምጧል። በዚህም መሠረት በዲስትሪክቱ ውስጥ ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱ ተገልጿል። የሞንጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት የ MCPS ተማሪዎች እና ሰራተኞችን የኮቪድ-19 ክትትል ለማድረግ አሁን ሁኔታዎችን የሚመረምሩ ባለሙያዎችን እየላከ ነው። MCPS ተጨማሪ ተተኪ መምህራንን ቀጥሯል፥ ጥቂት ያልተሟሉ ተተኪ የሚያስፈልጋቸው ቦታዎችንም እያየ ነው። ከጃንዋሪ 21፣ 2022 ጀምሮ MCPS ሁሉንም የአውቶቡስ መስመሮች በተሟላ ሁኔታ አገልግሎት ተሰጥቷል።

  1. MCPS ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ስለሚካሄዱ ዝግጅቶች ማሻሻያ የተደረገባቸው የተመልካቾች ብዛት ገደብ

ለሁሉም ቤት ውስጥ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ለሚካሄዱ ዝግጅቶች የተመልካቾች ውሱንነት ከ 25 በመቶው የመቀመጫ አቅም ወደ 50 በመቶ እንዲሆን ተሻሽሏል። በዚያው ደረጃ ላይ ይቆያሉ። አሁንም በሁሉም የ MCPS ትምህርት ቤቶች እና መገልገያዎች ውስጥ ማስክ ያስፈልጋል። ስለ አትሌቲክስ የኮቪድ-19 መረጃ በዚህ ድረ ገጽ ይመልከቱ። እንዲሁም ወደ R.A.I.S.E አትሌቲክስ ስለመመለስ ጋዜጣ መመልከት ይችላሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools