በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ጭምብል አጠቃቀም አማራጭ የሚሆን ከሆነ ማወቅ ያለብዎት ነገር

የትምህርት ቦርድ (BOE) በመጪው ማርች 8 ስብሰባ ላይ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ “ጭምብል አጠቃቀም አማራጭ ፖሊሲ” ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። በስብሰባው ላይ፣ ከፌዴራል፣ ከስቴት እና ከአካባቢው መመሪያ ጋር በማጣመር ጠቃሚ መረጃ ላይ ውይይት ይደረጋል፣ እና—በወረርሽኙ ያለበት ሁኔታ ወይም በሆስፒታል የህሙማን ቁጥር መጨመር ከሌለ—ጭምብሎችን የመጠቀም ሁኔታ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አማራጭ መሆናቸው ተገቢ ይሆናል። ይህንን ውሳኔ የሚሰጠው የትምህርት ቦርድ (BoE) ይሆናል።

ይህ ውይይት በቅርብ ጊዜ በሜሪላንድ ስቴት ለት/ቤቶች የተላለፈውን የማስክ አጠቃቀም መመሪያ ውሳኔ ተከትሎ የተሻሻለውን የበሽታ መቆጣጠሪያ ማእከላት እና መከላከያ (CDC) መመሪያ በትምህርት ቤቶች ውስጥ አጠቃላይ ማስክ መጠቀም ግዴታ እንደማይሆን የተሰጠውን ውሳኔ በመከተል ነው።

በጭንብል አጠቃቀም ፖሊሲያችን ላይ የሚደረጉ ለውጦች አንዳንዶች የሚቀበሉት ቢሆንም ለሌሎች ደግሞ አሳሳቢ ሊሆን ይችላል።  በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ጭምብል ማድረግ የሚፈልጉ ወይም መቀጠል የሚፈልጉ ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች እና አስተዳዳሪዎች ይኖራሉ። ያንን ማክበር አለብን።

እንደ ዲስትሪክት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በዚህ ጊዜ ጭምብል ስለመጠቀም ወይም ስለማስወገድ የግለሰብ ውሳኔዎችን ማህበረሰባችን እንዲያከብር እንጠብቃለን። ሰራተኞቻችን እና ተማሪዎቻችን ደግነትን፣ ተቀባይነትን እና አካታችነትን ማክበር አለባቸው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች እና ከቤተሰቦች ጋር በመገናኘት በትጋት ይሰራል፣ ሁላችንም ጭምብል ለመልበስ ወይም ጭምብል መጠቀምን ለመተው የሚደረገውን የግለሰብ ውሳኔ ማክበር አስፈላጊ መሆኑን እናውቀዋለን።

የመጓጓዣ እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሚካሄዱ ሁነቶች
በተጨማሪም በትምህርት ቤቶቻችን አውቶቡሶች ላይ ማስክ መጠቀም በፍላጎት ላይ የተመሠረተ አማራጭ ሊሆን ይችላል። የአየር ሁኔታ ሲፈቅድ መስኮቶችን መክፈታችንን እንቀጥላለን። በስፖርታዊ ዝግጅታችን እና በአካል በምናቀርባቸው ዝግጅቶች ጭምብሎችን መጠቀም እንዲሁ በፍላጎት የሚደረግ አማራጭ ይሆናል።

ቀጣይነት ያለው የቫይረስ ቅነሳ (የቫይረስ ስርጭትን መቀነስ)
የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት የሚከተሉትን ጨምሮ ብዙ ፈርጀ ያለው የኮቪድ-19 ቅነሳ ስትራቴጂ ይኖረዋል።

  •  በቤት ውስጥ የሚደረግ ፈጣን የኮቪድ ምርመራ
  • በዘፈቀደ እና በፍጥነት በትምህርት ቤት ውስጥ የሚደረግ የቫይረስ ምርመራ
  • በሁሉም ሕንፃዎች ውስጥ የተሻሻሉ HVAC ሲስተሞችን መዘርጋት
  • ለሁሉም የዕድሜ ቡድኖች የክትባት ክሊኒኮችን ተደራሽ ማድረግ
  • የተሻሻለ የጽዳት አጠባበቅ
  • በዚህ የትምህርት ዓመት KN-95 ጭንብል ስርጭት

 

ምንም እንኳ የኳራንቲን ማቆያ እና ራስን የማግለል ጊዜ ከ10 ቀን ወደ 5 ቀናት የቀነሰ ቢሆንም፥ የቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ እነዚህ እርምጃዎች እና የካውንቲ ጥረቶች ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት ቤት አካባቢን ለማረጋገጥ ረድተዋል። CDC በአሁኑ ጊዜ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማህበረሰቡ ላይ ያለውን ተጽእኖ በመለካት ሞንትጎመሪ ካውንቲን “በዝቅተኛ” ደረጃ ላይ አስቀምጧል።

ክትባት መውሰድ ደህንነታችን የተጠበቀ እና ጤናማ ሆኖ ለመቆየት በጣም አስፈላጊው መንገድ ሆኖ ይቀጥላል። ክትባት ለመውሰድ ብቁ ከሆኑ እባክዎን ይከተቡ ወይም ቡስተር ይውሰዱ።

ቅዳሜ፣ ማርች 5 እና እሁድ፣ ማርች 6 በትምህርት ቤቶች የክትባት ክሊኒኮች ይኖራሉ። ስለ ካውንቲ የክትባት ቦታዎች መረጃ እዚህ ይገኛል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በካውንቲያችን እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለውን የቫይረስ ሁኔታ ይቆጣጠራል። ስለ ጭምብል አጠቃቀም መመሪያ መቀየር ካስፈለገ፣ ከአካባቢያዊ እና ከስቴት የጤና አጋሮቻችን እንዲሁም ከ MCPS COVID-19 አማካሪ ቡድን ጋር በመተባበር ውሳኔዎች ይደረጋሉ። የኮቪድ-19 ዳሽቦርድ ጠቃሚ መገልገያ ነው።

ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን።

ጠቃሚ መረጃዎች
ለቤተሰቦች

ለሰራተኞችEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools