የትምህርት ቦርድ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጭምብል መጠቀም በፍላጎት ምርጫ መሆን እንዳለበት ወስኗል

March 8, 2022

ማርች 8 በተደረገው የሥራ ስብሰባ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች እና መገልገያዎች ጭምብል/ማስክን መጠቀም በፍላጎት ምርጫ መሆን እንዳለበት ድምጽ ሰጥቷል። ይህ አዲስ መመሪያ ወዲያውኑ ተግባራዊ ይደረጋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው ከሜሪላንድ ስቴት ለትምህርት ቤቶች የተላለፈውን የማስክ አጠቃቀም መመሪያ ለማቋረጥ እና ተሻሻለውን የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC) መመሪያ ጋር የተጣጣመ የሜሪላንድ ስቴት ውሳኔን ተከትሎ ነው።
የሰራተኞቻችንን እና የተማሪዎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ሌሎች የኮቪድ-19 መከላከያ ስልቶችን መጠቀም ይቀጥላል፣ እነዚህም በትምህርት ቤት ውስጥ ፈጣን እና የዘፈቀደ ምርመራ፣ ወደ ቤት የሚወሰዱ መመርመሪያ ኪት ማሰራጨት፣ HVAC ሲስተሞችን ማሻሻል እና የክትባት አቅርቦትን መጨመር ይሆናሉ። ጭንብል በቤት ውስጥ፣ ከቤት ውጭ እና በትምህርት ቤት አውቶቡሶች ላይ ጭምብል መጠቀም በፍላጎት የሚደረግ አማራጭ ይሆናል። ማስክ ለመጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህን ማድረጉን ሊቀጥል ይችላል፣ እና ልጅዎ ከፈለገ(ች) ከትምህርት ቤታቸው ማስክ ሊጠይቁ ይችላሉ።

on or offጭንብል፡ ቢሆንም ባይሆንም እኔ ብቻ ነኝ
አንዳንዶች አዲሱን የማስክ ፖሊሲ ቢቀበሉም፣ ሌሎች ለውጥ በመደረጉ ሊያሳስባቸው ይችላል። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ጭምብል ማድረግን ለመቀጠል የሚፈልጉ ተማሪዎች፣ መምህራን እና አስተዳዳሪዎች ይኖራሉ። ያንን ማክበር አለብን። ስለዚህ፣ "ቢሆንም ባይሆንም እኔ ብቻ ነኝ" የሚያመለክተው ማስክን መልበስ የግለሰብ ምርጫ ሊሆን እንደሚችል እና አንዳችን የሌላውን ምርጫ ማክበር እንዳለብን ማሳሰቢያ ነው።
በዲስትሪክቱ ውስጥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ ጭንብል ስለመጠቀም የግለሰብ ውሳኔዎችን እንዲያከብር ይጠበቃል። ሰራተኞቻችን እና ተማሪዎቻችን ደግነትን፣ ተቀባይነትን እና አካታችነትን ማክበር አለባቸው። የእያንዳንዱን ግለሰብ ውሳኔ ልክ እንደ ሆነ ለማክበር የጋራ ግንዛቤን ለማሳደግ MCPS ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች እና ከቤተሰቦች ጋር በመተባበር ይሰራል።

MCPS ይህንን ጠቃሚ መልእክት በፖስተሮች፣ በራሪ ወረቀቶች፣ በቪዲዮ የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያዎች፣ በማህበረሰብ መልእክቶች እና በማህበራዊ ሚዲያዎች በማጋራት ማህበረሰባችን የግለሰብ ምርጫዎችን መቀበል እንደሚያስፈልግ ያበረታታል። ከተማሪዎች እና ከቤተሰቦች ጋር በራሳቸው በኩል ግንኙነት እንዲያደርጉ ለትምህርት ቤቶች መገልገያዎች ይሰጣሉ።
የወላጅ መገልገያዎች
የሚገርም ነው፡ ተማሪዎችን ጭምብል ማውለቅ ሊያስጨንቃቸው ይችላል
ከፊት ጭንብል ስለማውለቅ በጉልበተኝነት የሚያሾፉትን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል
ጉልበተኝነት እና ትንኮሳ ሪፖርት የሚደረግበት የ MCPS ቅፅ
ስለ ጉልበተኝነት እና ትንኮሳ የ MCPS መረጃ

ጠቃሚ ማሳሰቢያ፡ ከታመሙ፣ ቤት ይቆዩ። እንደ ኮቪድ-19 አይነት ምልክቶች ያለው/ያላት ማንኛውም ተማሪ ወይም ሰራተኛ ቤት መቆየት አለበ(ባ)ት። ምልክት ያለባቸው ሰዎች ከኮቪድ-19 ምልክቶች ነፃ ከሆኑ ብቻ ወደ ትምህርት ቤቶች ሊመለሱ የሚችሉት፣ 100.4 ወይም ከዚያ በላይ ትኩሳት፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ ሳል፣ የመተንፈስ ችግር፣ ተቅማጥ፣ ማስታወክ እና ጣዕም ወይም የማሽተት ስሜት ማጣት ከሌላቸው ብቻ ነው። ወደ ትምህርት ቤት ለመምጣት እና ለመስራት በቂ ጤንነት እንዳለህ(ሽ) ለማወቅ ይህን ዕለታዊ የጤንነት ማረጋገጫ ዝርዝር ተጠቀም(ሚ)።

ኳራንቲን እና ራስን ማግለል መመሪያዎች አንድ አይነት ናቸው።
ፖዚቲቭ (በሽታው የተገኘበት) የኮቪድ-19 ሁኔታዎችን ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች የኳራንቲን እና ራስን የማግለል መመሪያዎች አሁንም አልተቀየሩም። አንዳንድ የጤና ሁኔታዎች ከተሟሉ ራስን የማግለል ፖሊሲው ለአምስት ቀናት ነው። ይህ CDC፣ ከሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት መመሪያዎች ጋር ይስማማል።
እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ፦ https://www.montgomeryschoolsmd.org/coronavirus/quarantine.aspx

ክትባት

ለማስታወስ ያህል፣ ኮቪድ-19 ለመዋጋት እና ትምህርት ቤቶቻችንን የሁሉንም ተማሪዎቻችንን ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ክትባት መውሰድ ምርጡ መሳሪያ ነው። ዕድሜያቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ልጆች የኮቪድ-19 ክትባት ለመውሰድ ብቁ ናቸው። የእርስዎ ልጅ ብቁ ከሆነ(ች) እና የኮቪድ-19 ካልወሰደ(ች) እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ከዚህ መረጃ ይውሰዱ https://www.montgomeryschoolsmd.org/Coronavirus/Vaccinations/

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ክሱልስ ከ CDC የሚገኘውን የኮቪድ-19 መረጃ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ጋር በመተባበርና አስፈላጊ ከሆነ በትምህርት ቤት ህንጻዎች፣ መገልገያዎች እና በትምህርት ቤት አውቶቡሶች ውስጥ ስለ ጭንብል አጠቃቀም ጉዳይ እንደገና ያጤናል።Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools