የሐሙስ፣ ማርች 24 አምስት ጉዳዮች እነሆ! ከስፕሪንግ ዕረፍት ሲመለሱ ማወቅ ያለባቸውን መመሪያዎች ጨምሮ አስፈላጊ የኮቪድ-19 ማሳሰቢያዎችን፣ ያካትታሉ። ስለ አእምሮ ጤንነት እና ቀውስ ሪሶርሶች መረጃ፣ የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ዳሰሳን ስለማጠናቀቅ፣ ከትምህርት ቤት ውጪ ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እድሎች እና ስለእግረኞች ደህንነት ጠቃሚ ምክሮችን ያጠቃልላል።
ይጠንቀቁ፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አላበቃም።
ከኮቪድ-19 ተጽኖ ነፃ በመሆን ከስፕሪንግ ዕረፍት መመለስ እና የትምህርት ዓመቱን ያለ ኳራንቲን ወደ ነበረበት ለመመለስ እንዲያስችለን በንቃት፥ አጽንኦት/ትኩረት በመስጠት ጥንቃቄ ማድረግን ይጠይቃል። ይሄ ሁላችንንም የሚመለከት ጉዳይ ነው። እባክዎ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በህብረተሰባችን ውስጥ እንዲቀንስ ያደረገውን የተሳካ የማስወገጃ ስልቶችን መከተልዎን ይቀጥሉ።
ኮቪድ-19 ምርመራ፡
ማሳሰቢያ፡ የኮቪድ-19 ምልክቶች 100.4 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ትኩሳት፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ ሳል፣ የመተንፈስ ችግር፣ ተቅማጥ ወይም ማስታወክ ወይም ጣዕም ወይም ሽታ ማጣት ናቸው። ይህን ጠቃሚ የተማሪ የጤንነት ማረጋገጫ ዝርዝር ይጠቀሙ።
ስርጭት፡-
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የኮቪድ-19 ፈጣን የቤት መመርመሪያ ቁሳቁሶችን ከማርች 28 እስከ ኤፕሪል 6 ያከፋፍላል።
የአጠቃቀም መመሪያዎች፦
ቪዲዮ፡ የኮቪድ-19 ፈጣን መመርመሪያ መሣሪያ አጠቃቀም መመሪያ
በዚህ ድረገጽ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ፤ በራሪ ወረቀቶች ላይ ያለውን መመሪያ ያንብቡ።
እንግሊዘኛ / እስፓኒሽ / 中文 / ፈረንሳይኛ / ፖርቺጊዝ / ቻይንኛ / tiếng ቪትናም / አማርኛ
(ማሳሰቢያ፦ እነዚህ ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ የሚከናወኑ ፈጣን መመርመሪያዎች ናቸው፡ እባክዎ ከመጠቀምዎ በፊት በመሳሪያዎቹ እሽግ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ያንብቡ)
በትምህርት ቤት ምርመራ እንዲደረግ መስማማትዎን ይግለጹ
MCPS በት/ቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ምልክቶችን ለሚያሳዩ ተማሪዎች እና ለሌሎችም በዘፈቀደ ፈጣን ምርመራ ያደርጋል። ወላጆች ለዚህ ምርመራ ፈቃድ መስጠት አለባቸው ይህን ቅጽ በመሙላት። ስለ ት/ቤት የኮቪድ-19 ምርመራ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
ሌሎች መታወቅ ያለባቸው ጠቃሚ ነገሮች
የአእምሮ ጤንነት እና የቀውስ ድጋፍ መርጃዎችን ለሚፈልጉ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች MCPS የኦንላይን መረጃ አለው። እያንዳንዱ ትምህርት ቤት ካውንስለር፣ የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስት፣ የተማሪ ሰራተኛ እና የትምህርት ቤት ነርስን ያካተተ የተማሪ ድጋፍ ቡድን አለው።
መገልገያዎች/ሪሶርሶች:
በአካባቢያችን እና በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ሁላችንም ካሉን በጣም አስፈላጊ ስራዎች አንዱ የተማሪዎች ደህንነት ነው። ለሁሉም ሰው ደህንነት ቅድሚያ መስጠት አለበት. ልጆች በሰላም ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ እና እንዲመለሱ እንፈልጋለን። ጥቂት አጋዥ ማሳሰቢያዎችን እነሆ፦
ለ ተጓዦች / ለተሣፋሪዎች / ነጂዎች ጠቃሚ ምክሮች፦
ትምህርት በማይሰጥባቸው ቀናት MCPS በአካል፣ ቀጥታ እና በጥያቄ ለኤለመንተሪ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የሚኖራቸውን እድሎች ዝርዝር አዘጋጅቷል። ከእነዚህ ተግባራት መካከል አንዳንዶቹ ከ MCPS ጋር ግንኙነት የላቸውም። ከእነዚህ ፕሮግራሞች በአንዱ ላይ ፍላጎት ካለዎት፣ እባክዎን እነዚህን ድርጅቶች በቀጥታ ያግኙ። መጪዎቹ ቀናት፡- ሐሙስ፣ ማርች 24 (በቅድሚያ የሚለቀቁበት ቀን)፣ አርብ፣ ኤፕሪል 1 (በቅድሚያ የሚለቀቁበት ቀን) እና ሰኞ፣ ኤፕሪል 11 የሚጀምረው የስፕሪንግ ዕረፍት እስከ ሰኞ፣ ኤፕሪል 18 ድረስ ይቆያል።
የዳሰሳ ጥናቱ ስም የማይገለፅበት ከመሆኑም በላይ በሚከተሉት ሰባት ቋንቋዎች ይገኛል።
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org