ሜይ 10, 2022

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ለቀጣይ የትምህርት ዘመን ለታታሪ እና ከፍተኛ ችሎታ ላሳዩ መምህራኖቻችን፣ የድጋፍ አገልግሎት ሰጪዎች፣ አስተዳዳሪዎች እና ሌሎች ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ ከሶስቱ የሰራተኛ ማህበሮቻችን ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን በደስታ እንገልፃለን። ላለፉት ሁለት ዓመታት ጉልህ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙንም፣ MCPS ታላቅ የትምህርት ስርዓት መሆኑን ሳያጓድል ቀጥሏል፣ በአብዛኛው የላቀ ብቃታቸውን ላሳዩት እና ለሚሸለሙ እና እውቅና ለሚሰጣቸው ሰራተኞች ምስጋና ይግባቸው። አዲሶቹ ኮንትራቶች ሁሉም ሰራተኞች ለእያንዳንዱ ተማሪ ጥሩ ትምህርት በመስጠት ያሳዩትን ጽናት እውቅና የምንሰጥበት አንዱ መንገድ ነው። ከሰራተኛ ማኅበሮቻችን-MCEA፣ MCAAP፣ SEIU ጋር ያለው ትብብር እና ወደ እድገት ያመራው ህብረት፣ እነዚህ ስምምነቶች MCPS አዋቂዎች ለመስራት የሚጓጓበት እና ልጆች በሁሉም የህዝብ ትምህርት ውስጥ ለመማር ጥሩ ከሚባሉት ቦታዎች አንዱ ሆኖ እንዲቆይ ያግዛል።

መፍትሔ በመሻት፣ እንደሁኔታው በማመቻቸት እና በቅልጥፍና፣ የ MCPS ሠራተኞች በማህበረሰባችን ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ እና በአስቸጋሪ ጊዜያት ጀግንነታቸውን አሳይተዋል። በዚህ የትምህርት አመት ሙሉ ጊዜያቸውን ወደ ክፍል ከመመለሳቸው በፊት ባለፈው አመት ሰራተኞቻችን በቨርቹወል እና ከሁለቱም በመደባለቅ ሰርተዋል። አዳዲሶቹ የሰራተኞች ስምምነቶች እነዚህን ጥረቶች ይገነዘባሉ፣ እና ሰራተኞቻችን ያከናወኑትን ጉልህ ስኬቶቻቸውን የሚያረጋግጡ ማካካሻዎችን እና እውቅና መስጠቱ ትልቅ ገድል ነው። እነዚህ አዳዲስ ስምምነቶች ማህበረሰባችንን ለማገልገል ለመቀጠል የሚገባንን ተጨማሪ ማበረታቻ እየሰጡ አስተማሪዎች እና ሰራተኞቻችንን እውቅና ለመስጠት፣ ለመሸለም እና በሥራቸው ላይ ለማቆየት የምንሰራበትን አንድ ተጨማሪ መንገድ እንደሚከፍቱ ተስፋችን ነው።

እነዚህ ስምምነቶች ለሁሉም ሰራተኞች MCPS ትልቅ ደረጃ ያለው ዋና መዳረሻቸው እንደሆነ ያስገነዝባቸዋል። አዲሶቹ ስምምነቶች የ 3.35% የኑሮ ውድነት እና የደመወዝ ደረጃ ጭማሪን ያካትታሉ፤ ይህም በእኩል፣ ውጤታማ በሆነ መልኩ፣ ከ 6% በላይ የሰራተኞቻችን የደመወዝ ጭማሪ ይሆናል ማለት ነው። ይህ ከአስር አመታት በላይ ባለው ጊዜ ውስጥ በአጭር ጊዜ የተከናወነ ከፍተኛው ጭማሪ ነው። በስምምነቱ ውስጥም መምህራኖቻችን በተሻለ ሁኔታ እንዲሰሩ ያላቸውን ፍላጎት ለመደገፍ ለሙያዊ እድገት ቁርጠኝነት፣ለሠራተኞች፣ ለተማሪዎቻችን እና ለማህበረሰባችን ደህንነት፣ ከፍተኛ የአገልግሎት ዘመን ላደረጉ አስተዳዳሪዎች የተደረጉ ማሻሻያዎች አዲስ ትኩረት ናቸው። ይህ ሁሉ ለሰራተኞቻችን የምንሰጠውን ከፍተኛ ዋጋ እና ለት/ቤቶቻችን የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ እንደምናደንቅ ተጨማሪ ማረጋገጫ ሆኖ ያገለግላል።

እነዚህ ኢንቨስትመንቶች የቅርብ ጊዜ የኮሌጅ ተመራቂዎችን፣ ልምድ ያላቸውን አስተማሪዎች እና የስራ ለውጥ ፈጣሪዎችን በመሳብ ረገድ የ MCPS ቤተሰብን እንዲቀላቀሉ እና ተማሪዎቻችንን ማገልገላችንን ስንቀጥል ከኛ ጋር እንዲቆዩ በማበረታታት ትልቅ እገዛ ያደርጋል።

people at tableበቅርብ ሳምንታት ከማህበረሰባችን ጋር ስንወያይ በነበሩት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ጨምሮ ሰራተኞቻችን በየእለቱ የሚሰሩት ስራ ወደፊት አብረን የምንሰራውን ስራ እንድንከታተል ያነሳሳናል/ያበረታታናል።

  • መተማመንን መገንባት፣ ዳግም መገንባት እና ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ፤
  • ለሰራተኞች እና ተማሪዎች የአእምሮ ጤንነት እና ደህንነትን መደገፍ፣ እና
  • በዲስትሪክቱ ፍትሃዊ በሆነ የመማር ማስተማር ላይ ማተኮር።

ለሰራተኞቻችን እውቅና መስጠት፣ ሽልማት በመስጠት መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ማለት ለሁሉም ተማሪዎቻችን የወደፊት ስኬት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው።

ሦስቱ የሰራተኞች ስምምነቶች ከጁላይ 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ህዝብን ለሚያገለግሎ ሰራተኞች ያለውን ሰፊ ቁርጠኝነት ለመጠበቅ እና ዲስትሪክቱን በሜሪላንድ እና በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ በርካታ ቀጣሪዎች ብልጫ ያለው አድርጎ ለማስቀጠል MCPS የበኩሉን ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን እንደሚቀጥል አመላካች ናቸው።
የዚህ ታላቅ ቡድን አካል መሆን ከፈለጉ እዚህ ያመልክቱ!

ከልብ

Monifa McKnight, Ed.D.
Interim Superintendent of Schools
ሞኒፋ ቢ. ማክነይት ዶ/ር
ተጠባባቂ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንትEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools