ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጤና መኮንን የተላለፈ ጠቃሚ መልእክት

November 18, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ለሁላችሁም መልካም የምስጋና ጊዜ እንዲሆንላችሁ ምኞቴን በመግለጽ ልጀምር! ተሰባስበን መጪዎቹን በዓላት ለማክበር ስንዘጋጅ፥ ለጤንነት ማድረግ ያለብንን ጥንቃቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት የበዓል ጊዜውን እንዴት እንደምንደሰት ማሰብ አለብን። እባኮትን በበዓላቱ ሰሞን ስለ ጤንነት መደረግ ያለባቸውን የጥንቃቄ ማሳሰቢያዎች በዚህ መልእክት ስር ይመልከቱ።CDC የጉንፋን መሰል ህመምን ለመከላከል የእለት ተእለት እርምጃዎች መመሪያ፣ ፍሉ እና RSV ጨምሮ እነዚህን አጠቃላይ የጤና ምክሮች የሚያካትቱ የበዓል ጊዜያት የጤና ጥበቃ ጥንቃቄ ስልቶችን ያቀርባል።

ከእረፍት በፊት እነዚህን የጤና ነክ ዜናዎችን ማካፈል እፈልጋለሁ፦ 

  1. MCPS የአካባቢን የበሽታ መዛመት አዝማሚያዎችን በቅርበት ለመከታተል እና ለትምህርት ቤቶቻችን እና የስራ ቦታዎቻችን ድጋፍ ለመስጠት ከአካባቢያችን የጤና ዲፓርትመንት ጋር መስራቱን ይቀጥላል።  ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኮቪድ-19 ስርጭት ሁኔታ የተረጋጋ ሲሆን በሪጅናችን ኢንፍሉዌንዛ ጨምሯል፣ በትኩሳት እና በመተንፈሻ አካላት ህመም ምክንያት ከሥራ የመቅረት ሁኔታ ጨምሯል።  የመተንፈሻ ቫይረሶችን ስርጭት ለመቀነስ የሚረዱ ጥሩ የኢንፌክሽን ቁጥጥር ስልቶችን እና የጤና አጠባበቅ ባህሪያትን መከታተል እንቀጥላለን።  ከሕዝብ የጤና ጥበቃ አጋሮቻችን ጋር፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ያልተቋረጠ ትምህርት በመስጠት ለመደገፍ ግባችንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ግብዓቶችን እና መመሪያዎችን ለት/ቤቶች እንሰጣለን ።
  2. የኮቪድ-19 ቤት ውስጥ መመርመሪያ ኪቶች ከኖቬምበር 23 በፊት ለሰራተኞች እና ለተማሪዎች ይሰራጫሉ። እንደ ጉዞ እና ትላልቅ ማህበራዊ ስብሰባዎች ያሉ የበዓላት ተግባራት ለኮቪድ-19 የመጋለጥ እድልን ሊጨምሩ ስለሚችሉ ሁሉም ሰው የቤት ውስጥ ምርመራ ማድረጉን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። iHealth የምርመራ ኪት ካገኙ፣ አገልግሎቱ የሚያበቃበትን ቀን/expiration date በዚህ ሠንጠረዥ ላይ መመልከት እንዳለብዎት ያስታውሱ።InteliSwab አዲስ የምርመራ ኪት ወስደው ከሆነ፣ እነዚህን የቪዲዮ መመሪያዎች ማየት ያስፈልግዎታል። የካውንቲው ጤና ዲፓርትመንት ለቤተሰብ አባላት፣ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች ነጻ የምርመራ መሣሪያዎችን ያቀርባል።

    ለተመላሽ ሰራተኞች እና ለተማሪዎች ምርመራ ማድረግ ግዴታ አይደለም። በግል የመጋለጥ አደጋን ግምት ውስጥ በማስገባት የኦንላይን መተግበሪያ በመጠቀም ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶችን ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው በሰራተኞቻችን እና ቤተሰቦች እንተማመናለን።  ምልክቶቹ ኮቪድ-19 ወይም ሌላ ጉንፋን መሰል በሽታ መሆኑን ለማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህ ምርመራ ማድረግ እና CDC ራስን የማግለል መመሪያዎችን መከተል ኮቪድ-19 መሆኑን ለመለየት እና የወረርሽኙን  ተጨማሪ ስርጭት ለመከላከል ጠቃሚ መንገድ ነው። 

ወረርሽኙ ከጓደኞች እና ከቤተሰብ ጋር የደስታ ጊዜን ስለ ማሳለፍ አስፈላጊነት እና በጤና እና ደህንነት ላይ ያለንን የጋራ ሀላፊነት መገንዘብ እንዳለብን አሳይቶናል።  በድጋሚ፣ ለት/ቤታችን ማህበረሰብ ጤንነትና መጠበቅ በመከባበር እና በደግነት ቁርጠኝነት ያሳዩትን ሁሉንም አመሰግናለሁ።
ከልብ

Patricia Kapunan, M.D., M.P.H.
MCPS Medical Officer

MCPS የበዓል ጊዜያት የጤና ጥበቃ ማሳሰቢያዎች
  • የኮቪድ-19 እና የጉንፋን/ፍሉ ክትባት ይውሰዱ። ክትባቱ ከባድ በሽታን ለመከላከል የሚረዳ ከመሆኑም በላይ በተለይም ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በጣም አስፈላጊ ነው። MCPS በሳምንቱ መጨረሻ እና ከትምህርት በኋላ በትምህርት ቤት የኮቪድ-19 ክትባት ክሊኒኮችን ማስተናገዱን ይቀጥላል። የፍሉ ክትባቱ በዶክተር ቢሮዎች እና በግል ፋርማሲዎች ይገኛል።
  • ከታመሙ ቤት ይቆዩ። ለኮቪድ-19፣ ቢያንስ ለ 5 ቀናት በቤት ውስጥ እንዲቆዩ የሚመከሩትን CDC የኳራንቲን መመሪያዎች ይከተሉ። ለፍሉ/ጉንፋን እና ለሌሎች የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች ተማሪዎች እና ሰራተኞች 24 ሰአታት ከትኩሳት ነፃ ከሆኑ እና ጥሩ ስሜት ከተሰማቸው ወደ ትምህርት ቤት መምጣትና መስራት ይችላሉ።
  • ጤናማ ልምዶችን ተለማመድ። በደንብ እጅዎን ይታጠቡ ወይም ከጀርሞች እጅዎን ለማፅዳት የእጅ ማጽጃ ይጠቀሙ። ሳል እና ማስነጠስን ለመሸፈን ቲሹ (ወይም እጅጌዎን) ይጠቀሙ።
  • የፊት ጭንብል መጠቀምን አስፈላጊነት ያስቡበት። ጭንብል መጠቀም የመተንፈሻ ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ይረዳል እንዲሁም በቅርብ ግንኙነት ከፍተኛ የበሽታ መተላለፊያ ሁኔታዎች ውስጥ ተጋላጭ የሆኑ በተለይም ቀላል የሕመም ምልክቶች ላለባቸው ሰዎች ይመከራል። የፊት ጭንብል በአብዛኛዎቹ የትምህርት ቤት መገልገያዎች አማራጭ ቢሆንም፣ ግለሰቦች እራሳቸውን ወይም ሌሎችን ለመጠበቅ በማንኛውም ጊዜ ጭምብል ማድረግን ሊመርጡ ይችላሉ። ኮቪድ-19 ከ 5 ቀናት በኋላ ከኳራንቲን የሚመለሱ ሰዎች እስከ 10 ቀን ድረስ ጭምብል ማድረግ እንዳለባቸው የ CDC መመሪያ መሆኑን ያስታውሱ። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የስርጭት ሁኔታዎች ምክንያት ሰራተኞች እና ተማሪዎች ለጊዜው ጭምብል እንዲያደርጉ ሊጠየቁ ይችላሉ።

ከ CDC ተጨማሪ ግብዓቶች
የኮቪድ-19 እራስን በቤት ውስጥ ወይም በማንኛውም ቦታ ምርመራ ማድረግ
የኮቪድ-19 ፈጣን የምርመራ መመሪያ ቪዲዮ

ተጨማሪ ሪሶርሶች ከአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ/American Academy of Pediatrics:፦
የኮቪድ-19 የመረጃ ምንጭ
RSV፡ ከጉንፋን በላይ በሚሆንበት ጊዜ
ፍሉ/ጉንፋን - ወላጆች ማወቅ ያለባቸው ነገር




Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools