ስለ ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል "Carver Educational Services Center" የህዝብ ተደራሽነት እና ደህንነት ማክሰኞ፣ ጁን 27

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ አባላት

በመጪው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ ባለው ፍላጎት ምክንያት ማክሰኞ፣ ጁን 27፣ 2023፣ የሚከተሉት የደህንነት እርምጃዎች ይተገበራሉ።

  • "Carver Educational Services Center building at 850 Hungerford Dr. in Rockville" ህንፃ ውስጥ ለመግባት የሚኖረው እድል የሚያካትተው ቀጠሮ የተያዘላቸውን ንግግር አድራጊዎች፣ ተጋባዥ ተሳታፊዎችን እና ክፍሉ የሚችለውን ያህል ለሌሎች እንግዶችን ነው። 
  • ለተሳታፊዎች ምንም ትርፍ ክፍል አይኖረንም።
  • በህንፃው በስተምስራቅ በኩል ያለው የመኪና ማቆሚያ ለማንኛውም ትልቅ ቡድን ስብሰባዎች የተመደበ ቦታ ነው።

 

ሁሉንም የትምህርት ቦርድ ስብሰባዎች በዲስትሪክቱ ድረ-ገፅ www.montgomerschoolsmd.org MCPS-TV YouTube ቻናል ላይ እና Comcast Channel 34 (HD 1071), Verizon Channel 36, RCN Channel 89 ላይ በሚገኘው MCPS-TV በመጠቀም በኦንላይን መመልከት እንደሚቻል ማስታወስ እንወዳለን።

በማህበረሰባችን ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና መከባበር የሰፈነበት አካባቢን ማጎልበት ላይ ለምታሳዩት ትብብር እና ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት ምስጋና እናቀርባለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools