ይህ ኢሜይል በሚገባ አይታይም ወይ? በአሳሻችሁ/browser ተመልከቱት ቀን፦ ፌብሩዋሪ 8፣ 2023

ከበላይ ተቆጣጣሪ ዶ/ር ሞኒፋ ማክናይት (Dr. Monifa B. McKnight) ቢሮ

Book

ውድ የ MCPS ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ሰራተኞች,
ሪፖርት ካርዶች ባለፈው ሰኞ ቤት በመድረሳቸው የተነሳ፣ በመጀመሪያው ሴሚስተር ስለነበሩን ስራዎች እና ስለገጠሙን ተግዳሮቶች አንዳንድ ነጥቦችን ከእናንተ ጋር ለማጋራት ጓጉቻለሁ።

አዲስ የትምህርት አመት

የ 2022-23 የትምህርት አመትን የጀመርነው 160,000 ከሚደርሱ ተማሪዎች ጋር ነው። 210ኛ ትምህርት ቤታችንን ከፍተናል – ሀሪየት ተብማን (Harriet Tubman) አንደኛ ደረጃ ት/ቤት። እናም፣ በሀገሪቷ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ሰራተኛ የመቅጠር አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም፣ MCPS የትምህርት አመቱን የጀመረው 99% ሰራተኞችን አሟልቶ ነው!

ደህንነት እና ጥበቃ ላይ ትኩረት

በፎል (መኸር) የአትሌቲክ ዝግጅቶች ላይ የተፈጠሩት ጥቂት ክስተቶች፣ ወደ ፊት ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ለመቀጠል MCPS፣ ወላጆች እና የህግ አስከባሪዎች የአትሌቲክስ ደህንነት ዕቅድ እንዲያዘጋጁ አድርጓል። ዶ/ር ፓትሪስያ ካፑናን (Dr. Patricia Kapunan)፣ የእኛ አዲስ ዋና የህክምና መኮንን/ባለሙያ፣ ስለ ኮቪድ-19፣ ፍሉ (ጉንፋን) እና RSV ሶስትዮሽ-ስጋት ታሳስበናለች። ስለ ከመጠን በላይ ዕፅ መጠቀም እና ህልፈተ ህይወቶች/ሞቶች – በአብዛኛው ከፌንታኒል (Fentanyl) ጋር በተጣመሩ ኦፒኦዶች (opioids) ምክንያት በሚከሰቱ – ላይ የማስጠንቀቂያ ደውል እንድናሰማ ከሞንርጎመሪ ካውንቲ አጋሮቻችን ጋር አብረን እየሰራን ነው። ይሄንን አካሄድ ለመቀልበስ፣ እንዲሁም በፀረ-ሴማዊነት ላይ እየጨመሩ የመጡትን አስደንጋጭ ድርጊቶች ለማስወገድ፣ ማስተማር እና ሀብቶቻችንን/ግብዓቶቻችንን ማቀናጀታችንን ቀጥለናል።

ፍትሀዊ ማስተማር እና መማር

ከእኛ የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት የተገኙት ግኝቶች ለህዝቡ እና ለትምህርት ቦርድ በፎል (መኸር) ላይ ቀርበው ነበር፣ በዚህም MCPS ን ወደ ሁሉን-አቀፍ ትግበራ ዕቅድ ማዘጋጀት አሳድጎታል። እናም፣ ከኮቪድ-19 ተፅዕኖዎች የመጣውን “የመማር እጦት” ማስተካከል/መቀልበስ አሁንም ከባድ ቢሆንም፣ የእድገት እና የመሻሻል መስኮችንም ግን እያየን ነው።

የበጀት ዓመት FY 2024 የስራ ማስኬጃ በጀት

የበላይ ተቆጣጣሪ በጀት በዲሴምበር ላይ ለትምህርት ቦርድ ቀርቧል፣ ትኩረቱ የነበረውም የትምህርት ልህቀትን ማጠናከር ነበር። ቁልፍ ኢንቨስትመንቶች (መዋለ ንዋይ ማፍሰሶች) በ ቅድመ የልጅነት እና ሁለት ቋንቋ መማር፣ ለእቃዎች እና ለአገልግሎቶች ዋጋ ንረት ምላሽ መስጠት፣ እና ቅጥርን እና ሰራተኞችን ማቆየትን ለመደገፍ ለሰራተኞች በገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ ደመወዞችን ማቅረብ ለ 2024 የበጀት አመት እንደ ዋነኛ ድጋፎች ከቀረቡት ምክረ ሀሳቦች መካከል ይጠቀሳሉ።

የተማሪ ደህንነትን መደገፍ

ከሞንትጎመሪ ካውንቲ አጋሮቻችን ጋር በመስራት 19 ለደህንነት/ጤናማነት ድልድይ (Bridge to Wellness) ማዕከላት በ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተከፍተዋል፣ እና ነፃ፣ አዲስ የተለቀቀ የሞባይል መተግበሪያ – “Stronger Student” (“ጠንካራ ተማሪ”) – የአዕምሮ ጤና እና ደህንነት መረጃ ለመስጠት በተማሪዎች ተዘጋጅቷል።

የአሰራሮች እና ቴክኖሎጂ ማሻሻያዎች

በሀገር ውስጥ ትልቁ የሆነውን የኤሌክትሪክ የት/ቤት ባስ መጓጓዣዎች ከመመደብ አንስቶ፣ እስከ አዲሱ በቀለም-ኮድ የተደረገ/የተመደበ የስራ ሂደት ማሳያ መልእክቶች፣ እና እስከ ለወላጆች የት/ቤት ባስ የሚገኝበት ቦታ የሚነግር መተግበሪያ ድረስ፣ በሁሉም ደረጃ የአሰራር ልህቀቶችን ለማሳካት በ MCPS ጥረቶች እየተካሄዱ ነው። በተጨማሪም የአጠቃላይ MCPS ማህበረሰብን ተሞክሮ ለማሻሻል ለት/ቤቶች እና ቤተሰቦች የሁለትዮሽ ግንኙነት ስርዓቶችን ፈጠራዎች እየፈለግን/እየፈተሽን ነው።

ግንኙነት / የማህበረሰብ ተሳትፎ

የምትፈልጉትን ተጨማሪ መልካም ዜና፣ እና የምትፈልጉትን ተጨማሪ መረጃ እያመጣን ነው፣ ይሄን የምናደርገውም የላቁ/ብልሀት የተሞላባቸው የማህበራዊ እና ባህላዊ የሚድያ ቻናሎችን/መስመሮችን ጥቅም ላይ በማዋል ነው። በተጨማሪም ወላጅ የትምህርት ክፍለ ጊዜያት/መርሀ ግብሮች፣ ተደጋጋሚ ዝግጅቶች፣ ከማህበረሰብ ባለ ድርሻ አካላት ጋር ስብሰባዎች እና ግንኙነቶች፣ የበጀት ፎረሞች፣ እና የበላይ ተቆጣጣሪ ማክናይት (McKnight) 48 ጉብኝቶች ወደ MCPS ት/ቤቶች!

መልካም ዜና

የፌርላንድ (Fairland) አንደኛ ደረጃ መምህር የሚልከን አስተማሪ ሽልማትን (Milken Educator Award) መቀበል። የኬኔዲ (Kennedy) ሁለተኛ ደረጃ መምህር በብሔራዊ የሙዝቃ ትምህርት ማህበር (National Association of Music Education) ክብርን ማግኘት። የዚህ አመት 13 ፖዚ ፋውንዴሽን (Posse Foundation) ስኮላርሺፕ ተቀባዮች/አሸናፊዎች፣ የ MCPS 147 ለብሔራዊ የብቃት ስኮላርሺፕ (National Merit Scholarship) ግማሽ ፍፃሜ ተወዳዳሪዎች፣ 3ቱ በሪጄነሮን ሳይንስ ውድድር (Regeneron Science Competition) የመጨረዛ ዙር ተወዳዳሪ ተብለው ተሰይመዋል፣ ከክዌስት ብሪጅ (QuestBridge) 14 ስኮላርሺፖችን ውስደዋል። የ $10 ሚልዮን ስጦታ ከሬልስ ፋውንዴሽን (Rales Foundation) ለተማሪ ስኮላርሺፖች።

እና፣ ለወደፊት…

በሴፕቴምበር ላይ፣ ለተማሪዎች እና ለማህበረሰባችን ፈታኝ ነገር እንዲሞክሩ አቅርቤ ነበር እና አሁንም እውነታ ነው። “በትምህርት ቤት የሚቀርቡላችሁን አስደናቂ እድሎች ተጠቀሙባቸው። ለሁሉም የማህበረሰባችን አባላት፣ የማቀርበው ፈተና ይሄ ነው፦ በዚህ ስራ ላይ አጋራችን ሁኑ። በአንድነት፣ ነገ የሚገባልን ቃል ኪዳን ብሩህ መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለች።” ለቀሪው የትምህርት አመት፣ እድሎቹ ይቀጥላሉ። ጊዜው አሁን ነው።

ከልብ

Dr. Monifa B. McKnight ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክናይት,
Superintendent of Schools የት/ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት