ከ MCPS የት/ቤት ስርዓት ህክምና ቢሮ ጠቃሚ መልዕክት

በሚቀጥለው ሳምንት ለአዲሱ የትምህርት አመት መልሰን አብረን በመሆናችን በጣም ደስ ብሎናል! ተመሳሳይ ቦታዎችን ለመጋራት በምንመለስበት ወቅት፣ የተማሪዎቻችን እና የሰራተኞቻችን ጤናና ደህንነት ቅድሚያ መስጠታችን ይቀጥላል።  በት/ቤታችን ማህበረሰብ ላይ ኮቪድ-19 ያለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ፣ ከመቼውም በተሻለ መልኩ መሳሪያዎች፣ ልምዶችና እውቀት አለን። ሰራተኞችና ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲመለሱ ክትባትን፣ ምርመራን እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል ማድረግን በተመለከት የሚጠቅሙ አንዳንድ ነገሮች ከስር ተዘርዝረዋል፦
የኮቪድ-19 ክትባት የት/ቤት ማህበረሰባችንን ይረዳል
ክትባት በኮቪድ-19 ከመያዝ የሚመጡ ከፍተኛ ችግሮች በግለሰብ ላይ የሚፈጥሩትን አደጋ ለመቀነስ ጠቃሚ መንገድ ነው። ከፍተኛ የክትባት ሽፋን መጠን መኖሩ የት/ቤት ማህበረሰባችን ላይ ኮቪድ-19 የሚኖረውን አጠቃላይ ችግር/ከባድ ሁኔታ ለመቀነስ እና ትምህርት እንዲቀጥል ይረዳል፣ ምክንያቱም ትንሽ ምልክት የሚታይባቸው ግለሰቦች ጥቂት ቀናት ብቻ ከትምህርት ወይም ከስራ ቀናት እንዲቀሩ በማድረግ የበለጠ በትምህርት ላይ እንዲሳተፉ ያስችላል። ተማሪዎች ብቁ የሆኑባቸውን ሁሉንም የሚመከሩ የኮቪድ-19 ክትባቶች እና ማበረታቻዎች (boosters) እንዲጠቀሙ አጥብቀን አንመክራለን። አሁን ላይ፣ የኮቪድ-19 ክትባትን ሰራተኞች በህክምና ከቫይረሱ ነፃ እንደሆኑ ማረጋገጫ/ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር እንዲወስዱ ይጠበቅባቸዋል። ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና የቤተሰብ አባላት የኮቪድ-19 ክትባትን ከትምህርት ሰአት በኋላ ወይም በሳምንቱ መጨረሻ/እረፍት ቀናት በሚደረጉ ክንውኖች/ዝግጅቶች የሚወስዱበት አጋጣሚዎች መፍጠርን አሁንም እንቀጥላለን።
ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ ለጠንካራ የትምህርት አመት ጅማሬ
ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች እና ተማሪዎች ወደ ት/ቤት በሚመለሱበት ጊዜ ፈጣን የቤት-ውስጥ የኮቪድ-19 ምርመራን ያበረታታል። ምርመራ ኮቪድ-19 ንቁ/በሚጎዳ መልኩ ይዟቸው በጊዜያዊነት መነጠል/መወሸብ ያለባቸውን ግለሰቦች ለመለየት ጠቃሚ መንገድ ነው፣ ይሄም የሚያስፈልገው የበለጠ መተላለፍን ለማስቀረት እና የት/ቤት ማህበረሰባችንን በተቻለ መጠን ጤናማ አድርጎ ለማቆየት ነው።
ከጉዞ መመለስ፣ ወይም በትልቅ ቡድን መሰባሰብ አይነት የበጋ (summer) ማገባደጃ/መጨረሻ ተግባራት፣ ለኮቪድ-19 ተጋላጭነትን ይጨምራል። ሰራተኞች እና ተማሪዎች ትምህርት ከተጀመረም በኋላ መመርመርን ሊያስቡ ይችላሉ፣ ይሄም የላብ አደሮችን ቀን ተከትሎ በሚኖር ጉዞ፣ ወይም ከትምህርት አመት መጀመሪያ ጋር ቀናቸው የሚገጥም ከፍተኛ የአደጋ ተጋላጭነት ማህበራዊ ክንውኖች ናቸው። ምርመራ ግዴታ አይደለም፣ እና ተጋላጭነትን መለየት/መገመት ሰራተኞች እና ቤተሰቦች ራሳቸው እንደሚያደርጉ እንዲሁም እንደሚመረመሩ እና ከተገኘባቸው የምርመራ ውጤቱን ሪፖርት እንደሚያደርጉ በእነሱ ላይ እንተማመናለን።
የምርመራ መሳሪያዎች በት/ቤቶች ይገኛሉ፣ በ8/27 ላይ በ MCPS አመታዊ ወደ-ት/ቤት መመለስ አውደ ርዕይ(Back-to-School Fair)፣ እና በ  8/27 እና 8/28 ላይ በሚደረጉበት/ቤት ውስጥ በሚኖሩ የሳምንቱ መጨረሻ/እረፍት ቀናት ክትባት ክሊኒኮች ነው። በተጨማሪም ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች ነፃ ፈጣን የምርመራ መሳሪያዎችም የሚገኙት በአብዛኛዎቹ የህዝብ ላይብረሪ መገኛ ቦታዎች፣ ወይም በፖስታ ከአሜሪካ (U.S.) መንግስት ወደ ቤት በሚቀርብ ነው።MCPS ኮቪድ-19 ሪፓርት ማድረጊያ ቅፅ በመጠቀም ሪፖርት መደረግ ያለባቸው ቫይረሱ እንዳለ የሚያሳዩ የምርመራ ውጤቶች ብቻ ናቸው። የምርመራ ውጤታቸው ኮቪድ-19 እንዳለ የሚያሳይ ግለሰቦች የበሽታ መከላከል ማዕከልን (CDC) መነጠያ/ውሸባ መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል።
ለጠንካራ ጅማሬ እና በከፍተኛ ተጋላጭነት ሁኔታዎች ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል ማድረግ
ከዛሬ ጀምሮ፣ የበሽታ መከላከል ማዕከል (CDC)የሞንትጎመሪ ካውንቲ ኮቪድ-19 አደጋ ተጋላጭነት ደረጃ “ዝቅተኛ” ነው።  አሁን ላይ፣ በ MCPS ህንፃዎች እና ባሶች ላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል ማድረግ በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ግዴታ አይደለም። የበሽተኛ እንክብካቤ ላይ አሁን እየሰሩ የሚገኙ የጤና ክፍል ሰራተኞች ወይም ማንኛውም በህክምና ስራዎች ላይ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ግለሰብ ከDHHS እና ከCDC የሚቀርቡ በቫይረስ የመያዝን መከላከያ መመሪያዎችን መከተል ይኖርበታል፣ ይሄም አስፈላጊ ሲሆን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል ማድረግን ያካትታል።
በተጨማሪም፣ በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ ግን ግለሰቦች ወይም ቡድኖች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል በጊዜያዊነት ማድረግ ሊጠበቅባቸው ይችላል፦

  • አንድ ተማሪ በትምህርት ቀን ውስጥ የኮቪድ-19 ምልክቶች ከታዩበት/ባት እና ለምርመራ ወደ ጤና ክፍል ከቀረበ/ች
  • አንድ ተማሪ በት/ቤት ውስጥ ተመርምሮ/ራ ኮቪድ-19 ከተገኘበት/ባት እና መጥተው እስኪወስዱት/ዷት እየጠበቁ ከሆነ
  • ወረርሽኝ በሚከሰትበት ወቅት፣ የኮቪድ-19 ምልክት ለማያሳዩ ግለሰቦች ከኳረንቲን/ውሸባ እንደ አማራጭ ሆኖ
  • ከኮቪድ-19 እያገገሙ የሚገኙ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ቢያንስ ለአምስት ሙሉ ቀናት ተነጥሎ መቆየትን ከጨረሱ በኋላ፣ እና ወደ ት/ቤት ወይም ስራ ለመመለስ ደህንነት ከተሰማቸው

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል ስለማድረግ ምክሮች እና ግዴታዎች በትምህርት ዘመኑ/አመቱ ውስጥ ሊለወጡ እንደሚችሉ ይጠበቃል፣ ይሄም የሚሆነው የኮቪድ-19 መረጃዎች የሚያሳዩት አካሄድ እና ሳይንሱ ሲቀየር ነው። በተገቢው መንገድ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል ማድረግ ለማይችሉ ግለሰቦች፣ ሌላ የመከላከያ እርምጃዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ።  
እባክዎትን ያስታውሱ፣ ምንም እንኳን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል ማድረግ አሁን ላይ በብዙ ሁኔታዎች ላይ የምርጫ ጉዳይ ቢሆንም፣ ሁሉም ሰራተኞችና ተማሪዎች የግል ጤናቸውን ለመጠበቅ፣ በማንኛውም የአደጋ ተጋላጭነት ደረጃ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል ማድረግ ቢወስኑ ይበረታታሉ። በትምህርት ቀን ቆይታ እንዲጠቀሙት MCPS ለሰራተኞችና ተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል ማቅረብ ይቀጥላል።
አዲሱ የትምህርት አመት መጀመሪያው በጣም ቀርቧል!  አሁን ላይ በመነሳሳት፣ በታደሰ አላማ እና በደስታ ስንመለስ፣ የትምህርት ቤት ማህበረሰባችንን በደህና ለማቆየት በጋራ እንስራ።
ከሰላምታ ጋር፣
ዶክተር ፓትሪስያ ካፑናን (Patricia Kapunan, M.D.)
MCPS የህክምና ባለሙያ