በጋራ የተሰጠ ማህበረሰብ መልእክት

ስለ አትሌቲክስ ደህንነት

ሴፕቴምበር 6, 2023

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎችን የምንወክል ቁልፍ መሪዎች እንደመሆናችን፣ ባለፈው አርብ፣ ሴፕቴምበር 1 በቤተዝዳ የተካሄደውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፉትቦል ጨዋታ ወቅት የተፈጠረውን ድብድብና ረብሻ ተከትሎ የተወሰዱትን እርምጃዎች ሪፖርት ለማድረግ እና ለማህበረሰብ ደህንነት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ለመድገም እየጻፍን ነው። 

በቤተዝዳ ቼቪ ቼዝ እና በዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የተደረገውን የፉትቦል ጨዋታ ተከትሎ፣ በቤተዝዳ ሜትሮ ስቴሽን አካባቢ በተደረገው ትልቅ ፍልሚያ በርካታ ተማሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ወዲያውኑ በትብብር ውይይት ጀምረዋል።

የዚህ ሥራ ዋናው ግብ የተከሰተውን ነገር በትክክል መረዳት እና የተሳተፉበት ተማሪዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ማረጋገጥ ነው። ከሁሉም የማህበረሰብ ፖሊስ አጋሮች ጋር ያለው የመግባቢያ ሰነድ በተለይ በትምህርት ቤቶች ላይ ለሚከሰቱ የዲሲፕሊን ጥሰቶች ምን አይነት እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚቻል እና ድርጊቶቹ እንዴት በወንጀል ተግባር እንደሚቆጠር ይዘረዝራል።  

ያሉት ማስረጃዎች ተገምግመዋል እናም በዚህ ጊዜ MCPS የተማሪዎች የስነምግባር ደንብ ጋር በማጣጣም ተገቢው የዲሲፕሊን እርምጃ መተግበሩን ማረጋገጥ እንችላለን። ነገር ግን፣ ምንም እንኳን የወንጀል ምርመራው እየቀጠለ ቢሆንም፣ በወንጀል የተከሰሱ ተማሪዎች የሉም። 

የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት በፎል የአትሌቲክስ ወቅት በየሳምንቱ ለእያንዳንዱ የፉትቦል ጨዋታ ሁሉን አቀፍ የደህንነት ዕቅዶችን ይጠብቃል። ከፎል የአትሌቲክስ ወቅት በፊት፣ MCPD እና MCPS ለእያንዳንዱ የፉትቦል ጨዋታ አጠቃላይ የኦፕሬሽን ደህንነት ዕቅዶችን ለመወያየት የትብብር ስብሰባ አድርገዋል። እነዚህ ስብሰባዎች ከ 2022 ጀምሮ በስራ ላይ ያለውን የደህንነት እቅድ ስርዓት ለመፍጠር አግዘዋል። MCPD እና MCPS የት/ቤት እና የማህበረሰብ ደህንነትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ አጋሮች ሆነው ይቀጥላሉ፣ እና በየሳምንቱ ስለእነዚህ እቅዶች ማሻሻል በተደጋጋሚ ይወያያሉ። 

“ደህንነትን ከትምህርት ቤት ግቢ ባሻገር እንዴት ማስጠበቅ እንችላለን?” የሚል ጥያቄ ተነስቷል። ይህ ተግዳሮቶች ይኖሩታል፤ ነገርግን ከካውንቲው የደህንነት እና የፖሊስ አጋሮቻችን ጋር በመሆን በርካታ አማራጮችን እየፈለግን ነው። በመሰረቱ የፉትቦል ጨዋታዎችን አስመልክቶ የMCPS ሰራተኞችን በማህበረሰባችን ቁልፍ ቦታዎች ላይ በማስቀመጥ እኛ እና ማህበረሰቡ የምንመለከተው መልእክቶችን ለተማሪዎቻችን መላላክን ያካትታል።

ወደፊት በሁሉም የፉትቦል ጨዋታዎች ላይ ደህንነትን ለማጠናከር የሚከተሉትን እርምጃዎች እንወስዳለን።

  1. ፎል 2023 የአትሌቲክስ ደህንነት ዕቅዳችን ላይ ያሉትን የሚከተሉትን እርምጃዎች እንጠቀማለን።

  • ተማሪዎች የትምህርት ቤት መታወቂያ ማቅረብ አለባቸው

  • እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ከተወዳዳሪ ትምህርት ቤቶች ውጪ ያሉ ተመልካቾች ከጎልማሳ ሰው ጋር መሆን አለባቸው

  • በጀርባ የሚያዙ ቦርሳዎች አይፈቀዱም እና ሌሎችም።  

  1. የአትሌቲክስ ደህንነት እቅድ በተጨማሪ ሌሎች እርምጃዎችንም እንድንተገብር ያስችለናል። ስለዚህ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ፥ ሁሉም የቫርሲቲ ፉትቦል ጨዋታዎች በሚከተለው እርከን 2 መሠረት ይከናወናሉ።

    • ኩነቱን ለመምራት እንዲቻል ለመርዳት የተመልካቾች ቁጥር በስታዲየሙ አቅም 75% ይገደባል።

    • ተገቢ ባልሆኑ ባህሪያት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦች ከድህረ ውድድር ወይም ከበርካታ ውድድሮች ሊገለሉ ወይም ሊታገዱ ይችላሉ።

    • ተጨማሪ የቀን ብርሃን ባለበት ጊዜ ውድድሮች/ጨዋታዎች እንዲካሄዱ እና የዝግጅት መሪዎችን ለመርዳት እንዲያመች የጨዋታ ጊዜያት/ቀናቶች ሊቀየሩ ይችላሉ።

    ተጨማሪ ሁኔታዎች ከተከሰቱ በደህንነት እቅድ ውስጥ ካለው የውሳኔ አሰጣጥ መመሪያዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ወደ ዕቅዱ እርከን 3 መሸጋገርን ጨምሮ ተጨማሪ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ።

  1. እንዲሁም፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ በተለዩ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ለምሳሌ፦ ተማሪዎች ከጨዋታ በኋላ ሊሰበሰቡ በሚችሉባቸው አካባቢዎች የፖሊስ መኮንኖችን ለመመደብ ቃል ገብተዋል።

ይህ ክስተት ለመላው ማህበረሰባችን ትምህርት የሚሰጥ ጊዜ ሆኖ ሊያገለግል ይገባል። የመከባበር፣ የመቻቻል እና ግጭትን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት እሴቶችን በጋራ ማጠናከር አለብን። ተማሪዎቻችን ልዩነቶቻቸውን ለመፍታት ወደ ሁከት እንዳያመሩ ማድረግ የምንችለው “ሁሉም በአንድ ላይ አሁን” የሚለውን መርህ ግንዛቤ በመፍጠር ነው። ሁላችንም በጋራ፣ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ከልጆቻቸው ጋር ተገቢ ያልሆነ ጥቃት እና ድብድብ፣ ሊያስከትል ስለሚችለው አስከፊ ውጤት ከልጆቻቸው ጋር እንዲነጋገሩ እናበረታታለን። እነዚህ ውይይቶች በማህበረሰባችን ውስጥ የምንፈልጋቸውን/የምንወዳቸውን እሴቶች ለማጠናከር ወሳኝ ናቸው።

እንደ ማህበረሰብ መሪዎች፣ ይህንን ክስተት በሚገባ ለመፍታት እና አዎንታዊ ለውጥ ለማስፈን እንደ እድል ሆኖ እንደሚያገለግል ቁርጠኞች ነን። በጋራ፣ አንድ የሚያደርገንን ትስስር ማጠናከር እና ተማሪዎቻችን ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ደግ/ሩህሩህ እና ውጤታማ የህብረተሰብ አባላት እንዲሆኑ መርዳት እንችላለን።

ከመልካም ወዳጅነት ጋር

Dr. Monifa B. McKnight Superintendent of Schools
ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክናይት የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት

Marcus Jones
Chief, Montgomery County Police



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)